ከፍርድ ቤት ውጭ በሕግ የዲኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት የሚሰጡ ዉሳኔዎችንም ሆነ በሕግ በተሰጣቸው ኃላፉነት የሚሰጧቸው አስተዲደራዊ ውሳኔዎች በዲኝነታዊ ክለሳ ሂደት በማለፍ በፍርድ ቤት መታየት የሚገባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79(1)፣ 78(4) እና 37፣ እንዱሁም አንቀጽ 13(1)፣ የፍ/ሕ/ቁጥር 401/1 እንዱሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 12/2፣ 321 እና የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ አንድ አስተዲደራዊ ውሳኔ በሕግ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ እስካልተደነገገ ድረስ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ሥርዓት ታይቶ ሉታረም የሚችለው በሰበር ከመታየቱ በፉት እንደ ነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ወይም በዲኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ከታይ በኋላ ስለመሆኑ የዳኞች አስተዲደር ጉባኤው በሚሰጠው ውሳኔ ላይም ሆነ ከውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ጋር በተያያዘ የሕጋዊነት ቅሬታ ያለው ዲኛ ወይም የጉባኤ ተሿሚ ቅሬታውን በምን አግባብ ለማን ማቅረብ እንዲለበት በፋዳራልም ሆነ በክልል ሕግጋተ መንግስታት በግልጽ የተዘረጋ ሥርዓት ካለመኖሩም በተጨማሪ በዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ስለዚህ ጉዲይ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ጽ/ቤት እና አቶ አበባዉ ታደሰ
No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ኑረዱን ከድር ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ በክልል ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የተሰጠ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ በሰበር መታየቱ አግባብ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ።ጉዲዩ የተጀመረዉ ተጠሪ ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ (ከዚህ በኋላ ጉባኤ በሚል የሚጠቀስ) ባቀረቡት ቅሬታ መነሻ ሲሆን የቅሬታቸዉም ይዘት በአጭሩ፡- ጉባኤዉ በቀን 25/05/2010 ዓ/ም ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ በየደረጃዉ ለሚገኙ ሰብሳቢ ዳኞች እና ለሂደት መሪዎች የደመወዝ ጭማሪ እንዱደረግ ወስኗል።በዚህ ዉሳኔ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ እና እርከን ከተሰራ በኋላ ደመወዝ የተጨመረ ሲሆን አመልካች የሥራ ሂደት መሪ በመሆኔ የደመወዝ ጭማሪዉ ተግባራዊ ከተደረገበት ከቀን 01/06/2010ዓ/ም ጀምሮ ለሥራ መደቡ የተፈቀደዉን የወር ደመወዝ ብር 13,702.00 እየተከፈለኝ ቆይቷል።ከዚህም ላይ ጡረታ ሲቆረጥ ቆይቷል።ነገር ግን ጉባኤዉ በቀን 28/09/2012 ዓ/ም ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ የዳኞችን እና የጉባኤ ተሿሚዎችን ደመወዝ እንዱሻሻል ሲወስን አስቀድሞ በሂደት መሪነት ይከፈለኝ የነበረዉን ደመወዝ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት የኃላፉነት አባል ነዉ በሚል በመቀነስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲኛ ይከፈል የነበረዉን ደመወዝ ብር 12,702.00 በመነሻነት በመዉሰድ የደመወዝ ማሻሻያዉ እንዱሰራ ተደርጓል።በመሆኑም የደመወዝ ማሻሻያ ሲደረግ ለስላቱ መነሻ መሆን የሚገባዉ ብር 12,702.00 ሳይሆን አስቀድሞ በሂደት መሪነቴ ይከፈለኝ የነበረዉ ደመወዝ ብር 13,702.00 በመሆኑ ስላቱ በዚህ አግባብ ተሰርቶ እንዱከፈለኝ በማለት ቅሬታቸዉን ለጉባኤዉ አቅርበዋል።
ጉባኤዉ በቀን 26/06/2013 ዓ/ም ባካሄደዉ ስብሰባ በሰጠዉ ዉሳኔ ጉባኤዉ በቀን 25/05/2010ዓ/ም ባካሄደዉ ስብሳባ የወሰነዉ ክፍያ የኃላፉነት እንጂ ደመወዝ አይደለም።በቀን 28/09/2012ዓ/ም በተደረገዉ ጉባኤም የደመወዝ ማሻሻያ በተመለከተ የቀረበዉን ጥናት በማጽደቅ በእነዚህ የኃላፉነት መደቦች ላይ ተመድበዉ ለሚሰሩ ኃላፉዎች ደመወዛቸዉ በያለበት ፍርድ ቤት ዲኛ ደረጃ እንዱሆን ሆኖ ለኃላፉነታቸዉ ደረጃ እና መጠን በልዩ ሁኔታ የተሻሻለ የኃላፉነት ክፍያ እንዱከፈላቸዉ በሚል ወስኗል።በቅሬታዉ መሰረት የደመወዝ ማሻሻያ ማድረግ የጉባኤዉን ዉሳኔ መጻረር ይሆናል።እንዱሁም ከአዱሱ ደመወዝ ጭማሪ በፉት በኃላፉነት ላይ በነበሩትና ከደመወዝ ጭማሪ ወዱህ ወደ ተጠቀሱት የኃላፉነት ቦታ በሚመጡት ኃላፉዎች መካከል የደመወዝ ልዩነት የሚፈጥር በመሆኑ ተገቢነት የለዉም በማለት ጥያቄዉን ዉድቅ አድርጓል።
ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁኑን 1ኛ ተጠሪ በተጠሪነት በመጨመር ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዉ ችልቱ ግራ ቀኙን በመ/ቁጥር 03-104522 ላይ አከራክሮ በቀን 30/11/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ጉባኤዉ በአዋጅ ቁጥር 209/2006 መሰረት የዳኞችን እና የጉባኤ ተሿሚዎችን ደመወዝ ጥቅማጥቅም የመወሰን ሥልጣን ያለዉ አካል ነዉ።ጉባኤዉ የሚሰጣቸዉ ዉሳኔዎች አግባብነት ለመከለስ በሕግ ሥልጣን የተሰጠዉ ላላ አካል የለም።በመሆኑም ጉባኤዉ በተለያዩ አስተዲደራዊ ጉዲዮች ላይ የሚሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ እንደሆነ ይቆጠራል።የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) እና በተሻሻለዉ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17 በግልጽ እንደሚደነግገዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን እንደሚኖረዉ ያስገነዝባል።በዚህም ጉዲይ ዉሳኔ የሰጠዉ ጉባኤዉ ስለሆነ እና ዉሳኔዉም የመጨረሻ በመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን ስላለዉ አመልካቾች ችልቱ ስልጣን የለዉም ሲለ ያቀረቡት ተቃዉሞ ተቀባይነት የለዉም።
በልላ በኩል ጉባኤዉ በቀን 25/05/2010ዓ/ም የወሰነዉ ደመወዝ ነዉ ወይስ የኃላፉነት አበል የሚለዉን በመመርመር በጉባኤዉ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 209/2006 ላይ እና በላልች የዳኞች መተዲደሪያ ደንቦች ላይ ለደመወዝ ትርጓሜ ስላልተሰጠ በክልለ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 2/9 ላይ የተሰጠዉን ትርጓሜ መዋስ ይገባል በማለት ጉዲዩን ከዚህ አንጻር መርምሯል።በዚህ መሰረት ጉባኤዉ በቀን 25/05/2010ዓ/ም ለሰብሳቢ ዳኞችና ለሂደት መሪዎች ክፍያ ሲወስን መጠኑን የወሰነዉ ሰራተኞች የሚያገኙትን መነሻ ደመወዝ መሰረት በማድረግ ደረጃ እና እርከን መስራቱን የጉባኤዉ ቃለ ጉባኤ ያሳያል።ከፍ ሲል ከተመለከተዉ የደመወዝ ትርጓሜ አንጻር በክፍያዉ ላይ ጡረታ ሲቆረጥ መቆየቱ ሲታይ ጉባኤዉ የወሰነዉ ክፍያ ደመወዝ እንደሆነ ችልቱ ተገንዝቧል።ስለሆነም ጉባኤዉ በቀን 25/05/2010ዓ/ም ለሰብሳቢ ዳኞችና ለሂደት መሪዎች የወሰነዉ ክፍያ የኃላፉነት አበል ሳይሆን ደመወዝ በመሆኑና ዉሳኔዉ ፀንቶ ባለበት የዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ደመወዝ በተሻሻለ ጊዜ ለስላቱ በመነሻነት ሉወሰድ የሚገባዉ ተጠሪ አስቀድሞ በሂደት መሪነታቸዉ ሲከፈላቸዉ የነበረዉ ደመወዝ ብር 13,702 ሆኖ እያለ በብር 12,702 መነሻ ደመወዝ መሰራቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት ጉባኤዉ በቀን 26/06/2013ዓ/ም ያስተላለፈዉን ዉሳኔ በመሻር ጉባኤዉ በቀን 25/05/2013ዓ/ም ባደረገዉ ስብሰባ ለሰብሳቢ ዳኞችና ለሂደት መሪዎች የወሰነዉ ክፍያ ደመወዝ ነዉ ሲል ወስኗል።
አመልካቾች በቀን 07/01/2014 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡- በፋዳራለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3 ፣ በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 67(1/ሐ) እና የክልለ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17/2 ስር በተደነገገዉ መሰረት በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ሉታዩ የሚገባቸዉ ጉዲዮች በክልለ ፍርድቤቶች ታይተዉ የመጨረሻ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ጉዲዮች ብቻ እንጅ በማንኛዉም አካል የተሰጠ ማናቸዉንም ዉሳኔ እንዲልሆነ በመግለጽ አመልካቾች ያቀረብነዉን መቃወሚያ ተቀብል አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን ሳይኖረዉ የጉባኤዉን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።ጉባኤዉ ፍርድ ቤቶችን እና ዳኞችን ለማስተዲደር በሕግ ሥልጣን የተሰጠዉ ሲሆን አከራከሪዉ ጉዲይ የደመወዝ ማሻሻያ እና የኃላፉነት አበል ክፍያ በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ በመሆኑ የክርክር አመራር ሂደትን ተከትል አከራክሮ የወሰነዉ አይደለም።በመሆኑም ዉሳኔዉ አስተዲደራዊ እንጂ በዲኝነት ነክ አግባብ ታይቶ የተወሰነ አይደለም።በመሆኑም የክልለ ሰበር ችልት ሥልጣን ሳይኖረዉ አስተዲደራዊ ዉሳኔ በመመርመር የሰጠዉ ዉሳኔ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። 1ኛ አመልካች በጉዲዩ ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ በላለበት ዉሳኔ የሰጠዉም ጉባኤዉ ሆኖ እያለ ተጠሪ 1ኛ አመልካችን በተጠሪነት በመሰየም አቤቱታ ለክልለ ሰበር ማቅረባቸዉ ተገቢ አይደለም በማለት ችልቱ 1ኛ አመልካችን ከክርክሩ ዉጭ እንዱያደርግ የቀረበለትን ክርክር ምንም ምክንያት ሳይገልጽ 1ኛ አመልካችን የክርክሩ አካል አድርጎ የሰጠዉ ዉሳኔ የ1ኛ አመልካችን በፋዳራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1 ስር የተደነገገዉን ፍትህ የማግኘት መብት የሚቃረን ነዉ።
እንዱሁም ጉባኤዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ አባል የሆኑበትን ኮሚቴ በማቋቋም እንዱጠና በማድረግ የደመወዝ ክፍያን በአንድ በኩል በልላ በኩል የሥራ ኃላፉዎች በኃላፉነታቸዉ ምክንያት ለሚያከናዉኑት ተጨማሪ ተግባር ሉከፈላቸዉ የሚገባዉን ተጨማሪ የኃላፉነት ክፍያ ራሱን አስችል በመለየት ያቀረበዉን የጥናት ውጤት መሰረት በማድረግ በሥራ ሂደት ኃላፉነታቸዉ ለሚሰሩት ተጨማሪ ሥራ ራሱን የቻለ የሥራ ኃላፉነት ክፍያ እንዱከፈላቸዉ የተወሰነ እንጂ ደመወዝ አለመሆኑን ዉሳኔዉ በግልጽ ያሳያል። ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈዉ በሕግ የተሰጠዉን ሥልጣን በመጠቀም በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም። ጉባኤዉ ከቀን 01/11/2008ዓ/ም ጀምሮ የክልለ ዳኞች ደመወዝ ወጥነት ያለዉ (flate rate)እንዱሆን ወስኗል።የጉባኤው ውሳኔ ተሽሮ ተጠሪ በጠየቁት መሰረት የኃላፉነት አበል እንደደመወዝ የሚቆጠር ከሆነ በተመሳሳይ ሥራ ላይ ለሚገኙ ሰዎች የተለያየ ደመወዝ የሚከፈልበትን ሁኔታ በመፍጠር ለተመሳሳይ ሥራ እኩል ክፍያ የሚለውንና የእኩልነት መርህ የሚቃረን ይሆናል። በዚህ አግባብ በጉባኤው የተሰጠ ውሳኔ በፍርድ ቤቶች ታይተው እንዱከለሱ የሚደረግ ከሆነ የዲኝነት ነጻነትና ተጠያቂነት መርህን የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግልጽ የሆነውን ጉባኤው በቀን 25/05/2010ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውንና ለክርክሩ መሰረት ያልሆነውን የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አዋጅ ስለደመወዝ የሰጠውን ትርጉም በመዋስ በጉባኤው የተሰጠው ውሳኔ የደመወዝ ጭማሪ ነው በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ስህተት ነው። እንዱሁም አመልካች ለተጨማሪ ኃላፉነታቸዉ ከሚከፈላቸው ክፍያ ላይ የጡረታ መዋጮ ከፍለው ከሆነ ተመላሽ እንዱደረግላቸው ከሚመለከተው አካል መጠየቅ ከሚችለ በስተቀር የጡረታ መዋጮ መክፈላቸው ክፍያውን ደመወዝ አያሰኘውም። ጉባኤው በቀን 25/05/2010ዓ/ም የሰጠውን የክፍያ ውሳኔ እና ከዚህ በፉት የነበረውን ደመወዝ ክፍያ መጠን እንደገና በማየት በቀን 28/09/2012ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የነበረውን የደመወዝ መጠን አና የኃላፉነት ክፍያ ከፍ አድርጎ በማሻሻል ራሱን የቻለ ውሳኔ አስተላልፎል።ጉባኤው ይህንን ማድረጉ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ተግባራዊ አድርጓል ከሚያስብል በስተቀር የክልለ ሰበር በውሳኔዉ ላይ እንዲሰፈረው አስቀድሞ የሰጠው ውሳኔ ፀንቶ እያለ ያልተገባ ውሳኔ ሰጥቷል የሚያሰኝ አይደለም።
ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ የሰጠው ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ሳይኖረው በመሆኑ፣1ኛ አመልካች በጉዲዩ ተጠያቂ የሚያደርገው ምክንያት ባለመኖሩ፣በጉባኤው የተወሰነው ደመወዝ ሳይሆን የኃላፉነት አበል በመሆኑ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የጉባኤውን ውሳኔ የከለሰው የጉባኤውን ሥልጣን በሚጋፊ መልኩ በመሆኑ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልን በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን አከራክሮ የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የሰጠውን ዉሳኔ በመከለስ የጉባኤውን ዉሳኔ የሻረበትን አግባብ ከክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 67/1 እና በክልለ አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17/2 አንጻር ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ ሰጥቶ ተጠሪ በቀን 05/04/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
የመልሳቸውም ይዘት በአጭሩ፡-አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡበት ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1/ሐ እና መ) ስር የተደነገገውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የሚያሰኙ መመዘኛዎችን የሚያሟላ ባለመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ በዚህ ችልት ሉመረመር አይችልም ተብል አቤቱታዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 9 መሰረት ውድቅ ላደረግልኝ ይገባል። የሰበር አቤቱታው የተጣሰውን ሕግና የተፈጸመውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የማያሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ሥርዓቱን ጠብቆ ያለቀረበና የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ ዉድቅ ይደረግልኝ።አቤቱታው አግባብነት የላላቸውን አገላለጾችን የክልለን ሰበር ሰሚ ችልት ፍርድ የሚኮንን በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 91(3 እና 4) እና 230 መሰረት ሉሻሻል ወይም ውድቅ ላደረግ ይገባል።የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በፋዳራለ ሕገ መንገስት አንቀጽ 80(3/ለ) እና በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 67(2/ሀ) በክልል ጉዲይ ላይ በተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ያለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የማረም ሥልጣን ተሰጥቶታል።
በተጨማሪም በክልለ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17/2 ስር …መሰረታዊ የሕግ ስህተት ታይቶባቸዋል ' የሚባለትንና' የሚከተለትን ክልላዊ ጉዲዮች“ በሚል ከደነገገው መረዲት የሚቻለው በአንቀጽ 17(12/ሀ እና ለ) ውጪ ያለትን አስተዲደራዊ ውሳኔዎችን የሚመለከት እንጂ ሰበር ሰሚ ችልት ከፉደል ሀ-ሐ ከተዘረዘሩት ውጪ ሉያይ አይችልም የሚል ትርጉም ሉሰጠዉ አይችልም።በዚህ ሕግ አንቀጽ 17/3 ላይ ‛በሰበር እንዱታይ የሚቀርብ ማናቸዉም አቤቱታ“ የሚለዉ በአንቀጽ 17/2 ስር ‛የሚባለትን“ ከሚለው ቃል ጋር እንዱሁም በፋዳራልና በክልል ሕገ መንግስቶች ላይ ከተመለከተው ጋር ተጣምረው ሲተረጎሙ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በአስተዲደር አካላት የሚሰጡትን የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች የመመልከት ሥልጣን እንዲለው የሚያሳይ በመሆኑ የክልለ ሰበር ይህንን መሰረት በማድረግ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።
አመልካቾች በሰ/መ/ ላይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ጠቅሰው ቢከራከሩም ይህ ትርጉም ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የለዉም።ይልቁንም በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም የዐቃቤ ሕግ ጉባኤ በዱስፔሉን ጉዲይ የሰጠው ውሳኔ በሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ የሕግ ስህተት ከመታረሙ አንጻር ሲታይ በክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የተሰጠ ውሳኔ ላይ ያለውን የሕግ ስህተት ለማረም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የመመርመርና የማረም ሥልጣን እንዲለው ነው። እንዱሁም የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ውሳኔ የሕግ ስህተት በክልለም ሆነ በፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት ቀርበው ሉታረሙ እንደሚችለ በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቷል።
ጉባኤው የሁለም ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች ደመወዝ 82% ተሰልቶ ይከፈል የሚል ጥቅል ዉሳኔ ወስኖ እያለ ደመወዙን ሲያሰላ ሲከፈል የነበረዉን ደመወዝ በመቀነስ የኃላፉነት አበል ክፍያ በሚል ቀንሶ ያሰላዉና በጀት የሚያዘው የ1ኛ አመልካች አስተዲደር በመሆኑ በክርክሩ መግባቱ ተገቢ ነዉ ሉፈጸም የሚችል ውሳኔ እንዱሰጥም የሚያደርግ በመሆኑ የክልለ ሰበር በዚህ ረገድ አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ባለመቀበለ የተፈጸመ ስህተት የለም።
ተጠሪ ጉባኤው ደመወዝና የኃላፉነት አበል የመወሰን ሥልጣን የለውም የሚል ቅሬታ አላቀረብኩም።ችልቱም በዚህ መልኩ አልወሰነም።ተጠሪ ቅሬታ ያቀረብኩበት ጉባኤው በቀን 26/06/2013ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው። ጉባኤው በቀን 28/09/2012ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ላይ 82% እየተጨመረ ተሰልቶ ይከፈል ሲል ደመወዝና የኃላፉነት አበልን ለይቶ ውሳኔ ሰጥቷል።የተጠሪ ቅሬታ በጉባኤው ውሳኔ መሰረት የ1ኛ አመልካች አስተዲደር የተጠሪን ደመወዝ ሲያሰላ በብር 13,702.00 ላይ 82% ጨምሮ ማስላት ሲገባው ከነበረኝ ደመወዝ ቀንሶ ብር 12,702.00 ይዞ 82% ያሰላበት መንገድ ተገቢ ባለመሆኑ ለፍርድ ቤቱ አስተዲደር ቅሬታ አቅርቤ ምላሽ ሳይሰጠኝ ቀርቷል።ለጉባኤው ያቀረቡኩትን ቅሬታም ጉባኤው የተሰላበት መንገድ ትክክል ነው በማለት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል።ጉባኤው በቀን 25/05/2010ዓ/ም ደመወዝና የኃላፉነት አበል ለይቶ በወሰነዉ መሰረት ሲከፈለኝ ከነበረዉ ከብር 13,702.00 ደመወዝ ላይ የጡረታ መዋጮ ስከፍል እንደቆየሁ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አረጋግጦ የሰጠዉ ጉባኤዉ ወስኖ የነበረዉ ደመወዝ እንጂ የኃላፉነት አበል አይደለም በማለት በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ተብል የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾችም በቀን 04/05/2014 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመለከተው የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ውሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘውን ጭብጥ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም የዚህን ውሳኔ የሚሹ ዋና ዋና ጭብጦች የአማራ ክልል ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ(ጉባኤ) የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር አይቶ የመዲኘት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የክልለ ሰበር የጉባኤውን ውሳኔ በስረ ነገሩ አይቶ ሽሮ በመወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት አለ ወይስ የለም? የሚለ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለእነዚህ ጭብጦች ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ይረዲ ዘንድ አንድን የመጨረሻ ውሳኔ በሰበር (cassation) በማየት፣ በይግባኝ (appeal) በማየት እና በዲኝነት አይቶ በመከለስ (judicial review) መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት ምንድነው? እንዱሁም ተጠሪ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት ዲኝነት ጥያቄ በሰበር ላታይ የሚገባ ነው ወይስ በዲኝነታዊ ክለሳ ላታይ የሚገባ ነዉ? የሚለትን ተጓዲኝ ጭብጦች ጭምር መመርመር እንደሚገባ ተገንዝበናል።
ከላይ የተጠቀሱትን ጭብጦች ከመመርመራችን በፉት ተጠሪ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለውም በማለት የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1/ሐ እና መ)ን በመጥቀስ ያቀረቡትን መቃወሚያ በቀዲሚነት ተመልክተናል።በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1/ሐ እና መ) ስር በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልቶች ታይተው በተሰጡ የመጨረሻ ውሳኔዎች ላይ ተፈጽመዋል ሉባለ የሚችለ እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ታይተዉ ሉታረሙ የሚችለ መሰረታዊ የሕግ ስህተቶችን በተመለከተ በዝርዝር ተደንግጓል። እነዚህም ምክንያቶች (1) በአዋጁ አንቀጽ 2(4/ሀ) ስር በተመለከተው መሰረት ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በሚቃረን አኳኋን በክልል ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ፤
(2) በአዋጁ አንቀጽ 2(4/ሸ) ስር እንደተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በሚቃረን አኳኋን በክልል ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ፤
(3) በአንቀጽ 2(4/ለ) እና 10(1/መ) ላይ እንደተመለከተው የሕዝብን ጥቅም በሚመለከት እና ሀገራዊ ፊይዲ ባለው ጉዲይ ሕግን አላግባብ በመተርጎም ወይም ለጉዲዩ አግባብነት የላለዉ ድንጋጌ ተጠቅሶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ሲሆን ከሚለ ሦስቱ ምክንያቶች መካከል ቢያንስ አንደን የሚያሟላ እና ፍትህን የሚያዛባ ጉልህ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት የመጨረሻ ውሳኔ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው።
የተያዘው ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል የተባለበት ምክንያት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን አከራክሮ የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የሰጠውን ውሳኔ በመከለስ የጉባኤውን ውሳኔ የሻረበት አግባብ የክልለን ሕገ መንግስት አንቀጽ 67/1 የሚቃረን መሆን አለመሆኑን እንዱመረመር ነው።አመልካቾች በአቤቱታቸውም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ በሕገ መንግስት አና በማቋቋሚያ አዋጁ የተሰጠውን ሥልጣን ተግባራዊ እንዲያደርግ የሚያደርግ ውሳኔ ከመሆኑም በተጨማሪ በፋዳራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) ስር ከተሰጠው ስልጣን ዉጭ በመውጣት የጉባኤውን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ የፋዳራለንም ሆነ የክልለን ሕገ መንግስት እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አስቀድሞ በሰ/መ/ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነው በማለት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1ሐ እና መ) ማዔቀፍ ውስጥ ላታይ የሚገባ ጉዲይ ነው በማለት ተከራክረዋል።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/2 ስር የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልለ ጉዲይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዲኝነት ሥልጣን ይኖረዋል ሲል ደንግጓል።በተመሳሳይ በአማራ ክልል በተሻሻለው ሕገ መንግስት አንቀጽ 67(1/ሀ) ስር ዝርዝሩ በሕግ በሚወሰነው አግባብ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክልላዊ ጉዲዮችን በተመለከተ ከፍተኛና የመጨረሻው የዲኝነት ሥልጣን እንዲለው ተደንግጓል። እንዱሁም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/2 ስር ከተደነገገው በተጨማሪ በዚሁ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) ስር ዝርዝሩ በሕግ በሚወሰነው መሰረት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን እንዲለው ተደንግጓል።
እኛም ከፍ ሲል በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስር ከተጠቀሱት መመዘኛዎች እና በፋዳራለና በክልለ ሕግጋተ መንግስታት አንጻር ጉዲዩን እንደተመለከትነው የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የሰጠውን ውሳኔ በሰበር ተመልክቶ የወሰነው በክልለ እና በፋዳራል ሕግጋተ መንግስታት የተሰጠውን ሥልጣን በሚቃረን አኳኋን መሆን አለመሆኑ፣ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ የክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ በክልልም ሆነ በፋዳራል ሕግጋተ መንግስታት የተሰጠውን ሥልጣን ተግባራዊ እንዲያደርግ የሚያደርግ ውጤት ያለው መሆን አለመሆኑን እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በሰ/መ/ እና በላልችም መዛግብት ላይ ከተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር ተገናዝቦ በአዋጁ አንቀጽ 10(1/ሐ እና መ) ማዔቀፍ ስር ሉመረመር የሚገባዉ ጉዲይ እንደሆነ ተገንዝበናል። በመሆኑም ተጠሪ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በሰበር ለማየት ሥልጣን የለውም ሲለ ያቀረቡትን ተቃዉሞ አልተቀበልንም።
በመጀመሪያም ከላይ ተጓዲኝ ጭብጦች ናቸው ብለን የያዝናቸውን ጭብጦች መርምረናል።አንድን የመጨረሻ ውሳኔ በሰበር በማየት (cassation) ፣ በይግባኝ (appeal) በማየት እና በዲኝነት አይቶ በመከለስ (judicial review) መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት ምንድነው የሚለዉን በቅድሚያ መመልኩቱ ተገቢ ይሆናል። ከመዝገበ ቃላት ትርጓሜ የተነሳን እንደሆነ ሰበር ወይም cassation በሚል የሚታወቀው ቃል በታዋቂዉ ብላክስ ልዉ መዝገበ ቃላት ላይ እንደተመለከተው ካሰር (casser) ከሚል የፈረንሳይኛ ቋንቋ ግስ የመጣ ቃል ሆኖ የቃለ ጥሬ ትርጉምም የአንድን ፍርድ/ውሳኔ የተፈጻሚነት ኃይል(force) መስበር እና ሕጋዊ ዉጤት እንዲይኖረው ማድረግ(invalidate)፣መሻር ወይም ተግባራዊነቱን ማስቀረት ነው የሚል ትርጓሜ የተሰጠው ነው። (cassation comes from the French verb casser and its literal meaning is to “quash the force and validity of a judgement.(black’s law dictionary 5ኛ እትም ገጽ 197 ይመለከቷል።
) የሰበር ሥርዓት ምንጭ የሲቪል ሕግ ሥርዓት ሲሆን እዛን ግራዊች(Ezan Grouich) የተባለ ሰዉ (The Soviet Codes of Law)በሚል ባሳተሙት መጸሀፊቸው ላይ እንደገለጹት በራሽያ ፋዳሬሽን የሰበር ስርዓት የመጨረሻ የዲኝነት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የሕግ ስህተት ያለበትን የመጨረሻ ፍርድ የተፈጻሚነት ኃይል በመስበር በምትኩ ላላ ፍርድ የሚሰጥበት ሥርዓት ነው ሲል ይገልጸዋል። በልላ በኩል Peter Herzos እና Martha Weser እንዱሁም Mauro Cappelletti እና Joseph M.
Perillo በፈረንሳይና በጣሉያን የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ እንደ ቅደም ተከተላቸው መጽሐፍት የፃፈ የሕግ ምሁራን መጽሐፍቻቸው ላይ የሰበር ሥርዓት በእነዚህ አገራት አንድ የይግባኝ የሚታይበትን ሂደት የጨረሰ የሕግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ፍርድ የመጨረሻ የዲኝነት አካል በሆነው ፍርድ ቤቶቻቸው ታይቶ የሚሻርበት ወይም ወደ ሥር ፍርድ ቤት በመመለስ የሚወስኑበት እንጂ የራሳቸውን አዱስ ውሳኔ የሚሰጡበት እንዲልሆነ ይገልጻለ።ከዚህ የምንገነዘበው በሰበር የሚታየው በመጨረሻ ፍርድ ቤት እንደሆነ ፣በሰበር የሚታየውም ፍርድ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ፍርድ ሆኖ በይግባኝ የሚታየበትን ሂደት የጨረሰ የሕግ ስህተት ያለበት የመጨረሻ ፍርድ እንደሆነ እና ፈረንሳይና ጣሉያን የሰበር ፍርድ ቤቶች የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ከመሻር ባለፈ እንደ ራሺያ ፋዳሬሽን ፍርድ ቤት አዱስ ውሳኔ እንደማይሰጡ ነው።
በአገራችን ‛ስለሰበር“ ምንነት ትርጓሜ የሰጠ ሕግ ባይኖርም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4 እና 5) ስለመሰረታዊ የሕግ ስህተት እና ስለመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠው ትርጓሜ የምንገነዘበው ሰበር የሚያየው የፋዳራለ የመጨረሻ ዲኝነት አካል በሆነው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተደራጀ ሰበር ሰሚ ችልት መሆኑ፣ የሚያያውም ውሳኔ በዚሁ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና በበታች መደበኛ ፍርድ ቤቶች ታይቶ የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተትን ብቻ ሳይሆን በሕግ የመዲኘት ሥልጣን በተሰጠው አካል፣በተቋማት ወይም በአማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዳዎች የተሰጠ እና ለጉዲዩ እልባት የሚሰጥ ፍርድ፣ብይን፣ትእዛዝ፣ውሳኔ እና/ወይም የይግባኝ ሂደቶችን የጨረሰ ፍርድ፣ብይን፣ትእዛዝ ወይም ውሳኔን እንደሚጨምር ተደንግጓል።እንዱሁም በአገራችን እስካሁን በሰበር ችልቱ ከዲበረው ዲኝነታዊ ፍልስፍና (judicial jurisprudence) እንደሚታወቀው ሰበር ችልት ያለዉ ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት አርሞ ዉሳኔውን ከመሻር እና ጭብጥ ይዞ ከመመለስ ባለፈ በጉዲዩ ላይ አዱስ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ጭምር እንዲለው ነው። ይህም የእኛ አገር የሰበር ሥርዓት ከላልች ከላይ ከተጠቀሱት ውሳኔዎችን በሰበር የማየት ሥርዓት ከዘረጉ አገራት ሥርዓት አንጻር ሲነጻጸር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ከማረም አኳያ ሰፉ ሥልጣን እንዲለው የሚያስገነዝብ ነው።ይህም የሆነው በሕገ መንግስቱ ይህ ሥርዓት እንዱዘረጋ መነሻ ምክንያት የሆነው የሕግ አተረጓጎም ወጥነት የማምጣትና በዚህም ዜጎች በእኩልነት ተጠቃሚ እንዱሆኑ የማድረግ ዓላማ በተሟላ መልኩ ከግብ እንዱደርስ ለማድረግ እንደሆነ ይታመናል።
በልላ በኩል ዲኝነታዊ ክለሳ (judicial review) ከላይ በተጠቀሰው መዝገበ ቃላት ላይ፡ A court's power to review the actions of other branches or levels of government; esp.,the courts' power to invalidate legislative and executive actions as being unconstitutional. …And a court's review of a lower court's or an administrative body's factual or legal findings.(black’s law dictionary 9 ኛ እትም ገጽ 924). የሚል ትርጓሜ የተሰጠው ሲሆን ይህም በግርድፈ ላልቹ የመንግስት አካላት (ሕግ አውጭው እና ሕግ አስፈጻሚው) እንደ ቅደም ተከተላቸው የሚያወጡት ሕግ ፣ የሚፈጽሟቸው ተግባራት እና የሚያስተላልፊቸው ውሳኔዎች ሕገ መንግስታዊ መሆን አለመሆናቸውን (constitutionality) እና ሕጋዊነታቸውን (legality) ፍርድ ቤቶች የሚከልሱበትንና ጉድለት ካለባቸዉም ተግባራዊ እንዲይሆኑ የሚወስኑበትን ሥርዓት የሚመለከት ነው የሚል ይዘት ያለው ነው።
እንዱሁም ከተለያዩ የሕግ ድርሳናት መገንዘብ እንደሚቻለው በዲኝነታዊ ክለሳ (judicial review) የሚታዩ ጉዲዮች እንደየአገራት የሕግ ሥርዓት ሉሰፊና ሉጠብ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ አውጪው የወጣ ሕግ እና የተላለፈ ዉሳኔ ፣የሕግ አስፈጻሚው ወይም የአስተዲደር አካላት ተግባራትና ውሳኔዎች በዲኝነት አካል የሚከለስበት ሥርዓት በሰፉው የሚታወቅ ነው።አገራት በሕግ አውጭው የወጣ ሕግ ወይም የተላለፈ ውሳኔ እንደዚሁም በአስፈጻሚው/በአስተዲደር አካል የሚፈጸሙ ተግባራት ወይም የሚተላለፈ ውሳኔዎችን ሕገ መንግስታዊነት እና/ወይም ሕጋዊነት (Constitutionality and legality) በዲኝነት አይተው እንዱከልሱ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ይሰጣለ።ሕገ መንግስትን መተርጎምን የሚጠይቁ የሕገ መንግስታዊነትና ሕጋዊነትን ጥያቄዎችን ተቀብለው ሕገ መንግስትን ተርጉመው የሕግ አውጪውን ሕግና ውሳኔ እንዱሁም የሕግ አስፈጻሚውን ሕግ፣ውሳኔ ወይም ላላ ተግባር በዲኝነት አይተው እንዱከልሱና የመጨረሻ ውሳኔ ኢንዱሰጡ አሜሪካ እና ሕንድ የመሰለ አገራት ለመደበኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶቻቸው ሥልጣን የሚሰጡ ሲሆን እንደ ጀርመን ፣ኦስትሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ያለ አገራት ደግሞ ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶቻቸው ሥልጣን ይሰጣለ።
እነዚህ ፍርድ ቤቶች አንድ ሕግ ወይም አስተዲደራዊ ውሳኔ ሕገ መንግስቱን የሚጥስ ወይም የሚቃረን እንዱሁም የሕጋዊነት ጉድለት አለበት የሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ ሕጉን ከሕግነት ተራ በማስወጣት ተፈጻሚ እንዲይሆን ለማድረግ የአስተዲደር ውሳኔውም ተግባራዊ እንዲይሆን ለመወሰን የሚከተለበት አካሄድም እንደዚሁ የተለያየ ነዉ። አሜሪካ የዲኝነታዊ ክለሳ የምታደርግበት ሞዳል ያልተማከለ ዲኝነታዊ ክለሳ ሥርዓትን (The decentralized model of judicial review) ሲሆን በዚህ ሞዳል መሰረት የክለሳ ጥያቄዉ ከበታች ፍርድ ቤት ጀምሮ በየደረጃዉ ይግባኝ ሥርዓት በሚመስል አካሄድ ታይቶ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የመጨረሻ አስገዲጅ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንዱቋጭ ታደርጋለች።
እንደጀርመን ያለት ደግሞ የክለሳ ጥያቄዉ በቀጥታ ለሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እንዱቀርብ የሚያደርግ ሥርዓት(The centralized model of judicial review) የሚከተለ ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት ክለሳ ተደርጎ የመጨረሻና አስገዲጅ ውሳኔ እንዱሰጥበት ያደርጋለ።በደቡብ አፍሪካ ደግሞ የአንድ ሕግ ሕገ መንግስታዊነትና እና የአንድን የአስተዲደር/የአስፈጻሚ አካል ተግባር/ውሳኔ ሕገ መንግስታዊነትና ሕጋዊነት በተመለከተ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የሕገ መንግስታዊነት ትርጉም (Preliminary Constututional Interpretation) ሕገ መንግስቱን ተርጉሞ እንዱወስን ሥልጣን ትሰጥና የሕገ መንግስታዊነት ጥያቄ የተነሳበት ሕግ እና የሕገ መንግስታዊነትና የሕጋዊነት ጥያቄ የተነሳበት የአስፈጻሚ/የአስተዲደር አካል ተግባር/ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲይኖራቸው የመጨረሻውን ዉሳኔ የመስጠት ሥልጣን የሚኖረዉ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ነዉ የሚል ሥርዓት በሕገ መንግስቷ እንደዘረጋች በዘርፈ የተጻፈ ድርሳናት ያሳያለ።
የእኛን አገር ስርዓት የተመለከትን እንደሆነ በሦስቱ የመንግሥት አካላት መካከል ማለትም በሕግ አውጭው፣ ሕግ አስፈጻሚው እና በሕግ ተርጓሚው መካከል በፋዳራልና በክልል ሕግጋተ መንግስታት በተመለከተው አግባብ የሥልጣን ክፍፍል ያለ ቢሆንም በመካከላቸው የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ተጠብቆ (check and balance) እየተሰራ መሆኑ የሚረጋገጥበት ሥርዓት ከላለ ተቋማቱ በሕግ የተጣለባቸውን የዜጎችን ሰብዓዊና ዱሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር አይችለም። በአንጻሩ የእርስ በእርስ ክትትልና ሚዛኑን ጠብቆ የመስራት መርህ አተገባበር አለአግባብ ጣልቃ መግባትን ካስከተለ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዲቱ ስለሚያመዝንና የተጣለባቸውን ግዳታ እንዲይወጡ ሉያደርጋቸው ስለሚችል ቁጥጥሩ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ መፈጸም አለበት።
አስተዲደራዊ አካላት የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በፍ/ሕ/ቁጥር 401/1 እንደተመለከተው ከተሰጣቸው ሥልጣን በማለፍ ከወሰኑ (ultra virus) ወይም በተሰጣቸው ሥልጣን ስር ሆኖ ነገር ግን በሕጉ የተመለከቱትን አስገዲጅ ሁኔታዎችና ፍርም ሳይከተለ የሚፈጽሙት ተግባር ወይም ውሳኔ ፈራሽ ነው።
በአስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ የዲኝነት ክለሳ መኖር ካለበት ዋና ዋና ምክንያቶች አንደ የመንግሥት አካላት የሥልጣን ክፍፍል መርሕ ነው። በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79/1 መሰረት የዲኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል። ይህም ከሕገ-መንግሥታዊ ክርክሮች (constitutional disputes) ውጭ ማንኛውም በፍርድ ቤት ታይተው ሉወሰኑ የሚችለ ጉዲዮች (justiciable matters) ላይ ፍርድ ቤቶች ዲኝነታዊ ክለሳ የማድረግ (judicial review) ተፈጥሮአዊ የሆነ ዲኝነታዊ ሥልጣን (inherent judicial power) እንዲላቸው ያሳያል። በፍርድ ቤት ታይተው ሉወሰኑ የሚችለ ጉዲዮች የሚለውም የጉዲዮቹ ባሕሪ በፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር ሉወድቁ የማይችለ፣ አከራክሮ ሉፈጸም የሚችል ውሳኔ ላሰጥባቸው የማይችለ ጉዲዮችን የሚመለከት ሲሆን በልላ በኩል ጉዲዮቹ በፍርድ ላታይ የሚችለ እንኳን ቢሆን ላልች የመንግሥት አካላት በሕገ-መንግሥት ባለው የሥልጣን ክፍፍል መርሕ መሰረት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን (constitutionally mandated powers) መሰረት አድርገው የሚወስኗቸው ጉዲዮችንም ይጨምራል። በልላ በኩል የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78/4 እና 37 ላይ የተደነገገው አንድ ላይ ሲነበብ በሕግ የተደነገገን የዲኝነት ሥርዓትን የሚከተል የዲኝነት ነክ አካላት በሕግ የመዲኘት ሥልጣን ሉሰጣቸው እንደሚችል ያስገነዝባል። የእነዚህ አካላት የዲኝነት ሥልጣን በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን በግልጽ ሕግ ለመዲኘት ሥልጣን ሲሰጣቸውና የሚሰሩበት የተደነገገ የዲኝነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ይህን ተከትለው ሲሰሩ የሚኖራቸው ሥልጣን ነው። ይህም በዘመናዊው የመንግሥት ሥርዓት መንግሥት ብዙ ጉዲዮች ላይ ሰፉ ሥልጣን ያለው አስፈጻሚዉ አካል በመሆኑ ለመንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል የዲኝነት ነክ ሥልጣን አስፈላጊ በመሆኑ፣ የተወሰኑ ጉዲዮች ደግሞ ፍሬ ነገሮችን ለመመልከት ልዩ ዔውቀት (specialization) የሚጠይቁ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን የሥራ ጫና ለማቃለል ሥራ ላይ ይውላለ።
ነገር ግን ጠንካራና አስተማማኝ የዜጎች ሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ዳሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሕግ የበላይነትን ማስፈን ወሳኝ ነው። በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት መግቢያ ላይ እንደተመለከተው የሕግ የበላይነትን የተረጋገጠበት አሰራር መዘርጋት የሕገ-መንግሥቱ ዋነኛ ዓላማ ሲሆን አንደ መስፈርት ደግሞ የዜጎችን በፍርድ ሉታዩ የሚችለ ጉዲዮች በነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዱታይ መደረጉ ነው።የሕግ የበላይነት መርሕ ሰፉ ሀሳቦችን የያዘ ቢሆንም በሕግ ሥልጣኑ የተገደበ መንግሥት እንዱኖርና የዜጎች መብት የተከበረበት ሥርዓትን ለመፍጠር የሚረዲ ነው። በፋዳራለ ሕገ-መንገሥት መግቢያ ላይ የተመለከተው የሕግ የበላይነት ዓላማ ከግብ የሚደርሰው የመንግስት አካላት ለሚወስደት እርምጃ ተጠያቂ መሆንና ኃላፉነት መውሰድ ሲችለ ነው።ይህም ከሚረጋገጥባቸው መንገድች አንደ በሰጡት አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ መብቱ የተነካበት ሰው ጉዲዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሲችልና ፍርድ ቤቶችም ተገቢውን መንገድ ተከትለው ጥያቄ የቀረበበት ዉሳኔ ሕጋዊነትን የተከተል መሆን አለመሆኑን በዲኝነት ማየት ሲችለ ነው። እንዱሁም የአስተዲደር አካላት የሰጡት ውሳኔ በሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት የተከተለና ዜጎች ተገቢው የመሰማት መብት (due process of law) ያገኙ ስለመሆኑ ቁጥጥር ለማድረግ በአስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ የዲኝነት ክለሳ ያስፈልጋል።
በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 79(1) መሰረት የዲኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ ተደንግጓል።በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ላይ ሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች በፍርድ ሉዲኙ የሚችለ እስከሆኑ ድረስ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ጉዲዮችን እንዱመለክት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78 መሰረት ሥልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ቀርቦ መታየቱ ነጻ የዲኝነት አካል ያስፈለገበት ዓላማ ሉሳካ የሚችልበትና ሰዎች ያላቸውን መብት በሕግ ማስከበር የሚችለበት ዋነኛ መሣሪያ አስተዲደራዊ ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ ማየት መቻል ነው። የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃም አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ የዲኝነት ክለሳ አስፈላጊ መሆኑን ያሰገነዝባል። በኢፋዱሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 13(1) ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና ማስከበር ኃላፉነት ከተሰጣቸው አካላት ዋነኛው የዲኝነት አካለ በመሆኑ የአስተዲደር አካላት ከዜጎች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲይኖር ለመከላከል ሆነ ጥሰት ሲኖር ዜጎች ጥሰቱን የሚያሳርሙበት ዔድል ስለሚያስፈልግ አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ የዲኝነት ክለሳ የግድ የሚል ስለመሆኑ ያስገነዝባል። ስለሆነም ከፍርድ ቤት ውጭ በሕግ የዲኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት የሚሰጡ ዉሳኔዎችንም ሆነ በሕግ በተሰጣቸው ኃላፉነት የሚሰጧቸው አስተዲደራዊ ውሳኔዎች በዲኝነታዊ ክለሳ ሂደት በማለፍ በፍርድ ቤት መታየት ይኖርባቸዋል።
በልላ በኩል የይግባኝ(Appeal) አቀራረብ ሥርዓት ምንነት የተመለከትን እንደሆነ ይግባኝ የሚባልበት ሥነ ሥርዓት በዋናነት በበታች መደበኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ በየተዋረደ ባለት የበላይ መደበኛ ፍርድ ቤቶች በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት እንደገና የሚመረመርበትን የሚመለከት ነው።
(የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 12/2፣ 321 እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 54 ይመለከቷል።) በተጨማሪም አስተዲደራዊ ውሳኔ ወይም የዲኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠው አካል(Quasi-judicial organ) የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው በተቋቋመና በከፍተኛው የዲኝነት-ነክ ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በሕግ በግልጽ ከተደነገገም እነዚሁ አካል የሰጡት ውሳኔ በከፍተኛው መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚታይበትን ሥነ ሥርዓት የሚመለከት ነው።(ለአብነት በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 69/2፣98/4፣ 115/2፣ 153/8፤ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 29(1 እና 4) እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ይህንን አዋጅ በተካው አዱስ አዋጅ ላይ በተመሳሳይ በአንቀጽ 56(1 እና 4) እና በላልችም ላይ ተደንገገው ይመለከቷል።የይግባኝ ሥርዓትን ከዲኝነታዊ ክለሳ የሚለዩትም ምክንያቶች በይግባኝ ጊዜ በልዩ ሁኔታ በሕግ እስካልተገደበ ድረስ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበታች ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረውን ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን፣በውስን ሁኔታዎች አዱስ ማስረጃ መቀበልንና የበታች ፍርድ ቤቶች ወይም የዲኝነት-ነክ አካል የሰጡት ውሳኔ የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ድምዲሜ ስህተት አለበት ብል ሲያምን ዉሳኔዉን ሽሮ አዱስ ውሳኔ መስጠትን ጭምር የሚያካትት ሲሆን በዲኝነታዊ ክለሳ ደግሞ ሕግ አውጪው ያወጣው ሕግ፣ሕግ አስፈጻሚው የፈጸመዉ ተግባር(የወሰነው ውሳኔ) እንዱሁም የዲኝነት-ነክ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል የወሰነዉ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ ብቻ ተመስርቶ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን በመከለስ ሕገ መንግስታዊ ወይም ሕጋዊ አይደለም የሚል ከሆነ ተፈጻሚ እንዲይሆን መወሰን ወይም ውሳኔውን ሽሮ እንደገና ታይቶ እንዱወሰን መመለስ አሉያም የክለሳ ጥያቄዉን ውድቅ በማድረግ ውሳኔውን ማጽናት እንጂ የራሱን አዱስ ውሳኔ አይሰጥም።
ከላይ በዝርዝር ከተመለከትነው ከተለያዩ አገራት ልምድ፣ በአገራችን በተለያዩ ሕግጋት እና በዲኝነት ሥራ ከዲበረው ተሞክሮ (judicial jurisprudence) ከተንጸባረቀው የምንገነዘበውም አንድን ዉሳኔ በሰበር የማየት፣ በይግባኝ የማየት እና በዲኝነት አይቶ የመከለስ ሥርዓት በጽንሰ ሀሳብ ደረጃም ሆነ በአተገባበራቸው የተለያየ የክርክር አመራርንና መነሻ ምክንያትን የሚጠይቁ እንደሆኑ ነው።በአገራችን በፋዳራል ደረጃ በልዩ ሁኔታ በሕግ በግልጽ በተቃራኒዉ እስካልተደነገገ ድረስ አንድ በፍርድ ቤት፣ በአስተዲደር አካል ወይም ዲኝነት ነክ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ ውሳኔ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ሉመረመር የሚችለው እንደነገሩ ሁኔታ በሕግ በተዘረጋው በይግባኝ እና በዲኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ብቻ ነው።ምክንያቱም የሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ብቻ መርምሮ ስህተቱን የሚያርም ውሳኔ መስጠት በመሆኑ ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አካል የተሰጠ ውሳኔ በተለይም በዲኝነታዊ ክለሳ ላታይ የሚችል ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ ሳይታይ በቀጥታ ለሰበር ሰሚ ችልት የሚቀርብ ከሆነ በመደበኛ ፍርድ ቤት በክለሳ ሥርዓት ሉመረመሩ የሚችለና ፍሬ ነገሮችን ከማስረጃ አንጻር ጭምር መመርመርንና ማረጋገጥን የሚጠይቁ የክርክር ነጥቦች ወይም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልሆኑ ስህተቶች የሚታረሙበትን ሂደት የሚገድብ ይሆናል።
እንዱሁም አንድ አስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ ነው ተብል እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ፣በዲኝነታዊ ክለሳ ቀጥልም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ሥርዓት ታይቶ የማይታረም ከሆነ የሕገ መንግስት የበላይነት መርህ፣የዱሞክራሲያዊ መንግስት መገለጫ የሆነው የተጠያቂነት መርህ እና የዱሞክራሲያዊ መንግስት የሥልጣን ክፍፍል መሰረታዊ መርህ የሆነው የመንግስት አካላት እርስ በእርሳቸው የሚኖራቸዉ የሥልጣን ክትትልና ሚዛን የመጠበቅ (Check and Balance) መርህ እንዱሸራረፍ ያደርጋል።በመሆኑም በሕግ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ለሰበር ቀርቦ እንዱታይ እስካልተደነገገ ድረስ በሰበር ከመታየቱ በፉት እንደነገሩ ሁኔታ በይግባኝ ወይም በዲኝነታዊ ክለሳ ሥነ ሥርዓት ላታይ ይገባል።
ከፍ ሲል በዝርዝር የተመለከትነው በአብዛኛዉ የፋዳራል ሕግጋትን ማዔከል ያደረገ ቢሆንም በክልል ደረጃ የሚኖረው የሰበር ሥርዓትም ሆነ ዲኝነታዊ ክለሳ ከላይ ከተመለከትነው የሕግ እና የጽንሰ ሀሳብ ትንተና አንጻር ሲታይ በፋዳራል ደረጃ ከተዘረጋው የሰበር ሥርዓትና ዲኝነታዊ ክለሳ በመሰረታዊነት የተለየ አይደለም።
ከላይ የተመለከትነውን ትንታኔዎች መሰረት አድርገን የያዝናቸዉን ጭብጦች ስንመረምር ከላይ ይዘቱ ከተገለጸዉ የግራ ቀኙ ክርክር መገንዘብ እንደሚቻለው ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ላቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ነው። ጉባኤው በክልለ አዋጅ ቁጥር 209/2006 አንቀጽ 4/1 መሰረት እንደገና የተቋቋመ ሲሆን በክልለ ሰበር እና በዚህ ችልት ደረጃ 2ኛ ተጠሪ ሆኖ የተሰየመው የጉባኤው ጽ/ቤት ደግሞ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አካል ሆኖ እንደተደራጀ የዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 ይዘት ያስገነዝባል። በተለይ ጉባኤው ከሦስቱ የመንግስት አካላት በተለየ ማንነት የሶስቱን የመንግስት አካላት ስብጥር ይዞ ነገር ግን ደግሞ በአስተዲደራዊ ተጠያቂነት ረገድ ለክልለ ምክር ቤት ተጠሪ ሆኖ እንደተቋቋመ ከክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 66(4/ሐ) እና ከአዋጅ ቁጥር 209/2006 አንቀጽ 7(1/ሐ) መገንዘብ ይቻላል።በመሆኑም ጉባኤዉ ሕገ መንግስታዊ ተቋም እንደሚባለት ተቋማት ሉቆጠር የሚችል እንጂ ከሦስቱ የመንግስት አካላት የአንደን መደብ ይዞ የተቋቋመ አይደለም።ይህ ልዩ የሚያደርገው ባህርይ ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልለ ሕገ መንግስትና በማቋቋሚያ አዋጁ ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባሩ አንጻር የእለት ተእለት ተግባሩን ሲያከናውን አስተዲደራዊ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ነው። በዚህ መልኩ ጉባኤው የዳኞችን እና የጉባኤውን ተሿሚዎች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ወይም የኃላፉነት አበል በተመለከተ ውሳኔ የሚሰጠው በክርክር መልክ ሰምቶና አከራካሪውን ጭብጥ በማስረጃ አጣርቶና ማስረጃ መዝኖ ሳይሆን አስፈላጊውን ጥናት አስደርጎ አስተዲደራዊ ሥልጣኑን (ኃላፉነቱን) በመጠቀም አስተዲደራዊ ውሳኔ በማሳለፍ እንደሆነ መገንዘብ የሚቻል ነው።
በልላ በኩል ጉባኤው አንድ ዲኛ በዱሲፔሉን ምክንያት ጥፊት ፈጽሟል ብል ከሥራ እንዱሰናበት ውሳኔ መስጠት እንዱችል ወይም በሕመም ምክንያት ዲኛዉ ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን አልቻለም ብል እንዱሰናበት ውሳኔ እንዱሰጥ በክልለ ሕገ መንግስትና በጉባኤው ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ለጉባኤው ሥልጣን ተሰጥቶታል።በዚህ መልኩ ጉባኤው ውሳኔ የሚሰጠው ክርክርና ማስረጃዎችን ሰምቶና መርምሮ እንዱሁም ማስረጃዎችን መዝኖ የአከራካሪዉን ጭብጥ መኖር አለመኖር ካረጋገጠ በኋላ በመሆኑ የዲኝነት-ነክ ሥልጣኑን ተጠቅሞ የሚፈጽመዉ ተግባር ነዉ። የዲኝነት-ነክ ሥልጣኑን ተጠቅሞ በዚህ አግባብ የሚሰጠውም ውሳኔ በክልለ ምክር ቤት ተመርምሮ የሚጸድቅበት ሥርዓት በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 66/4 እና አዋጅ ቁጥር 209/2006 አንቀጽ 7(1/ሐ እና 6) እና 24(1/ሀ፣ሐ እና መ) በግልጽ ተመልክቷል።በመሆኑም በዚህ ሥልጣኑ የሚሰጠው ዉሳኔ በክልለ ምክር ቤት ሉመረመር ተመርምሮ ተገቢው ውሳኔ ላሰጥበት ከሚችል በስተቀር በልዩ ሁኔታ በሕግ እስካልተደነገገ ድረስ በመደበኛ ፍርድ ቤት በዲኝነት የሚታይ አይደለም።
ከላይ በተመለከተው መሰረት ጉባኤው ከዲኝነት-ነክ ሥልጣኑ ዉጭ በሆነ አግባብ ሥልጣንና ተግባሩን መነሻ በማድረግ በሚያስተላልፊቸው አስተዲደራዊ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ በጥቅለ ሕገ መንግስትንና ሕግን በሚቃረን (Unconstitutionality and Illegality) አኳኋን ወስኗል የሚባል ቢሆን፤በዝርዝር የተመለከትን እንደሆነ ከሥልጣን ገደቡ ዉጭ በመውጣት(ultra virus) ወስኗል፣ ጉባኤዉ ፍቅድ ሥልጣኑን ተጠቅሞ የወሰነው በቂ ምክንያት መሰረት ሳያደርግ (Irrational or unreasonable)ነው፣የሰጠው ውሳኔ በሥልጣን ገደቡ ውስጥ ቢሆንም ውሳኔዉ የሚመለከታቸውን ሰዎች (የዳኞችን ወይም የጉባኤ ተሻሚዎችን) መብትና ጥቅም ለመጠበቅ የግድ መከተል ያለበትን የሥነ ሥርዓት ሂደት ለአብነት ሰዎቹ ስለጉዲዩ ያላቸዉን ሀሳብ ሳይሰማ (Procedural impropriety) ወስኗል፣ እንዱሁም የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ውሳኔዉ የሚመለከታቸውን ሰዎች መብትና ጥቅም የሚመለከት የሆነ እንደሆነ መብትና ጥቅማቸው ከሚገባው በላይ እንዲይጎዲ ሚዛናዊ ሆኖ (Proportionality) መወሰን ሲገባው ሚዛናዊ ያልሆነ ውሳኔ ሰጥቷል፣ ዲኝነታዊ ክለሳ ሲደረግ ከግምት ሉገቡ የሚገባቸውን ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸውን የመሰማትና ላልች የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት (due process of law) ላልች መሰል መመዘኛዎች ከግምት ሳያስገባ ወስኖ ከሆነ በውሳኔዉ መብቱ በተነካበት ሰው አቤቱታ መነሻ በዲኝነታዊ ክለሳ ታይቶ ጉድለቱ እንዱታረም ሉወሰን ይገባል።
እንዱሁም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች መሰረት ባደረገ መልኩ በዲኝነታዊ ክለሳ ታይቶ ከመወሰኑ በፉት የጉባኤው ውሳኔ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ የሚታይበት ሥነ ሥርዓት በክልለ ሕገ መንግስትም ሆነ በክልለ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ የተዘረጋ መሆን አለመሆን መርምረናል።
ጉባኤው በሚሰጠው ውሳኔ ላይም ሆነ ከውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ጋር በተያያዘ የሕጋዊነት ቅሬታ ያለው ዲኛ ወይም የጉባኤ ተሿሚ ቅሬታውን በምን አግባብ ለማን ማቅረብ እንዲለበት በፋዳራለም ሆነ በክልል ሕግጋተ መንግስታት በግልጽ የተዘረጋ ሥርዓት ካለመኖሩም በተጨማሪ በጉባኤው ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 209/2006 ላይ ስለዚህ ጉዲይ በግልጽ የተዘረጋ ሥርዓት የለም።ጉባኤዉ በማቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 7/6 መሰረት ከሚሰጠው ውሳኔ ውጭ በላልች ጉዲዮች ላይ የሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ እንደሆነ በዚሁ በጉባኤው ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 26/2 ተመልክቷል።በአዋጅ ቁጥር 209/2006 አንቀጽ 7(1/ሀ እና ሰ) ላይ እንደተመለከተው ከዲኝነት ሥራ ጋር የተያያዙ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የሥራ ሂደት መሪዎችና ሰብሳቢ ዳኞችን በጉባኤው ሰብሳቢ አቅራቢነት መርጦ የሚሰይመውና ደመወዝ እና አበላቸውን የሚወስነው ጉባኤው ነው።በዚህ መሰረት የአንድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥራ ሂደት መሪ እና ሰብሳቢ ዲኛን ደመወዝና የኃላፉነት አበል በተመለከተ ጉባኤው የሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ነው ማለት ነው። የመጨረሻ ዉሳኔ ነው የሚለው አገላለጽ ይግባኝ ልባልበት የማይችል ዉሳኔ ነው የሚል ሀሳብ የያዘ ነው።
በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡት የሥራ ሂደት መሪ በነበርኩበት ጊዜ ሲከፈለኝ የነበረው የወር ደመወዝ ብር 13,702.00 ሆኖ እያለ አመልካቾች አለአግባብ ብር 1000.00 ቀንሶብኛል በማለት ተቀነሰብኝ ያለት ገንዘብ ተመላሽ እንዱደረግላቸውና ለወደፉትም በዚያዉ መሰረት ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ለጉባኤው ቅሬታ አቅርበው ጉባኤው በሰጠው ውሳኔ አስቀድሞም የተወሰነልት ደመወዝ ሳይሆን የኃላፉነት አበል ስለሆነ የደመወዝ ማሻሻያ ሲደረግ የኃላፉነት አበል ተቀንሶ የደመወዞ መጠን ብቻ መሰረት ተደርጎ የደመወዝ ማሻሻያው መሰላቱ ተገቢ ነው ሲል የተጠሪን ቅሬታ ዉድቅ በማድረግ በሰጠዉ አስተዲደራዊ ውሳኔ መብቴ ተነክቷል በሚል ነዉ።በዚህ መልኩ ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 209/2006 አንቀጽ 26/2 ስር በተደነገገዉ መሰረት ተጠሪ ይግባኝ ሉያቀርቡ አይችለም።ይህ ድንጋጌ ከርዔሱ ጀምሮ ስለይግባኝ አቀራረብ የሚደነግግ እንጂ ዲኝነታዊ ክለሳ (judicial review) የሚመለከት ባለመሆኑ ዲኝነታዊ ክለሳን የሚከለክል አይደለም።
እንደሚታወቀዉ የይግባኝ መብት በሕግ የሚገኝ መብት(statutory right)ነው።ተጠሪ ጉባኤው ከላይ በተመለከተው መሰረት በሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማቅረብ መብት እንደማይኖራቸዉ በጉባኤው ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ እንደተደነገገ ከላይ ተመልክተናል።በልላ በኩል ጉባኤው በዚህ መልኩ የሚሰጠው ዉሳኔ ልክ ዲኝነት-ነክ ሥልጣኑን ተጠቅሞ የሰጠው ውሳኔ በክልለ ምክር ቤት ተመርምሮ ተገቢው በሚወሰንበት አኳኋን ለክልለ ምክር ቤት ቀርቦ የሚመረመር ስለመሆኑ በግልጽ ሥርዓት የተዘረጋለት አይደለም።በመሆኑም በክልልም ሆነ በፋዳራል ሕግጋተ መንግስታት አንቀጽ 9 ላይ ሕግጋተ መንግስታቱ እንደቅደም ተከተላቸው በክልለና በአገሪቱ የበላይ ሕግጋት በመሆናቸው የጉባኤው ውሳኔ ይህንን መርህ ያከበረ(ሕገ መንግስታዊ ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶች ያከበረ) መሆን ካለመሆኑ አንጻር፣ የጉባኤው ውሳኔ እና ውሳኔ የተሰጠበት ሂደት በአንቀጽ 12 ስር ስለመንግስት አሰራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የተደነገገውን መሰረት ያደረገ ከመሆን አለመሆን አኳያ፤ እንዱሁም የጉባኤው ውሳኔ በሕግጋተ መንግስታቱ አንቀጽ 37/1 ላይ የተደነገገውን የተጠሪን ፍትህ የማግኘት መብት ያከበረ ከመሆን አለመሆን ጋር እና በጥቅለ የሕገ መንግስቱ ዓላማ የሆነውን የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት መሆን ካለመሆኑ አንጻር ተገናዝቦ ጉባኤው የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ሕጋዊነት በዲኝነታዊ ክለሳ እና በሰበር አቀራርብ ሥርዓት ሉመረመር ይገባል። ምክንያቱም በክልለ ምክር ቤት በማይታይ ጉዲይ ላይ በጉባኤው የተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ በዲኝነት አካል የማይታይ ከሆነና በሕገ መንግስት የተረጋገጠ መብት የሚጥስ ውሳኔ ጸንቶ እንዱቀጥል የሚደረግ ከሆነ የሕገ መንግስት የበላይነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል ፤በሕግጋተ መንግስታቱ ስለመንግስት አሰራር ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የተደነገገው በጉባኤው አስተዲደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ተፈጻሚ ሳይሆን እንዱቀር እድል ይፈጥራል፤ በጉባኤው የሚተዲደሩ ሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ሳይረጋገጥ እንዱቀር ያደርጋል። ይህ እንዱሆን መፍቀድ ደግሞ ሕገ መንግስቱ በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ አሰራር እንዱረጋገጥ የያዘዉ ዓላማ ከግብ እንዲይደርስ ስለሚያደርግ ሉፈቀድ የሚገባ አይደለም። በዚህ አግባብ የጉባኤው አስተዲደራዊ ውሳኔ በዲኝነት ላታይ የሚገባው ነው ካልን በዲኝነታዊ ክለሳ ከመታየቱ በፉት በክልለ ሰበር ታይቶ መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ እንደሚከተለው መርምረናል።
በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17/1 ስር በተደነገገው መሰረት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር ማየት የሚችለው በአንድ ጉዲይ ላይ በተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሲኖር ነው። ይህ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በሰበር አይቶ የማረም ሥልጣን በአንድ አስተዲደራዊ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተነሳ የሕጋዊነት ጥያቄ በዲኝነት አይቶ ከመከለስ የተለየ ነው። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በጉባኤው ወይም በልላ አስተዲደራዊ አካል የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ የማየት ሥልጣን እንዲለው በአዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17 ላይ አልተደነገገም። በመሆኑም በክልለ ሰበር ችልት ከመመርመሩ በፉት በፋዳራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1 እና 80/2 እንዱሁም በክልለ በተሻሻለው ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1 እና 67(2/ሀ) መሰረት በመጀመሪያ በዲኝነታዊ ክለሳ በክልላዊ ጉዲይ ከፍተኛ እና የመጨረሻ የዲኝነትሥልጣን በተሰጠው በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉባኤው ውሳኔ ሉከለስ ይገባል። ከላይ እንደተገለጸው በዲኝነታዊ ክለሳ በዚህ አግባብ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ሳይሰጥ በጉባኤው በተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ቀጥታ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ ጉዲዩ በዲኝነታዊ ክለሳ ቢታይ ኖሮ ሉመረመሩ የሚገባቸው ከፍሬ ነገር ጉዲዮች ጋር ጭምር ሉያያዙ የሚችለ ነጥቦች እንዲይመረመሩ ያደርጋል። በተጨማሪም ከላይ አንደተመለከትነው በዲኝነታዊ ክለሳ አስተዲደራዊ ውሳኔው ተከልሶ ውሳኔው ከላይ ከጠቀስናቸው መመዘኛዎች አንጻር ጉድለት እንዲለበት ከተረጋገጠ ዲኝነታዊ ክለሳ ያደረገው ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለጉባኤው ከመመለስ ውጭ ስህተቱን አርሞ በራሱ አዱስ ውሳኔ ስለማይሰጥ ጉዲዩ አስቀድሞ በዲኝነታዊ ክለሳ አለመታየቱ እና በቀጥታ ለክልለ ሰበር ቀርቦ እንዱታይ መደረጉ (ሰበር ተገቢ የመሰለዉን አዱስ ው ሳኔ የመስጠት ሥልጣን ስላለዉ) የጉባኤው ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ ታይቶ ጉድለት ካለበትም በዲኝነታዊ ክለሳ ሥርዓት ውሳኔ አሰጣጥ መሰረት ጉባኤው እንደገና አይቶ መወሰን እንዱችል ጉዲዩ ሉመለስለት የሚችልበትን አግባብ በማጥበብ አስተዲደራዊ ሥልጣኑን የሚገድብ ይሆናል።
በልላ በኩል አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው የጠቀሱት ከዚህ ቀደም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 18/04/2006ዓ/ም (ቅጽ 15 የታተመ) ፣ ተጠሪ የጠቀሷቸው በሰ/መ/ ላይ በቀን 22/01/2005ዓ/ም እና በሰ/መ/ ላይ በቀን 23/02/2005(ቅጽ 14 ላይ እንደታተመው) የሰጠው የሕግ ትርጉም የዲኝነት-ነክ ሥልጣን ባላቸው አካላት ተወስኖ በውሳኔዎቹ ላይ በተጠቀሱት ሕጎች በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት በይግባኝ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ በመሰጠቱ ለሰበር የቀረበ ጉዲይን መሰረት ተደርጎ የተሰጡ የሕግ ትርጉሞችን የሚመለከቱ በመሆናቸውና በያዝነው ጉዲይ ጉባኤው አስተዲደራዊ ውሳኔ የሰጠው የዲኝነት-ነክ ሥልጣኑን በመጠቀም ባለመሆኑ ለተያዘው ጉዲይ ተፈጻሚነት ያላቸው አይደለም። እንዱሁም በሰ/መ/ ላይ በቀን 17/04/1998ዓ/ም (በቅጽ 3 ላይ እንደታተመው የተሰጠው ትርጉም) በዲኝነት-ነክ አካል በይግባኝ ጭምር ታይቶ ውሳኔ በተሰጠበት ጉዲይ ላይ ለመደበኛ ፍርድ ቤት አዱስ ክስ ማቅረብ አይቻልም ተብል ትርጉም የተሰጠበት በመሆኑ ከተያዘው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዲይ ላይ የተሰጠ የሕግ ትርጉም አይደለም።ስለሆነም ግራ ቀኝ እነዚህን የሰበር ሰሚ ችልት የሕግ ትርጎሞችን በመጥቀስ ያቀረቡትን ክርክር ከተያዘው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዲይ ላይ የተሰጡ ትርጉሞች ባለመሆናቸው ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት የላቸውም ብለናል።
ሲጠቃለል የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ዲኝነታዊ ክለሳ የማድረግ ሥልጣን ጭምር እንዲለዉ በክልለ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ በልዩ ሁኔታ ያልተደነገገ በመሆኑ ጉባኤው የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ 479 LWLS በዲኝነታዊ ክለሳ ሥርዓት ከመታየቱ በፉት በስረ ነገሩ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር ማየቱ በፋዳራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/2 እና በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 67(2/ሀ) ላይ በተደነገገው መንፈስና ይዘት መሰረት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልላዊ ጉዲይ ላይ በጉባኤው የተሰጠውን አስተዲደራዊ ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ የማየት ሥልጣን እንዲለው የሚያስገነዝበውን ያላገናዘበ በመሆኑ ሥነ ሥርዓታዊ ስላልሆነ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1/ሐ) መሰረት ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ብለናል።በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-104522 ላይ በቀን 30/11/2013 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በጉባኤው የተሰጠ ውሳኔ በዲኝነታዊ ክለሳ እንዱታይ ሥልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት አቤቱታ ከማቅረብ ይህ ውሳኔ አያግዲቸዉም።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸውን እንዱችለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለክልለ ሰበር ችልት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸው።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.