በስራ ሂደት አስተባባሪ የስራ ሀላፉነት በስራ መዘርዜር አግባብ ስራን አለመስራት ምክንያት የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመ በወ/ህ/አ.420(2) መሰረት የስራ ሀላፉነትን ባለመወጣት የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ እንጂ ስራዎችን መከታተልና መቆጣጠር ሲገባ ይህንን ግዳታ ባለመወጣት በስር የማስተባብር የስራ ሀላፉነት በአግባቡ ባለመቆጣጠር የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመመምራትና የደረሰን ጉዲት በመጥቀስ የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(2) መሰረት በማድረግ ክስ የሚቀርብ የአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ዓ/ህግ እና አቶ አዱስ አለሙ
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- መዓዚ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሀይ መንክር ኑረዱን ከድር እስቲበል አንዶለም አመልካች፡- የአ.ብ.ክ.መ. ጠቅላይ ዓ/ህግ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አዱስ አለሙ - አልቀረቡም መዜገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
በዙህ መዜገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ ከባድ የዕምነት ማጉደል ወንጀልን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ በቀን ሰኔ 23/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት በመሻር ተጠሪን በነጻ ያሰናበተበትን ውሳኔ በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በቀን ነሐሴ 13/2011 ዓ.ም በጻፈው የወንጀል ክስ በአሁን ተጠሪ እና በላልች ሁለት የስር ተከሳሾች ላይ በሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተጠሪ የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/2/ እና የጥሬ ገንዘብ አያያዜ መመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 23/1/ እና 24/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በደብረሲና ጤና አጠባበቅ የግዥ ፊይናንስ ንብረት አስተዲደር ደጋፉ የስራ ሂደት አስተባባሪ በመሆን ስራ ከጀመረበት ታህሳስ 25/2003 ዓ.ም እስከ ግንቦት 17/2011 ዓ.ም ድረስ ሲሰራ በነበረበት ወቅት የስር 1ኛ ተከሳሽን በስሩ የሚያስተባብር እንደመሆኑ በአግባቡ ባለመቆጣጠር የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመመምራት 252,871.60 ብር (ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ሽህ ስምንት መቶ ሰባ አንድ ብር ከስልሳ ሳንቲም) እንዱጎድል በማድረግ በፈጸመው ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
በማስረጃነትም የተጠሪን የሥራ ድርሻ የሚገልጽ ሰነድ፣ የኦዱት ሪፖርት፣ የጤና ጣቢያው የገንዘብ እንቅስቃሴን የሚገልጽ ሰነድ፣ ተጠሪ ለፖሉስ የሰጠውን ቃልና የሰው ማስረጃ አያይዘዋል።
ተጠሪ ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል የሰጡ ሲሆን ወንጀለን ያልፈጸሙና የተቋሙ ገንዘብ ወጭና ገቢ ሲደረግ የነበረው በተጠሪ ሳይሆን በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፉ በመሆኑ ስለገንዘቡ ጉዲይ እውቅና የላላቸው መሆኑን በመጥቀስ ጥፊተኛ አለመሆናቸውን ገልጸው ተከራክረዋል።
አመልካችም እንደ ክሱ ያስረደልኛል በሚል ምስክሮችን ያቀረበ ሲሆን 1ኛና 2ኛ የአመልካች ምስክሮች የኦዱት ባለሙያ ሲሆኑ ከታህሳስ 2009 አስከ ሰኔ 2010 ዓ.ም ያለው ሂሳብ ኦዱት ሲደረግ በክሱ የተገለፀው ብር የጎደለ መሆኑን፣ በክልለ የጥሬ ገንዘብ አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 23 መሰረት ከ ሰላሳ ሽህ ብር በላይ በካዜና መቀመጥ የላለበት መሆኑን የሚደነግግ በመሆኑ ተጠሪና ሂሳብ ኦፉሰሩ ገንዘቡን በመቆጣጠር ከጉድለት ሉታደጉት የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል። 3ኛ የአመልካች ምስክር ደግሞ የመስሪያ ቤቱ ተረኛ ጥበቃ መሆኑን ገልጾ በእለቱ ግንቦት 17/2011 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ንብረት ሲረከቡ የገንዘብ ቤቱ ቁልፍ ሳይቆለፍ ተንጠልጥል ስላዩት አልረከብም ብለው ለህግ አካል አሳውቀው ሲታይ ካዜናው ያልተቆለፈና ቁልፈ የሚሰራ መሆኑን አስረድቷል።
ክሱንና የቀረቡትን ማስረጃዎች የመረመረው ፍ/ቤትም ተጠሪ በቀረበባቸው ክስ ስር እንዱከላከለ ብይን የሰጠ ሲሆን ተጠሪም የመ/ምስክሮች አቅርበው ያሰሙ ሲሆን 1ኛ የተጠሪ መ/ምስክር ተጠሪ ሲሆኑ በሰጡት የምስክርነት ቃልም የግዥ አስተባባሪ ቢሆኑም ምን ያህል ገንዘብ በካዜና እንደሚኖር እውቅና የላላቸው መሆኑን፣ የፊይናንስ ቢሮ በሩ አልተቆለፈም ብለው እንደደወለለትና በቦታው ተገኝተው ሲመለከቱትም ተጨራምቶ ተንጠልጥል እንዲገኙት፣ ካዜናው ውስጥ ብር የላለ መሆኑን፣ የሂሳብ ስራውን የሚቆጣጠረው ኃላፉው መሆኑን፣ ገንዘብ ላይ ተጠሪ አዝም ተቆጣጥሮም ፈርመውም የማያውቁ መሆኑን አስረድተዋል። 2ኛ የመ/ምስክር ደግሞ ከሂሳብ ኦፉሰሯ ጋር በመሆን ባላንስ ሰርተው ለበላዮቻቸው የሚያሳውቁ መሆኑን፤ ባንክ እንዱገባ ደብዲቤ ሲፃፍላቸው ባንክ የሚያስገቡ መሆኑን፣ ይህ ጠፊ የተባለው ገንዘብ ግን ወደ ባንክ ይግባ ሲባል ተጠሪን ጨምሮ ለእናቶች ገቢ ማሰባሰቢያ ወፍጮ ይገዚበታል በሚል ገንዘቡ በካዜና እንዲለ ተጠሪም የሚያውቅ መሆኑን፣ ተጠሪ አስተባባሪ በመሆናቸው ገንዘቡ እንዱገባ ለኃላፉው መናገር አለባቸው በማለት አስረድተዋል።
3ኛ መ/ምስክር በበኩላቸው የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ መሆናቸውን፣ በቀን የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለሂሳብ ሰራተኛ እንደሚሰጡ፣ ሂሳብ ሰራተኛ ደግሞ ሰርቶ ለዋና ገንዘብ ያዥ አስገብቶ የመስሪያ ቤቱ ዋና ኃላፉ ይፈርምብትና የሚላክ መሆኑን እንጅ ተጠሪ ሲፈርም አይቶ የማያወቅ መሆኑን፣ አስረድተዋል። 4ኛ መ/ምስክር ደግሞ የመ/ቤቱ የሥራ ባልደረባና ተጠሪ የቅርብ አለቃው መሆኑን፣ የቢአስሲ ውጤቶችን አብረው የሚሰሩ መሆኑን፣ የገንዘብ ስራዎችንና ደብዲቤዎችን ለኃላፉ የሚጽፍ መሆኑን ገልጾ ተጠሪ ምን ምን ተግባሮችን እንደሚሰራና የስራ ኃላፉነቱን የማያውቅ መሆኑን አስረድቷል። በልላ በኩል በሰነድ ማስረጃነት ልዩ ልዩ ደብዲቤዎችን አያይዞል።
ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ክስና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በቀን የካቲት 11/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት ተጠሪ የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆኑ በመ/ቤቱ የስራ መዘርዜር የሂሳብ አያያዜ ማንዋል ላይ የግዥ ፊይናንስ ንብረት አስተዲደር ደጋፉ የሥራ ሂደት አስተባባሪ የስራ ኃላፉነቶች ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ የመ/ቤቱን የባንክ አካውንትና በካዜና ያለ ገንዘብ አያያዜ የመከታተልና የመቆጣጠር እንዱሁም የመፈረምና የመቆጣጠር ሃላፉነት የተሰጠው በመሆኑና በራሱ ቸልተኝነት በተገቢው መንገድ ክትትልና ቁጥጥር ባለማድረጉ የተገኘ ጉድለት በመሆኑ በቀረበበት ክስ ተከላከል በተባለበት የወንጀል ህግ ጥፊተኛ ነው በሚል በአራት ዓመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራት እና ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ ብር) የገንዘብ ቅጣት እንዱቀጡና ለአንድ ዓመት ያህል ከህዜባዊ መብታቸው በማገድ ውሳኔ አስተላልፎል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ያጸና ሲሆን የክልለ ሰበር ችልት በበኩለ የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ የመስሪያ ቤቱ የግዥና ፊይናንስ የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆኑ በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት ደግሞ ገንዘብ ያዥ እንደነበሩ የተረጋገጠ መሆኑን፣ ገንዘብ የሚቀመጠው እና ወደ ባንክ ገቢ የሚደረገው በገንዘብ ያዥ መሆኑን፣ ተጠሪ ገንዘቡ በገንዘብ ያዥ እጅ ከሆነ ገቢ አለመደረጉን የሚያውቅበት አግባብ ስለመኖሩ በማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን፣ ይህ ጉድለት ሲከሰት የተጠሪ አስተዋጽዖ በግልጽ ስለመኖሩ የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን በመግለጽ የሥር ፍ/ቤት በገንዘብ ያዥ አማካኝነት የጎደለን ገንዘብ ተጠሪ የወንጀል ኃላፉነት አለበት ተብል የመንግስትን አሰራር በማያመች አኳኋን የመምራት ወንጀል ድርጊት በመፈጸማቸው ጥፊተኛ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን በነጻ አሰናብቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 8/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔና ትዕዚዜ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዙህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም ተጠሪ የጤና ጣቢያው የግዥና የፊይናንስ የሥራ ሂደት አስተባባሪ እንደሆነና የሥር 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት ደግሞ በተጠሪ ስር ያለ ተጠሪ ሉቆጣጠረው የሚገባው ገንዘብ ያዥ ሰራተኛ መሆኑ ተረጋግጦ እያለና በኦዱት መመሪያ መሰረት ከብር 30,000.00 (ሰላሳ ሽህ ብር) በላይ በካዜና ሉቀመጥ የማይገባ መሆኑ ተደንግጎ እያለ እንዱሁም የተጠሪ ኃላፉነት በስራ መዘርዜር ውስጥ ገንዘብ ገቢና ወጭ በመፈረም የሚቆጣጠር መሆኑ ተገልጾ እያለ የስር ሰበር ችልት ገንዘብ ገቢ ማድረግ ያለበት ገንዘብ ያዥ ነው በሚል ከጭብጥ የወጣ ውሳኔ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን፣ ተጠሪ በቀረበበት የሙስና ወንጀል ሉጠየቅ አይገባም ከተባለ እንኳን በወንጀል ህጉ አንቀጽ 420 መሰረት ሉጠየቅ ሲገባው የስር ፍ/ቤት በነጻ ማሰናበቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን ጠቅሰው የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ እንዱሻርላቸው በማመልከታቸው ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ የጤና ጣቢያው የግዥ ፊይናንስ የስራ ሂደት አስተባባሪ ስለመሆናቸው በስራ መዘርዜሩም ላይ መስሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብና በካዜና ያለውን የገንዘብ አያያዜ የመከታተልና የማጣራት ኃላፉነት ያለባቸው ስለመሆኑ በተገለፀበት በገንዘብ ያዡ በኩል የጎደለውን ገንዘብ በተመለከተ ገንዘቡ ገቢ አለመደረጉን ተጠሪ በሚያውቅበት አግባብ አመልካች በማስረጃ ያላስረዲ በመሆኑ የመንግስትን አሰራር በማያመች አኳኋን የመምራት ወንጀል ድርጊት መፈፀማቸው አልተረጋገጠም በሚል ተጠሪን በነፃ በማሰናት የወሰነበትን አግባብ የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ ከወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/2/ እንዱሁም ላልች ተያያዥ ነጥቦች አንጻር ለመመርመር ለዙህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመታዘዘ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን ጥር 24/2014 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ በአመልካች የተጠቀሰው ገንዘብ በካዜና ስለመኖሩ ተጠሪ የሚያውቁበት አግባብ የላለና የአመልካች ማስረጃም ተጠሪ ገንዘቡን ስለማወቃቸው ያላስረደ መሆኑን፣ የኦዱት ስራ ሲደረግ የገንዘቡ ወጭና ገቢ ደረሰኞች በተጠሪ ስም ያልተቆረጡ መሆኑን፣ የቀረበው ሰነድና የሰው ምስክሮች ገንዘቡ በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፉ ትዕዚዜ ገቢና ወጭ ሲደረግ የነበር መሆኑን ያስረደ መሆናቸውን፣ ተጠሪ በወንጀል ህግ ቁጥር 23 መሰረት ወንጀለን የመፈጸም የሀሳብ ክፍል የላላቸው መሆኑን፣ ገንዘብ ያዥው ያለውን ገንዘብ ካላሳወቃቸው በምንም ሁኔታ ሉያውቁ የማይችለና ገንዘብ ያዡንም አልተቆጣጠርክም ሉያስብል የማይችል መሆኑን፣ በመስሪያ ቤቱ ያለውም ልማድ ገንዘብ ያዡ ለበላይ ኃላፉ በጽሁፍ እያሳወቀ ገንዘቡን ገቢና ወጭ እያደረገ ሲሰራ የቆየ መሆኑን፣ የገንዘብ መባከን ሰራተኛውን ላለመቆጣጠራቸውና ላለመምራቱ ብቸኛ መስፈርት ላሆን ያማይገባ መሆኑን ገልጸው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት መልሳቸውን አቅርበዋል።
አመልካች በተጠሪ በቀረበባቸው መልስ ላይ የመልስ መልስ ለማቅረብ ከፈለጉ ለምርመራ ከተቀጠረበት ቀን በፉት እንዱያቀርቡ ቢታዘዘም የመልስ መልሳቸውን ያላቀረቡ በመሆናቸው የአመልካችን የመልስ መልስ የማቅረብ መብት ችልቱ ቀሪ አድርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ከሰበር ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዜገብ ይዘት አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ ተመርምሯል።አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ክሱን ያቀረበው የአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(2)ን በመጥቀስ ተጠሪ የደብረ ሲና ጤና ጣቢያ የግዢ ፊይናንስ ንብረት አስተዲደር ደጋፉ የስራ ሂደት አስተባባሪ ሆነው ሲሰሩ የጤና ጣቢያው ዋና ገንዘብ ያዥ ሆነው ሲሰሩ በባንክ በጤና ጣቢያው አካውንትና በካዜና ያለን ገንዘብ አያያዜ ሉከታተለና ሉቆጣጠሩ ሲገባ በዙህ አግባብም በካዜና ሉቀመጥ የሚገባው እስከ ብር 30,000.00 ብቻ ላሆን የሚገባ በመሆኑ ከዙህ በላይ የሆነው ገንዘብ ወደ ባንክ ሂሳብ እንዱገባ የማድረግ ኃላፉነት እያለባቸው ይህንን ባለማድረግ ብር 252,871.60 እንዱጎድል ያደረጉ መሆኑን በመጥቀስ በመሆኑ የተጠሪ ወንጀል ኃላፉነት የመነጨው በህግ የታዘዘውን ካለማድረግ (Omission) መሆኑን ከክሱ አቀራረብ ለመረዲት ይቻላል።
የአዋጁ አንቀፅ 13(2) በአንቀፅ 13(1) ከፉደል ሀ እስከ ሐ የተመለከቱን ዜርዜር የህግ ነጥቦች መሰረት በማድረግ የከበደ የወንጀል ኃላፉነትን ለመጣል የተቀመጠ ሲሆን አንቀፅ 13(1) ከፉደል ሀ እስከ ሐ የተመለከቱትን ዜርዜር ሁኔታዎች ስንመለከታቸው ጥቅም መውሰድን ወይም ጥቅም የሚያስገኝን ውል መዋዋልን፤ውል ማቋረጥን፤የመንግስት ወይም የህዜባዊ ድርጅትን ጥቅም የሚጎዲ ተግባርን መፈፀምን ለመቅጣት የተደነገጉ መሆናቸው አንቀፅ 13 ከመነሻውም ካለማድረግ (Omission) ይልቅ ማድረግን (Comission) ለመቅጣት በህጋችን የተካተተ መሆኑን ያሳያል።ይህም አመልካች በተጠሪ ላይ በስራ ኃላፉነታቸው መሰረት ሉከታተለና ሉቆጣጠሩ ሲገባ ግዳታቸውን ባለመወጣት የደረሰን ጉዲት በመጥቀስ የአዋጁን አንቀፅ 13(2) መሰረት በማድረግ ማቅረቡ የህጉን ዜርዜር ሁኔታ መሰረት ያላደረገ ክስ ማቅረቡን፤የሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዙህ ድንጋጌ መሰረት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መስጠቱና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ስህተት ሉያርም ሲገባ ማፅናቱ የአዋጁን አንቀፅ 13(2) መሰረት ያላደረገ መሆኑን ያሳያል።
ተጠሪ በመ/ቤቱ የስራ መዘርዜር የሂሳብ አያያዜ ማንዋል ላይ የግዥ ፊይናንስ ንብረት አስተዲደር ደጋፉ የሥራ ሂደት አስተባባሪ የስራ ኃላፉነቶች ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ የመ/ቤቱን የባንክ አካውንትና በካዜና ያለ ገንዘብ አያያዜ የመከታተልና የመቆጣጠር እንዱሁም የመፈረምና የመቆጣጠር ኃላፉነት በተጠሪ ላይ የተጣለ ሀላፉነቶች መሆናቸው ማስረጃን የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ እያለ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችም ተጠሪ ይህንን ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት በክሱ ላይ የተመለከተው ጉዲት መድረሱን በዋነኝነትም ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ምስክሮች እያስረደ፤የተጠሪ 2ኛ ምስክርም ተጠሪ አስተባባሪ በመሆናቸው ገንዘቡ ባንክ እንዱገባ ለኃላፉው መናገር ያለባቸው መሆኑን ገንዘቡ ካዜና መኖሩን እያወቁ ይህንን ሳያደርጉ መቅረታቸውን እያስረደ ይህም የተጠሪ ምስክር ጭምር ተጠሪ በስራ መዘርዜሩ አግባብ አለመስራታቸውን እያስረደ ይህ ሁኔታ ደግሞ በወ/ህ/አ.420(2) መሰረት የስራ ሀላፉነትን ባለመወጣት የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ ሆኖ እያለ ተጠሪን በነፃ ማሰናበቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተጠሪ በወ/ህ/አ.420(2) ስር ጥፊተኛ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ፍርድ ሰጥተናል።
ቅጣትን አስመልክቶ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ድርጊት በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን ማንዋል ቁ.02/2006 መሰረት የወንጀል ደረጃ ያልወጣለት በመሆኑ በዙህ ድንጋጌ አግባብ የሚጣለው ቀላል የእስራት ቅጣት እስከ 5 አመት ሉደርስ እንደሚችል ከወ/ህ/አ.420(2) እና 106(1) የጋራ ንባብ የምንረዲው በመሆኑ ዜቅተኛውን ከ10 ቀን እስከ 1 አመት ከ3 ወር ቀላል እስራትና ከብር 10.00 እስከ ብር 3,333.33 የሚያስቀጣ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተያዘውን ዜቅተኛ የወንጀል ደረጃ በመውሰድ 1 አመት እስራትን ስንወስድ በዜቅተኛው እርከን 5 ላይ የገንዘብ መቀጮው ብር 3,100.00 እርከን 4 ላይ የሚያርፍ ሲሆን በስር ፍርድ ቤት የተያዘትን 3 ማቅለያዎች ከግምት ውስጥ ስናስገባ የእስራት ቅጣቱ እርከን 2 ላይ የገንዘብ መቀጮው እርከን 1 ላይ የሚያርፍ በመሆኑ ተጠሪ በዙህ ጉዲይ የታሰሩበት ጊዛ ካለ ታስቦ በሶስት ወር ቀላል አስራትና በብር 1,000.00 ሉቀጡ ይገባል በማለት በአብላጫ ድምፅ ፍርድ ሰጥተናል።
1.የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.101212 ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.195(2)(ለ)(2) ተሻሽሎል። ተጠሪ በወ/ህ/አ.420(2) ስር የስራ ሀላፉነትን ባለመወጣት በሚፈፀም ወንጀል ጥፊተኛ ናቸው ብለናል።
2.ተጠሪ በዙህ ጉዲይ የታሰሩት ካለ ታስቦ በሶስት ወር ቀላል አስራትና በብር 1,000.00 ሉቀጡ ይገባል ብለናል።
ትዕዚዜ የክፍለ ፖሉስ ተጠሪን ለማረሚያ ቤቱ እንዱያስረክብና ማረሚያ ቤቱ ከላይ በተመለከተው የቅጣት ውሳኔ አግባብ እንዱያስፈፅም ታዞል።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዜገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።