No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ አፈወርቅ ያለዉ ተጠሪ፡- 1ኛ/ አቶ በላይ ኢሳያስ 2ኛ/አቶ አማኑ ሲናማዉ መዛገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዘህ መዛገብ የቀረበዉ ጉዲይ የአፈጻጸም ክርክር መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች የአፈጻጸም ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ የአፈጻጸም ተከሳሾች ነበሩ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአፈጻጸም ክስ የቀረበዉ በግራቀኙ መካከል በቤትና ቡና ተክል ይዜታ ላይ በነበረዉ የሁከት ይወገድ ክርክር ጉዲዩ በሽማግላ እንዱታይ ተደርጎ በሽምግልና ታይቶ አመልካች የሀብት ግምት ብር 71,260 ብር ለተጠሪዎች እንዱከፍል ተጠሪዎችም ይህንኑ ሀብት እንዱያስረክቡ ተስማምተዉ ይኸዉ እርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ተመዛግቦና ጸድቆ ያደረ መሆኑን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎች ቀደም ሲል 40,000 ብር ተረክበዉ እያለ ቀሪ ብር ተረክበዉ ሀብቱን እንዱያስረክቡ ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል አመልካች የአፈጻጻም ክስ መንገሺ ወረዲ ፍርድ ቤት ላይ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸዉ አመልካች ቀሪዉን ብር በዉለ/ስምምነቱ/ በተገለጸዉ ጊዚ ዉስጥ አልከፈለም በሚል ስምምነቱ እንዱፈርስ እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቀዋል። የወረዲዉ ፍርድ ቤት በሁለቱም መዛገብ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ ዉለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት እንደዉለ ተጠሪዎች ቀሪ ገንዖብ ተቀብለዉ ንብረቱን እንዱያስረክቡ በማለት የአፈጻጸም ትእዙዛ ሰጥቷል። ተጠሪዎች በዘህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ለማጃንግ ብ/ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረባቸዉ ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በግራቀኙ መካከል የተደረገዉ የእርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት የጸደቀ በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ ህግ ቁ/277 መሰረት የአፈጻጻም ክስ የሚቀርብበት ነዉ በዘሁ መሰረት እንዱፈጸም በወረዲ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተገቢ ነዉ በማለት የተጠሪዎችን ይግባኝ ባለመቀበል የወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አጽንቷል።ተጠሪዎች ለክልለ ሰበር ችልት አቤቱታ በማቅረባቸዉ ሰበር ችልቱ ግራቀኙን አከራክሮ እንደዉለ ካልተፈጸመ አንደኛዉ ወገን ዉል እንዱፈርስ መጠየቅ ይችላል የሚለዉን ተቀብል የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1675-1678 ያለዉን በመጥቀስ ዉለ እንዱፈርስ ዉሳኔ ሰጥቷል። ለዘህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አከራካሪዉን ይዜታና ቤት አስመልክቶ ተጠሪዎች ዉል ይፍረስልን በማለት በጠየቁት መሰረት አመልካች ጉዲዩ በሽምግልና አልቋል በፍርድ ቤም የተመዖገበ ነዉ ሲል ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ ተደርጎ ዉል ይፍረስ በማለግራቀኙ በ26/08/08 ዓ.ም ካደረጉት ዉል እና ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ 277 አንጻር ለመመርምር እንዱቻል ጭብጥ ተይዜ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተረደርጓል።በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በግራቀቡ መካከል በ26/08/08 ዓ.ም የተደረገዉ ስምምነት አመልካች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ቀሪ ገንዖብ ከፍል እንዱረከብ እንደነበር እና አመልካች በተገለጸዉ ጊዚ ገንዖብ የለኝም በማለቱ ዉለ እንዱፈርስ ተጠሪዎች ዲኝነት መጠየቃቸዉ እንዱሁም የክልለ ሰበር ችልት ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ እንደሆነ በመግልጽ ዉሳኔዉ እንዱጸና ተከራክረዋል።አመልካችም የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዖዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዖብ መርምረናል ። መዛገቡን መርምረን እንደተገነዖብነዉ በግራቀኙ መካከል በነበረዉ የሁከት ይወገድ ክስ ላይ ጉዲዩ በሽምግልና እንዱታይ በፍ/ቤት መስማማታቸዉን ተከትል ግራቀኙ በሽማግላ ተስማምተዉ ስምምነቱም በ26/08/08 ዓ.ም ተፈርሞ በፍርድ ቤት ተመዛግቦና ጸድቆ መዛገቡ የተዖጋ ስለመሆኑ ግራቀኙ ያልካደት እና በስር ፍርድ ቤትም በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን ነዉ።ስምምነቱ ላይ የተመለከተዉም ጉዲይ ግራቀኙን ያከራከረዉን ቤትና የቡና ተክል ይዜታ ግምት ብር 71,260 አመልካች ለተጠሪዎች እንዱከፍል ተጠሪዎችም ይህንኑ ንብረትና ይዜታ እንዱያስረክቡ የሚል ሲሆን እንደዉለ አስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ግራቀኙ ግደታዎቻቸዉን ለመፈጸም መስማማታቸዉም አላከራከረም። አመልካች በዘህ ስምምነት መሰረት እንዱፈጸም ሲጠይቅ ተጠሪዎች ቅድሚያ ብር 40,000 ወስደዉ ቆይተዉ ቀሪዉን ብር 31,260 እንዱቀበለና ንብረቱን እንዱያስረክቡ ፊቃደኛ ስላልሆኑ የአፈጻጸም ትእዙዛ እንዱሰጥለት የሚል ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ ክስና ክርክር አመልካች ሰኔ 30 ላይ ቀሪዉን ብር ስላልከፈለ ዉለ እንዱፈርስ የሚል ነዉ።
በመሰረቱ በፍርድ ቤት በክርክር ላይ ባለ ጉዲይ ተከራካሪ ወገኖች ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተዉ እርቁም በጽሁፍ ተደርጎ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከመዛገቡ ጋር እንዱያያዛ ከተደረገ ይህ እንደፍርድ ቤቱ ፍርድ ተወስድ የሚፈጸም ወይም የአፈጻጸም ክስ የሚቀርብበት ስለመሆኑ የፍብ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 277 /1 እና 2/ ድንጋጌ ይዖት ያስገነዛባል። በዘህ ረገድ ይህ ሰበርችልት በመዛገብ ቁ/52752፣85873 እና ላልችም ተመሳሳይ ጉዲዮች ላይ አስገዲጅ ዉሳኔ መስጠቱ ይታወቃል። በተያዖዉም ጉዲይ በግራቀኙ መካከል በፍርድ ቤት የተመዖገበ ስምምነት መኖሩ አከራካሪ አይደለም ።ይህ ስምምነት እንደፍርድ ቤት ፍርድ የሚወሰድ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ እንደስምምነቱ ካልተፈጸመ ስምምነቱ በዲኝነት አካል ዖንድ ቀርቦ የፍርድ ሃይል ያህል ተወስድ በዘሁ መሰረት እንዱጸም የአፈጻጸም ክስ ማቅረብ መብት ይኖራቸዋል እንጂ እንደመደበኛ ዉል ዉል እንዱፈርስ አዱስ ክስ የሚቀርብበት ላሆን አይገባም ።ከዘህ ባለፈ እንደማናቸዉም ፍርድ የአፈጻጸም ክስ ሲቀርብ ፍርደ/ስምምነቱ/ ሉፈጸም የማይቻልበት ህጋዊ ምክንያት ካለ በክርከር ሂደት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ መርምሮ በህጉ አግባብ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/386፣ 392 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዖት መገንዖብ ይቻላል። በዘህ መዛገብ ከቀረበዉ ክርክር መገንዖብ የሚቻለዉ አመልካች የሚከራከረዉ ተጠሪዎች ቀሪ ገንዖብ እንዱቀበለና ንብረቱን እንዱያስተላልፈ በአፈጻጸም እንዱገደደ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ አመልካች በዉለ በተገለጸዉ ጊዚ ማለትም ሰኔ30/2008 ዓ.ም ቀሪዉን ብር 31,260 ባለመክፈለ ዉለ እንዱፈርስ በማለት ተከራክረዋል። ከላይ እንደተገለጸዉ ሁለቱም ወገኖች እንደስምምነቱ/በፍርድ/መሰረት እንዱፈጸም ግደታዉን ያልፈጸመ ወገን በፍርድ አፈጻጸም ማስገደድ መብት አላቸዉ።ከዘህ ባሻገር የትኛዉ ወገን ነዉ ግደታዉን ለመወጣት ፈቃደኛ ያልሆነዉ የሚለዉን ክርክር አስመልክቶ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ሽማግላዎቹን አስቀርቦ እንዲረጋገጠዉ ተጠሪዎች ቀሪዉን ብር ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ አመልካች በአደራ ሽማግላዎች እጅ እንዲስቀመጠ እና እንደስምምነቱ ላለመፈጸም መሰናክል የፈጠሩት ተጠሪዎች መሆናቸዉን አረጋግጦ ዉሳኔ ስለመስጠቱ የተረጋገጠ ፍሬነገር ነዉ።ስለሆነም የክልለ ሰበር ችልት ይህን የተረጋገጠ ፍሬነገር እንዱሁም የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ 277 ይዖት እና ዓላማ ጋር በማያያዛ የፋዳራል ሰበር ችልት ከላይ በተገለጸዉ መዛገብ የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ባላገናዖበ ሁኔታ በፍርድ ቤት ተመዛግቦ ያደረ እና እንደፍርድ ቤት ፍርድ ተወስድ የአፈጻጸም ክስ የሚቀርብበትን ስምምነት የፍ/ብህግ ቁ/1675-1678 መሰረት አድርጎ ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተጸመበት ሆኖ አግኝተናል።በዘሁ አግባብ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
1ኛ/ የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ/00603/09 በ18/09/09 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/ መሰረት ተሸሯል።
2ኛ/ የመንገሺ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/00681/08 የሰጠዉ ዉሳኔ እና የማጃንግ ብ/ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/26781 የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል። የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ ብለናል ።ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ።