የጦር መሳሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ መሰረት ይህ አዋጅ ወጥቶ በሥራ ላይ ከመዋለ በፉት በፈቃድም ሆነ ያለፈቃድ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች በአዋጁ ለፈቃድ ማውጫ በተቀመጠው አንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ እንዱሁም በተለምድ የጦር መሳሪያ የሚያዝባቸዉ አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ እና ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፉት የጦር መሣሪያ የያዙ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 8(1) መሰረት እንዱያስመዘግቡ በተፈቀደዉ የሁለት ዓመት ጊዜ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና አቶ ካሳሁን ግዛቸው፣ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና 450 የአዋጁን አንቀጽ 4፣ 22(2)፤ እንዱሁም 22(3) ድንጋጌዎች በመተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ስላለመሆኑ በአፍሪካ ቀንድና በታላላቅ ሀይቆች አካባቢ ሕገ ወጥ ትናንሽና ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በናይሮቢ ከተማ የተፈረመውን የናይሮቢ ፔሮቶኮል ለማጽደቅ አዋጅ ቁጥር 429/1997፣የጦር መሣሪያዎችን፤ መለዋወጫዎቻቸውንና አካልቻቸውን እንዱሁም ፈንጂዎችን በሕገ ወጥ ማምረትንና ማዘዋወርን ለመከካከል የወጣው ፔሮቶኮልም አዋጅ ቁጥር 735/2004፣ በኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4፣ 22(2)፣ 23(2) ንዐስ አንቀጽ 3 በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 እና 2፣ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፤ እንዱሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2(2) (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ መዝገቦች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።) አቶ ኢሳያስ መኮንን
No summary available.
ሐምል 28 2015 ዓ.ም የሰ.መ.
የሰ.መ.
ዳኞች፡- ቴዎድሮስ ምሕረት አበባ እምቢአለ እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ በሰ.መ.
አመልካች፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ፡ አቶ ካሳሁን ግዛቸው የቀረበ የለም በሰ.መ.
አመልካች፡ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር - አልቀረበም ተጠሪ፡ አቶ ኢሳያስ መኮንን- ጠ አበበ መንግስቱ - ቀረቡ በሰ.መ. እና በሰ.መ. ላይ የሰበር ትርጉም የሚሻው ጭብጥ አንድ በመሆኑ ሁለቱም መዛግብት ተጣምሮ ተመርምረው ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የክርክሩ አመጣጥ በሰ.መ. ላይ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. በ29/10/14 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በ7/2/15 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል እና በሰበር መዝገብ ላይ ደግሞ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. በ12/7/14 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በ24/9/14 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል የሰበር አቤቱታ በመቅረቡ ነው።
ጉዲዩ የጦር መሳሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕግጋት እና አሰራሮች ሳይመዘገቡ ወይንም ፈቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሣሪያ የሚጠቀሙ ሰዎች ለምዝገባ በተሰጠው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በወንጀል ተጠያቂ ላሆን የሚችል መሆን/አለመሆኑን የሚመለከት ነው። ከሥር ፍርድ ቤት ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰበር መዝገብ አቶ ካሳሁን ያዛቸው ላይ የመሰረተው ክስ የጦር መሳሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(2) እና 22(3) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ በክሱ በተመለከተው ጊዜ እና ቦታ የውግ ቁጥር የላለው አውቶማቲክ ሲ.ኤ.ኤል.ኤም 8 የሆነ መሣሪያ ከ05 (አምስት) መሰል ጥይቶች ጋር ይዞ በመገኘቱ እንዱሁም በፍርድ ቤት ብርበራ ትዕዛዝ ቤቱ ሲፈተሸ አምስት ፍሬ የሽጉጥ ጥይቶችን አስቀምጦ ተገኝቷል የሚል ሲሆን፤ በሰ.መ. በሆነው መዝገብ ደግሞ በአቶ ኢሳያስ መኮንን ቸኮል ላይ የቀረበው ክስ ከላይ የተገለጹትን የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በክሱ በተጠቀሰው ቀን፤ ጊዜ እና ቦታ መኖሪያ ቤቱ ሲፈተሽ ህጋዊ ፈቃድ ካለው ማካሮቭ ሽጉጥ የውግ ቁጥሩ የሆነ ከመሰል 8 ጥይቶች እና አንድ ካርታ ጋር ፈቃድ የላላቸው ላላ 31 ፍሬ የሽጉጥ ጥይቶች እና አንድ ካርታ ጋር ይዞ የተገኘ በመሆኑ በፈጸመው ብዛት ያለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል በሚል ቀርቦባቸዋል።
በሰበር መዝገብ ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ መኮንን የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ስር የተመለከተው አንድ ዓመት የመመዝገቢያ የእፍይታ ጊዜ ከማለቁ በፉት ልከሰስ አይገባም በማለት ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ የመረመረው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በሥራ ላይ የዋለው ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን መሳሪያው በተጠሪ እጅ የተገኘው ታህሳስ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ነው። አዋጁ ምዝገባ ያልተደረገላቸው የጦር መሳሪያዎችን በተመለከተ ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የእፍይታ ጊዜ የሰጠ በመሆኑ የተሰጠው የመሸጋገሪያ ጊዜ ሳያልቅ በአዋጁ ስር ክስ መቅረብ የለበትም በማለት በወ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ 130(2)(ሐ) መሰረት ክሱን ውድቅ በማድረግ ብይን ሰጥቷል።
በሰ.መ. አቶ ካሳሁን ግዛቸውም ክሱ ደርሷቸው የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክደው ተከራክረዋል። ዐቃቤ ሕግም ክሴን ያስረደልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ ሲሆን በሰነድ ማስረጃነትም ተጠሪ በወ.መ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 27(2) እና 35 መሰረት የሰጡትን ቃል አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም ባደረገው ምርመራ፡- በክሱ ላይ በተገለፀው ጊዜ እና ቦታ ተጠሪ የተባለውን ሽጉጥ እና ጥይቶች ይዞ መገኘቱ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ ተጠሪ ሽጉጡንና ጥይቶቹን ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ መያዙን የሰጠው የዔምነት ቃል ያስረዲል። በተጠሪ እጅ የተገኙት ሽጉጥ እና ጥይቶች ፈቃድ አልወጣባቸውም። አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ፈቃድ ሳይኖራቸው መሣሪያ የያዙ ሰዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሚቋቋመው ተቆጣጣሪ ተቋም ፈቃድ መውሰድ ያለባቸው መሆኑና በተጠቀሰው ጊዜ ፈቃድ ያላገኙ ሰዎች የያዙት የጦር መሣሪያ ለተቆጣጣሪው ተቋም ማስረከብ እንዲለባቸው የሽግግር ግዜ በአዋጁ ቁጥር 23 (1), (2) እና (3) ሥር ተደንግጓል። የጊዜ ሰላዲ የተሰጠው ለመመዝገቢያ እና ፈቃድ መውሰጃ የሽግግር ወቅት በመሆኑ የእፍይታ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አዋጁ ተፈፃሚ የሚሆንበት ዔድል አይኖርም። ተጠሪ ፈቃድ የላለው የጦር መሣሪያ ይዟል ተብል ክስ የቀረበበት ሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም አዋጁ ከወጣ በአምስት ወር ግዜ ውስጥ ሆኖ የአንድ ዓመት ግዜ ሉጠናቀቅ ሰባት ወር ሲቀረው በመሆኑ የወንጀል ተጠያቅነት የለበትም። ዐቃቤ ሕግ እንደ ክስ አመሰራረቱ የተጠሪ ድርጊት ወንጀል መሆኑን ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ አላስረዲም በማለት በወ.መ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 141 መሰረት መከላከል አያስፈልገውም በሚል በብይን በነፃ አሰናብቶታል።
አመልካችም በሁለቱም መዛግብት ላይ የተሰጠውን ብይን በመቃወም ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ በይግባኝ ሰሚው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሰረዙ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አስቀድሞ በሰ.መ. ላይ የተሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚጣረስ ፤ የአዋጁ ዓላማ ለብዙሐኑ ደህንነት ሲባል ያለፈቃድ በግለሰቦች እጅ ገብተው የሚገኙ የጦር መሣሪያዎችን መዝግቦ ህጋዊ የቁጥጥር ስርዓትን መዘርጋት ሆኖ እያለ በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ ያለጠያቂ ህገ ወጥ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ ይችላል በሚል የተሰጠው ብይንና ውሳኔ የአዋጁን አላማ ስለሚቃረን በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4) (ለ) ድንጋጌ መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በሚል ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. እና በመ. ከሰጠው አስገዲጅ ውሳኔዎች አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል ተብል ተጠሪዎች በሰጡት መልስ በአዋጁ በግልጽ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳያልፍ ክስ መቅረቡ የህጋዊነት መርህን የሚጣረስ ከመሆኑም በላይ አመልካች የጠቀሳቸው አስገዲጅ የሰበር ውሳኔዎች ከተያዘው ጉዲይ ጋር የማይገናኙ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ሆኖ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የሰ.መ.ን በተመለከተ ተጠሪ በ24/6/15ዓ.ም በተጻፈ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(1) መሰረት ቀድሞ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. በሰ.መ. በተሰጠ አስገዲጅ ውሳኔ የተሰጠ የህግ ትርጉም እንዱሻሻል ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እንዱታይ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት በችልቱ ታምኖበት እንዱሁም በሰ.መ. ላይ አከራካሪው ጭብጥ በሰ.መ. ከቀረበው ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ምክንያት ሁለቱም መዝገቦች ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት ታይተው ጉዲዩ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ባለው የአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ ሕጉ ከመውጣቱ በፉት የፀና ፈቃድ ሳይኖራቸው በግለሰብ ደረጃ ሉያዝ የሚችል የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የአዋጁን አንቀጽ 4(2) እና 22(3) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነት ማስከተል አለማስከተለን በጭብጥነት በመያዝ የሥር ፍርድ ቤቶች ብይንና ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
የኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ለማውጣት ካስፈለገበት ምክንያቶች ውስጥ ከፉለ ግለሰቦች የታጠቋቸው የጦር መሣሪያዎች ህብረተሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ ተግባር የሚውለበትን ዔድል መፍጠር መሆኑን ፤በሥራ ላይ ባለ ሕጎች ያልተሸፈኑ ጉዲዮችን በዝርዝር ሕግ በመደንገግ ወጥነት ያለው ሥርዓት መፍጠር መሆኑን፤ ሀገራችን ያፀደቀቻቸው ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማስፈፀምና ዓለማቀፍ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓትን መዘርጋት በማስፈለጉ እንደሆነ ከአዋጁ መቅድም(Preamble) መረዲት ይቻላል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በታላላቅ ሀይቆች አካባቢ ሕገ ወጥ ትናንሽና ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በናይሮቢ ከተማ ሚያዝያ 13 ቀን 1996 የተፈረመውን የናይሮቢ ፔሮቶኮል ለማጽደቅ አዋጅ ቁጥር 429/1997 ወጥቶ በሥራ ላይ ውሎል። የጦር መሣሪያዎችን፤ መለዋወጫዎቻቸውንና አካልቻቸውን እንዱሁም ፈንጂዎችን በሕገ ወጥ ማምረትንና ማዘዋወርን ለመከካከል የወጣው ፔሮቶኮልም አዋጅ ቁጥር 735/2004 ሆኖ ፀድቋል።፡ ማንኛውም ሰው የፀና ፈቃድ ሳይኖረው በኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4 ሥር የተዘረዘሩትን ተግባራት መፈፀም ክልክል ነው። በአዋጁ አንቀጽ 22(2) ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም ሰው በአዋጁ የተመለከተውን ክልከላ እና ግዳታ በመተላለፍ የፀና ፈቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ ፤ የጦር ሜዲ መነጽር ፤ በጦር መሳሪያ ላይ ሉገጠም የሚችል ማንኛውም አይነት መነጽር ወይም የጦር መሳሪያ ሲተኮስ ድምጽ ለማስወገድ የሚያገለግል መሳሪያ ወደ ሀገር ያስገባ ፤ ከሀገር ያስወጣ ፤ያስቀመጠ ፤ የተገለገለ ፤ ያሳየ ፤ የደለለ ፤
የሸጠ ፤ የገዛ ፤ ያጓጓዘ፤ ያመረተ ፤ ያሰለጠነ ፤ የጠገነ ወይም ያስወገደ ፤ በማናቸውም መንገድ ያስተላለፈ ወይም የያዘ እንደሆነ ከአንድ አመት እስከ ሶስት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል በማለት ደንግጓል። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 3 የተፈጸመው ወንጀል ብዛት ባለው የጦር መሳሪያ ሲሆን ቅጣቱ ከስምንት አመት እስከ ሀያ አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከመቶ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል በማለት ደንግጓል። በልላ በኩል የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ህጎችና አሰራሮች ሳይመዘገቡ ወይም ፈቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ሰዎች በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የግዜ ሰላዲ መሰረት በአካል ቀርበው ፈቃድ መጠየቅ እና በዚህ አዋጅ መሰረት የተመለከቱ መስፈርቶችን አሟልተው በተቆጣጣሪ ተቋሙ ፈቃድ መውሰድ አለባቸው በማለት ደንግጓል። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 3 በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 እና 2 መሰረት ፈቃድ ያላገኙ ሰዎች የያዙትን የጦር መሳሪያ ለተቆጣጣሪው ተቋም ማስረከብ አለባቸው በማለት ደንግጓል። አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዳሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደር፤ አጠቃቀም እና ቁጥጥር መመሪያ ከሀምላ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ መዋለን የመመሪያው ቁጥር 58 የሚያመለክት ሲሆን የጦር መሣሪያ ፈቃድ የሚሰጠው በአዋጁ አንቀጽ 7 እና በመመሪያው አንቀጽ 10 ሥር የተመለከቱ መስፈርቶችን አሟልቶ ለተገኘ ሰው ነው። ፈቃድ ሉሰጠው የሚገባው የጦር መሣሪያ ምንጩ መሣሪያ እንዱያመርት ወይንም እንዱሸጥ ፈቃድ ከተሰጠው ተቋም በግዥ የተገኘ ፤ ከመንግስት ግምጃ ቤት ፤ በዓለም ዓቀፍ ድርጅት ወይንም በውጪ ሀገር ተወካይ ወደ ሐገር ውስጥ የገባ ፤ በውርስ ፤ በሽልማት ወይንም በስጦታ የተገኘ ፤
አዋጁ ከመጽደቁ በፉት ተመዝግቦም ይሁን ሳይመዘገብ በሰው እጅ ተይዞ የነበረ፤
በተለያዩ የፀጥታ አካላት እጅ የሚገኝ እና በሕገ - ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ወይም ተደብቆ የተገኘ ላሆን እንደሚችል አንቀጽ 14 ያመለክታል። ለግለሰብ የሚፈቀደው የጦር መሣሪያ ዓይነት እና ብዛት በመመሪያው አንቀጽ 19 ሥር ተዘርዝሯል።
የጦር መሣሪያ ለመታጠቅ ብቁ የሚያደርጉ ዝርዝር መስፈርቶችም በመመሪያው አንቀጽ 15 ሥር ተመላክቷል። በቀደሙት ሕጎች ላይ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 በሕግ አውጪው ወጥቶ ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ ይገኛል። የአዋጁ ዓላማ በግለሰብ ደረጃ ሉያዝ የሚችልን የጦር መሣሪያ በፈቃድ በመያዝ የሕብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ተግባር እንዱውል ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሣሪያ የያዙ ፈቃድ ማግኘት ለሚችለ ሰዎች ፈቃድ መስጠት ፤ ያለፈቃድ በግለሰቦች እጅ ተይዞ ከቆዩት የጦር መሣሪዎች በፈቃድ ሉያዝ የማይችለውን የጦር መሣሪያ በመሰብሰብ የነበረውን የሕግ ክፍተት በመሙላት ወጥነት ያለው የጦር መሣሪያ አያያዝ ሥርዓትን ለመዘርጋት ነው። ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የጦር መሣሪያ ምንጩ በሕገ - ወጥ መንገድ የሚዘዋወር እና በሕገ - ወጥ መንገድ ተቀምጦ የተገኘ ላሆን እንደሚችል ከአዋጁ እና መመሪያው ድንጋጌዎች ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 ወጥቶ በሥራ ላይ የዋለው ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም ከላይ የተመለከቱ ተግባራት ፈጽሞ የሕጉን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ግዜ አስፈላጊ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 4 እና 22(2) ሥር የተመለከተው ክልከላ እና የወንጀል ተጠያቂነት አዋጁ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕጎች እና አሰራሮች ሳይመዘገብ ወይንም ፈቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሣሪያ የያዙ ወይንም የሚጠቀሙ ሰዎች ተቆጣጣሪው አካል በሚያወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት በአዋጁ እና መመሪያው የተመለከቱ መስፈርቶችን አሟልተው ፈቃድ እንዱወስደ የአዋጁ አንቀጽ 23(1) ደንግጓል። ስለዚህ አዋጁ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም በሥራ ላይ እንደዋለ በማግስቱ የፀና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሣሪያ የያዙትን ሰዎች በወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ በፈቃድ የጦር መሣሪያ ሉይዙ ለሚችለ ሰዎች ፈቃድ ለመስጠት እና ፈቃድ ከማይሰጣቸው ሰዎች እጅ ደግሞ መሣሪያዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችል ግዜን ወስኖ የጦር መሳሪያ አስተዲደር እና ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው። አዋጁ በሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስቀድሞ ያለፈቃድ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎችን የአዋጁን አንቀጽ 4 እና 22(2) ድንጋጌዎች በመተላለፍ በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች በአዋጁ በተቀመጠው አግባብ ፈቃድ እንዲይወስደ እንቅፊት ስለሚሆን በሕጉ የተመለከተውን የምዝገባ ሥርዓት ያሰናክላል።
ከዚህ ቀደም የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ዐቃቤ ሕግ የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(2)ን ጠቅሶ የመሰረተው የወንጀል ክስ በክልለ በየደረጃው ጉዲዩን ባዩት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በመጨረሻ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ በተሰጠ ውሳኔ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ፈቃድ የላለውን የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎች መሳሪያውን አስመዝግበው ፈቃድ ለመውሰድ የሚችለበትን የጊዜ ሰላዲ ወስኖ ወደስራ ያልገባ በመሆኑ ተጠሪ በዚህ ጊዜ ውስጥ መሳሪያውን ይዞ መገኘቱ ወንጀል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ተከሳሽን በነጻ በማሰናበቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታ አቅርቦ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ላይ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የአዋጁን አንቀጽ 23(2)ን በመተርጎም ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ ላይ ‛…የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ከአዋጁ መሰረታዊ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የዚህ ድንጋጌ ዋናው ዓላማ ፈቃድ የላላቸው ሰዎች ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሳሪያውን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሉያጋጥማቸው ከሚችለው የህጋዊነት ጥያቄ ለመጠበቅ እንጂ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያለማንም ጠያቂ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ አይደለም። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪው የጦር መሳሪያን አስመልክቶ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ለመሆኑ አልያም ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ እያለ የተያዘ ስለመሆኑ እንዱሁም በመሳሪያው ላይ ፈቃድ ያላወጣው ተቆጣጣሪ ተቋሙ ወደ ስራ ባለመግባቱ ነው በሚል ያቀረበው ክርክርም ሆነ ከዚህ አንጻር የተረጋገጠ ነገር በላለበት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የአዋጁን ድንጋጌ ባልተገባ መንገድ ተርጉሞ ተጠሪን ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።“ በማለት የክልለን ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ በመሻር የስር የወረዲ እና የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
በተመሳሳይ መልኩ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ላይ ሕዲር 27 ቀን 2014 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ‛…የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ ከአዋጁ መሰረታዊ አላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የድንጋጌ ዋና አላማ ፈቃድ የላላቸው ሰዎች ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሳሪያውን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሉያጋጥማቸው ከሚችለው የህጋዊነት ጥያቄ ለመጠበቅ እንጂ እስከ አንድ አመት ድረስ ያለማንም ጠያቂ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ አይደለም።“ በማለት የክልለን ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ በመሻር የስር የወረዲው እና የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
በተጠቀሱት መዛግብት ላይ በሰበር ችልቱ የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2)ን አተገባበር በተመለከተ የተሰጠው ትርጉም ከአዋጁ ዓላማ እና ከሚከተለት የወንጀል ሕግ መርሆዎች አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል።
የወንጀል ሕግ ዓላማ የሕዝቦችን ፤ የነዋሪዎችን ሰላም ፤ ደህንነት ፤ ሥርዓት ፤ መብት እና ጥቅም ማረጋገጥ ሆኖ ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀልች እና ቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቅያ በመስጠት ፤ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ግዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ መሆኑን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1 ያመለክታል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 22(2) ፤ እንዱሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2(2) ስር ፍርድ ቤት አንድ ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይንም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ በሕግ ካልተደነገገ በስተቀር ሉያስቀጣ እንደማይችል ተደንግጓል። ይህም የሕጋዊነት መርህ(Principle of Legality)አንደኛው መገለጫ እና የወንጀል ሕግ መሰረታዊ መርህ በመሆኑ በጥብቅ ተግባራዊ መደረግ የሚገባው ነው። በዚህ መሰረት ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ መመስረት የሚችለውም ሆነ ፍርድ ቤት የወንጀል ክሱን ሰምቶ በተከሳሹ ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ የሚችለው ሕገ ወጥነቱና እና አስቀጭነቱ (ወንጀልነቱ) በሕግ የተደነገገውን ድርጊት ወይም አል ድርጊት በተመለከተ ብቻ ነው።
በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23/2 መሰረት አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁሙ ናቸው ተብል በሕጉ የተመለከተው ሕጋዊ ፤ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው። ይህ ድንጋጌ በውስጡ ያለ ሕግ ወንጀልም ሆነ ቅጣት አይኖርም የሚለ መርሆች የያዘ ነው።
የወንጀል ድርጊትን በማመሳሰል (by analogy) መፍጠርም አይቻልም። በልላ ሕግ በተለየ መልኩ ካልተደነገገ በቀር የወንጀል ሕጉ መርሆች በላልች የወንጀል ድርጊት እና ቅጣት በሚደነግጉ ሕጎች ላይ ተፈፃሚነት ያላቸው መሆኑን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 3 ያስረዲል። የወንጀል ሕግ የሰውን ማህበራዊ ኑሮ ደረጃን ፣ የዘርን ፣ የብሓርን ፣ የብሓረሰብን ፣ የቀለምን፣ የጾታን ፣ የቋንቋን ፣ሃይማኖትን ፣የፕለቲካን ወይም የላላ አስተሳሳብን ፣ የሃብትን ፣ የትውልድን ወይም ላላ አቋምን ልዩነት ሳያደርግ በእኩል ተፈፃሚ እንደሚሆን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 4(1) ይደነግጋል።
የኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ስር አዋጁ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ሳይመዘገቡ ወይም ፍቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ሰዎች በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት በአካል ቀርበው ፈቃድ መጠየቅ እና መስፈርቱን በማሟላት ፈቃድ መውሰድ እንዲለባቸው ሲደነገግ አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ ለሚኖረው ሕጉ ከመጽናቱ በፉት ያለፈቃድ ወይንም በፈቃድ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች አዋጁ ከፀና አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በወንጀል ተጠያቂ ሳይሆኑ ወደሕጋዊ ሥርዓት ለማስገባት ሕግ አውጪው በግልጽ አቋሙን መግለጹን የሚያሳይ ነው። በዚህ መልኩ ሕጉ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አስቀድሞ ያለፈቃድ ለተያዘ የጦር መሣሪያ የወንጀል ተጠያቂነት እንዲይኖር ደንግጎ ሳለ የአንድ አመት ጊዜ ከማለቁ በፉት መሳሪያውን ለማስመዝገብ ሂደት ያልጀመሩ ሰዎች የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል በሚል ከላይ በተጠቀሱት ሁለቱም መዛግብት ላይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ከሕገ መንግስት አንቀጽ 22(2) ፣ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1 ፣አንቀጽ 2(2) ፣ (3) ፣ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 23(1) እና (2) አንፃር እንዱሁም ሕግ አውጪው በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 በተመለከተው አግባብ በሕጋዊ መንገድ መሣሪያ ለመታጠቅ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብ እና መመሪያ በማውጣት ወጥነት ባለው መልኩ በሥራ ላይ ለማዋል የተቀመጠው የአንድ ዓመት ግዜ ሳይጠናቀቅ አዋጁ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ሳይመዘገቡ ወይም ፍቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ሰዎች በአንድ ዓመቱ ጊዜ ውስጥ መቼ እንደሚያስመዘግቡ ማወቅና መለየት አይቻልም። ይህንን የሚያውቀው መሳሪያውን ለማስመዝገብ የወሰነ ሰው ነው። በዚህ ረገድ ሕጉ አስመዝጋቢው ላይ የጣለው ግዳታ የላለ ከመሆኑም በላይ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ መቼ ማስመዝገብ እንዲለበት የሚወስነው መሳሪያውን ይዞ የሚገኘው ሰው ብቻ ነው። በዚህ መሰረት በተሰጠው አንድ ዓመት ጊዜ ባለት የመጀመሪያው ቀናት ለማስመዝገብ ሂደቱን የጀመረም ሆነ በዓመቱ መጨረሻ ወር ባለት ቀናት መዝጋቢው አካል ያወጣውን የጊዜ ሰላዲ ተከትል መሳሪያውን ለማስመዝገብ ሂደት ውስጥ የገባ ሰው ወይም አንድ አመት ጊዜ ሳያልፍ መሳሪያ ይዞ የተገኘ ሰው በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 በሕጋዊ መንገድ በፈቃድ ብቻ የጦር መሣሪያን ለመያዝ የተዘረጋውን ሕጋዊ ሥርዓት ጥሷል በሚል በአዋጁ አንቀጽ 23(2) መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት ሉኖርበት አይገባም።
የሕጋዊነት መርህ በውስጡ ከያዛቸው ሐሳቦች አንደ ሰዎችን አስቀድሞ ማስጠንቀቅን ሲሆን በዚህ ሚዛን የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ሲመዘን የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ዜጎች ከአዋጁ በፉት በእጃቸው የያዙትን መሳሪያ እንዱያስመዘግቡ ማሳወቅና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የማስመዝገብ ግዳታን መጣል ነው። ይህ ድንጋጌ ባይኖር ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ መያዝ ወይም መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነት ሉያስከትል ይችል የነበረ ሲሆን እንደ ግብ የተያዘው በዚህ መልክ የተያዘ የጦር መሳሪያ በሽግግር ጊዜው ውስጥ ወደ ሕጋዊ ስርዓት በማስገባት በሕጉ የታሰበውን ዓላማ ማሳካት ነው። ስለዚህ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልተመዘገበ መሳሪያ መያዝ በራሱ ወንጀልን የሚያቋቁም ሳይሆን በሚወጣው የጊዜ ሰላዲ የማስመዝገብ ግዳታን የሚጥል ነው። በተያዙት ሁለቱም ጉዲዩች የክሱ የሕግ መሰረት በሆኑት የአዋጁ አንቀጽ 4(2) እና 22(2) በግልጽ እንደተመለከተው የወንጀለ መቋቋም የጸና ፈቃድ አለመኖርን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በዚሁ አዋጅ ከአዋጁ መጽናት በፉት የተያዙ ነገር ግን ያልተመዘገቡትን መሳሪያዎች ለማስመዝገብ እና ፈቃድ ለማግኘት እንዱቻል የአንድ ዓመት የሽግግር ጊዜ ተሰጥቷል። ስለዚህ የጸና ፈቃድ አለመኖርን ታሳቢ የሚያደርገው አዋጅ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ፈቃድ ላሰጥ የሚችልበትን ሁኔታ ስላስቀመጠ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ወንጀለ ሉቋቋም የሚችልበትን ሁኔታ አስቀርቷል። በአንድ አመት ውስጥ በነባሩ ሕግ ያልተመዘገበ መሳሪያ እንዱያስመዘግብ በሕግ ጊዜ የተሰጠው ሰው በዚህ ጊዜ ውስጥ ሕግ ተላልፍ የጦር መሳሪያ ይዘዋል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ላሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም።
ከላይ በተጠቀሱት የሰበር መዛግብት ላይ በተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ መሆን የሚቻለው በምዝገባ ሂደት ውስጥ በመግባት በመሆኑ በአንድ በኩል የአንድ አመት ጊዜ ለመጠናቀቅ ገና የስድስት ወር ጊዜ ቀርቶት እያለ የምዝገባ ሂደት ያልጀመረ መሳሪያ የያዘ ሰው መሳሪያ መያዙ ከታወቀበት በወንጀል እንዱጠየቅ የሚያደርግ በልላ በኩል መሳሪያ መያዙ ሳይታወቅበት የአንድ አመት ጊዜ ሉጠናቀቅ ጥቂት ግዜ ቀርቶት እያለ መዝጋቢው አካል ባወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት ወደ ምዝገባ ሂደት የገባ ሰው በወንጀል ተጠያቂ እንዲይሆን የሚያደርግ ይሆናል። ይህም የኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በዜጎች መካከል በእኩልነት ተፈጻሚ እንዲይሆን የሚያደርግ አለታዊ ውጤት የሚያስከትል ስለሚሆን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 3 እና 4 ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ ነው።
ከዚህም በላይ በተጠቀሰው መዝገብ የተሰጠው ትርጉም መሳሪያ ለማስመዝገብ የሚቀርቡ ሰዎች ጭምር በወንጀል ተጠያቂ የማድረግ ውጤት ያለውና አዋጁ በመግቢያው ያሰባቸውን ግቦች የሚያከሽፍ ይሆናል። አዋጁ የጊዜ ገደብ ያስቀመጠው ከአዋጁ መውጣት በፉት በነበረው የምዝገባ ስርዓት የማይታወቁ የጦር መሳሪያዎችን ወደሕጋዊ ስርዓት ለማስገባት በመሆኑ ለዚህ ዓላማ በሚወጣው መመሪያ መሰረት በአንድ ዓመት ውስጥ በቀድሞ ሕግ ያልተሸፈኑትን መሳሪያዎች ወደ ሕጋዊ ስርዓት ለማስገባት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምዝገባውን ለማካሄድ እንዱቻል ሰዎች ከተጠያቂነት ነጻ ሆነው ማስመዝገብ እንዱችለ ስርዓት ለመፍጠር የታሰበ ነው። ወንጀል እንዱከላከልና ተፈጽሞም ሲገኝ እንዱመረምር ስልጣን የተሰጠው አካል ከላይ በተሰጠው አስገዲጅ ትርጉም መሰረት ከአዋጁ በፉት የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎችን ሕጋዊ አድርጎ ሉመዘግብ የሚችልበት መንገድ አይኖርም። ይልቅም ለምዝገባ ዓላማ የሚቀርቡ ሰዎችን በሙለ የወንጀል ተጠያቂ እንዱሆን ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህ ደግሞ በሕግ አውጪው ያልታሰበ ከመሆኑም በላይ አዋጁንም ሆነ አፈጻጸሙን ውድቅ የሚያደርግ ነው። የተጠቀሰው ድንጋጌ አሻሚ ቢሆን እንኳ መተርጎም ያለበት የሕጉን መንፈስ ጠብቆ በሕግ አውጪው የታሰበውን ግብ ለማሳካት መሆን እንዲለበት ወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2(4) ይደነግጋል። ስለዚህ የሕግ አውጪውን ሐሳብ ማሳካት የሚቻለው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ሰዎች ከተጠያቂነት ፍርሀት ውጪ በመሆን ስልጣን የተሰጠው አካል ዘንድ ቀርበው ቀደም ሲል በነበረው ሕግ ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ ማስመዝገብ ሲችለ ብቻ ነው። ከዚህ በተቃራኒ ያለው አተረጓጎም ከላይ የቀረቡት ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው አዋጁን እንዲይፈጸም የሚያደርግ በመሆኑና ሕግ መተርጎም ያለበት ሕግ አውጪው ያሰበውን ዓላማ ለማሳካትና የሕጉን መንፈስ ተከትል በመሆኑ ቀደም ሲል የተሰጠው ውሳኔ ይህን መስፈርት የሚያሟላ አይደለም።
በተያዙት ጉዲዮች የተከሰሱ ዓይነት ሰዎችን ለመለየት የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ‹‹ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ሳይመዘገቡ ወይም ፈቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ሰዎች…›› የሚል አገላለጽ ይጠቀማል። መልስ ሰጭዎች በዚህ አገላለጽ ስር የሚወድቁ መሆኑ አላከራከረም። በነዚህ ሰዎች ላይ የተጣለው ግዳታ ተቆጣጣሪው አካል በሚያወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት ቀርበው በእጃቸው የሚገኝን የጦር መሳሪያ ማስመዝገብና መስፈርቱን ካሟለ ፈቃድ ማውጣት ነው። ከዚህ አልፍ በሽግግር ጊዜው ውስጥ በሚታዩት መዝገቦች በተለዩት ፍሬ ነገሮች መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርበት ሁኔታ አልተመለከተም። ግለሰቦች በአዋጁ መሰረት ለመመዝገብ እና ፈቃድ ለማግኘት ጠይቀው ካልተፈቀደላቸው ውጤቱ የሚሆነው የጦር መሳሪያውን ማስረከብ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 23(3) ተደንግጓል። ስለዚህ በዚህ አገላለጽ የሚሸፈኑ ሰዎች በሙለ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በእጃቸው የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ማስመዝገብ፣ ፈቃድ መውሰድ ወይም ይህ ካልተሳካ የጦር መሳሪያውን የማስረከብ ግደታን ከመወጣት ባለፈ የወንጀል ተጠያቂነት ሉጣልባቸው የሚችልበት ሁኔታ በሕጉ አልተመለከተም።
አንድ ሕግ የሕጉን ይዘት ከመወሰን ባለፈ የጊዜ ተፈጻሚነት ላይ በመበየን የሕጉን ውጤት ወዱያው፣ በሂደት ወይም በሁኔታዎች መሟላት ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ በግልጽ ያስቀምጣል። የአንድ ሕግ መውጣት ከሕጉ በፉት የተጀመሩ ወይም በሂደት ላይ ያለ ጉዲዮችን በተመለከተ ያለውን ተፈጻሚነት የሚገዙ ድንጋጌዎችን በማካተት የሽግግሩ ሂደትን የተሳለጠ ማድረግ የተለመደ ነው። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ በቀድሞውና በአዱሱ ሕግ መካከል በድልድይነት የሚያገለግል ነው። ለተከሳሽ የሚጠቅም ካልሆነ በስተቀር የወንጀል ሕግ ተፈጻሚነት የወደፉት (prospective) በመሆኑ ጥያቄው ላሆን የሚችለው ሽግግሩ በቀድሞ ሕግ የነበረውን ሁኔታ በአዱሱ ሕግ እንዳት እንደሚስተናገድ ማሳወቅ ነው። ስለዚህ የሽግግር ድንጋጌ ቀደም ሲል ያለት ሁኔታዎች ወይም ድርጊቶች በአዱሱ ሕግ እንዳት እንደሚስተናገደ በግልጽ ለማመልከት የሚያገለግል ነው። አዋጁ ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ የዋለ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረው ሕግን ስለሻረው ከዚህ በኋላ የሚቀርቡ ክሶች ይህን አዋጅ መሰረት አድርገው ነው። ቀደም ሲል በነበረው ሕግ መሰረት የተከናወኑ ተግባራትም የሚበየኑት በዚሁ አዋጅ ነው። ከአዋጁ ግልጽ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው አዋጁ ከመውጣቱ በፉት የጦር መሳሪያ የያዙና ፈቃድ የላላቸው ወይም ያላስመዘገቡ ሰዎች ላይ አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆነው በሕግ በተመለከተው አግባብ የአንድ ዓመት ጊዜ ገደቡ ሲያበቃ እንደሆነ ነው።
በአዋጁ አንቀጽ 23 የተካተተው የሽግግር ጊዜ ድንጋጌ ዓላማ ደግሞ የአንድ ሕግ ተፈጻሚነትን ከመጀመሩ በፉት የሚኖረውን ሂደት መግዛት እና ተፈጻሚነትን ማሻሻል ሲሆን የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ ወይም ሁኔታው ሲሟላ ቀሪ የሚሆን ነው። ውጤቱም በሽግግር ድንጋጌ በተመለከተው ሁኔታ ጉዲዮች ላይ ሕጉ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፉት ያለው ሂደት የሚጀመርበት ነው። ይህም ከላይ በዝርዝር ከቀረበው የአዋጁ ዓላማ እንዱሁም ሕግ ወዱያውኑ ተፈጻሚ ሲደረግ ሉያስከትል የሚችለው ችግር ከመቅረፍ አንጻር ከታየ ሕግ አውጪው የሽግግር ጊዜውን የሕጉን ተፈጻሚነት በማዘግየት ለሕጉ ዓላማ መሳካት በጥንቃቄ የወሰነ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የአዋጁ አፈጻጸም በዚህ የጊዜ ገደብና በተጠቀሱት ሁኔታዎች በእንጥልጥል እንዱቆይ ተደርጓል። በዚህም የሽግግር ድንጋጌ ምክንያት ወንጀለን ለማቋቋም ከሚያስፈልጉ ሁኔታዎች ውስጥ የሕግ መስፈርት ስለማይሟላ የወንጀል ተጠያቂነትን መፍጠር አይቻልም። ድርጊቱ በልላ ሁኔታ ጥፊት ቢሆንም በሽግግር ጊዜ ውስጥ የወንጀል ተጠያቂነት የላቀውንና ሕግ አውጪው ያሰበውን አጠቃላይ ዓላማ ማሳካት እንዱቻል በጊዜያዊነት ቀሪ ተደርጓል።
የሕጋዊነትም ሆነ የእኩልነት መርሁ ተፈጻሚነት ከአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ጋር ተገናዝቦ የሚታይ በመሆኑ አዋጁ ስራ ላይ ከመዋለ በፉት በእጁ የጦር መሳሪያ የያዘ ሰውን የሚመለከት ነው፤ አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ነጻ የጦር መሣሪያ ዝውውር የመፍቀድ ዓላማ የለውም፤
ዓላማው አስቀድሞ በእጃቸው መሣሪያ የያዙ ሰዎች በሕግ አግባብ ማስተዲደር እና ከሕግ ውጭ የጦር መሣሪያ የያዙ ሆነ የሚያዘዋውሩ ሰዎችን በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ ነው። በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 22/2 እና 22/3 መሰረት የወንጀል ክስ ሲያቀርብ የጦር መሣሪያው ተከሳሽ የሆነው ወገን ይዞ የተገኘው በአዋጁ አንቀጽ 23/2 በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ከሆነ መሳሪያው አዋጁ ከጸና በኋላ በተከሳሹ የተያዘ ስለመሆኑ ተጨማሪ የማስረዲት ግዳታ ይኖርበታል። በተጨማሪም የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) በሚተገበርበት ግዜ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 481 ስለጦር መሳሪያ መነገድ ወንጀል ጸንቶ ያለና ተፈፃሚነት ያለው ህግ ከመሆኑ አኳያ የመሸጋገሪያው ግዜ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚፈቅድ ሆኖ መተርጎም ተገቢነት የላለው በመሆኑ አስገዲጅ የሕግ ትርጉሙ ሉለወጥ የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም በአዋጁ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ መሰረት አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ወጥቶ በሥራ ላይ ከመዋለ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም በፉት በፈቃድም ሆነ ያለፈቃድ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች በአዋጁ ለፈቃድ ማውጫ በተቀመጠው አንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ ፤እንዱሁም በተለምድ የጦር መሳሪያ የሚያዝባቸዉ አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ እና ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፉት የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች ሲሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 8(1) መሰረት እንዱያስመዘግቡ በተፈቀደዉ የሁለት ዓመት ጊዜ ዉስጥ የአዋጁን አንቀጽ 4 ፣ 22(2) ፤ እንዱሁም 22(3) ድንጋጌዎች በመተላለፍ በወንጀል ተጠያቂ ሉሆኑ አይገባም።
በተያዘው ጉዲይ በሁለቱም የሰበር መዛግብት ተጠሪዎች የኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(2) እና 22(3) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ተከሰው በሰበር መዝገብ ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ መኮንን የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ስር የተመለከተው አንድ ዓመት የመመዝገቢያ የእፍይታ ግዜ ከማለቁ በፉት ልከሰስ አይገባም በማለት ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ አመልካች በተጠሪው ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ መሆኑን ፤ እንዱሁም የሰበር መዝገብ ተጠሪ የሆኑት አቶ ካሳሁን ግዛቸው ፈቃድ የላለው የጦር መሣሪያ ይዟል ተብል ክስ የቀረበባቸው ሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም አዋጁ ከወጣ በአምስት ወር ግዜ ውስጥ ሆኖ የአንድ ዓመት ግዜው ሉጠናቀቅ ሰባት ወር ስለሚቀር የወንጀል ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል የተሰጠው ብይንና ውሳኔ ሉነቀፍ የሚችል ባለመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
በ7/2/2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ.መ.ህ.ሥ.ሥ.ቁ 195(2) (ሀ) መሰረት ጸንተዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ ‛…የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ከአዋጁ መሰረታዊ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የዚህ ድንጋጌ ዋናው ዓላማ ፈቃድ የላላቸው ሰዎች ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሳሪያውን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሉያጋጥማቸው ከሚችለው የህጋዊነት ጥያቄ ለመጠበቅ እንጂ እስከ አንድ አመት ድረስ ያለማንም ጠያቂ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ አይደለም።“ በማለት ለጦር መሳሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ የሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጧል።
የጦር መሳሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አዋጁ ከጸናበት ከ30/4/12 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አንድ አመት ይኽውም እስከ 30/4/13 ዓ.ም ባለው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አዋጁ ከመጽናቱ በፉት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ያልተመዘገበ ወይም ፈቃድ ያልተሰጠው በሰው ሉያዝ የሚችል የጦር መሣሪያን የያዘ ወይም የተጠቀመ ሰው የአዋጁን አንቀጽ 4(2) እና 22(3) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነት የለበትም በማለት ለአዋጁ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.