ፍርድ ቤቶች ከተካራካሪ ወገኖች መካከል ጣልቃ ገብ ተከራካሪው በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት ወደ ክርክሩ እንዱገባ እና ክርክሩን እንዱያቀርብ ባላደረገበት ሁኔታ፣ ዲኝነት ባልተከፈለበት፣ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ንብረት የዉርስ ሀብት ሳይሆን የ3ኛ ወገን ንብረት ነዉ በማለት መወሰን የማይቻል ስለመሆኑ። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.182 (2)፤40 (2)
No summary available.
ህዲር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የዉርስ ማጣራት ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች 1ኛ ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች ተከሳሾች፣ እና እንዱሁም በዘህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑት አቶ ተክለወልድ ክብካብ 2ኛ ከሳሽ፣ ዖርትሁን ተስፊዬ እና መና ግርማ ጣልቃ ገቦች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.205535 በ17/9/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች ባቀረቡት ክስ የሟች አቶ ክብካብ ገ/ማርያም እና የወ/ሮ በቀለች ወ/ማርያም የዉርስ ሀብትን በተመለከተ የዉርስ አጣሪ እንዱሾምልን በማለት ዲኝነት ጠይቋል። የሥር ተከሳሾች በዘህ ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በአማራጭ ፍሬ ነገር ክርክር ያቀረቡ ሲሆን፤ ጣልቃ ገቦችም በበኩላቸዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የፍሬ ነገር መልስ አቅርቦ ተከራክሯል። ከዘህ በኋላ የሥር ፍ/ቤቶች ተከሳሾች እና ጣልቃ ገቦች ያነሱትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የዉርስ አጣሪ በመሾም የዉርስ ሀብቱን እንዱያጣራ በሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረት የዉርስ አጣሪ በ14/6/2009 ዓ.ም የተጻፈ ሪፖርት አቅርቧል።
የዉርስ አጣሪ ሪፖርት ሲታይ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጽ/ቤት በዉርስ አጣሪዉ ዖንድ ጣልቃ ገብቶ አቤቱታ እንዲቀረበ መገንዖብ ተችሎል። የዉርስ አጣሪዉ የዉርስ ሀብቱን በማጣራት ሪፖርቱን ለፍ/ቤቱ አቅርቧል። የዉርስ አጣሪዉ ሪፖርቱን ለፍ/ቤቱ ካቀረበ በኋላ በሪፖርቱ ላይ አስተያየታቸዉን የሰጡት ከሳሾች፣ ተከሳሽ እና ጣልቃ ገቦች እንጂ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጽ/ቤት እንዲልነበረ የሥር ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዉሳኔዉ እንደጠቀሰዉ ፣በዘህ መዛገብ ጣልቃ ገብ ሆኖ ያልተመዖገበዉ በዉርስ ማጣራት ሂደቱ ግን ጣልቃ ገብ የነበረዉ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጽ/ቤት ዖንድ ያቀረበዉን አቤቱታ በመጥቀስ፣ ክርክሩን በመመርመር ለክርክር ምክንያት የሆነዉ 3 ክፍልች ቤት የቤተክርስቲያን ንብረት እንጂ የዉርስ ሀብት አይደለም እና የተጠሪዎች አዉራሽ በይዜታዉ ላይ የሰሯቸዉ 7 ክፍልች ቤት ላይ ወራሾች መብት የላቸዉም በማለት ወስኗል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቤተክርስቲያኑ የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆን ሳያደርግ የሰጠዉን ዉሳኔ በተመለከተ የሥር ከሳሽ ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ተከሳሾችን ብቻ መልስ ሰጪዎች በማድረግ ያቀረበ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዔዙዛ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ እና ትዔዙዛ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካቾች ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ በአራዲ ክ/ከተማ ወረዲ 8 ቀበላ 15/16 የሚገኘዉ እና በቤት ቁጥር 032 የሚታወቀዉ የዉርስ ሀብት አይደለም እና የኪራይ ገንዖብን በተመለከተ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በማለት ቅሬታቸዉን በመዖርዖር ዉሳኔዉ እንዱታረምላቸዉ ጠይቋል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች እንዱሰጡ ባዖዖዉ መሰረት በ30/2/2011 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ በዘህ ጉዲይ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጽ/ቤት የክርክሩ ተሳታፉ ሆና ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ንብረት ተወስኖላታል፤
ስለሆነም ቤተክርስቲያኗ በዘህ ችልትም የክርክሩ ተካፊይ እንዱትሆን በማድረግ ንብረቱ የዉርስ ንብረት አይደለም ተብል እንዱወሰንልን በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ይህ በእንዱህ እንዲለ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት በ8/4/2011 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ፡ ለክርክር ምክንያት የሆኑት ቤቶች የዉርስ ሀብት ሳይሆኑ የቤተክርስቲያኗ እና በሥር ፍ/ቤቶች እንደተፈረዲለት መሆኑን በመጥቀስ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ እንዱፈቀድለት ጠይቋል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጣልቃ ገብ ቤተክርስቲያን ያቀረበዉን አቤቱታ በመመርመር ጣልቃ ገብ የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆን በማዖዛ፤ አመልካች ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ላይ መልስ እንዱሰጥ ባዖዖዉ መሰረት በ6/6/2011 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት ግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዘህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት የሚገባዉ ፤በዘህ ጉዲይ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት የክርክሩ ተሳታፍ ሳይሆን ዉሳኔ መስጠቱ እና የሥር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም ይህን ሳያርም የሥር ዉሳኔ ማጽናቱ በሕጉ አግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ መሆኑን ተገንዛበናል። በዘህ መሰረት የአሁን ጣልቃ ገብ ለክርክር ምክንያት የሆኑት ቤቶች እና ይዜታዉ የዉርስ ሀብት ሳይሆን የቤተክርስቲያን ንብረት ነዉ በማለት በዉርስ አጣሪ ዖንድ ክርክር እንዲቀረበ ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ መገንዖብ ይቻላል። ነገር ግን የዉርስ አጣሪ ሪፖርቱን ለፍ/ቤት በሚያቀርበበት ወቅት የአሁን ጣልቃ ገብ የክርክሩ ተሳታፉ በመሆን በሪፖርቱ ላይ አስተያየቱን እንዲላቀረበ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዉርስ አጣሪዉን ሪፖርት ተከትል ግራ ቀኛቸዉ ያቀረቡትን ክርክር ሲመረምር፣ የአሁን ጣልቃ ገብ ቤተክርስቲያን የክርክሩ ተካፊይ መሆን ለዉሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊና ምቹ መሆኑን እስከገነዖበ ድረስ፣ ፍ/ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.40 (2) መሰረት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት ወደ ክርክሩ እንዱገባ በማድረግ በቀረበዉ ሪፖርት ላይ አስተያየቱን እንዱሰጥ በማድረግ ጉዲዩን በመመርመር በሕጉ አግባብ ተገቢ ነዉ ያለዉን ብይን ወይም ዉሳኔ መስጠት ይገባዉ ነበር። ነገር ግን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ጣልቃ ገብ የክርክሩ ተካፊይ ባልሆነበት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.40 (2) መሰረት ወደ ክርክሩ እንደገባ ክርክሩን እንዱያቀርብ ባላደረገበት ሁኔታ፣ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ሶስት ክፍልች ቤት እና ይዜታዉ የዉርስ ሀብት ሳይሆን የአሁን ጣልቃ ገብ ቤተክርስቲያን ንብረት ነዉ በማለት መወሰኑ፣ የክርክሩ ተካፊይ ላልሆነ እና ዲኝነት ላልጠየቀ አካል ዉሳኔ መስጠቱን የሚያሳይ ነዉ። ይህ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.182 (2) ድንጋጌ የሚቃረን አካሄድና ዉሳኔ አሰጣጥ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም። ከዘህ አንጻር የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመር የሥር ፍ/ቤት በዉሳኔዉ የፈጸመዉን ስህተት ማረም ሲገባዉ ዉሳኔዉን በትዔዙዛ ማጽናቱ ሕጉን የሚቃረን አካሄድና ዉሳኔ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በዘህ ጉዲይ የአሁን ጣልቃ ገብ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት የክርክሩ ተሳታፉ ሳያደርጉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.142796 በ16/2/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.205535 በ17/9/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዖጋዉን መዛገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተጠቀሰዉ መሰረት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.40 (2) መሰረት የክርክሩ ተሳታፉ እንዱሆን በማድረግ፣ የዉርስ አጣሪዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ የበኩለን አስተያየትና ክርክር እንዱያቀርብ በማድረግ፣ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር፣ በሕጉ አግባብ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻላል።
መዛገቡ ተዖግቷል።
No topics extracted.