የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል አለ ከተባለ በአጓጓዡ እና በእቃ አስጫኙ መካከል ከዚህ ውል ጋር ተያይዞ በመካከላቸው ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች ተፈጻሚነት የሚኖረው ህግ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጅ እንደሚሆን በአዋጅ ተደንግጎ እያለ ይህን ልዩ ህግ በመተው ጉዲዩ ከውል ውጪ ሃላፉነትን በሚመለከቱ የፍትሀ ብሓር ህግ ድንጋጌዎች ላታይ የሚችል ስላለመሆኑ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 3/1 በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል መነሻ በአጓጓዡ እና በእቃ አስጫኙ መካከል በተጭበረበረ ሰነድ ወጪ የተደረገን እቃን በሚመለከት ክስ ከቀረበ፤ ክሱ የቀረበው በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል መሰረት በመሆኑ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይርጋ ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 40(1) እና (2) እንጂ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 2143/1 የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፕርት ልጅስቲክ ድርጅት እና ማርቪልደን ካንፒኒ ሉሚትድ የተመለከተው ድንጋጌ ስላለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፕርት ልጅስቲክ ድርጅት፡- ነ/ፈጅ ሚኪያስ ሙሴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ማርቪልደን ካንፒኒ ሉሚትድ፡- ጠበቃ ፍቅሩ ባቲሶ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በባህር እና በየብስ ተጓጉዞ ሞጆ ደረቅ ወደብ የደረሰ እቃ በሐሰተኛ የማስጫኛ ሰነድ ወጪ ተደርጓል በሚል የእቃው ዋጋ እንዱከፈል በአጓጓዡ ላይ ለቀረበ ክስ ተፈጻሚነት የሚኖረው ህግ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጅ ነው ወይስ ከውል ውጪ ኃላፉነትን የሚመለከተው የፍትሐ ብሓር ህጉ ድንጋጌ ነው የሚለውን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች 4ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ባቀረበው ክስ በአመልካች በመርከብ ተጭኖ ወደ ሀገር የገባ እቃ ሞጆ ደረቅ ወደብ ከደረሰ በኋላ አመልካች እቃውን በሐሰተኛ ሰነድ በመልቀቅ ግዳታውን ስላልተወጣ ከስር 1ኛ-3ኛ ካለት ተከሳሾች ጋር አመልካች በአንድነት እና በነጠላ የእቃውን ዋጋ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል። አመልካች በበኩለ ተጠሪ የክሱን አጠቃላይ ይዘት እና ዋና ዋና ዝርዝሮችን የሚገልጽ ማስጠንቀቂያ እቃውን ከተረከበበት ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ክስ እስከተመሰረተበት ጊዜ ድረስ ስላልሰጠኝ ክሱ በስድስት ወር ይርጋ ይታገዲል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቃወሚያው ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ አመልካች ስራውን የሚያከናውነው በአዋጅ ቁጥር 548/99 መሰረት በመሆኑ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 40/2 መሰረት እቃውን ከተረከበበት ወይም መረከብ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ተጠሪ የክሱን ዝርዝር የያዘ ማስጠንቀቂያ ስላልሰጠ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት በብይን የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል። ተጠሪ በዚህ ብይን ላይ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቅሬታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪ ክስ ያቀረበው በተጭበረበረ ሰነድ ወጪ የተደረገን እቃ በሚመለከት ነው። ይህም ክሱ ከመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል ጋር ተያይዞ የቀረበ አለመሆኑን ያሳያል። በመሆኑም ለጉዲዩ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይርጋ ድንጋጌ አዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 40/2 ሳይሆን የፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 2143/1 ላይ የተመለከተው የ2 ዓመት ይርጋ ስለሆነ የተጠሪ ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን ሽሮ በፍሬ ነገር ክርክሩ ላይ ተገቢው ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን ወደ ስር ፍርድ ቤት መልሷል።
አመልካች በመጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትን ውሳኔን በመቃወም ለማሳረም ሲሆን የቅሬታው ይዘት ተጠሪ በማጓጓዣ ውል መሰረት ለአመልካች እቃ ማስረከቡን አልካደም። የአመልካች የውል ግዳታ የሚያበቃው ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ እቃውን ሲያስረክብ በመሆኑ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ በጉዲዩ ላይ ተፈጻሚነት አለው። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአዋጁ ተፈጻሚነት እቃው በጉዞ ላይ እያለ ብቻ እንደሆነ በመቁጠር ለጉዲዩ ከውል ውጪ ኃላፉነትን የሚመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚ ላሆን ይገባል ማለቱ ተገቢ አይደለም። ጉዲዩ ከውል ውጪ ድንጋጌዎች መሰረት መታየት አለበት ቢባለ እንኳን በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ አንቀጽ 24 መሰረት የአዋጁን መከራከሪያ አመልካች ማንሳት ይችላል። በመሆኑም የይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይሻርልኝ በማለት ጠይቋል።
የሰበር አጣሪ ችልት የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ ይርጋን በተመለከተ ጉዲዩ ላታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 40/2 መሰረት ነው? ወይስ በፍ/ህ/ቁጥር 2143 መሰረት ነው?
የሚለውን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፍ ባቀረበው መልስ በሐሰተኛ ሰነድ እቃውን ከሞጆ ደረቅ ወደብ የተረከበው ክፍያ ሳይፈጽም የእቃው ገዢ ነው። ችግሩ የተፈጠረው በሻጭ እና በገዢ መካከል ስለሆነ ለጉዲዩ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ተፈጻሚነት የለውም። አዋጁ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታ ያስቀመጠው ከተጫነ እቃ ጋር በተያያዘ የጎደለ፣ የተበላሸ ወይም የጠፊ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ከውል ውጪ ለመጣ ኃላፉነት ህጉ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታ አይጥልም። በሀሰተኛ ሰነድ እቃ ከደረቅ ወደብ ሲወጣ አመልካች የማጣራት ኃላፉነቱን ባለመወጣቱ ምክንያት የሚቀርብ ክርክር በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ መሰረት ላታይ አይገባም በመባለ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለላለ ቅሬታው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በግንቦት 03 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል። የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በስር ፍርድ ቤት ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ያቀረበው ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ እቃ በአመልካች በመርከብ ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ሞጆ ደረቅ ወደብ ከደረሰ በኋላ አመልካች በሀሰተኛ ሰነድ ንብረቱን ማስረከብ ለላለበት ሰው ስላስረከበ ከላልች ተከሳሾች ጋር በአንድነት እና በነጠላ የእቃውን ዋጋ ይክፈለኝ በሚል ነው። አመልካች በበኩለ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጅ መሆኑ በዚህ አዋጅ መሰረት ተጠሪ በስድስት ወር ውስጥ የክሱን ዝርዝር የያዘ ማስጠንቀቂያ ስላልሰጠኝ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። ተጠሪ ለመቃወሚያው በሰጠው ምላሽ አመልካች እቃውን በተጭበረበረ ሰነድ ማስረከብ ለማይገባው ሰው አስረክቧል የሚል በመሆኑ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት የለውም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ነው የሚል አቋም ይዟል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ሳይሆን የፍትሐ ብሓር ህጉ ከውል ውጪ ኃላፉነትን የሚመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ነው የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። በመሆኑም በመጀመሪያ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የትኛው ህግ ነው? የሚለውን መለየት ይሆናል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል መኖሩ እና በዚህ ውል መነሻነት ተጠሪ ለአመልካች እቃውን ማስረከቡ በግራ ቀኙ የታመነ ጉዲይ ነው። በአዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 2/1 ላይ መልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ማለት ምንማለት እንደሆነ የተተረጎመ ሲሆን ቢያንስ በሁለት የተለያዩ የማጓጓዣ አይነቶች፤ ወጥ በሆነ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል መሰረት መልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አከናዋኙ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ተረክቦ በማጓጓዝ ላላ አገር ውስጥ የሚገኝ የማስረከቢያ ቦታ ለማስረከብ የሚደረግ የማጓጓዝ ስራ መሆኑን ያመለክታል። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል የትራንስፕርት አከናዋኙ እቃውን ተረክቦ ከአንድ በላይ በሆኑ የማጓጓዣ ዘዳዎች ማለትም በባህር እና በየብስ ወይም በአየር እና በየብስ ወይም በሶስቱም መንገድች ካጓጓዘ በኋላ በማስረከቢያ ቦታ ላይ ለህጋዊ ተረካቢ ለማስረከብ የሚደረግ ውል መሆኑን ነው። ይህም ማለት የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አከናዋኙ ወይም አጓጓዡ እቃውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ እስኪያስረክብ ላለው ጊዜ የተረከበውን እቃ ደህንነት ጠብቆ ለህጋዊ አካል ለማስረከብ ግዳታ የሚገባበት ውል ነው። እንደዚሁም የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አከናዋኙ የኃላፉነት የጊዜ ወሰን በአዋጁ በአንቀጽ 15/1 ላይ በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አከናዋኙ ለእቃው ኃላፉ የሚሆነው ከተረከበበት እስከ ሚያስረክብበት ላለው ጊዜ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል በአጓጓዡ ላይ እቃውን ከተረከበበት ጀምሮ እስከ ሚያስረክብ ባለው ጊዜ ውስጥ በእቃው ላይ ለሚደርስ ጉዲት ማለትም በእቃው መበላሸት ወይም መጥፊት በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዲት ከውል የመነጨ ኃላፉነትን የሚያስከትል ይሆናል።
በአጓጓዡ እና በእቃ አስጫኙ መካከል የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል አለ ከተባለ በመካከላቸው አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ተፈጻሚነት የሚኖረው ህግ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 548/99 አንቀጽ 3/1 ላይ ተመልክቷል። ተጠሪ ይህ አዋጅ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት የለውም በማለት የሚያቀርበው አንደ መከራከሪያ አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆነው እቃው በጉዞ ላይ እያለ ጉዲት ቢደርስበት ነው። ነገር ግን ጉዲቱ የደረሰው በተጭበረበረ ሰነድ ለማይመለከተው ሰው ርክክብ በመደረጉ ስለሆነ አዋጁ ተፈጻሚነት የለውም በሚል ነው። ከላይ እንደተገለጸው በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል መሰረት እቃውን ያጓጓዘው አመልካች ነው። ይህ ከሆነ አመልካች በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውለ መሰረት ላጓጓዘው እቃ ኃላፉነት የሚኖርበት እቃውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚያስረክብ ላለው ጊዜ ነው። አመልካች እቃውን ለተገቢው ሰው አለማስረከቡ ወይም በሀሰተኛ የማጓጓዣ ሰነድ ለማይመለከተው ሰው ማስረከቡ በውለ ከማስረከብ ጋር ተያይዞ ካለበት ኃላፉነት አንጻር የሚታይ ይሆናል። በመሆኑም በግራ ቀኙ መካከል የማጓጓዣ ወይም የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት ውል እያለ እና ከዚህ ውል ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር አለመግባባት በግልጽ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ተፈጻሚ እንደሚሆን በአዋጁ ተደንግጎ እያለ ይህን ልዩ ህግ በመተው ጉዲዩ ከውል ውጪ ኃላፉነትን በሚመለከቱ የፍትሐ ብሓር ህጉ ድንጋጌዎች ላታይ አይችልም።
ላላው የተጠሪ ክርክር ችግሩ የተፈጠረው በተጠሪ እና በእቃው ገዢ መካከል ስለሆነ ጉዲዩ በተጠቀሰው አዋጅ ላታይ አይገባም የሚል ነው። በእርግጥ ተጠሪ ከእቃው ገዢ ጋር ያለው ክርክር ወይም ገዢው የእቃውን ዋጋ ባለመክፈለ የሚፈጠረው አለመግባባት በመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ላታይ እንደማይችል ግልጽ ነው። ነገር ግን ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 548/99 መሰረት መታየት አለበት የተባለው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለውን ክርክር እንጂ የስር ተከሳሽ ከሆነው ከእቃው ገዢ አንጻር ባለመሆኑ ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በግራ ቀኙ መካከል ለተነሳው ክርክር ተፈጻሚነት የሚኖረው ህግ የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጁ ሆኖ እያለ ይህ አዋጅ ተፈጻሚነት የለውም ማለቱ የአዋጁን ተፈጻሚነት ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው።
በመቀጠል በግራ ቀኙ መካከል ተፈጻሚነት ያለው የመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አዋጅ ነው ከተባለ የተጠሪ ክስ በይርጋ ይታገዲል ወይስ አይታገድም? የሚለውን ስንመለከት በአዋጁ አንቀጽ 40 ላይ ይርጋን አስመልክቶ የተለያዩ ድንጋጌዎችን ይዟል። በዚህም መሰረት ከመልቲ ሞዲል ትራንስፕርት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች በሁለት ዓመት ጊዜ ዉስጥ ካልቀረቡ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆኑ፣ ይሁንና ርክክቡ ከተፈጸመበት ቀን በኋላ ባለት ስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ የክሱን አጠቃላይ ይዘት እና ዋና ዋና ዝርዝሮች የሚገልጽ የጽሐፍ ማስታወቂያ ወይም የዔቃዎች ርክክብ ያልተደረገ ከሆነ የዔቃዎች ርክክብ መደረግ ከነበረበት ቀን ቀጥል ካለዉ ቀን ጀምሮ ክስ ካልተመሰረተ የስድስት ወር ጊዜ እንዲበቃ ክሱ በይርጋ እንደሚቋረጥ ከአዋጁ አንቀጽ 40(1) እና (2) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ ሁለቱ ድንጋጌዎች ይዘት መረዲት የሚቻለዉ አንደኛ የይርጋዉ መቁጠሪያ ጊዜ የሚጀምረዉ የዔቃዎች ርክክብ ከተደረገበት ቀን ወይም ርክክብ ያልተደረገ ከሆነም መደረግ ከነበረበት ጊዜ እንጂ ከሳሽ በዔቃዎቹ ላይ ጉዲት መድረሱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ አለመሆኑን ነዉ። ሁለተኛዉ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ እና የስድስት ወር የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆኑባቸዉ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸዉን ነዉ። በዚህም መሰረት የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆነዉ ከሳሽ ርክክቡ ከተደረገበት ወይም ርክክቡ ያልተደረገ ከሆነም መደረግ ከነበረበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ የክሱን ዋና ዋና ይዘት የያዘ ማስታወቂያ ለተከሳሽ ማድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን መሆኑንና ከዚህ ዉጭ ባለዉ ሁኔታ ማለትም ርክክቡ ከተደረገበት ወይም መደረግ ከነበረበት ቀን ጀምሮ የክሱን ዋና ዋና ይዘት የሚያሳይ ማስታወቂያ በስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ለተከሳሽ ያላስታወቀ ከሳሽ ርክክቡ ከተፈጸመበት ወይም መፈጸም ከነበረበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ለፍርድ ቤት ካላቀረበ ክሱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በተያዘው ጉዲይ የእቃው ርክክብ መደረግ የነበረበት ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. መሆኑን አመልካች የገለጸ ሲሆን ተጠሪ ርክክብ የተደረገው ወይም ላደረግ የሚገባው በዚህ ቀን አለመሆኑን ክድ ያቀረበው ክርክር የለም። ይህ ከሆነ ተጠሪ ከህዲር 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሚቆጠር 6ወር ውስጥ የክሱን ዋና ዋና ዝርዝር የያዘ ማስጠንቀቂያ ለአመልካች መስጠት ወይም በ6 ወር ውስጥ ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ነበረበት። ተጠሪ ግን በተገለጸው የ6 ወር ጊዜ ውስጥ ለአመልካች ማስጠንቀቂያ ያልሰጠ ወይም ለፍርድ ቤት ክስ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው። በመሆኑም ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የስር የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪ ክስ በይርጋ ይታገዲል ማለቱ ህጉን የተከተለ ሆኖ እያለ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አግባብነት የላለውን ድንጋጌ በመጥቀስ በይርጋ አይታገድም ማለቱ በህግ አተረጓጎም እና አፈጻጸም ረገድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡
1ኛ. የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ በታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
2ኛ. የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በየካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
3ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ትእዛዝ በዚህ መዝገብ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።