ከይዞታ ላይ አላግባብ ተቀንሶ የተሰጠ ካርታ ይምከንልኝ የዲኝነት አቤቱታን ጨምሮ የአስተዲደር ስነ ስርዓት አዋጅ ከወጣ በኋላ በአስተዲዲር መስሪያ ቤቶች በዔለት ዔለት ስራቸዉ መሰረት የሚሰጡ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው አካል በአስተዲደር ስነ ስርዓት አዋጅ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ያለትን ሂደቶች ተከትል ሳይጨርስ (exhaustion of available remedies) በአስተዲደራዊ ተቋሞቹ የቅሬታ ማስተናገጃ ቅሬታ ሰሚ አካል ጋር ቀርቦ ተቋሙ የመጨረሻ ዉሳኔውን ባልሰጠበት ሂደት ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በቀጥታ ክስ ለማየት ስልጣን ያላቸው ስላለመሆኑ የፍ/ስ/ሰ/ህግ ቁጥር 9(2)፣ እና የአስተዲደር ስነ ስርዓት አዋጅ 1183/2013 አንቀጽ 2(3)፣ 43 እና 44
No summary available.
መ/ ህዲር 30 ቀን 2015 ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ላሉሴ ደሳለኝ ደጀኔ አያንሳ ሀብታሙ እርቅይሁን እስቲበል እንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ሀና ሰለሞን ዘነበ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- 1.ወ/ሮ አስናቀች ወልዳ ገ/ማሪያም - አልቀረቡም 2.የካ/ክ/ከ/መ/ል/ማ/ጽ/ቤት - ዐቃቤ ህግ ወንድሽ አለሙ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶታል።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ በ07/12/2013 ዓም የሰጠዉ ፍርድ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ በ22/02/2014 ዓም በትዕዛዝ ያፀናዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለ አቀረቡ ነዉ።
የጉዲዩ መነሻ የሆነዉ አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራክረዋል።ለክርክሩ መሰረት የሆነዉ በአመልካች በኩል በ20/08/2013 ዓ/ም በተጻፈ ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ ሲሆን ይዘቱም፡-በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 06 የቤት ቁጥር 1168 የቦታዉ ስፊት 692 የሆነ ቦታ ከሟች እናታቸዉ በስጦታ ያገኙ መሆኑን 1ኛ ተጠሪ የዉርስ ይጣራ ጥያቄ አቅርበዉ ዉደቅ ሆኖባቸዉ ሳለ 2ኛ ተጠሪ በህገ ወጥ መንገድ 692 ካ/ሜትር ይዞታዉን በእጃቸዉ አድርገዉ ሲገለገለበት የነበረዉ ይዞታ ከአመልካች ይዞታ ላይ ተቀንሶ ለ1ኛ ተጠሪ ካርታ መስጠቱን ካርታ የወጣላቸዉ በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ በቀን 25/05/2004 በካርታ ቁጥር የካ/172834/04 ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ የአመልካችን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ ካርታዉ እንዱመክን ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተጠሪ በ05/06/2013 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት መልስ በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 06 የቤት ቁጥር 1169 ከ1988 የአየር ካርታ እና ከ1991 ከተሰጠዉ ካድስተር ቢል መነሻነት ከሟች አባታቸዉ ጋር ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ በመያዝ ሲገለገለበት ቆይተዉ ወንድማቸዉም በ1992 ሲሞት የሟች አባታቸዉና የሟች ወንድማቸዉ ወራሽ በመሆን የያዙት ይዞታ መሆኑን፤ በይርጋ ይታገዲል የተባለዉ የቤት ቁጥር 1168ን በተመለከተ እንጂ የቤት ቁጥር 1169 አለመሆኑን፤ለአመልካች በኑዛዜ የተላለፈላቸዉ ይዞታ ስፊቱ 505 ካ/ሜትር ብቻ ሆኖ ሳለ ተወስድብኛል በሚል ያቀረቡት ክስ በማሰረጃም የተደገፈ አይደለም፤ሰለሆነም ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ የሚመክንበት ምክንያት የለም በሚል ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ በ26/06/2013 ዓም በተጻፈ ያቀረቡት መልስ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ በመመሪያ ቁጥር 17/2006 መሰረት በስአይኤስ እና በጂአይኤስ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ ከወረዲዉ አስተዲደርም በማረጋገጥ ቅሬታም ካለ ማስታወቅያ በመለጠፍ ቅሬታ አለኝ የሚል ወገን ባለመቅረቡ በዚህ አግባብ የተሰጠ ካርታ ነዉ፤በቤት ቁጥር 1169 በሟች አቶ ወልደ ገ/ማርያም መሆኑን አረጋግጠን በህጉ መሰረት የሰጠነዉ ካርታ ነዉ፤የአመልካች ይዞታ የተነፃፃሪ ይዞታ እንደመሆኑ መጠን አጠቃላይ የሚደርሳቸዉ ይዞታ 505 ካ/ሜትር ነዉ፤ በይዞታዉ መሰረት ካርታ ሰርተን ሰጥተናል፤ከአመልካች ይዞታ ላይ ተቀንሶ ለ1ኛ ተከሳሽ የተሰጠ ካርታ የለም፤ይዞታዉ ቀደሞም የቤት ቁጥር 1169 የሟች አቶ ወልዳ ገ/ማሪያም ከሞቱ በኋላ ይዞታዉ በትንሳኤ ወልዳና በአስናቀች ወልደ ተይዞ የነበረ ስሆን ትንሳኤ ወልዳ በመሞታቸዉ ሟች አቶ ወልዳ ገ/ማሪያም ብቸኛ ወራሽ 1ኛ ተጠሪ በመሆናቸዉ በዚህ አግባብ ካርታ ለ1ኛ ተጠሪ ተሰርቷል፤በተጭበረበረ መንገድ የተሰጠ ካርታ የተያዘ ጉዲይ በቤት ቁጥር 1168 እንጂ 1169ን አልነበረም፤ ተይዞ የነበረዉ ጉዲይም የቤት ቁጥር 1169 ብቻ ሳይሆን የቤት ቁጥር 1168ን በአጠቃላይ በመሆኑ እንዱሁም የቤት ቁጥር 1169 የሟች አቶ ወልዳ ገ/ማርያም መሆኑ ያላከራከረና 1ኛ ተጠሪም ወራሽ መሆናቸዉ እስካልተሻረ ድረስ በወቅቱ 1ኛ ተጠሪና ወንድማቸዉ አቶ ትንሳኤ ወልዳ ንብረቱን በጋራ ማስተዲዲር ይችለ ነበር፤አመልካች በቤቱ ላይ መብት ያላቸዉ ሰለመሆኑ ሳያረጋግጡ ክስ ያቀረቡ በመሆኑ ክሱ ዉድቅ ይሁን ሲለ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የአመልካችን ይዞታ በማካተት ለ1ኛ ተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ተሰጥቷል ወይስ አልተሰጠም? የሚለዉን ጭብጥ በመያዝ የቤቱን ማህደር በማስቀረብ የሰዉ ምስክሮች በመስማት ጉዲዩን መርምሮ የአመልካችን ጥቅም በሚጎዲ መልኩ ለ1ኛ ተጠሪ ካርታ የተሰጠ መሆኑን ያቀረቡት ማሰረጃዎች የሚያስረደ ባለመሆናቸዉ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ ሉመክን አይገባም በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካችም በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የቀረበዉን የይግባኝ ቅሬታ ሰርዟል።
አሁን የቀረበዉ የሰበር አቤቱታም ከፍ ሰል የተገለፀዉን ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምላቸዉ አመልካች ጥር 20 ቀን 2014 ዓም በተጻፈ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም፡- ተጠሪ የአባታቸዉ ንብረት እንዱጣራላቸዉ የጠየቁት በመዝገብ ላይ በቀን 30/03/2007 ዓ.ም ሲሆን ካርታ የተሰጣቸዉ በ2004 ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ዉርስ ባልተጣራበት ካርታ መስጠቱ ትክክል አይደለም፤1ኛ ተጠሪ ከአባታቸዉ የሚወርሱት ቀድሞ ወደ ስማቸዉ ያዛወሩት የቤት ቁጥር 1169 የሆነዉ ቤት ብቻ ነዉ፤ ካርታዉ በተገቢ መንገድ የተሰጣቸዉ አይደለም፤ዉርስ ይጣራ ብለዉ ያቀረቡት ክስም በይርጋ ይታገዲል የተባለ መሆኑን፤የስር ፍርድ ቤትም ይህንን በአግባቡ ሳይመረምረዉ እና ሳይመለከተዉ ክሱን ዉድቅ ማድረጉ ትክክል አለመሆኑን፤ ዉርስ ይጣራ ጥያቄያቸዉ ወይም ክስ ያቀረቡት በፍ/ስ/ስ/.ህግ ቁጥር 5(1) መሰረት የአባታቸዉ የዉርስ ንብረት ይጣራ ጥያቄ ዉድቅ የተደረገ መሆኑን፤ሟች አባታቸዉ ትተዉ የሞቱት የዉርስ ንብረት የላለ መሆኑን ፤1ኛ ተጠሪ ተለይቶ የተላለፈላቸዉ ንብረት በላለበት ካርታ መሰጠቱ ትክክል አለመሆኑን እያስረዲሁ የስር ፍርድ ቤት ክሴን ዉድቅ ማድረጉ ትክክል አይደለም፤ይዞታዉን በተመለከተ በእጄ ያለዉ ይዞታ ምን ያህል እንደሆነ በትዕዛዝ ሳያጣራ ዉሳኔ መስጠቱ ትክክል አለመሆኑን፤የአመልካች ካርታ የተሰራዉ በአየር ካርታ ልኬት ሲሆን የ1ኛ ተጠሪ ደግሞ በአካል በመሄድ መሆኑን ከአ/አ/መ/ል/ማ/ቢሮ የተሰጠዉ ምላሽ መገለጹ በሁለት ዓይነት ልኬት በአንድ የጋራ መብት የሚጋሩ ባለ ይዞታዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥር በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ተጨማሪ ትዕዛዝ በመስጠት ሳያጣራ ማለፈ ትክክል አይደለም፤በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሻር ጠይቀዋል።
ሰበር አጣሪ ችልትም መዝገቡን መርምሮ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የሚከራከሩበት መሬት ልኬት በንፅፅር የተሰራዉ እንዳት እንደሆነ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአ/አበባ ከተማ አስተዲደር መሬት ልማት ቢሮ እንዱያጣራለት ባዘዘዉ መሰረት ቢሮዉ የግራ ቀኙን ማህደር ተመልክቶ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ ይዞታ ተገቢዉን አንጻር ተለክቶ ንፅፅሩ የተሰራዉ በ1988 አየር ካርታ መነሻ ተደርጎ ሲሆን የተጠሪ ንፅፅሩ የተሰራዉ በወቅቱ በልኬት ጊዜ በያዙት ቦታ መጠን መሆኑን ገልጾ በዚህ መልኩ በተለያየ ልኬት ንፅፅሩ መሰራቱ ተገቢ ያለመሆኑን በገለፀበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች በዚህ ላይ ምንም ሳይለ በማለፍ የመወሰናቸዉ አግባብነት ለማጣራት ያስቀርባል ተብል ግራ ቀኙ የፁሐፍ ክርክር አቅርበዋል።
በዚሁ መሰረት 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ያቀረቡት መልስ ይዘቱም፡-የአ/አበባ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመነት ቢሮ የግራ ቀኛችን ተከራካሪ ወገኖች ይዞታዉ የተለየበትን አግባብ ማስረጃ ግልፅ ድጋሚ ማብራሪያ የማያስፈልገዉ የ1ኛ ተጠሪ ሳይሆን አመልካች ካርታ ያገኙበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን ያረጋገጠ ነዉ፤የስር ፍርድ ቤት ተገቢዉን ጭብጥ በመያዝ በሰዉ ምስክር በሰነድ ማስረጃ በማጣራት ዉሳኔ የሰጠ መሆኑን ፤የ1ኛ ተጠሪ መብት በይርጋ ያልታገደ መሆኑን በመግለጽ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ ይጽናልን ሲለ ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩለ ያቀረቡት መልስ ለአመልካች የተሰራዉ ካርታ ከፍተኛ ካ.ሜትር ተወስድ መሆኑን ለ1ኛ ተጠሪ ደግሞ በአነስተኛ ካርታ የተሰራላቸዉ መሆኑን ከአ/አበባ ከተማ መሬት ማናጅመንት የተላካዉ ምላሽ የተገለጸ በመሆኑ፤አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ካርታ ይምከን የሚል እንጂ ሰለ ዉርስ ሀብት የጠየቁት ነገር የለም በዚህ ችልት የሚስተናገድ አለመሆኑን፤የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ዉድቅ ያደረገበት ተገቢዉን ጭብጥ በመያዝ ማስረጃ መርምሮ በመሆኑ በተሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም በሚል ተከራክረዋል።
አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከግራ ቀኙ የቀረበዉ ክርክር ከፍ ሲል የተገለጸዉን ሲመስል ይህ ፍርድ ቤትም የቀረበዉ ክርክር ለሰበር አቤቱታ መሰረት ከሆነዉ ዉሳኔ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካለዉ ህግ አንጻር ጉዲዩን መርምረናል።እንደመረመርነዉም ምላሽ የሚሻዉ ጉዲይ በአመልካች በኩል የቀረበዉን ክስ ለመዲኘት የስር ፍርድ ቤት የሥረ ነገር ስልጣን አላቸዉ ወይስ የላቸዉም የሚለዉ ሆኖ ተገኝቷል።በአመልካች በኩል የቀረበዉ ክስ የተጠየቀዉ ዲኝነት ከይዞታዬ ላይ ተቀንሶ ለ1ኛ ተጠሪ ካርታ የተሰራላቸዉ በመሆኑ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ ይምከን የሚል ሰለመሆኑ ከስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ለመረዲት ችለናል።ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን ጉዲይ ለማስተናገድ ስልጣን ያለቸዉ ወይም የላላቸዉ መሆኑን በመመርመር ተገቢዉን ዉሣኔ መሰጠት ያለባቸዉ ሰለመሆኑ በፍ/ስ/ሰ/ህግ ቁጥር 9(2) ስር ተመላክቷል።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልትም በመዝገብ ላይ ገዥ ዉሳኔ ሰጥቷል።የአስተዲደር ዉሳኔዎችን የሚታዩበት ሁኔታ የፈዳራል የአስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2013 ወጥቶ ተግባራዊ ተደርጓል።የአመልካች ክስም የቀረበዉ ይህ አዋጅ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ነዉ።የአስተዲዲር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ማዉጣት ያስፈለገዉ የአስተዲደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትለትን ጣልቃ ገብነት በህግ የሚመሩበትና ለህግ የሚገባ መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉና የአስተዲደር ተቋማት የዉሣኔ አሰጣጥና የመመሪያ አወጣጥ መርሆዎችና ሥነ ሥርዓት እንዱሁም የአስተዲደራዊ ዉሣኔዎች ቅር የተሰኘ ሰዉ የዉሣኔዎችንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዲደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ስለመሆኑ የአዋጁ መግቢያ በግልጽ አስቀምጧል።ከአዋጁ መግቢያ በዝርዝር ስንመለከት የአስተዲደር ህግ የስራ አስፈፃሚዉን ሰልጣን ግዳታና ተግባር እንዱሁም የተግባራቱን ህጋዊነት የሚመለከት ህግ ሲሆን እየተለጠጠ እና እየተወሳሰበ ከመጣዉ የመንግስት አስተዲደር ስራ አንፃር የአስተዲደር አካላት ከህግ አስፈፃሚነት ስልጣናቸዉ ባሻገር በተግባር ህግ የማዉጣትና ህግ የመተርጎም ተግባራትን የሚያከናዉኑ በመሆኑ የአስተዲደር ህግ እነዚህን ተግባራት ከመፍቀድ ባሻር የአስተዲደር አካላት ተግባራት በጠባቡ ተግባራዊ እንዱደረጉ በማድረግ ለአስተዲደር አካላት ስልጣን ገደብ የሚያበጅ የህግ ማዔቀፍ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ።የአስተዲደር ህግ የስራ አስፈፃሚዉን የስልጣን ገደብ ከማበጀት ባሻገር ፍርድ ቤቶች ከአስተዲደራዊ ጉዲዮች ጋር በተያያዘ ሚናቸዉ እስከየት ድረስ እንደሚዘልቅ የሚወስን በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በስራ አስፈፃሚዉ ስልጣን ጣልቃ በመግባት ህገ መንግስታዊ የሆነዉን የስልጣን ክፍፍል መርህን እንዲይጥሱ ይረዲል።ከዜጎች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት አንፃር ስንመለከተዉም ከላይ እንደተመለከተዉ የአስተዲደር ህግ የአስተዲደር አካላትን ስልጣን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የህግ ማዔቀፍ በመሆኑ ዉጤታማ ተግባራዊነቱ የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብትና ነፃነት እንዲይጣስ ዋስትናን የሚሰጥ ነዉ።በዚህ አግባብም የአስተዲደር ህግ ተግባራዊ ማድረግ የግለሰቦች ሰብአዊና ዱሞክራሲያዊ መብቶች በተጨባጭ እንዱረጋገጡ ያስችላል።በዚህም አግባብም በህገ መንግስቱ የተቀመጡትን የህገ መንግስታዊነት የመንግስት መርሆዎች በተጨባጭ እንዱረጋገጡ በማድረግ የህግ መንግስቱን መርሆዎች ማስፈፀም የአስተዲደር ህግ መሰረታዊ ህግ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ።የአስተዲደር መስሪያ ቤቶች አስተዲደራዊ ድንጋጌ የማወጣት(ከፉል የህግ አዉጪነት ስልጣን) እና አስተዲደራዊ ዉሳኔ ሰጪነት (በከፉል የዲኝነት ስልጣን)ያላቸዉ ሲሆን ከፉል የዲኝነት ስልጣናቸዉን በተመለከተ ጥብቅ እና ዝርዝር ለሆነ የስነ ስርዓትና የማስረጃ ህግ ደንቦች እንዱገዙ የማይገደደ ቢሆንም እንደ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ሁለ ፍሬ ነገሩን በመስማት፤በመመዘን እና በመመርመር አረጋግጠዉ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ የግለሰቦችን መብትና ጥቅም ሉነካ የሚችል ዉጤት ያለዉ ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን አላቸዉ። የአስተዲደር ዉሳኔ ማለት መመሪያ ማዉጣትን ሳይጨምር የአስተዲደር ተቋማት በዔለት ተዔለት ተግባር ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ የሚሰጠዉ ዉሳኔ መሆኑን በማመልከት የአስተዲደር ሰነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2013 አንቀጽ 2(3) የአስተዲደር አካለን የህግ ማስፈፀም እና ከፉል የዲኝነት ስልጣኑን በማደባለቅ የተሰጠ ትርጉም የተከተለ ቢሆንም የአስተዲደር መስሪያ ቤቶች ዲኝነታዊ ወይም የህግ አዉጪነት ስልጣናቸዉ አተገባበርን አስመልክቶ ብቻ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ቁጥጥር ላደረግበት የሚችል በመሆኑ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የአጣሪነት ስልጣን የሚኖራቸዉ የአስተዲደር አካላት የአስተዲዲር ስልጣናቸዉን በመገልገል ተገቢዉን ማጣራት በማድረግ በሚሰጡት ትዕዛዝ፤ዉሳኔ፤በማድረግ ወይም ባለማድረግ በሚገለፅ አስተዲደራዊ ይዘት ባለዉ ዉሳኔ ላይ ላሆን ይገባል።
በእጃችን ወደ አለዉ ጉዲይ ስንመጣ አመልካች በስር ፍርድ ቤት የጠየቁት ዲኝነት ከይዞታቸዉ ላይ ተቀንሶ አለአግባብ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ያሰጠዉ ካርታ ይምከን የሚል ነዉ።ካርታ የመስጠትም ሆነ የማምከን ሰልጣን ያለዉ ካርታዉን የሰጠዉ አካል ነዉ።በተያዘዉ ጉዲይ ካርታ የመስጠት ሰልጣን የ2ኛ ተጠሪ ስለ መሆኑ አላከራከረም።ይህ ማለት የአስተዲደር ዉሳኔ ሰለመሆኑ ያሳያል።በአስተዲደር ስነ ስርዓት አዋጅ 1183/2013 አንቀጽ 2(3) መሰረት አስተዲዲር ዉሳኔ አስተዲዲር መስርያ ቤቶች በዔለት ዔለት ስራቸዉ መሰረት የሚሰሩት ስራ ነዉ።ከአስተዲደራዊ ዉሳኔዎች ዉስጥም ካርታ ማምከን አስተዲደራዊ ዉሳኔ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ።አስተዲደራዊ ዉሳኔዎች ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 44 መሰረት ለተቋቋመ የአስተዲደር ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል በአንቀጽ 43 ቅሬታ የሚቀርብበትና ይህ ቅሬታ ሰሚ አካል በአንቀጽ 46 መሰረት የተቋሙን መጨረሻ ዉሳኔ ሲሰጥ በአንቀጽ 49(1)አግባብ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታ የሚቀርብበት ነዉ።በአመልካች በኩል የቀረበዉ ክስም በአዋጁ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ያለትን ሂደቶች ተከትለዉ ያንን ከጨረሱ (exhaustion of available remedies) በኋላ መምጣት ሲገባቸዉ ቀጥታ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አዋጁን ያገናዘበ ሆኖ አላገኘንም።ተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት መዝገብ (ያልታተመ) ገዥ ዉሳኔ ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ሰጥቷል።ጉዲዩ መጀመሪያ የቀረለበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የቀረበለት ጉዲይ ካርታ ይምከን ዲኝነት ጥያቄ ሆኖ ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን በመጀመሪያ ማየት ሲገባዉ ዋናዉ ጉዲይ ላይ ዉሳኔ መስጠቱ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ማረም ሲገባዉ ሳያርም በትዕዛዝ መዝገብ መዝጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ዉሳኔ ነዉ ብለን ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1.የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ በ 07/12/2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ የፈዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ በ22/02/2014 በትዕዛዝ ያፀናዉ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348(1)መሰረት ተሽሯል።
2.በአመልካች በኩል በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ በአስተዲደር ስነ ስርዓት አዋጅ 1183/2013 አንቀጽ 43 እና 44 የተዘረጋዉን ስነ ስርዓት ሳይጠብቅ የቀረበ ስለሆነ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለዉም ብለናል።
3.አመልካች በአዋጁ የተዘረጋዉን ስርዓት ጠብቀዉ ጉዲያቸዉን የማቅረብ መብት ይህ ዉሳኔ አያግዲቸዉም ብለናል።
4.በዚህ ችልት ለተደረገዉ ክርክር ላስከተለዉ ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
5.የዉሳኔዉ ግልባጭ የስር ፍርድ ቤት ይድረስ።
No topics extracted.