No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካቾች ሕዲር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ተክተው የሚከራከሩላቸው ም/ኮ/ር አብርሃ እቁባይ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካቾች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
የስር ከሳሽ በቀን 20/03/2009 ዓ.ም የተጻፈ የክስ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ ይህ ክስ በቀን 05/07/2010 ዓ.ም የተሻሻለ መሆኑን፤ በቀን 21/06/2011 ዓ.ም ደግሞ በድጋሚ ተሻሽል የቀረበ መሆኑን መዛገቡ ያመለክታል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት በሰጠው ፍርድ ላይ ከሳሽ በቀን 05/07/2010 ዓ.ም/ ለመጀመሪያ ጊዚ የተሻሻለው/ ከመዖገባ በኋላ አሻሽለው ያቀረቡት ክስ ይዖት እና አመልካቾች ለዘሁ ክስ በቀን 05/08/2010 ዓ.ም የሰጡትን መልስ ይዖት ከመዖገበ በኋላ የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ከከሳሽ በተሰጠ ውክልና መሰረት ቤቱ ከ1ኛ አመልካች ወደ 2ኛ አመልካች በሽያጭ የተላለፈ መሆኑ የተገለጸ ቢሆንም የሽያጭ ውለ በማስረጃነት አልቀረበም፤ በቤቱ ማሕደር ውስጥ ያለት ሰነድች የሚያሳዩት ቤቱ በከሳሽ ስም የሚገኝ መሆኑን እንጂ አመልካቾች አድርገነዋል የሚለት የሽያጭ ውል የለም፤ ከሚመለከታቸው የአስተዲደር አካላት የቀረቡት የቤቱ ማሕደሮች የቤቱ ባለይዜታ ከሳሸ መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው፤ ስለሆነም አመልካቾች ቤቱን ለቀው ለከሳሽ ሉያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል።
አመልካቾች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ክሱ ለመጨረሻ ጊዚ የተሻሻለው በቀን 21/06/2011 ነው፤ ክሱ የተሻሻለው ቀደም ሲል ከሳሽ የነበሩት ሰው ስለሞቱ እና ወራሻቸው ስለተተካ ነው፤ ሆኖም በሁለቱም ክሶች ላይ የተጠየቀው ዲኝነት ምንም ዓይነት ለውጥ የላለው ነው፤ የስር ፍርድ ቤት በቀን 05/07/2010 ዓ.ም የቀረበውን ክስ መነሻ ቢያደርግም ማስረጃው ሲመረመር የአመልካቾች መልስ እና ማስረጃ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከደረሰበት መደምደሚያ መረዲት ተችሎል፤ አመልካቾች መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጡት መልስ የሽያጭ ውለን በማስረጃነት አልጠቀሱትም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ቤቱን እንዱያስረክቡ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት የአመልካቾችን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት በትዔዙዛ ሰርዜታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዖቱም፡- አከራካሪውን ቤት 1ኛ አመልካች ለ2ኛ አመልካች ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገ እና በሰነድች ማረጋገጫ ጽ/ቤት በተመገበ የሽያጭ ውል የሸጡ ስለመሆኑ 2ኛ አመልካች ሚያዛያ 08 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰጠሁት መልስ ጋር ተያይዝል፤ ማስረጃው አልቀረበም ቢባል እንኳን ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ሲባል ፍርድ ቤቱ ሉያስቀርበው ይገባ ነበር፤ የስር ፍርድ ቤት የሽያጭ ውለ በማስጃነት ቀርቦለት ሳለ በግራቀኙ መካከል የሽያጭ ውል ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም በማለት ቤቱን ለተጠሪ እንድናስረክብ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በ1ኛ እና በ2ኛ አመልካች መካከል ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም የተፈጸመ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን ሚያዛያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም ካቀረቡ መልስ ጋር በማያያዛ ያቀረቡ መሆናቸው በተገለጸበት የሽያጭ ውል አልቀረበም በማለት አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ የመወሰኑን አግባብነት ከመሰረታዊ የክርክር አመራር መርሕ ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት በሰጡት መልስ የሽያጭ ውለን በማስረጃነት አላቀረቡም፤ 1ኛ አመልካች ለመጀመሪያው ክስ በሰጡት ምለሽ ተከሳሽ አከራካሪውን ቤት ታሕሳስ 30 ቀን 2000 ዓ.ም መሸጣቸውን የገለጹ ሲሆን በዘሁ ምላሽ ላይ ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ቤቱን 2ኛ አመልካች መግዙታቸውን መግለጻቸው ሁለት ውል እንዲለ የሚያሳይ ሲሆን በማስረጃ ዛርዛሩ ላይ ግን አንድም ውል አላያያዘም፤ የተሻሻለው ክስ ከቀረበ በኋላ አመልካቾች ተጣምረው ተከሳሽ ሆነዋል፤ የሁለቱም አመልካቾች ጠበቆች በጋራ ፈርመው በሰጡት ምላሽ ከማን እና መቼ ቤቱን እንደገዘ አልገለጹም የሽያጭ ውለንም በማስረጃነት አላቀረቡም፤ ስለሆነም ይህንኑ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
No topics extracted.
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል። የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዖውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
በዘህ ችልት ትዔዙዛ መሰረት የቀረበውን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመ. የሆነውን መዛገብ እንደተመለከትነው፡-የሥር ከሳሽ የነበሩት ም/ኮ/ር አብርሃ እቁባይ በአሁን 1ኛ አመልካች ላይ ብቻ ክስ አቅርበው የነበሩት ሕዲር 20 ቀን 2009 ዓ.ም መሆኑን፤
ይህ ክስ በመጀመሪያ መጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ.ም የተሻሻለ መሆኑን፤ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በድጋሚ ተሻሽል የቀረበ መሆኑን፤ አመልካቾች ለመጀመሪያ ጊዚ መጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ.ም ተሻሽል ለቀረበው ክስ በየፉናቸው መልስ የሰጡት ሚያዛያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም መሆኑን እና ከዘህ መልሳቸው ጋር 2ኛ አመልካች በአከራካሪው ቤት ላይ ተደርጓል የተባለውን የሽያጭ ውል እና ቤቱ በስማቸው የተመዖገበ መሆኑን የሚያሳይ የይዜታ ማረጋገጫ ማስረጃ ያቀረቡ መሆኑን፤ ለሁለተኛ ጊዚ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ተሻሽል ለቀረበው ክስ ደግሞ አመልካቾች በጋራ በመሆን መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም መልስ የሰጡ መሆኑን እና ከዘሁ መልሳቸው ጋር በ2ኛ አመልካች ስም የተመዖገበ የይዜታ ማረጋገጫ የምስክርነት ወረቀት በማስረጃነት ያቀረቡ ሲሆን የሽያጭ ውለ ግን በማስጃነት ያልቀረበ መሆኑን፤ ፍርድ ቤቱም ለመጀመሪያ ጊዚ መጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ.ም ተሻሽል የቀረበውን ክስ እና አመልካቾች ለዘሁ ክስ ሚያዛያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጡትን መልስ መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የሰጠ መሆኑን መዛገቡ ያመለክታል።
በመሰረቱ አንድ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 መሰረት ተሻሽል እንድቀርብ ፍርድ ቤቱ ፈቅድ ክሱ ተሻሽል በቀረበ ጊዚ ቀድሞ የነበረውን ክስ ቀሪ የማድረግ ውጤት ያለው ሲሆን ፍርድ ቤቱም በጉዲዩ ላይ ውሳኔ ላሰጥ የሚችለው የተሻሻለውን ክስ እና ተሻሽል በቀረበው ክስ ላይ ተከሳሹ የሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 ድንጋጌ ይዖት መገንዖብ ይቻላል።
በያዛነው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው ለመጀመሪያ ጊዚ መጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ.ም ተሻሽል የቀረበውን እና ለዘሁ ክስ በየፉናቸው ሚያዛያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጡትን መልስ መሰረት በማድረግ ነው። ሆኖም ተጠሪ ያቀረበው ክስ ለሁለተኛ ጊዚ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ተሻሽል የቀረበ እና ለዘሁ ክስ አመልካቾች በጋራ በመሆን መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም መልስ የሰጡ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ክሱ ከመሻሻለ በፉት ቀርቦ በነበረው እና ክሱ ከተሻሻለ በኋላ ቀሪ የሆነውን የግራቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ነው። ስለሆነም በዘሁ አግባብ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ሥርዓት ሥሕተት የተፈጸመበት ነው። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ መስጠት የሚገባው ተጠሪ በድጋሚ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም አሻሽለው ያቀረቡትን ክስ እና ለዘሁ ክስ አመልካቾች በጋራ በመሆን መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጡትን መልስ መሰረት በማድረግ ላሆን ይገባል ብለናል።
በልላ በኩል የሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሉያስረክቡ ይገባል ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰ ቢሆንም 2ኛ አመልካች ቤቱ ከ1ኛ አመልካች በሽያጭ ተላልፍልኛል በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም የሽያጭ ውለን በማስረጃነት አላቀረቡም በማለት ነው። ሆኖም አመልካቾች ምንም እንኳን በድጋሚ ተሻሽል ለቀረበው ክስ መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም መልስ ሲሰጡ የሽያጭ ውለን በማስረጃነት ያላቀረቡት ቢሆንም መጋቢት 05 ቀን 2010 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዚ ተሻሽል ለቀረበው ክስ 2ኛ አመልካች ሚያዛያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም መልስ ሲሰጡ በቤቱ ላይ ተደርጓል የሚለትን የሽያጭ ውል እና በ2ኛ አመልካች ስም የተመዖገበ የይዜታ ማረጋገጫ የምስክርነት ወረቀት በማስረጃነት ያያዘት መሆኑን መዛገቡ የሚያመለክት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ሲል ይህን ማስረጃ መመልከት እና የማስጃውን ትክክለኛነት አግባብነት ያለውን ትዔዙዛ በመስጠት ማስረጃውን ከሰጠው አካል ተጣርቶ እንዱቀርብለት በማድረግ መወሰን ይገባው ነበር። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዘህ አግባብ በማየት መወሰን ሲገባው አመልካቾች የሽያጭ ውለን በማስረጃነት አላቀረቡም በማለት ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 26/06/2012 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 11/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዖጋውን መዛገብ እንደገና በማንቀሳቀስ ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው መንገድ ጉዲዩን አጣርቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ት ዔ ዙ ዛ -የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዛገብ የሆነው መዛገብ ወደመጣበት ይመለስ።