No summary available.
የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ወ/ሮ ጽጌ ወርቁ፡- ቀርበዋል ተጠሪ- አቶ ኢሳያስ ተገኝ፡- አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርደ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ የጉዲዩም አመጣጥ ሲታይ በግራ ቀኝ መካከል ተደርጎ የነበረዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት የስጦታ እና የሽያጭ ውልች በአመልካች ጥያቄ መነሻነት ሚያዛያ 02 ቀን 2005 ዓ.ም እንዱፈርስ ተወስኗል። ከዘህ በኋላ አመልካች የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ የውለ መፍረስ ውጤት በውሳኔው ላይ ያልተካተተ እና ይህም ለአፈፃፀም የሚያስቸግር በመሆኑ ለአፈፃፀም ችልት ትዔዙዛ ይሰጥልኝ ሲለ ጠይቀዋል።
የአመልካችን አቤቱታ የመረመረው የስር ፍርድ ቤትም ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ውሳኔ የተሰጠው አመልካች በጠየቁት ዲኝነት መሰረት ሲሆን አመልካች የጠየቁት ዲኝነት ደግሞ ውለ ይፍረስልኝ የሚል ብቻ እንጂ ቤቱን ተጠሪ ያስረክበኝ የሚል አይደለም፤ አመልካች ቤቱ እንዱለቀቅላቸው ባልጠየቁበትና ይህም ባልተወሰነበት፣ እንዱሁም የአፈፃፀም ችልቱ ውሳኔው ግልጽ አይደለም የሚል ጥያቄ ባላቀረበበት አመልካች ትዔዙዛ እንዱሰጥ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገቢነት የለውም በማለት አቤቱታቸውን ውድቅ አድርታል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ለዘህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ የስር ፍርድ ቤት ለአፈፃፀም ችልቱ ትዔዙዛ እንዱሰጥልኝ አቤቱታ ያቀረብኩት ውሳኔ እንዱፈፀምልኝ ለአፈፃፀም ችልት አቤቱታ አቅርቤ የአፈፃፀም ችልቱ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስፈፀም እንደማይቻል ገልጾ መዛገቡን የዖጋው በመሆኑ ነው፤ የስር ፍርድ ቤትም በውሳኔው ላይ ያለውን ክፍተት ከፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1815 አንፃር የውለ መፍረስ ውጤት ምን እንደሆነ በማሳየት የአፈፃፀም ችልቱ ውሳኔውን የሚያስፈጽምበትን ሁኔታ መግለጽ እየተገባው ትዔዙዛ ላሰጥ አይገባም በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተፈፀመው ውል ፈራሽ ነው ከተባለ በኋላ ግራ ቀኙ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዱመለሱ ሳይወሰን መታለፈ ውሳኔው ሉፈፀም የሚችል መሆን አለመሆኑ መጣራት አለበት ተብል ስለታመነበት ለዘህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዘሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ሐምል 15 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሱ ለአፈፃፀም ክርክሩ መነሻ የሆነው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ አመልካች ቅሬታ ካላቸው በይግባኝ እንዱታረም ከመጠየቅ በስተቀር ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት ውሳኔው እንዱቀየር በአቤቱታ መጠየቅ አይችለም፤ ቤቱን ለመረከብ በግልጽ የተጠየቀ ዲኝነትም አልነበረም፤
ውለም ፈራሽ ከተደረገ በኋላ ቤቱን ለመረከብ አመልካች በልላ መዛግብ ክስ አቅርበው የቤቱ ባለቤት የሆነው የቦላ ክ/ከተማ ጣልቃ ገብቶ በቤቱ ላይ ያለውን መብት አስረድቶ የተወሰነለት በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዖው ጭብጥ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ለዘህ ሰበር መነሻ የሆነዉ አመልካች የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ለስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ሚያዛያ 02 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በዋለዉ ችልት የቤት ሽያጭ/ስጦታ ዉለ እንዱፈርስ የወሰነ ቢሆንም ዉጤቱን በተመለከተ በዉሳኔዉ የተገለጸ ነገር ባለመኖሩ ለአፈፃፀም አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰዉ ፍርድ ቤቱ ለአፈፃፀም ችልቱ ትዔዙዛ እንዱሰጥ በመጠየቃቸዉ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ ሲያደር የጠቀሰዉ ምክንያትም አመልካች ዉለ እንዱፈርስ ቀደም ሲል ክስ ሲያቀርቡ ዉለ ፈራሽ ሆኖ ቤቱንም ተጠሪ እንዱያስረክባቸዉ እንዱወሰን መጠየቅ ሲገባቸዉ ያልጠየቁ ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክቡ የሚል ዉሳኔም ባልተሰጠበት ሁኔታ የአፈፃፀም ትዔዙዛ ይሰጥልኝ በማለት አቤቱታ ማቅረባቸዉ ተገቢነት የላለዉ መሆኑን ነዉ።
በእርግጥ ምንም እንኳ ዉል እንዱፈርስ ክስ የሚያቀርብ ሰዉ ተከሳሽ በዉለ መሰረት የያዖዉን ንብረት እንዱያስረክበዉ ዲኝነት መጠየቅ ሳያስፈልገዉ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ዉለ እንዱፈርስ ዉሳኔ ሲሰጥ በዉለ ምክንያት ግራ ቀኝ የተቀባበለትን ነገር አንደ ለላላኛዉ እንዱመልስ ወይም ግራ ቀኝ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ የመወሰን ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1815 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ የምንገነዖበዉ ነዉ። ከዘህ አንፃር ሲታይ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ቀደም ሲል የዉል ይፍረስልኝ ክስ ሲያቀርቡ ተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክቧቸዉ ጭምር ዲኝነት መጠየቅ ነበረባቸዉ የሚለዉን እንደ አንድ ምክንያት መጥቀሱ ሉታረም የሚገባዉ ነዉ። በልላ በኩል ፍርድ ቤቱ ሚያዛያ 02 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉ ዉል እንዱፈርስ ሲወስን ተጠሪ በዉለ መሰረት የያዘትን ቤት (ካለ) ለአመልካች እንዱመልሱ የሚል ግልጽ ዉሳኔ አልሰጠም።
ፍርድ ቤቱ ይህን አለመወሰኑ ስህተት ነዉ ለማለት ይቻላል። በልላ በኩል የፍርድ ቤት ዉሳኔ መብቴን ነክቷል የሚል ሰዉ እንደሁኔታዉ በይግባኝ ወይም ፍርደን/ዉሳኔዉን በሰጠዉ ፍርድ ቤት አቤቱታዉን አቅርቦ ማሳረም የሚችልበት ሥርዓት በሀገራችን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ተቀርፆ እናገኛለን። በዘህም መሰረት ፍርድን/ዉሳኔን ፍርደን/ዉሳኔዉን በሰጠዉ ፍርድ ቤት በእራሱ ማሳረም የሚቻልባቸዉ ሥርዓቶችም አንደኛ በህጉ አንቀጽ 6 ላይ በተመለከተዉ አግባብ የሚቀርብ የዲግም ዲኝነት ጥያቄ ሲሆን፣ ሁለተኛ በአንቀጽ 207-211 ላይ የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲኖሩ እና ሦስተኛ በአንቀጽ 358 መሰረት በሦስተኛ ወገን የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ናቸዉ። ስለሆነም ፍርድ/ዉሳኔ እንዱታረም ፍርደን/ዉሳኔዉን ለሰጠዉ ፍርድ ቤት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሚኖረዉ ከእነዘህ ሦስቱ ዉስጥ አንደን የሚያሟላ ሆኖ ሲገኝ ነዉ። አመልካች ዉሳኔዉን ቀደም ሲል ለሰጠዉ ፍርድ ቤት ለዘህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነዉን አቤቱታ መሰረት ያደረጉት በህጉ አንቀጽ 6 እንዱሁም 358 ስር የሚወድቅ አይደለም። በህጉ አንቀጽ 208 ስር የሚወድቅ ነዉ ለማለትም፣ በዘህ ድንጋጌ መሰረት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሚኖረዉ እና ፍርድ ቤቱም ተቀብል ፍርደን/ዉሳኔዉን ማረም የሚችለዉ ፍርደ/ዉሳኔዉ የአፃፃፍ ስህተት፣ የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበ እና ባለማስተዋል የተዖለለ ስህተት የተፈጸመበት ሲሆን ነዉ። ይሁንና በተያዖዉ ጉዲይ ፍርድ ቤቱ ዉል እንዱፈርስ ወስኖ ንብረቱን አስመልክቶ ሳይወስን ማለፈ ስህተት ነዉ ቢባል እንኳ ይህ ስህተቱ ከአፃፃፍ ጉድለት ወይም ባለማስተዋል የተዖለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት ነዉ ለማለት የሚቻል ባለመሆኑ በአንቀጽ 208 ስር የሚወድቅ አይደለም። በመሆኑም አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ባለመቀበል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጸናዉ ዉሳኔ ላይ በዘህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘንም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዘህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.