No summary available.
ቀን፡-29/03/2014ዓ.ም ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡ አቶ ረጋሳ ጉርሙ ጠበቃ ጋዱሳ ቡታ ቀረቡ ተጠሪ፡ ወ/ሮ ዖነበች ገ/መንፈስ- ጠበቆች ዖበነ ፍቅሬ እና አዱሱ አየነው ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወዉ ጉዲይ ላይ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም ተብል የተሰጠዉን ብይን ለማስለወጥ ነዉ።የክርክሩ መነሻ የቤት ሽያጭ ውል የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላይ የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ከሟች ባለቤታቸው አቶ ተሾመ አፈወርቅ ጋር በመሆን በቀን 06/12/1996 ዓ.ም በአ/አ/ከ/ቂ/ክ/ከተማ ወረዲ 02 የቤት ቁጥር 047 የካርታ ቁጥር ሴ.ኬ.አሲ/02/31/1229/001040/01 የሚታወቅ መኖሪያ ቤት ለአመልካችና ለአቶ ፀጋዬ ገ/መንፈስ ሽጠዋል፣ቤቱን እንዱለቁ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/153563 ቤትን አንዱለቁልኝ ክስ አቅርቤ ፍ/ቤቱን አስፈቅጄ ያነሳሁት ቢሆንም ተጠሪ ቤቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ተጠሪ ቤቱን ለቀው እንዱወጡና እንዱያስረክቡኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋዋል።ተጠሪ በበኩላቸዉ በቀን 12/05/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረበውት መልስ አመልካች በመ/ቁ.153563 ላይ ቤቱን ከተጠሪ ለመረከብ ተመሳሳይ ክስ አቅርቦ አመልካቹ በውለ በተመለከተው ጊዚ የሽያጭ ገንዖቡን ባለመክፈለ የውል ግዳታውን ስላልተወጣ የባለቤትነት መብት ስለላው ለቀን ልናስረክብ እንደማይገባ መከራከሪያ አቅርበን እያለ አመልካች በቀን 10/04/2011ዓ.ም በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.278 መሰረት በፈቃደ ክሱን ለመተው ማመልከቻ አቅርቦ ፍ/ቤቱም በ11/04/2011ዓ/ም ከሻስ ክስ በማቋረጡ ለተጠሪ ወጪና ኪሳራ እንዱከፍል በማለት መዛገቡን ዖግቷል፣ስለሆነም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወዉ ጉዲይ አዱስ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም፣በተጨማሪም የቤት ሽያጭ ውለ ተፈጽሟል የተባለዉ ከ16 እና ከ17 ዓመታት በፉት ስለሆነ በፍ/ህ/ቁ/1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዲል፣እንዱሁም በፍ/ህ/ቁ. 2892(3) መሰረት ሻጩ ውለን እንደ ውለ ቃል ከመፈፀም መዖግየቱን ከተረዲበት ጊዚ ጀምሮ እስከ 1(አንድ) ዓመት ድረስ ውለ እንዱፈፀምለት ካልጠየቀ በቀር ገዠው ውለ በግዳታ እንዱፈፀም የማድረግ መብቱን ያጣል፣ስለዘህ በ1 (አንድ) ዓመት ውስጥ ስላልጠየቀ በይርጋ ውድቅ ይደረጋል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በፍሬነገር ረገድ አማራጭ ክርክር ማቅረባቸዉን መዛገቡ ያሣያል።
ፍ/ቤቱም በተጠሪ በኩል የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የግራ ቀኝ ክርክር ሰምቶና መርምሮ በመጀመሪያዉ ክስ አመልካች ክሱ እንዱቋረጥ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ላላ ጊዚ ክስ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ እንዱፈቀድላቸው የጠየቁ ሳይሆን ክርክሩ እየገፊ በመምጣቱ ውጣ ውረድች ስለበዙባቸው ክሱን ማቋረጥ እንደፈለጉ የሚያሳይ ነው።ፍ/ቤቱም ከሳሽ(የአሁኑ አመልካች) ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል ከሳሽ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278 /2/ መሰረት በማየት ጉዲዩን በተመለከተ አዱስ ክስ እንዱያቀርቡ አልፈቀደም።እንዱህ ከሆነ አመልካች ክሱን የተውት ከፍ/ቤት ፈቃድ ውጭ እንደሆነና አመልካች አስፈላጊውን ኪሳራ ለተጠሪ ከፍለው መዛገቡ መዖጋቱን እንዱሁም አመልካችም ጉዲዩን በተመለከተ አዱስ ክስ ማቅረብ እንደማይችል በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.279(1) ስር ተደንግጓል፣ስለዘህ አመልካች አሁን አዱስ ክስ ማቅረባቸው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(2) እና 279(1) መሰረት አግባብነት የለውም በማለት ክሱን ውደቅ አድርጓል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ይግባኙ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰት መዛገቡን ዖግቷል።የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዘህ ላይ ነዉ።
አመልካች በዘህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ይዖት ባጭሩ፤ቤቱን እንዱለቁልኝ ሲጠይቅ ተጠሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.153563 ላይ ክስ መስርቼ ስንከራከር ከቆየን በኋላ ፍ/ቤቱን አስፈቅጄ ክስ ያቋረጥኩበት ምክንያት ተጠሪ የባለቤቴ እህት በመሆናቸው እና ተጠሪ የሽያጭ ውል ይፍረስልኝ ጥያቄም ውለ ህጋዊ ነው ተብል ስለተወሰነ ከዘህ በኋላ ተጠሪ አለቅም የሚለበት ምንም ህጋዊ ምክንያት የለም በፈለኩ ጊዚ ይለቁልኛል በሚል እሳቤ ፍ/ቤት አስፈቅጄ ክሱ ተቋርጧል።
ፍ/ቤት ሳላስፈቅድ በራሴ ፈቃድ ለመተው ቢፈልግ ኖሮ ፈቃድ ለመጠየቅ አቤቱታ ለፍ/ቤት ባላቀረብኩ ነበር።የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 279(1) የሚመለከተው በራሱ ፈቃድ ፍ/ቤትን ሳያስፈቅድ ክሱን የተወ ወይም ያቋረጠ ከሳሽን ሲሆን እኔ ግን ለፍ/ቤት አመልክቼ ፍ/ቤቱም ክሴን እንዱተው የፈቀደልኝ መሆኑን የቀረበው ማስረጃ ያረጋግጣል።ስለዘህ አዱስ ክስ ማቅረብ አትችልም በማለት የተሰጠው ብይን የንብረት ባለቤት የመሆን መብቴን የሚቃረን ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ብይን ነው በማለት ብይኑ እንዱታረም አመልክተዋል።
No topics extracted.
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ለክርክር ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ግራ ቀኙ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ሉፈርስ አይገባም በሚል የተሰጠ ውሳኔ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ተጠሪ ቤቱን እንዱለቁ አመልካች በስር ፍ/ቤት ተጠሪ ላይ ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ ቀደም ሲል ተጠሪ ቤቱን ይልቀቁልኝ ብለው ክስ አቅርበው በራስዎ ፈቃድ አመለክተው እንዱቋረጥ አድርጓል በማለት አቤቱታቸው ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ 278 እና 279 ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ታዝል።
ተጠሪ በበኩላቸዉ በቀን 30/11/2013ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ በስር ፍርድ ቤት እየተከራከርን እያለ አመልካች ክሱን መተዋቸውን ለፍ/ቤት አመልክተዋል፣ነገር ግን ወደ ፉት በሙለ ወይም በከፉል አዱስ ክስ የማቅረብ መብት አልጠየቁም፣አላስጠበቁም፤የጀመርኩት ክስ በሙለ ፍቃድ ማቋረጠን አረጋግጣለሁ የሚል እንጂ አዱስ ክስ ለማቅረብ አይደለም፣የፍ/ቤቱም ትእዙዛ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ክስ መቋረጡ ያረጋግጣል።በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ክስ ሲቋረጥ ወደፉት ክስ ለማቅረብ ያልተፈቀደለት መሆኑን በፋደራል ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ አስገዲጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፣አዱስ ክስ ማቅረብ የሚቻለው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(2) መሰረት በፍ/ቤት ፈቃድ ሲቋረጥ ነው።ይርጋን በተመለከተ አመልካች ያቀረበው የመፊለም ክስ ሳይሆን በሽያጭ ውል መነሻ ተገደው ቤቱን እንዱያስረክቡኝ የሚል ስለሆነ እና በስር ፍ/ቤት ያልተነሳና በዘህ ረገድም የህግ ስህተት እንዲልተፈፀመ ስለተረጋገጠ አቤቱታው ውድቅ ሆኖ የስር ፍ/ቤት ውሰኔ እንዱፀና በማለት ተከራክረዋል።አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዛገቡ ጋር ተያይዝል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረናል።መዛገቡ መርምረን እንደተገነዖብነዉ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ተጠሪ የሸጡላቸዉን ቤት ለቀዉ እንዱያስረክቧቸዉ እንዱወሰን የሚል ሲሆን ከዘህ ቀደም ተመሳሳይ የዲኝነት ጥያቄ በመ/ቁ.153563 ላይ አቅርበዉ አመልካቹ ክሱን ለመተዉ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት መዛገቡ የተዖጋ መሆኑ አላከራከረም።ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ክሱን ሲያቋርጡ አዱስ ክስ እንዱያቀርቡ ፍርድ ቤቱ አልፈቀደላቸዉም በማለት ነዉ።አመልካች አጥብቀዉ የምከራከሩት ክሱን ያቋረጥኩት ፍርድ ቤቱን አስፈቅጄ ስለሆነ አዱስ ክስ ከማቅረብ አያግደኝም በማለት ነዉ።
በህግ በልላ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሒብሓር ክርክር የሚመራዉ በፍትሒብሓር ስነስርዓት ህግ በተደነገገዉ አግባብ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 1 ድንጋጌ ይዖት የምንገዖበዉ ጉዲይ ነዉ።የፍትሒብሓር ስነስርዓት ህግ ዓይነተኛ ኣላማ የፍትሒብሓር ክርክር የሚመራበትን ስርዓት በመደንገግ የፍርድ ሂደት በፍትሃዊነት እንዱመራ በማድረግ የተከራከሪ ወገኖችንም ሆነ የፍርድ ቤቱን ሀብት እና ጊዚ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክሩ እልባት እንዱያገኝ ማስቻል ነዉ።ይህንኑ ዓላማ ለማስካት ያስችላለ ተብለዉ ከተዖረጉት ስርዓቶች አንደ ከሳሽ ወገን በአንድ ጉዲይ ላይ ተደጋጋሚ ክስ እንዲያቀርብ ለመከላከል የተዖረጋዉ ስርዓት የሚመለከት ነዉ።በዘህ መዛገብ ለተያዖዉ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ ከሳሽ ወገን ክሱን ለመተዉ መቻለና ዉጤቱን የሚመለከተዉ ድንጋጌ ነዉ።
አንድ ክስ ከቀረበ በኋላ በማናቸዉም ጊዚ ከሳሹ ያቀረበዉን ክስ በማንሳት ከተከሳሾቹ አንደን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ከክሱ ዉጭ ለማድረግ ወይም ያቀረበዉን ክስ በሙለ ወይም በከፉል ለመተዉ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1/ ስር የተመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱ አቤቱታዉን ተቀብል ትእዙዛ በሚሰጥበት ጊዚ ከሳሽ ወገን ክሱን ለማንሳት ወይም ለማቋረጥ የጠየቀበትን ምክንያት መርምሮ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ከሳሹ አዱስ ክስ ለማቅረብ የሚችልበትን መብት መጠበቅ የሚችል ስለመሆኑ በዘሁ ድንጋጌ ንኡስ አንቀጽ (2) ስር ተመልክቷል።ከዘህ ድንጋጌ ይዖት መገንዖብ እንደሚቻለዉ በአንድ በኩል ከሳሹ በግል ጉዲዩ ላይ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ ክሱን ለመተዉ የሚችል መሆኑን በልላ በኩል ከሳሹ በፈቃደ በተወዉ ነገር ላይ አዱስ ክስ ለማቅረብ የሚችለዉ ፍርድ ቤት መብቱን የተጠበቀለት ሲሆን ብቻ መሆኑን ነዉ።በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/2/ ስር እንደተመለተዉ ከሳሹ በልላ ጊዚ አዱስ ክስ እንዱያቀርብ ሉፈቅድለት የሚችለዉም በክሱ አቀራረብ ስርዓት ጉድለት ያለበት ሲሆን ወይም አዱስ ክስ ለማቅረብ ሉያስፈቅድለት የሚችል በቂ ምክንያት ሲኖር እና ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ተቀብል መብቱን የጠበቀለት እንደሆነ ነዉ።በልላ አገላለጽ በቁጥር 278/2/ የተነገረዉን ባለመጠበቅ ከሳሹ ከፍርድ ቤት ፈቃድ ሳይቀበል ክሱን በሙለ ወይም በከፉል የተወ እንደሆነ አዱስ ክስ ለማቅረብ እንደማይችል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 289/1/ በግልጽ ተደንግጓል።ስለዘህም የቀረበዉ አዱስ ክስ ተገቢነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነዉ ክሱ በፍርድ ቤት ፈቃድ ወይም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ የተቋረጠ ወይም የተተወ መሆን አለመሆኑ በመመርመር እንደሆነ ያስገነዛበናል።
በተያዖዉ ጉዲይ ከስር ፍርድ ቤት መዛገብ ይዖት መገንዖብ እንደተቻለዉ አመልካች ቀደም ሲል በዘሁ ጉዲይ በመ/ቁ/ 153563 ላይ ያቀረበዉን ክስ ለመተዉ መፈለጉን ገልጾ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበዉ ማመልከቻ መሰረት መዛገቡ የተዖጋ ስለመሆኑና መዛገቡም የተዖጋዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ 278/1/ መሰረት መሆኑን ያመላክታል።የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ መርምሮ አመልካች ክሱን የተወዉ ላላ ጊዚ አዱስ ክስ ለማቅረብ ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ አግኝቶ አለመሆኑንና ያቀረበዉም ማመልካቻ ፈቃድ ለመጠየቅ ሳይሆን ክሱን መቋረጡን ፍርድ ቤቱ እንዱያዉቀዉ ለማድረግ የቀረበ ስለመሆኑ ይዖቱን ጭምር በመመርመር ያረጋገጠዉ ጉዲይ ነዉ።አመልካች አሁንም የሚከራከረዉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ማመልካቻ ፍርድ ቤቱን ለማሳወቅ ተደርጎ መወሰደ ስህተት ነዉ የሚል ነዉ።ይሁንና መዛገቡ እንደሚሳየን አመልካች በቀን 10/04/2011ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ማመልከቻ ይዖት ‹‹…ክርክሩ እየገፊ በመምጣቱ ከሳሽ አላስፈላጊ ዉጣ ዉረድችን በመተዉ የጀመርኩትን ክስ ክርክር በሙለ ፈቃድ ክሴን ለማቋረጥ …›› በሚል በቃለ መኃላ ተደግፍ የቀረበ አቤቱታ መሆኑን የሚገልጽ እንጂ በጉዲዩ ላይ ላላ ጊዚ አዱስ ክስ ለማቀርብ የፍርድ ቤቱን ፈቃድ የጠየቀ መሆኑን የሚያሣይ አይደለም።ክሱን ለማቋረጥ ያቀረበዉም ምክንያትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/2/ ስር ከተደነገጉት ምክንያቶች አንደም ስለመኖሩ የማያሳይ ነዉ።ፍርድ ቤቱ ማመልከቻዉን መርምሮ የሰጠዉ ትእዙዛ ይዖትም ክሱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1 መቋረጡን የሚገልጽ እንጂ አዱስ ክስ ለማቅረብ መብት የተጠበቀለት መሆኑን አያሣይም።የመዛገቡ ይዖት ይህንን የሚያሳይ ሆኖ እያለ አመልካች ፍርድ ቤት ፈቃድ አግኝቻለዉ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ መሰረት ያለዉ ሆኖ አላገኝም።ከዘህ አኳያ በተጠሪ በኩል የቀረበዉን መቃወሚያ መነሻ በማድረግ የስር ፍርድ ቤትም መ/ቁ/153563 ላይ የተጀመረዉ ክርክሩ የተቋረጠበትን አግባብ መርምሮ ከሳሹ ክሱን በራሱ ፈቃድ የተወዉ መሆኑን እንጂ በፍርድ ቤት ፈቃድ የተወዉ መሆኑን የሚያሣይ አይደለም የሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱ ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት የለም።እንዱህ በሆነ ጊዚ ደግሞ ከሳሽ ወገን በዘያዉ ጉዲይ ላይ አዱስ ክስ ማቅረብ እንደማይችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 289/1 በግልጽ ደንግጓል።የስር ፍርድ ብይን መሰረቱም ይኸዉ መሆኑን ተገንዛበናል።በመሰል ክርክሮች ላይ ይህ በሰር ችልት የሰጠዉ ዉሳኔም ይህንኑ የሚያጠናክር ነዉ።ሰበር መ/ቁ/116869 ፣158314 እና ላልች መመልከት ይቻላል።
ሲጠቃለል በዘህ ጉዲይ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትእዙዛ ይህንኑ የሥነስርዓት ህግ ድንጋጌ እና በተመሳሳይ ክርክሮች ላይ ሰበር ችልቱ የሰጠዉን ዉሳኔ ያገናዖበ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም።በዘሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/236492 ላይ በቀን 29/09/2012ዓ.ም የሰጠዉ ብይን እና ይህንኑ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/194704 ላይ በቀን 30/04/2013ዓ.ም የሰጠዉ ትእዙዛ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ጽንቷል።
2ኛ/በዘህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል ይመለስ።