የከተማም ሆነ የገጠር መሬት ድንበር መገፊት ጋር ተያይዜ የሚቀርበውን ጉዲይ ከሳሽ ወገን መጠኑን ገልጾ ከጠየቀው ዲኝነት እና በምስክሮች ወይም አስተዲዲሪ አካል አጣርቶ የቀረበው መጠን ከተጠየቀው ዲኝነት በላይ በሆነ ጊዚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መስጠት ያለባቸው ግዳታ ከሳሽ ወገን በጠየቀው ዲኝነት ልክ በመሆኑ በአስተዲዲሪ አካል ተጣርቶ የቀረበውን በማለፍ በተጠየቀው ዲኝነት ልክ መወሰን የሚገባ ስለመሆኑ። ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.182 (1) እና 224 (1)
No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ዮናስ ደስታ ጠበቃ ተስፊዬ ሙሉሳ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ነጋሽ ኃይላ- አልቀረ ቡም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዛገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር 1ኛ ተከሳሽ፣ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር በተደረገ በአደራ ማስቀመጥ ውል ከውጭ ሀገር ይዢ የገባሁትን 225,000.00 የአሜሪካን ድላር በአደራ አስቀምጬ ገንዖቡን የመመለስ ውል ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ/ም የተፈጸመ ቢሆንም በውለ መሰረት ያልመለሱት ቀሪ ገንዖብ 126,000.00 ድላር ወደድላር ሂሳብ አካውንቴ እንዱያስገቡልኝ እንዱወሰን የሚል ሲሆን አመልካች ባቀረቡት መልስ ውለ አሜሪካን ሀገር ስለተደረገ ፍርድ ቤቱ የመዲኘት ሥልጣን የለውም፤ ድላሩን በአደራ የሰጠኝ አሜሪካን ሀገር ሲሆን ያለውን ቀሪ ገንዖብ 90,551.00 ድላር አሜሪካን ሀገር መጥቶ መውሰድ ይችላል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ ገንዖቡን በአደራ የማስቀመጥ ውለ የተደረገው በኢትዮጵያ ቢሾፍቱ ከተማ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የመዲኘት ሥልጣን አለው፤ ነገር ግን የውጭ ሀገር ገንዖቡ ወደኢትዮጵያ ሲገባ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 49/2017 መሰረት ሕጋዊ ሥርዓቱን ጠብቆ ያልገባና የውጭ ሀገር ገንዖቡ በዘህ መጠን እና ለረጅም ጊዚ በግለሰብ እጅ እንዱቆይ የማይፈቅድ ስለሆነ በአደራ የማስቀመጥ ውለ በፍ/ሕ/ቁ. 1716(1) መሰረት ሕገ-ወጥ ነው፤ ሕገ-ወጥ ውል የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የላለ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ በፍ/ሕ/ቁ. 1716(1) መሰረት ሕገ-ወጥ ዓላማ ያለው ውል ነው የሚባለው የውለ ግዳታ በራሱ ሕገ-ወጥ ሲሆን እንጂ ከውለ በፉት የተፈጸመ ሕገ-ወጥ ተግባር መኖር አለመኖሩ መሰረት በማድረግ የሚወሰን አይደለም። ድላር በአደራ ማስቀመጥን ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሕግ ድንጋጌ የለም። ድላሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ የገባ ነው ቢባልና ውለ ፈራሽ ቢሆን እንኳን አመልካች ገንዖቡን የሚያስቀሩበትና ያላግባብ የሚበለጽጉበት ምንም የሕግ አግባብ የለም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር በፍሬ ነገሩ አከራክሮ እንዱወሰን ጉዲዩን መልሷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዘህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዖትም ድላርን በአደራ ማስቀመጥ በወንጀል ሕግ ቁጥር 346 እና የብሓራዊ ባንክን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 26(4) መሰረት የወንጀል ድርጊት ሆኖ የተመለከተ ነው። ተግባሩ ወንጀል በመሆኑ ውለ ሕገ-ወጥና ውጤት የላለው ነው። በሕግ ወንጀል የተባለን ድርጊት በፍርድ ሕጋዊ ማድረግ አይቻልም፤ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ድላር በአደራ ማስቀመጥ ውል ሕገወጥ ተግባር አይደለም መባለ ከመመሪያ ቁጥር 49/2017 እና ከፍ/ሕ/ቁ. 1716 አንጻር ተገቢነቱን ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ያዖዖ ሲሆን ተጠሪ ያቀረቡት መልስ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ውለ ሕገ-ወጥ ነው በማለት ያልተከራከሩ ስለሆነ በሥር ያልቀረበ ክርክር በዘህ ችልት ሉያነሱ አይገባም። የውለ ግዳታ ሕገ-ወጥ ሳይሆን ከውለ በፉት የተፈጸመ ሕገ-ወጥ ተግባር መኖር አለመኖሩን የውለን ዓላማ ሕገ-ወጥ አያደርገውም።
የተከፈለው ገንዖብ ሳይመለስ ይቀራል ማለት የፍ/ሕ/ቁ. 1815 የሚቃረን እና አንደኛው ተዋዋይ ወገን ያላግባብ እንዱበልጽግ የሚያደርግ ነው። ውሳኔው ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል ብለዋል።
አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ተጠሪ ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት ያለው መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዛ መዛገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር በተደረገ በአደራ ማስቀመጥ ውል ከውጭ ሀገር ይዢ የገባሁትን 225,000.00 የአሜሪካን ድላር በአደራ አስቀምጬ ገንዖቡን የመመለስ ውል ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ/ም የተፈጸመ ቢሆንም በውለ መሰረት ያልመለሱት ቀሪ ገንዖብ 126,000.00 ድላር ወደድላር ሂሳብ አካውንቴ እንዱያስገቡልኝ እንዱወሰን የሚል ነው። እንደሚታወቀዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1 መሰረት ማንኛዉም ሰዉ አንድን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠዉ አካል በማቅረብ ፍርድ ወይም ዉሳኔ(ፍትህ) የማግኘት መብቱን መጠቀም የሚችለዉና በተለይም ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዲዩን ተቀብል አከራክሮ ዉሳኔ ወይም ፍርድ ላሰጥ የሚችለዉ ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በፍርድ ሉወሰን የሚገባ ጉዲይ (justiciable matter) ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነዉ።
ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዚ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል። ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ከሚመረምራቸው ጉዲዮች መካከል የመጀመሪያው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 231(1)(ሀ) መሰረት በክስ አቤቱታው የተገለጸው የሚያስከስስ መሆን መሆን አለመሆኑን ነው። የክስ ምክንያት ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዳታ መኖሩን፣ የተጠየቀው ዲኝነት በፍርድ ቤት የሚዲኝ መሆን አለመሆኑን እና በክሱ ዛርዛር ውስጥ የተመለከቱት ጉዲዮች ቢረጋገጡ የተጠየቀውን ዲኝነት ለከሳሽ ለመወሰን ህግ የሚፈቅድ መሆን አለመሆኑን መመርመርን የሚጠይቅ ነው። ይህም የክስ ምክንያት የላለው ጉዲይ የሚለው በዋነኛነት ዲኝነቱን ለመጠየቅ ከህግ የመነጨ ግንኙነት እያለው ግን በፍርድ ቤት ሉዲኙ የማይችለ ጉዲችን (non-justiciable matters) ፍርድ ቤት አከራክሮ ሉፈጸም የሚችል ውሳኔ ላሰጥባቸው የማይችለ በመሆናቸውና ከሳሽ ወገን ክሱን ሲያቀርብ የጠቀሰው ወይም የገለጸው የክሱ መሰረት የሆነው ምክንያት በህግ የክስ መሰረት ላሆን የማይችል ከሆነ የማያስከስስ ነው ተብል ክሱ ውደቅ የሚደረግበት ሥርዓት ነው።
በተያዖው ጉዲይ ተጠሪ የጠየቁት ዲኝነት ከአመልካች ጋር ያደረጉት ድላር የማስቀመጥ የአደራ ውል መሰረት እንዱፈጸምላቸው ነው። ውል ሉመሰረት የሚገባው ሕጋዊ በሆነ ዓላማና ጉዲይ ላይ እንደሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 1678(ለ) ላይ ተመልክቷል። በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 346 ላይ የውጭ ሀገር ገንዖብን በአደራ ማስቀመጥ ወንጀል ሆኖ የተደነገገ ሲሆን በብሓራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 26 በአዋጁ ሆነ በመመሪያ የተመለከቱ ግዳታዎችን መተላለፍ ወንጀል ስለመሆኑ ተቀምጧል። የብሓራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤፍ.ኤክስ.ዱ. 49/2017 በክሱ የተመለከተውን መጠን ያሕል የውጭ ሀገር ገንዖብ መያዛ መከልከለ የተመለከተ ስለሆነ ድርጊቱ በአዋጁ መሰረት ወንጀል ነው። ተዋዋዮች የመዋዋል ነጻነት ቢኖራቸውም በሕግ የተመለከተውን አሥገዲጅ ሁኔታ አልፈው መዋዋል አይችለም። በዘህ ምክንያት ድላር በአደራ ማስቀመጥ ውል ሕገ-ወጥ ተግባር በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሕገ-ወጥ ውልን ሉያስፈጽሙ አይችለም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ (በቅጽ 06 እንደታተመ) ሕገ-ወጥ ውልን ለማስፈጸም የሚቀርብ ክስ፤ የክስ ምክንያት የላለውና በፍርድ ቤት ሉስተናድ የማይችል ስለመሆኑ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ስለሆነም ተጠሪ የድላር አደራ ማስቀመጥ ውል እንዱፈጸምላቸው ያቀረቡት ክስ ሕገ-ወጥ ውል እንዱፈጸም ዲኝነት የተጠየቀበት ስለሆነ ጉዲዩ የክስ ምክንያት የለውም ብለናል። ይግባኝ ሰሚ ችልት ውለ ሕገ-ወጥ ውል አይደለም በሚል በሥረ-ነገሩ እንዱታይ መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ሕዲር 23 ቀን 2014 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በመዛገብ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በውጤቱ ፀንቷል።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት የክስ ምክንያት የለውም በማለት ወስነናል።
በዘህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትዔዙዛ የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.