በሽያጭ ውል ገዥዉ እቃዉ እንደዉለ ትክክል አይደለም ወይም ጉድለት አለበት በማለት እንዱሟላ ወይም ጉድለቱ እንዱስተካከል ለመጠየቅ ያለዉ መብት በጊዛ የተገደበ በመሆኑ የተረከበዉን እቃ ባጭር ጊዛ ዉስጥ መመርመር እና ልዩነት ካለም ባጭር ጊዛ ዉስጥ ማስታወቅ ያለበትና በእቃዉ ላይ ጉድለት መኖር አለመኖሩን ለማስታወቅ የሚቻልበት ጊዛ በስምምነት የተወሰነ ከሆነ ገዥዉ በዉል በተወሰነዉ ጊዛ ዉስጥ የማስታወቅ ግዳታውን ካልተወጣ ይህን የሚያነሳዉን የመብት ጥያቄ ሉያጣ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2291(1) እና 2292፣ 2294፣ 2293 የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ በተሟላ ሁኔታ ሳይሰማ እና ሳይጣራ የሚሰጥ ዉሳኔ የክርክር አመራር ጉድለት ብቻ ሳይሆን የተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመሰማት መብት እና አንጻራዊ እዉነትን ከማረጋገጥ አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብል ሉታረም የሚገባ ስለመሆኑ
No summary available.
መ/ቁ/207371 ሚያዜያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ኤልባን ጌት ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪ፡- ዋቻሞ ዩንቨርሲቲ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ነዉ። የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ፡- የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ መጋቢት 01 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ክስ ተጠሪ ለመማር ማስተማር አገልግልት የሚውለ የህክምና ዕቃዎችን ግዥ ለመፈፀም በ2011 በጀት ዓመት ባወጣው ጨረታ ተወዲድረን ግምታቸው ብር 7,311,800.00 ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎችን ለማቅረብ ጨረታውን በማሸነፍ ሶስት ምስክሮች ባለበት በ17/05/2011 ዓ.ም በጽሁፍ ውል ፈጽመናል። በገባነው የውል ግዳታ መሰረት ስለ ዕቃዎቹ ልዩ አዋቂ ባለሙያዎችና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት አስተያየት መስጫ ቅጽ ላይ አረጋግጠው በ12/07/2011 ዓ.ም በንብረት ገቢ ደረሰኝ በሞዳል-19 ሙለ በሙለ ገቢ አድርገን ተጠሪም ክፍያ እፈጽማለሁ በማለት የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ቁጥር 0016 የብር 7,209,100.00 ቆርጠን ሰጥተነዋል፤ ተጠሪ ዕቃውን ከተረከበ በአንድ ሳምንት ውስጥ ክፍያውን መፈፀም እንዲለበት የውለ አንቀጽ 3 እና ልዩ ሁኔታዎች በሚለው ስር ግዳታ ያለበት ቢሆንም ግዳታውን አልፈፀመም፣ ስለዙህ ተጠሪ በዕቃዎቹ ላይ ምንም ቅሬታ ሳያቀርብ ለመልካም ስራ አፈፃፀም የተያዘውን ዋስትና ብር 731,180.00 እንዱለቀቅ በ28/07/11 ዓ.ም በዋስትና ወረቀቱ ጀርባ ላይ ፈርሞ በዩንቨርሲቲው ማህተም አረጋግጦ ለዋስትና ያስያዜነው ገንዘብ ተቀብለናል።ግዳታችንን 99% ከተወጣን በኋላ ብር 102,700 ዋጋ ያላቸውን ቀሪ እቃዎች በስፔስፉኬሽኑ መሰረት ብናቀርብም ባለሙያዎች በልላ መልክ ይቀየርልን በማለታቸው ለዕቃዎቹ መፈለጊያ አንድ ወር እንዱራዘም ጠይቀን በተራዘምልን ጊዛ ውስጥ ዕቃዎቹን በማስረከብ ማረጋገጫ ተቀብለናል።ተጠሪ ለተረከበው ዕቃ በውለ መሰረት ክፍያ እንዱፈጽም በተለያዩ ጊዛ ተጠይቆ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዙህ ተጠሪ ለተረከበው ዕቃ አጠቃላይ ዋጋ የብር 7,311,800.00 ከህጋዊ ወለድ፣የጠበቃ እና ላልች ወጪዎች ጋር እንዱከፍል እንዱወሰንልን በማለት ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ በቀን 07/12/2012 ዓ.ም ጽፍ በሰጠው መልስ አመልካች ከዕቃዎች ውስጥ አብዚኛውን ዕቃ በውለ መሰረት ቢያቀርብም በተ.ቁ.50 ላይ ያለውን ባዮ-ሜዱካል ላብ የተባለው ዕቃ በተመለከተ በተጠሪ በተዘጋጀ ዜርዜር ሁኔታ መስፈርት መሰረት መልቲ ሄድድ ማይክሮስኮፕ ሆኖ ፊይፍ ሄድድ ማይክሮስኮፕ የተባለውን ማቅረብ ሲገባው ባይናኩላር ኦልምፏስ ማይክሮስኮፕ የተባለውን ስላቀረበ በውለ መሰረት እንዱያስተካክል ቢጠየቅም ፍቃደኛ አልሆነም፣ስለዙህ እንደውለ ሳይፈጽም ስለክፍያ ክስ ማቅረብ ስለማይችል አመልካች በውለ መሰረት ግዳታ ሳይወጣ ተጠሪ ክፍያ ሉፈጽም አይችልም ተብል ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱወሰንልን በማለት መከራከሩን መዜገቡ ያሣያል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ያቀረበው ዕቃ ባይናኩላር ማይክሮስኮፕ እንጂ በውል የተጠቀሰው ኦልምፏስ ፊይፍ ሄድድ ማይክሮስኮፕ የሚባለውን አለመሆኑ ተረጋግጧል፣ አመልካች ለተጠሪ ያስረከበዉ እቃ በውለ ዜርዜር ሁኔታ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ ባለመሆኑ በውለ መሰረት ግዳታውን ተወጥቷል ለማለት አይቻልም፣ ስለዙህ በውለ የተመለከተ ግዳታውን ሳይወጣ ገንዘብ ይከፈለኝ የሚል ጥያቄ ማንሳቱ አግባብነት የለውም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዙህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙ አያስቀርብም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞል።
አመልካች በዙህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል እንዱታረምልን በማለት ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፡-ተጠሪ የመደባቸው ጥራት አረጋጋጭ እና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የእቃውን ትክክለኛነት አረጋግጠው መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በሞደል-19 ገቢ አድርገው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና እንዱለቀቅ ተጠሪ ለኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የፃፈው ደብዲቤ እና የፍደራል መንግስት ግዥ አስተዲደር ኤጀንሲ በውላችን አንቀጽ 28/4 መሰረት ስህተት ካለ ወዱያውኑ ማሳወቅ ሲገባው ከስምንት ወር በኋላ ተሳስቻለሁ በሚል ውል እንዱፈርስ ጥያቄ ሉያቀርብ አይገባም በማለት የግዥ አስተደደር ኤጀንሲ አመልካች ጥፊተኛ አይደለም በማለት የሰጠውን ሪፖርት ጭምር አቅርበን እያለ የስር ፍ/ቤት በዜምታ ማለፈ ስህተት በመሆኑ፤ የተጠሪ ምስክሮች ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ስለዕቃው እውቀት የላቸዉም የሚለው ቃል በጫና የሰጡት መሆኑ፤ ፍርድ ቤቱም ክሱን ውድቅ ማድረጉ የማስረጃ ምዘና መርህ የተከተለ አይደለም፤
አመልካች ገቢ ያደረገው ዕቃ እና በውለ የተመለከተው እቃ መካከል መሰረታዊ ልዩነት አለ ወይስ የለም? የተጠየቀው እቃ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በገበያ ላይ አለ ወይስ የለም? የሚለውን ከሚመለከተው አካል ወይም በባለሙያ ሳያረጋግጥ እንዱሁም አመልካች ውል ከመግባቱ በፉት በሁለቱ መካከል መሰረታዊ ልዩነት የላለ መሆኑን እና የተፈለገው ዕቃ በኢትዮጵያ ገበያ አለመኖሩን ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም በደብዲቤ ገልፆ እያለ ይህ በዜምታ መታለፈ አግባብነት የለውም። በውላችን አንቀጽ 10 መሰረት ዕቃዎች ላይ ጉድለት ወይም መሰረታዊ ስህተት ካለበት ወይም ቴክኒክ ኮሚቴው በስህተት የተቀበለውን ከሆነ በ28 ቀናት ውስጥ ቅሬታ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት የማቅረብ መብቱን ሳይጠቀም ከ8 ወር በኋላ የአመልካችን ክስ ተንተርሶ እንደውለ አልተፈፀመም ዉለ ይፍረስ የሚለዉ ክርክር ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 23895 የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው ተሽሮ የተጠየቀውን ገንዘብ ተጠሪ እንዱከፍለን እንዱወሰንልን በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ተጠሪ ዕቃውን ከተረከበ በኋላ ገንዘብ አልከፍልም ማለቱን አግባብነት እና የኢፋዱሪ የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዲደር ኤጀንሲ በቀን 25/09/2012 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ጥፊተኛ ከተደረገበት ዉሳኔ አንፃር ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ታዞል።
ተጠሪ በቀን 09/10/2013ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች በውለ መሰረት ለማቅረብ ተስማምቶ የነበረዉ የባዮ ሜዱካል ዕቃ መልቲ ሄድድ ማይክሮስኮፕ የምርት ስያሜም ኦልምፏስ የተባለው መሆኑን ነገር ግን አመልካች በርክክብ ወቅት ያቀረበው ባይናኩላር ማይሮስኮፕ በአንድ ጊዛ አንድ ሰው ብቻ ሉጠቀምበት የሚችል በዋጋም ሆነ በአገልግልታቸው ሰፉ ልዩነት አላቸው፤
አመልካች ከመነሻውም በጨረታ ሰነድ ዜርዜር የተገለፀውን አቀርባለሁ ብል ጨረታ ካሸነፈ በኋላ ውል ለመዋዋል በቀረበ ጊዛ ዕቃውን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጾ ባይናኩላር ለማቅረብ ጠይቆ ነገር ግን ተጠሪ በዜርዜር ከተመለከተው ውጭ እንደማይዋዋል ሲገልጽ በጨረታ ሰነደ ላይ የተገለፀውን ለማቅረብ ተስማምቶ ውል የተዋዋለ መሆኑን፤ ርክክብ ሲፈፀምም አመልካች ከቅን ልቦና ውጪ የባለሙያዎች የልምድ እና የእውቀት ውስንነት በመጠቀም ባለሙያዎችን በማሳሳት በውል ከተስማማው ዕቃ ውጪ ብራንደ ኦልምፏስ በመሆኑ ብቻ እና በተጠሪ ተቋምም ከዙህ በፉት ያልነበረ በመሆኑ የትምህርት ክፍለ ባለሙያዎችም አስፈላጊ ናቸው እንረከባቸው በማለት የሰጡትን አስተያየት እና ከባለሙያዎች ኮሚቴ የቀረበለት አስተያየት በዕቃ ርክክብ ወቅት በተፈጠረው ስህተት ምክንያት የተረከበ መሆኑን፤የተሻለ እውቀት ያላቸው መምህራን ለፈተና ከተመደቡበት ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ሲመለሱ ዕቃው ሰፉ ልዩነት ያለው መሆኑ ተረጋግጦ ክፍያ እንዲይፈፀም ታግድ ቆይቷል። ተጠሪም ይህንን እውነታ ለአመልካች ሲገለጽላቸው እንደውለ ትክክለኛ እቃ ለማቅረብ በወቅቱ ሀገር ውስጥ የማይገኝ በመሆኑ ዕቃዎቹን ለማስገባት ጊዛ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልፀው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገው መግባባት አመልካች እቃው በትክክለኛ እቃ እስከሚተካ ክፍያ እንደማይፈፀም ተስማምተን ቆይተናል፤
አመልካች ይህንን ክድ ያልተከራከረ በመሆኑና ዕቃው ሀገር ውስጥ የለም የሚለው ክርክር በውለ ከተመለከተው ውጪ እንዱያቀርብ የተሰጠው ፍቃድ የለም። የኢፋዱሪ የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዲደር ኤጀንሲ የጥፊተኝነት ውሳኔ ተጠሪ እቃውን ትክክለኛ ነው ብል መረከቡን እና ጉድለትም በጊዛ ማሳወቅ ነበረበት የሚለ ነጥቦች መሰረት በማድረግ መሆኑን፤ አመልካችም በትክክለኛ እቃ እተካለው በማለት ተጨማሪ ጊዛ ስለጠየቀና የድርጅቱ ባለቤት በደም ካንሰር በከፍተኛ ታሞ ስለነበረ ዕቃዎቹን ፈልገው በትክክለኛ ዕቃ ይተካለ በሚል በትዕግስት እየጠበቅን ባለበት ሁኔታ ክፍያ ጥያቄ ማቅረቡ እነዙህን ሁኔታዎች ከግምት ያላስገባ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ምንም አይነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች አቤቱታውን በማጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዜገቡ ጋር ተያይዞል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለበትን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። እንደመረመርነዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገዉ የላቦራቶሪ የእቃ አቅርቦትና ሽያጭ ዉል መሰረት ለመማር ማስተማር (የባዮ ሜዱካል ላብ) አገልግልት የሚዉለ እቃዎችን አመልካች ለተጠሪ ማስረከቡ አላከራከረም። ሆኖም ተጠሪ እቃዎቹን ከተረከበ በኋላ ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም በሚል ተገድ ክፍያ እንዱፈጽም እንዱወሰንለት አመልካች ካቀረበዉ ዲኝነት አንጻር በተጠሪ በኩል የቀረበዉ መከራከሪያ አመልካች ካስረከባቸዉ እቃዎች ዉስጥ በተራ ቁጥር 50 ላይ የተገለጸዉ እቃ በዉለ የተገለጸዉን ዓይነትና ዜርዜር መግለጫ (specification) ያሟላ ባለመሆኑ ክፍያ ለመፈጸም አልገደድም የሚል ሲሆን የስር ፍርድ ቤትም እቃዉ እንደዉለ አልቀረበም በሚል ተጠሪ ክፍያ ለመፈጸም አይገደድም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረዉ ተጠሪ እቃውን እንደተረከበ ጉድለት ስለመኖሩ በጊዛ አላስታወቀም ወይም መቃወሚያ አላቀረበም፤ ጉድለቱም መሰረታዊ መሆን አለመሆኑ አልተጣራም በማለት ነዉ።
ጉዲዩ የእቃ ሽያጭ ውልን የሚመለከት እንደመሆኑ የተከራካሪዎቹ ወገኖች መብትና ግዳታ መታየት ያለበት ስለ ልዩ ውልች በሚል በተደነገገው በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ(Title) አስራ አምስት ሥር ከቁጥር 2266 ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎች መሰረት ነው። እነዙህ ድንጋጌዎች የሻጩን መብትና ግዳታ እና ገዢውም መብትና ግዳታ የሚዘረዜሩ ሲሆን ከዙህም ዉስጥ ገዥዉ እቃውን እንደተረከበ ሉወስዲቸው የሚገቡ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ያመለክታለ። ሻጩ በውለ በተመለከተው መሰረት ትክክለኛውን እቃ ለገዢው የማስረከብ ኃላፉነት እንዲለበት እንደተደነገገው ሁለ ገዢም እቃው በውለ መሰረት የተሟላ አይደለም ወይም ጉድለት ያለበት ነው የሚል ከሆነ በሕጉ በተመለከተው የጊዛ ገደብ ውስጥ የመመርመርና የማስታወቅ ግዳታ አለበት።
(የፍ/ብ/ሕግ/ቁ/2287፣2288፣2291እና2292) ይመለከታል።
እቃዉ ጉድለት አለበት የሚባለዉ ሻጩ ከሸጠዉ ነገር አንደን ክፍል ብቻ የሰጠ እንደሆነ ወይም ሻጩ ላሰጥ በዉል ቃል ከገባበት ልክ አብልጦ ወይም አሳንሶ የሰጠ እንደሆነ ወይም በዉለ የተመለከተዉ ሳይሆን ላላ ነገር ወይም ዓይነቱ ላላ የሆነዉን ነገር የሰጠ እንደሆነ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2288 ድንጋጌ ይዘት ያሣያል።
በተያዘዉ ጉዲይ የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ የመረመረዉ የስር ፍርድ ቤት በዉለ ዜርዜር መግለጫ (specification) መሰረት አመልካች ማቅረብ የሚገባዉ (multi 5 headed Olympus micro-scope) መሆን ሲገባዉ አመልካች ያቀረበዉ (binocular Olympus microscope) መሆኑን አረጋግጦ ይህንኑ ምክንያት መሰረት በማድረግ አመልካች እንደዉለ ግዳታዉን ሳይወጣ ክፍያ መጠየቅ አይችልም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።ይህ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልካች የሚከራከረዉ በአንድ በኩል እቃዉ ጉድለት እንደላለበት ተጠሪ በራሱ ባለሙያዎች እና ቴክኒክ ኮሚቴ አረጋግጦ መረከቡ፤በልላ በኩል ጉድለት ስለመኖሩም በዉለ በተገለጸዉ አግባብ በ28 ቀናት ዉስጥ ያላስታወቀ መሆኑን በመግለጽ ነዉ። ሻጭ የሸጠዉ ነገር እንደዉለ ትክክል ካልሆነ ወይም ጉድለት ካለዉ ሻጭ ኃላፉነት እንዲለበት ግልጽ ነዉ። ገዥዉም የተረከበዉን እቃ በተቻለ ፍጥነት መርምሮ ጉድለቱን ለሻጭ የማስታወቅ ግዳታ አለበት።
ገዥዉ እቃዉ እንደዉለ ትክክል አይደለም ወይም ጉድለት አለበት በማለት እንዱሟላ ወይም ጉድለቱ እንዱስተካከል ለመጠየቅ ያለዉ መብት በጊዛ የተገደበ ነዉ።በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2291(1) እና 2292 ላይ እንደተመለከተዉ ገዥ የተረከበዉን እቃ ባጭር ጊዛ ዉስጥ መመርመር እና ልዩነት ካለም ባጭር ጊዛ ዉስጥ ማስታወቅ እንዲለበት ተመልክቷል።በእቃዉ ላይ ጉድለት መኖር አለመኖሩን ለማስታወቅ የሚቻልበት ጊዛ በስምምነት የተወሰነ ከሆነ ገዥዉ በዉል በተወሰነዉ ጊዛ ውስጥ የማስታወቅ ግዳታ ይኖርበታል።የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2294 ይመለከታል። ይህ ሳይፈጸም ቀርቶ እንደሆነ ገዥ በዙህ ረገድ የሚኖረዉን መብት ያጣል። የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2293 ይመለከታል። ከዙህ ሁለ ማየት የሚቻለዉ ገዥዉ የተረከበዉ እቃ ጉድለት ወይም እንደዉለ ትክክል መሆን አለመሆኑን ባጭር ጊዛ ዉስጥ የመመርመር እና ጉድለቱን ለሻጩ የማስታወቅ ግዳታዉን ካልተወጣ በጉድለት ምክንያት የሚያነሳዉን የመብት ጥያቄ ሉያጣ እንደሚችል ህጉ ያስገነዜባል።
ከዙህ አኳያ የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች አጥብቆ የተከራከረዉ ተጠሪ እቃዉን ከተረከበ በኋላ ጉድለት መኖሩን በዉለ በተገለጸዉ ጊዛ ዉስጥ አላስታወቀም በማለት ሲሆን ለዙህም በማስረጃነት የፍደራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዲደር ኤጄንሲ የሰጠዉን ዉሳኔ ዋቢ በማድረግ የተከራከረ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ እቃዉ እንደዉለ ትክክል አለመሆኑ የታወቀዉ ባለሙያዎች ከሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ተመልሰዉ ከመረመሩ በኋላ መሆኑን እና ቀደም ሲል የተረከቡት የኮሚቴ አባላት በቂ እዉቀትና ልምድ ስለላላቸዉ አመልካች ከቅን ልቦና ዉጪ በማሳሳት ያደረገዉ ነዉ በማለት ተከራክሯል። ከዙህ የግራ ቀኙ ክርክር አኳያ እልባት የሚሻዉና መጣራት ያለባቸዉ ጭብጦች ፡- 1ኛ/ተጠሪ የተረከበዉን እቃ ትክክለኛነት የመረመረዉ ጊዛዉን ጠብቆ ነዉ ወይስ አይደለም?
2ኛ/የምርምራዉን ዉጤት ለአመልካች በዉል በተገለጸዉ ጊዛ ዉስጥ አስታዉቋል ወይስ አላስታወቀም? ተጠሪ በዉለ በተገለጸዉ ጊዛ ካላስታወቀ ዉጤቱ ምንድነዉ?
3ኛ/እንደዉለ ትክክል አይደለም የተባለዉ እቃ ጉድለት ሉስተካከል የሚችል መሆን አለመሆኑ?
4ኛ/ጉድለቱን ማስተካከል የማይቻል ከሆነስ ዉጤቱ ምን ይሆናል? የሚለ ናቸዉ።በእነዙህ ጭብጦች ዘሪያ ግራቀኙ አለን የሚለትን ክርክርና ማስረጃ አቅርበዉ ካሰሙ በኋላ ጉዲዩ ከግራቀኙ ዉል እና አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር ተገናዜቦ እልባት ሉሰጠዉ የሚገባዉ ነዉ።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በዙህ አግባብ ተመልከተዉ ተገቢዉን ጭብጥ ይዘዉ ዉሳኔ መስጠት ሲገባቸዉ ጉድለት መኖሩ ተመስክሯል በሚል ምክንያት ብቻ የአመልካችን ክስ ሙለ በሙለ ዉድቅ ማድረጋቸዉ የክርክር አመራር ጉድለት ያለበት መሆኑን ያሣያል።
የግራቀኙን ከርክር እና ማስረጃ በተሟላ ሁኔታ ሳይሰማ እና ሳይጣራ የሚሰጥ ዉሳኔ የክርክር አመራር ጉድለት ብቻ ሳይሆን የተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመሰማት መብት እና አንጻራዊ እዉነትን ከማረጋገጥ አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብል ሉታረም እንደሚገባ ይህ ሰበር ችልት በተለያዩ መዜገቦች የሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ ያስገነዜባል። በዙህ ረገድ በሰበር መ/ቁ/37105፣47551፣49660 እና ላልች ተመሳሳይ ጉዲዮች ላይ የሰጠውን ዉሳኔ መመልከት ይቻላል።
ሲጠቃለል አመልካች ለተጠሪ ካቀረባቸዉ እቃዎች ዉስጥ 50ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተመዘገበዉ እቃ እንደዉለ ትክክል ባለመሆኑ ተጠሪ ክፍያ ሉፈጽም አይገደድም በማለት የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ አጠቃላይ የክርክሩን ይዘት እና በግራቀኙ የተደረጉትን ስምምነት እንዱሁም አግባብነት ያላቸዉን ጭብጦች እና ማስረጃ በተሟላ ሁኔታ የተመለከተ ባለመሆኑ በሰበር ችልት የተሰጡትን አስገዲጅ ዉሳኔዎች የሚቃረን ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4-ሐ/ሸ/ እና 10(1 /ለ) ድንጋጌዎች መሰረት ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል። በዙሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 252027 በቀን 25/05/2013ዓ.ም የሰጠዉን ፍርድ በማጽናት የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/203515 ላይ በቀን 28/08/2013ዓ.ም የሰጠዉ ትእዚዜ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2ኛ/ፍርድ ቤቱን የዘጋዉን መዜገብ በማንቀሳቀስ ከላይ በተገለጸዉ ጭብጥ ላይ ግራ ቀኙን አከራከሮ እና በማስረጃ አጣርቶ ተቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሰናል።ይጻፍ መዜገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።
No topics extracted.