አንድን የቀረበ የወንጀል ክስ ለማረጋገጥ የሚያስችለትን ማስረጃዎች የመለየት እና የመወሰን ስልጣኑ የዓቃቤ በመሆኑ ክሱን ያረጋግጡልኛል ያላቸውን ማስረጃዎች እስካቀረበ ድረስ የቀረቡት ማስረጃዎች በእርግጥም ክሱን በህግ በተቀመጠው የማስረዲት ደረጃ የሚያረጋግጡ መሆን ያለመሆናቸው ከሚመዘን በቀር አንድን የማስረጃ አይነት ለይቶ “ካላቀረብክ” ተብል የሚገደድበት የህግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 133፣ 134፣ 141 እና 149(1) በወንጀል ጉዲይ የሚቀርበው ማስረጃ ደግሞ በማስረጃነት እንዲይቀርብ በህግ በልዩ ሁኔታ ካልተከለከለ በቀር ስለ ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሉያረጋግጥ የሚችል ማናቸውም ማስረጃ ላቀርብ የሚችል ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 19(5) እና የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 137 የቀረበን ክስን ለማረጋገጥ ቀርበው ከተሰሙ ምስከሮች ውስጥ የግል ተበዲዮች በማስረጃነት ስለመቆጠራቸው እና ቀርበው ያለመሰማታቸው ላልች ማስረጃዎች እንዲይመዘኑ የማያደርግ እና ተከሳሽም ቢሆን የቀረበውን ማስረጃ በተገቢው ስርዓት ከሚጠይቅ በቀር ተበዲዮች በማስረጃነት ያለመቅረባቸው ለተከሳሽ መስቀልኛ ጥያቄን ከመጠየቅ አንፃር የመብት መጣበብ የሚፈጥር ስላለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/208644 ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
ሁለተኛ አመልካች ደግሞ በመ/ቁ/208645 ላይ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በተመሳሳይ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ በመሆኑ እና ጉዲዩ ለዙህ ሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብም በሁለቱም መዜገቦች ላይ የተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አንድ ዓይነት በመሆኑ ሁለቱ መዜገቦች ቀድሞ በተከፈተው በዙህ መዜገብ ላይ ተጣምረው ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከባድ የውንብድና ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ አመልካቾችን ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)፣ ለ)) እና 671(1(ሀ)) ድንጋጌን ጠቅሶ በአዲማ ልዩ ዝን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። በቀረበው ክስ ውስጥ የአሁን አመልካቾች እንደቅደም ተከተላቸው አንደኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ነበሩ። የክሱም ይዘት ተከሳሾቹ ከላልች ለጊዛው ካልተያዘት ቁጥራቸው ከ3-5 ከሚሆኑ ግብረ-አበራቸው ጋር በመሆን የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌን በመተላለፍ የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው አልያም ለላላ ሰው ለማስገኘት አስበው ህዲር 26/2012 ዓ.ም ከላሉቱ 10፡30 በአዲማ ከተማ አባገዲ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ “ዲዲ ሞል” ተብል በሚጠራው አካባቢ የአሁን አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾች አቶ አሉ መሀመድ የተባለት የግል ተበዲይ “ፍር ራነር” የተባለ እና የሰላዲ ቁጥሩ 128D75 ጅቡቲ፤ የዋጋ ግምቱ ብር 1,300,000(አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ ሽህ ብር) በሆነ መኪና ሁለተኛ የግል ተበዲይ የሆኑትን ወ/ሮ መታሰቢያ ወርቅአገኘሁ የተባለትን ጋቢና አስቀምጠው በማሽከርከር ላይ እያለ አመልካቾች የሰላዲ ቁጥሩ ለጊዛው ባልታወቀ ብረት መልክ ቪትዜ መኪና ተከትለው “መኪናው የተሰረቀ ስለሆነ አቁም!” በማለት በግል ተበዲይ ላይ መንገድ በመዜጋት ካስቆሙት በኋላ አንደኛ አመልካች በሹፋሩ በኩል ሄድ አንደኛ የግል ተበዲይን በቀኝ እጁ አንገታቸውን በማነቅ በግራ እጁ ደግሞ የመኪናውን ሞተር ካጠፊ በኋላ ሁለቱም አመልካቾች ተበዲዩን ጎትተው ከመኪናው በማውረድ መሬት ላይ ከደበደቡት በኋላ አንደኛ አመልካች መኪናው ውስጥ ገብቶ ማንቀሳቀስ ሲጀምር 2ኛ አመልካች በተሸከርካሪው የተሳፊሪ በር በኩል በመግባት ጋቢና የነበረችውን ሁለተኛ የግል ተበዲይን ጎትቶ ከመኪናው ውስጥ ወደ መሬት በመጣል መኪናውን፣ የሁለቱን ተበዲዮች ሁለት ዘመናዊ የእጅ ስልክ እና በክሱ ውስጥ የተጠቀሱትን ልዩ ልዩ ሰነድችን ይዘው ተሰውረዋል፤ በዙሁ ጉዲይ ላይ በፖሉስ ክትትል በመደረግ ላይ እያለ ታሀሳስ 08/2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ የአሁን አመልካቾች እና የስር ፍርድ ቤት 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአንድ መኪና ሆነው፤ 3ኛ እና 6ኛ ተጠርጣሪዎች የነበሩ ደግሞ በልላ መኪና ሆነው በክትትል ላይ የነበሩትን የፖሉስ አባላት ሲከታተሎቸው በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል፤ ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም የአሁን ሁለተኛ አመልካች እና የስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ ተዘረፈ የተባለው መኪና ቴዱ በተባለ ግበረአ-በራቸው እጅ እንደሚገኝ ለፖሉስ ጥቆማ ሰጥተዋል፤ ከዙህ አልፍ ቴዱ የተባለው ግበሬ አበራቸው መኪናው የት እንዲለ ለፖሉስ እንዱያሳውቅ በስልክ በነገሩት መሰረት እነርሱ በፖሉስ ቁጥጥር ስር እንዲለ ቴዱ የተባለው ግለሰብ ታህሳስ 11/2012 ዓ.ም ለፖሉስ ደውል መኪናው በቢሾፍቱ ከተማ ዘቃላ ማዝሪያ በተባለ ቦታ መቆሙን በነገራቸው መሰረት ፖሉሶቹ ከግል ተበዲይ ጋር ሆነው መኪናውን በተባለው ቦታ ቆሞ ያገኙት በመሆኑ ተከሳሾች አባሪ ተባባሪ በመሆን በድርጊቱ እና ድርጊቱ በሚያስከትለው ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው።
በዙሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት ሁለም ተከሳሾች ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ህግ ሶስት የሰው ምስክሮችን እና ድርጊቱ ሲፈፀም የተቀረፀ ቪዱዮ በማስረጃነት አቅርቧል። ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮ አመልካቾች እንዱከላከለ አዞል። የአመልካቾችን መከላከያ ማስረጃን ከሰማ በኋላም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን መርምሮ አመልካቾች የቀረበባቸውን ክስ አልተከላከለም በሚል በተከሰሱበት አንቀፅ ስር ጥፊተኛ ብል እያዲንዲቸውን በ14 (አሥራ አራት) ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኗል። ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ፀንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ነው። አመልካቾች በየራሳቸው ባስከፈቱት መዜገብ ላይ ሰኔ 01/2013 ዓ.ም በተፃፈ የተናጠል የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዙህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
በሁለቱም አመልካቾች በኩል የቀረበው የሰበር ቅሬታ መሰረታዊ ይዘትም በድርጊቱ የግል ተበዲዮች ናቸው የተባለት እና ቀጥተኛ የዓይንም ምስክር የሆኑት ግለሰቦች ቀርበው መሰማት ሲገባቸው “የለም” በሚል ድፍን ያለ መልስ ሳይቀርቡ መቅረታቸው መስቀልኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብታችንን አጧቧል፤ ቀርቦ የተሰማው የዐቃቤ ህግ አንድ የዓይን ምስክርም ወንጀለን ፈፀሙ ያላቸውን ሰዎች “በሰውነት ፈርጠም ያለ ናቸው” በሚል በምልክት ከመግለፅ ባለፈ አመልካቾችንም ሆነ ላልች አባሪዎች ናቸው የተባለትን ለይቶ አላመለከተም፤ የቪዱዮ ማስረጃ የተባለውም በጨለማ የተቀረፀ ሲሆን የሰውን እንቅስቃሴ ከሚያሳይ በቀር የሰዎቹን ማንነት የማያሳይ በመሆኑ አመልካቾች የወንጀል ድርጊቱ ተካፊዮች መሆናችንን የሚያረጋግጥ አይደለም፤
ተዘረፈ የተባለት ንብረቶችም በአመልካቾች እጅ ያልተያዘ ከመሆኑም በላይ በተያዜንበት እለት ከላልች ተከሳሾች ጋር ሆነን ስንቀሳቀስ የነበረው መኪና ለመግዚት እንጂ ተሰረቀ ከተባለው መኪና ጋር በሚገናኝ ምክንያት አይደለም፤ ተፈፀመ በተባለው የወንጀል ድርጊት ውስጥ የአመልካቾች የወንጀል ተሳትፍ ተለይቶ ባልተረጋገጠበት ከመነሻው ክሱን እንድንከላከል መታዘዘ አግባብ አይደለም፤ ያም ሆኖ አቅርበን ባሰማናቸው መከላከያ ምስክሮቻችን ወንጀለ ተፈፀመ በተባለበት ቀን እና ሰዓት በወንጀለ ስፍራ ያልነበርን ለመሆኑ አረጋግጠን እያለን በወንጀል ጥፊተኛ ተብለን መቀጣታችን አግባብ ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ በነፃ ልንሰናበት ይገባል የሚል ነው።
የሁለቱም አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ዐቃቤ ህግ በአሁን አመልካቾችና በዙህ ሰበር ክርክር ባልቀረቡ አባሪዎች ጋር ውንብድና ወንጅል ፈፅመዋል ተብል በቀረበባቸው ክስ አመልካቾች በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፈ ስለመሆኑ ለይተው ባልመሰከሩበት ጥፊተኛ ተብለው ቅጣት የተወሰነበትን አግባብነት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/44031 ላይ ከሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ጋር ተገናዜቦ በዙህ ችልት እንዱመረመር በመደረጉ ተጠሪ በሁለቱም መዜገቦች ላይ የፅሐፍ መልስ እንዱሰጥ ታዞል።
በዙሁ አግባብ ተጠሪ በዙህ መዜገብ ላይ የቀረበውን ክርክር አስመልክቶ ሐምል 27/2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ያቀረበ ቢሆንም በመ/ቁ/208645 ላይ ለቀረበው ጉዲይ የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት መልስ ባለመስጠቱ ይኸው መብቱ ታልፎል። ተጠሪ በዙህ መዜገብ ላይ ለቀረበው ቅሬታ የሰጠው መልስ ፍሬ ቃልም ቀጥተኛ የዓይን ምስክር ከላለ ወንጀል ፈጻሚዎች በልላ ማስረጃ ሉረጋገጥባቸው አይቻልም የሚል ህግ የለም፤ ቀርበው ከተሰሙት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ውስጥ 1ኛው ሁለት ፈርጣማ ሰዎች ከተሰረቀው መኪና ላይ የግል ተበዲዮችን አውርደው ሲጥሎቸውና መኪናውን ይዘው ሲሰወሩ ማየቱን፤ 2ኛ እና 3ኛ ምስክሮች ደግሞ ተጠርጣሪዎቹን በመጠርጠር ይዘው ሲጠይቋቸው ቴዱ ከተባለ ላላ ግለሰብ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ የተሰረቀውን መኪና ማስረከባቸውን እንዱሁም የቪዱዮ ማስረጃ መኪናውን ሰርቀው ሲያመልጡ የሚያሳይ በመሆኑ ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው ተረጋግጧል፤ ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ደግሞ እርስ በራሱ የሚጣረስ በመሆኑ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን የሚያስተባበል ባለመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ውድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉፀና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ ማንም ሰው በወንጀል ህግ ጥፊተኝነቱ ካልተረጋገጠ በቀር በወንጀል ሉቀጣ እንደማይገባ የወንጀል ህግ አንቀጽ 57(1) ይደነግጋል። ወንጀል ፈፀመ ተብል የተከሰሰውን ሰው አስመልክቶ የተከሰሰበት ድርጊት ወንጀል መሆኑን እና ድርጊቱንም የተከሰሰው ሰው የፈፀመው ስለመሆኑ አግባብነት ባለው ማስረጃ የማረጋገጥ ኃላፉነቱ የዐቃቤ ህግ ስለመሆኑ ከወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 133፣ 134፣ 141 እና 149(1) ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በወንጀል ጉዲይ የሚቀርበው ማስረጃ ደግሞ በማስረጃነት እንዲይቀርብ በህግ በልዩ ሁኔታ ካልተከለከለ በቀር ስለ ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሉያረጋግጥ የሚችል ማናቸውም ማስረጃ ስለመሆኑ የኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 19(5) እና የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 137 ድንጋጌ ያስገነዜባል። በልላ በኩል አንድን የቀረበ የወንጀል ክስ ለማረጋገጥ የሚያስችለትን ማስረጃዎች የመለየት እና የመወሰን ስልጣኑ የዐቃቤ ህግ ነው። እናም ክሱን ያረጋግጡልኛል ያላቸውን ማስረጃዎች እስካቀረበ ድረስ የቀረቡት ማስረጃዎች በእርግጥም ክሱን በህግ በተቀመጠው የማስረዲት ደረጃ የሚያረጋግጡ መሆን ያለመሆናቸው ከሚመዘን በቀር አንድን የማስረጃ አይነት ለይቶ “ካላቀረብክ” ተብል የሚገደድበት የህግ አግባብ የለም።
በቀረበው ጉዲይ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማረጋገጥ አለኝ ያለውን የሰው እና የቪዱዮ ማስረጃን አቅርቧል። በእርግጥ ቀርበው ከተሰሙት ምስከሮች ውስጥ የግል ተበዲዮች የለም። እነዙህ ተበዲዮች በማስረጃነት ስለመቆጠራቸው እና ቀርበው ስላልተሰሙበት ምክንያት የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ የሚገልፀው ነገር ባይኖርም አመልካቾች ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ ውስጥ ምስክሮቹ “የለም” በሚል ምክንያት መታለፊቸው ተመልክቷል። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን የግል ተበዲዮቹ ቀርበው ያለመሰማታቸው ላልች ማስረጃዎች እንዲይመዘኑ የሚያደርግ አይለም። አመልካቾችም ቢሆን የቀረበውን ማስረጃ በተገቢው ስርዓት ከሚጠይቁ በቀር ተበዲዮች በማስረጃነት ያለመቅረባቸው መስቀልኛ ጥያቄን ከመጠየቅ አንፃር የሚፈጥርባቸው የመብት መጣበበ የለም። በመሆኑም ከዙህ አኳያ የቀረበውን መከራከሪያ ችልቱ አልተቀበለውም።
ከዙህ በመለስ ያለውን በተመለከተ ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን መርምረውና መዜነው ተገቢ ነው ባለት ድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። ይህ የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ በዙህ ሰበር ሰሚ ችልት ሉለወጥ የሚችለው ውሳኔው በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያላደረገ እንደሆነ፤ ወይም በማስረጃ ምዘና ረገድ መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህ ጥሰት ስለመፈፀሙ ሲረጋገጥ፤ ወይም ማስረጃዎቹ መሰረት ተደርጎ በተሰጠ የህግ ትርጉም ውስጥ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት ሲኖር ስለመሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 78 እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10 ለችልቱ ከተሰጡት የዲኝነት ስልጣን መረዲት ይቻላል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካቾች “ወንጀል ስለመፈፀማችን አልተረጋገጠብንም እንዱሁም “በመከላከያ ማስረጃችን የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃን አስተባብለናል” ከማለት ባለፈ ከላይ በተመለከተው አግባብ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስሀተት ስለመኖሩ የተመለከተ ነገር የለም። በሰበር አጣሪ ችልቱ የተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብም ከማስረጃ ምዘና መርህ ጥሰት አንፃር ቀደም ተብል በዙሁ ችልት የተሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚጠቅስ ቢሆንም ከማስረጃ ምዘና ረገድ የስር ፈርድ ቤቶች የፈፀሙት የምዘና መርህ ጥሰት ተጠቅሶ የቀረበ የስበር ቅሬታ የለም። ከዙህ ይልቅ ማስቀረቢያ ነጥቡም ሆነ የአመልካቾች የሰበር ቅሬታ የግራ ቀኙ ማስረጃ በድጋሚ በዙህ ችልት እንዱመረመርና እንዱመዘን የሚጋብዜ ሆኖ ተገኝቷል። ሆኖም ማስረጃን መመርመር እና መመዘን የዙህ ሰበር ሰሚ ችልት የዲኝነት ስልጣን ባለመሆኑ ይህ የሚሆንበት የህግ አግባብ የለም። ሲጠቃለል በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ጥሰት ተፈፅሟል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ ባለመገኘቱ የአመልካቾች የሰበር ቅሬታ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በመ/ቁ/374045 መጋቢት 07 2012 ዓ.ም እና በመ/ቁ/374399 ላይ መጋቢት 22/2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዚዜ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁር 195(2(ለ(2))) መሰረት ፀንቷል።
ትዕዚዜ
የዙህ ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ከመ/ቁ/208645 ጋር ይያያዜ።
መዜገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.