No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የማይነቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረግ የእርቅ ስምምነት ሉያሟላ የሚገባዉን ፍርማሉቲ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ባሶ ሉበን ወረዲ ፍርድ ቤት ሆኖ በዘህ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሾች በመሆን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
የአሁን አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ በጁቤ ከተማ ቀበላ 01 ሰፈር 3 የሚገኝ 14 ዘንጎ ቆርቆሮ ቤት ያለቤትን በ250 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ ቤት ከአቶ ፍቃደ መኮንን እና ፈንታ ከበደ ገዛተዉ ካርታና ፕላን በጸደቀበት ወቅት በልጃቸዉ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ስም አስመዛግበዉ በራሳቸዉ ገንዖብ 52 ዘንጎ ቆርቆሮ አድርገዉ ያስገነቡትን ቤት ወደ ስማቸዉ እንዱያዙዉሩላቸዉ ተጠሪዎችን ሲጠይቁ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ በሽማግላ አማካኝነት ተደራድረዉ በቀን 20/06/2007 ዓ/ም ባደረጉት ስምምነት ተጠሪዎች ቤቱን ሉያስረክቧቸዉና አመልካቾች ደግሞ ለተጠሪዎች ብር 60,000.00 ለመክፈል ከተስማሙ በኋላ ተጠሪዎች ብር 60,000.00 ተቀብለዉ ግምቱ ብር 120,000.00 የሆነዉን ቤት እንዱያስረክቧቸዉ ሲጠይቁ ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን በመግለጽ ቤቱን እንዱያስረክቧቸዉ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ለክሱ ባሰሙት ክርክር ለክሱ መሰረት የተደረገዉ በቀን 20/06/2007 ዓ/ም የተጻፈ ዉል ዉላችን አይደለም። የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት ብለዉ በሀሰት በማዖጋጀት አስመስለዉ በመፈረም ያዖጋጁት ዉል በመሆኑ ሕጋዊ ዉል የለም። የቤቱን ስመ ሀብት ለማዜር ተስማምተን የተዋዋለልነዉ ዉል የለም።አመልካቾች የቤት ግንባታ እንዱገነቡ የፈቀደላቸዉ የለም።ቤቱን በአዱስ ማስተር ፕላን ያሰራነዉ እኛ ነን በማለት ክሱ ዉድቅ እንዱረግላቸዉ በመጠየቅ መከራከራቸዉን የክልለ ፍርድ ቤቶች ዉሳኔዎች ግልባጭ ያሳያል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ያየዉ የባሶ ሉበን ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/9 ላይ የግራ ቀኝ ምስክሮች በመስማትና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የእርቅ ስምምነት ሰነድ በመመርመር በቀን 20/10/2009ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪዎች ዉለን አልተዋዋልንም አሻራዉ ይመርመርልን በማለት በተከራከሩት መሰረት ፊርማ ለማስመርመር ለማመሳከሪያ የሚሆን የ2ኛ ተጠሪ ፊርማ ባለመገኘቱ ፊርማዉ ሉመረመር ባይችልም ምስክሮች ከሰጡት ምስክርነት ቃል በቀን 20/06/2007 ዓ/ም በክሱ የተጠቀሰዉን በ1ኛ ተጠሪ ስም ተመዛግቦ የሚገኘዉን ቤት አመልካቾች ብር 60,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ ከፍለዉ 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ቤቱን ለማስረከብ መስማማታቸዉን ማረጋገጡን በመግለጽ ዉለ የተደረገበትም ፍርም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1719/1 መሰረት ተቀባይነት ያለዉ ነዉ በማለት ተጠሪዎች ቤቱን እንዱያስረክቡና ስመ ሀብቱን በአመልካቾች ስም እንዱያዜሩ አመልካቾችም ብር 60,000.00 እንዱከፍለ ወስኗል።
የአሁን ተጠሪዎች በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምስራቅ ጎጃም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/4 ላይ በቀን 26/11/2009ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትዔዙዛ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዝል።በመቀጠልም አመልካቾች አቤቱታቸዉን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዉ ችልቱ በመ/2 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 29/02/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት በጽሁፍና ዉል ለመዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ቀርቦ መመዛገብ እንዲለበት ስለተደነገገ በተያዖዉ ጉዲይ ግራ ቀኝ ያደረጉት ዉል የቤት ስመ ሀብት ለአመልካቾች ለማዙወርና ብር 60,000.00 ለመክፈል የተደረገ ስምምነት እንደመሆኑ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት ስላልተደረገ ሕገወጥ በመሆኑ በዘህ ዉል መነሻ ተጠሪዎች ቤቱን እንዱያስረክቡ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ ሽሯል።አመልካቾች በቀን 27/05/2011 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በዘህ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዖት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ለክሱ መሰረት የተደረገዉ በቀን 20/06/2007 ዓ/ም የተፈጸመዉ ዉል በሽማግላ የተደረገ የእርቅ ዉል ስምምነት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት በዉል አዋዋይ ፉት እንዱደረግ ሕግ አያስገድድም።የእርቅ ዉል ስምምነት በዉል አዋዋይ ፉት ስላልተደረገና ስላልተመዖገበ ተፈጻሚነት የለዉም መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።ቤቱ የአመልካቾች እንደሆነና አመልካቾች እንደገነባን ተማምነን ተጠሪዎች ቤቱን ሉያስረክቡንና በስማችን ሉያዜሩ በሽምግልና ጨርሰናል።ቤቱን ገዛተን በ1ኛ ተጠሪ ስም ያደረግነዉ አመልካቾች አርሶ አደሮች በመሆናችንና 1ኛ ተጠሪ ልጃችን በመሆኑ እንጅ የሽያጭ ዉል ሳይኖረን እንደሽያጭ ዉል ተቆጥሮ መወሰኑ ከክርክሩ ጭብጥ ዉጭ ነዉ ተብል ሉታረም ይገባል።ለክሱ መሰረት የሆነዉ የእርቅ ስምምነት ሉፈጸም አይገባም ተብል መወሰኑ እርቅን ዋጋ ማሳጣት ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ ተብል ሉታረም ይገባል በማለት በመጠየቅ አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
No topics extracted.
ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉንና የሥር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔዎች መርምሮ የአመልካቾች ዲኝነት ጥያቄ የሽያጭ ዉል ይፍረስልኝ ሳይሆን ተጠሪዎች በሽማግላ በቀን 20/06/2007 ዓ/ም ለመፈጸም ግዳታ የገቡትን ገንዖብ ይክፈለኝ የሚል ሆኖ በስር ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 ተጠቅሶ ዉድቅ የመደረጉን አግባብነት ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ትእዙዛ መስጠቱን ተከትል ተጠሪዎች በቀን 18/02/2012 ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዖቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ከአመልካቾች ጋር በቀን 20/06/2007 ዓ/ም በሽማግላ የገባነዉ ምንም አይነት ስምምነት የለም።ዉል አለን በማለት ያቀረቡት ሰነድ በሀሰት የተዖጋጀ ነዉ።በሀሰት አዖጋጅተዉ ዉል አለን በሚል ያቀረቡት እማኝ ሽማግላ ያደረጓቸዉ ከአመልካቾች ጋር ጥቅም ተካፊዮች የሆኑ ልጆቻቸዉና ጓደኞቻቸዉ ናቸዉ።በዉለ ላይ ያለዉ ፊርማ የተጠሪዎች አይደለም ብለን የአሻራ ምርመራ እንዱደረግ ጠይቀን ሳይመረር ስለቀረ አሁንም እንዱመረመርልን እንጠይቃለን።ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ተጠሪዎች በምስራቅ ጎጃም ዜን ፍትህ መምሪያ ሰነድች ማረጋገጫና ምዛገባ የሥራ ሂደት ፉት በተደረገ የሽያጭ ዉል በግል ገንዖባችን 1ኛ ተጠሪ እማኝ ሆነዉ ከአቶ ፍቃደ መኮንን እና ከወ/ሮ ፈንታየ ከበደ የገዙነዉ እንጅ የአመልካቾች አይደለም።ቤቱን አመልካቾች አልገነቡም።ዉለ ሕገወጥ ዉል ስለሆነ እንደዉለ ለመፈጸም ሕግ ስለማያስገድደን የአመልካቾች አቤቱታ የሕግ መሰረት የለዉም ተብል ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
አመልካቾች በተጠሪዎች በቀረበ መልስ ላይ በቀን 19/03/2012 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዘህ በላይ የተመዖገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዖት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዖዉ ጭብጥ ጉድለት ያለበት በመሆኑ ጭብጡን በመለወጥ የማይነቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረግ የእርቅ ስምምነት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 ስር በተደነገገዉ መሰረት ካልተደረገ እና የዉለ መኖር ከተካደ ዉጤቱ ምን ላሆን ይገባል የሚል ጭብጥ በመያዛ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት አመልካቾች በራሳቸዉ ገንዖብ በልጃቸዉ በ1ኛ ተጠሪ ስም የገዘትና ተጨማሪ ግንባታ በመፈጸም አሻሽለዉ የሰሩት እንደሆነ በመግለጽ የተከራከሩ ቢሆንም የቤቱ ስመ ሀብት በአሁን 1ኛ ተጠሪ ስም ተመዛግቦ የሚገኝ መሆኑ በግራ ቀኝ የታመነ ፍሬ ነገር ነዉ።አመልካቾች ከተጠሪዎች ጋር በቀን 20/06/2007 ዓ/ም በአስታራቂ ሽማግላዎች አስታራቂነት ፈጸምን ባለት የእርቅ ዉል ተጠሪዎች ቤቱን ለአመልካቾች ለማስረከብና ስመ ሀብቱንም በአመልካቾች ስም አዙዉረዉ ለማስመዛገብ እንዱሁም አመልካቾችም ብር 60,000.00 ለተጠሪዎች ለመክፈል መስማማታቸዉን በመግለጽ በእርቅ ዉለ መሰረት ተጠሪዎች ቤቱን ለማስረከብና ስመ ሀብቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ በፍርድ ኃይል ተገደዉ እንደ ዉለ እንዱፈጽሙ ለማስወሰን ያቀረቡት ክስ መሆኑን ከክርክሩ ተረድተናል። የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት የግራ ቀኝ ምስክሮች ከሰማ በኋላ በግራ ቀኙ መካከል ለክሱ መሰረት የተደረገዉ የእርቅ ዉል መደረጉን እንዲረጋገጠ በመግለጽ ወስኗል። ሆኖም ተጠሪዎች አከራካሪዉን ቤት በስማቸዉ በዉል አዋዋይ ፉት በተደረገ ዉል ገዛተዉ በስማቸዉ አስመዛግበዉና አሻሽለዉ ገንብተዉ ይዖዉ የሚገኙት ቤት እንደሆነና ለክሱ መነሻ የሆነዉን የእርቅ ዉል ከአመልካቾች ጋር እዲልተዋዋለ፤ የእርቅ ዉለ በሀሰት የተዖጋጀና ፊርማዉም ራሳቸዉ ቤቱን ለአመልካቾች ለማስተላለፍ ተስማምተዉ የፈረሙት ሳይሆን በሀሰት ተመሳስል ተፈርሞ የቀረበ ነዉ በማለት ክደዉ መከራከራቸዉን ከወረዲ ፍርድ ቤት ጀምሮ ያሰሙት ክርክር ያሳያል።
ከዘህ በላይ እንደተመለከተዉ አመልካቾች ለክርክራቸዉ መነሻ ያደረጉት በቀን 20/06/2007ዓ/ም ከተጠሪዎች ጋር አደረግን ያለትን እና በተጠሪዎች የተካደዉን በሶስተኛ ሰዉ(ሽማግላ) አስታራቂነት የተዋዋለት ዉል መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3322/2 ስር በተደነገገዉ መሰረት ተዋዋይ ወገኖች በአስታራቂ አማካኝነት ሲስማሙ የገቡትን ግዳታ በግልጽ በጽሁፍ በማስፈር ካልተስማሙ በዉለ ሉገደደ እንደማይችለ ተደንግጓል። በዘህ ድንጋጌ ስር የእርቅ ዉለ የሚፈጸምበትን የአጻጻፍ ስርዓት(ፍርም) በተመለከተ የእርቅ ዉለ የተዋዋዮችን ግዳታ በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ በጽሁፍ እንዱደረግ የተደነገገ ቢሆንም የእርቅ ዉል በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት(ፍርድ ቤትን ጨምሮ) እንዱደረግ በፍትሐብሕር ሕጋችን ስለእርቅ በሚደነግገዉ ልዩ ክፍል ከቁጥር 3318 እስከ 3324 ድረስ ባለ ድንጋጌዎች በግልጽ አልተደነገገም።እነዘህ ድንጋጌዎች በዋናነት ተፈጻሚነታቸዉ ተዋዋይ ወጎኖች ወደ ፍርድ ቤት ያልመጣን የተጀመረ ክርክር ለማቆም ወይም ለወደፉት የሚፈጠረዉን ክርክር አስቀድመዉ ለማስቀረት በመፈለግ የሚያደርጉትን ዉል በተመለከተ ነዉ።
ከላይ የተመለከተዉ እንደተጠበቀ ሆኖ በፍርድ ቤት እየታየ ያለን ክርክር ተከራካሪዎች በእርቅ ለመጨረስ ሲፈልጉ የእርቅ ስምምነቱ የሚደረግበት ስነ ስርዓት፣ የእርቅ ስምምነቱ የሚይዙቸዉ ፍሬ ነገሮችና የእርቅ ስምምነቱ ጉዲዩን በያዖዉ ፍርድ ቤት ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተጣርቶ በፍርድ ቤቱ ጸድቆ ከፍርድ ቤቱ መዛገብ የሚያያዛበት ስርዓት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ከቁጥር 274-277 ድረስ ባለ ድንጋጌዎች ተዖርግቷል። አከራካሪዉ ጉዲይ በማንኛዉም አይነት መብት ላይ የተመሰረት ቢሆንም በእነዘህ ድንጋጌዎች መሰረት የእርቅ ስምምነት ሲፈጸም የእርቅ ዉለ በግልጽ ጉዲዩን እየዲኘ ባለዉ ፍርድ ቤት ጸድቆ ስለሚመዖገብ በማያሻማ ሁኔታ ተከራካሪዎች በአከራካሪዉ ጉዲይ ላይ ሉፈጸም የሚችል የእርቅ ዉል ስለመፈጸማቸዉ አስረጂ ይሆናል።
በልላ በኩል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/2 ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን ባለቤትነት… ለማስተላለፍ…የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ የክፍያ ወይም የማዙወር ስምምነቶች ሁለ በጽሁፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዛገብ ወይም ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል መደረግ እንዲለባቸዉ ተደንግጓል።በዘህ ድንጋጌ " 'የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ የክፍያ ወይም የማዙወር ስምምነቶች' ተብል የተገለጸዉ በእንግሉዛኛዉ ቅጅ ላይ 'Any contract by which an immovable is divided and any compromise relating to an immovable shall be in writing and registered with a court or notary.'" የሚል ይዖት ያለዉ ነዉ። ይህም በአማርኛዉ ቅጅ ላይ ስምምነቶች ሁለ ተበል የተገለጸዉ በእንግሉዛኛዉ ቅጅ any compromise ተብል ከተገለጸዉ ጋር ተያይዜ ስታይ በድርድር ወይም በእርቅ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረግ ስምምነቶችን የሚያካትት እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ። በተያዖዉ ጉዲይ ለክሱ መሰረት የሆነዉ ዉል የእርቅ ስምምነት እንጅ የቤት ሽያጭ ዉል ነዉ የሚል ክርክር በግልጽ ባይቀርብም የእርቅ ስምምነት የለም የሚል ክርክር በተጠሪዎች መቅረቡ እንደተጠበቀ ሆኖ የእርቅ ስምምነት የተደረገበት ዓላማ በተጠሪዎች ስም ተመዛግቦ የሚገኘዉን ቤት ስመ ሀብት ለአመልካቾች ማስተላለፍና ቤቱንም ለማስረከብ በአንጻሩ ደግሞ አመልካቾች ለተጠሪዎች ብር 60,000.00 እንዱከፍለ ለማድረግ በመሆኑ የዉለ ዓላማ ክፍያ ተቀብል የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ማስተላለፍ ነዉ።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት የቤት ባለቤትነትን ለማስተላለፍ የሚደረጉ ስምምነቶች ሁለ (ሰረዛ የተጨመረበት)በሕግ ፉት የጸኑ የሚሆኑት በጽሁፍ ሲደረጉ ብቻ ሳይሆን የኸዉ የጽሁፍ ዉል በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ አዋዋይ ፉት ወይም በፍርድ ቤት የተፈጸመ ሲሆን ነዉ። ሕጉ በዘህ አግባብ የተቀረጸበት ዋና ዓላማም የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን ለማስተላለፍ የሚደረጉ ስምምነቶች ጠበቅ ያለ ፍርም እንዱከተለ ልዩ አጽንኦት ለመስጠት መፈለጉን ለማሳየት እና በተዋዋዮች መካከል በሕግ ፉት የሚጻና ዉል እንዱኖር ለማድረግ ካለዉ ዓላማ እንደሆነ ይታመናል።ይህም ተዋዋዮች ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ለማስተላለፍ ያደረጉትን ዉል ፈቅደዉ የፈጸሙት መሆኑን ለማረጋገጥ፣ የንብረቱን ባለቤትነት የሚያስተላልፈዉ ሰዉ በንብረቱ ላይ የጸና የባለቤትነት መብት ያለዉ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ዉለ የተፈጸመበትን ትክክለኛ ቀን ለማረጋገጥ እድል በመስጠት የንብረት ባለቤትነት ለመጠበቅና የዉልች ዋስትና ለማረጋገጥ የሚሰጠዉ ጠቀሜታ የጎላ ነዉ።ስለሆነም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን ከማስተላፍ ጋር በተያያዖ የተከሰተ ክርክር ነገር ግን ወደ ፍርድ ቤት ያልቀረበ ወይም ለወደፉት የሚፈጠር ክርክር አስቀድሞ ለማስቀረት የሚደረግ የእርቅ ስምምነት በዘህ የሕግ ድንጋጌ ማዔቀፍ ዉስጥ ሉገዙ እንደሚገባ የድንጋጌዉ ይዖትና መንፈስ ያስገነዛባል።
በተያዖዉ ጉዲይ አመልካቾች ለክሳቸዉ መሰረት ያደረጉት ዉል በአስታራቂ አማካኝነት በተደረገ እርቅ ተጠሪዎች ክፍያ በመቀበል የቤት ባለቤትነትን ለማስተላለፍ ተስማምተዋል የተባለ ዉል የሚመለከት በመሆኑ ሕጉ በሚጠይቀዉ መሰረት በጽሁፍ የተደረገ ቢሆንም በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት ወይም በፍርድ ቤት የተደረገ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕጉ አንቀጽ 1723/2 ስር የተደነገገዉን ዉለን በሕግ ፉት የጸና የሚያደርገዉን ሁለተኛዉን መስፈርት አያሟላም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ክፍያ በመቀበል የቤቱን ስመ ሀብት ለማስተላለፍና ቤቱን ለማስረከብ ተደረገ የተባለዉንና ለክሱ መሰረት ተደረገ የተባለዉን ይህንን የእርቅ ዉል ተጠሪዎች አለፈጸምንም በእርቅ ዉለ ላይ በተጠሪዎች ተፈረመ የተባለዉንም ፊርማ አልፈረምንም በሀሰት የተዖጋጀ ነዉ በማለት በግልጽ ክደዉ የተከራከሩ በመሆኑ በተዋዋዮች መካከል ዉል አለመኖሩን ያሳያል።
ስለሆነም የሥር የባሶ ሉበን ወረዲ ፍርድ ቤት የእርቅ ዉል መደረጉን ምስክሮች እንዱያስረደ በማድረግ ምስክሮች የሰጡትን ቃል መሰረት በማድረግ በሕግ ፉት በሚጸና አኳኋን ያልተደረገና በተጠሪዎችም የተካደ የቤት ባለቤትነት ለማስተላለፍ የተደረገ የእርቅ ዉል ዉጤት እንዱኖረዉ መወሰኑና በዘህ ዉሳኔ ላይ የቀረበዉን ይግባኝ የምስራቅ ጎጃም ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሰረዘ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ይህንን ስህተት ጉዲዩን በሰበር ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማረሙ ሕጉን ተግባራዊ አደረገ ከሚያስብል በስተቀር የፈጸመዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/2 ላይ በቀን 29/02/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የባሶ ሉበን ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/9 ላይ በቀን 20/10/2009ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ እና የምስራቅ ጎጃም ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/4 ላይ በቀን 26/11/2009ዓ/ም የሰጠዉን ትእዙዛ በመሻር መወሰኑ ተገቢ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ት እ ዙ ዛ የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለክልለ ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።