በወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1 እና 540 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ ተራ የሆነ የሰዉ ግድያ ሙከራ ወንጀል ተፈጽሟል በሚል የቀረበን ክስ ጨምሮ በተከሳሽ ላይ በቀረበዉ የወንጀል ክስ የተጠቀሰዉ ድንጋጌ የሚያስቀጣዉ መነሻ ቅጣት ከአስራ ሁለት ዓመት ባነሰ ጽኑ እስራት ሆኖ በፍትሕ ሚኒስቴር የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ጣሪያ ደግሞ ከአስራ ሁለት ዓመት በላይ ከሆነና ተከሳሹ ጥፊተኛ ሆኖ ሲገኝ ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት ያነሰ ሉቀጣ የሚችልበት አጋጣሚ ሰፉ ከሆነ ተከሳሹ በላለበት ክርክር የሚሰማ ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) ዘነበች ቸሩ
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 27 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ አመልካች- በፍትሕ ሚኒስቴር - የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ዘነበች ቸሩ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1 እና 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተራ የሆነ የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል ፈጽሟል በሚል የተከሰሰ ሰው በላለበት ክርክሩ ላታይ የሚችል መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1 እና 540 የተደነገገዉን በመተላለፍ ተራ የሆነ የሰዉ ግድያ ሙከራ ወንጀል ፈጽማለች በሚል ክስ መስርቶባታል። ለተጠሪ በአድራሻዋ መጥሪያ እንዱደርሳት ታዞ በአድራሻዋ ባለመገኘቷ መጥሪያ ማድረስ ባለመቻለ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ መጥሪያ ጥሪ ተደርጎላትም አልቀረበችም።ይህንን ተከትል የስር ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/07/2014ዓ/ም በአብላጫ ድምጽ በሰጠዉ ትእዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) ላይ በተደነገገው መሰረት ተከሳሹ ከአስራ ሁለት ዓመት በታች በሚቀጣ ድንጋጌ የተከሰሰ እንደሆነ ክርክሩ በላለበት ሉቀጥል እንደማይችል ተደንግጓል። ተጠሪ በተከሰሰችበት ወንጀል ጥፊተኛ ብትሆን ልትቀጣ የምትችለው መነሻውን 5 ዓመት ጣሪያውን 20 ዓመት ነው። ፍርድ ቤቱም ተጠሪ ጥፊተኛ ሆና ከተገኘች በዚህ ፍቅድ ሥልጣን ዉስጥ ቅጣቱን ስለሚወስን ተጠሪ ከአስራ ሁለት ዓመት በታች ለትቀጣ ትችላለች።ስለሆነም ተጠሪ የተከሰሰችበት ወንጀል ከአስራ ሁለት ዓመት በታች ሉያስቀጣ የሚችል ስለሆነ በላለበት የሚታይ ባለመሆኑ ተጠሪ ሲገኙ መዝገቡን አመልካች ማንቀሳቀስ እንዱችል መብት ተጠብቆለታል በማለት መዝገቡን ዘግቷል።በሀሳብ የተለዩት ዲኛ ተጠሪ የተከሰሰችበት ድንጋጌ ምንም እንኳን መነሻ ቅጣቱ 5 ዓመት የሚል ቢሆንም መድረሻ ቅጣቱ እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ተጠሪ በላለችበት ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል በመሆኑ በላለችበት ክርክሩ ሉሰማ ይገባል የሚል ምክንያት አስፍረዋል።
አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን ቢያቀርብም ችልቱ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጉድለት የለበትም በሚል በመ/ ላይ በቀን 10/09/2014ዓ/ም በሰጠው ትእዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195/1 መሰረት ይግባኙን ሰርዞበታል።
አመልካች በቀን 25/11/2014ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ - ተጠሪ የተከሰሰችበት ድንጋጌ ላይ የተመለከተው መነሻ ቅጣት ምንም እንኳን 5 ዓመት ቢሆንም እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ተጠሪ በላለችበት ለመታየት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) የተደነገገው መስፈርት ተሟልቶ እያለ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩ በላለበት ላታይ አይችልም በማለት መዝገቡን መዝጋቱም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ችልት በዚህ ላይ የቀረበዉን ይግባኝ መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ታርሞ ክርክሩ ተጠሪ በላለችበት ሉቀጥል ይገባል ተብል ይወሰንልኝ በማለት ተከራክሯል።
የሰበር አጣሪ ችልት ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀፅ 27/1 እና 540ን ተላልፊለች በሚል የተመሰረተባት የወንጀል ክስ ተጠሪ በላለችበት ላታይ አይችልም በማለት የተወሰነበትን አግባብነት ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161 ጋር ተገናዝቦ ተጠሪ ባለችበት እንዱመረመር ትእዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪ በአድራሿዋ በአካል ባለመገኘቷ ትኖርበታለች በተባለው ቤት ላይ በአስተዲደሩ በኩል መጥሪያዉ ተለጥፍ ባለመቅረቧ መልስ የመስጠት መብቷ ታልፍ በላለችበት እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ከላይ እንደተገለጸዉ አመልካች በተጠሪ ላይ የመሰረተው የወንጀል ክስ ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 27/1 እና 540 ስር የተደነገገዉን ተራ የሆነ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። ተጠሪ ቀርበው እንዱከራከሩ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ በወጣ መጥሪያ ጥሪ ተደርጎላት ባለመቅረቧ አመልካች ተጠሪ በላለችበት እንዱታይ ጠይቋል። በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት እንዱያይ ክሱ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ)ን በመጥቀስ ተጠሪ የተከሰሰችበት ወንጀል ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት ያነሰ ሉያስቀጣ የሚችል በመሆኑ ክሱ ተጠሪ በላለችበት ላታይ የሚችል አይደለም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ባለመቀበል ተጠሪ ሲገኙ መዝገቡ እንዱንቀሳቀስ መብት ጠብቆ መዝገቡን ዘግቶታል። ይግባኝ ሰሚው ችልትንም የአመልካችን ይግባኝ ሰርዟል።እኛም ተጠሪ የተከሰሰችበት ወንጀል ተጠሪ በላለችበት ላታይ የሚችል አይደለም በሚል በመወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈጸም አለመፈጸሙን? በጭብጥነት በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከፍ ሲል በተገለጸዉ መሰረት ለተያዘው ጭብጥ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ይቻል ዘንድ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ፣ የኢፋዱሪ ሕገ መንግስትን ጨምሮ ሕገ መንግስቱ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በወጡት የኢፋዳሪ የወንጀል ሕግ እና የወንጀል ፍትሕ ፕሉሲ በዋናነት መሰረት በማድረግ በአገራችን ተግባራዊ እየሆነ ያለዉን የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ሞዳል ወይም ሞዳልች (Criminal Justice Administration Process Model/s) ምንነት መመርመር ይጠይቃል።
አገራት በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሥርዓታቸው አሜሪካዊው የሕግ ሉቅ ሓርበርት ፒከር (The American legal scholar, Herbert Packer) እ.ኤ.አ.1964 “The Two Models of the Criminal Proces (1964)” በሚል ባሳተሙት የምርምር ጽሁፊቸው ላይ ያስተዋወቁትን ሁለት የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ሞዳልችን በተለያየ ሁኔታና ደረጃ ተግባራዊ ያደርጋለ። እነዚህ የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ሞዳልች ወንጀል የመቆጣጠር እና ፍትሐዊ ሂደት የመከተል ሞዳልች (The Crime Control and Due Process Models) በሚል የሚታወቁ ናቸዉ። የእነዚህ ሞዳልች መገለጫዎች እና ዓላማዎች በጥቅለ የተመለከትን እንደሆነ ወንጀል የመቆጣጠር ሞዳል (The Crime Control Model) የሕብረተሰብን ሰላም፣ደህንነትና ጸጥታ ማረጋገጥን ዓላማዉ በማድረግ በቀዲሚነት ዋጋ የሚሰጠዉ ለቅልጥፍና እና የሕዝቡን ደህንነትና ንብረት ከጥቃት መከላከል ላይ ነው። ይህ ወንጀልን የመቆጣጠር ሞዳል የወንጀል ተጠርጣሪዎች መብት በመጠበቅ ላይ ትኩረት ማድረጉ አጥፉዎችን የማስቀጣቱን ሂደት አስቸጋሪ ስለሚያደርግ በዚህ ምክንያት ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ከሚያመልጡ አጥፉዎቹን ለመቅጣት በተዘረጋው ሂደት ንጹሀን የሚቀጡበት ሁኔታ ቢያጋጥም ይሻላል ብል ያምናል። ከዚህ እምነቱ በመነሳት በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ለማስቀጣት ጥቅም ላይ የሚያውለው ሂደት ተጠርጣሪውን እንደወንጀለኛ የሚገምት (Presumption of guilt) መሆኑ፣የወንጀልች አፈጻጸም መቀነስ ላይ ቅድሚያ መስጠት( Priority is reducing criminal conduct )፣የምርመራና የፍርድ ሂደቱን ፈጣን ማድረግና የመጨረሻ ውሳኔ በመስጠት ላይ ትኩረት የሚያደርግ በመሆኑ ከፍርድ ሂደት በፉት በተጠርጣሪው ጥፊተኝነት ላይ ድርድር ማድረግ እና ብዙ ሰዎችን አስሮ መመርመርን (Mass incarceration) ትኩረት የሚያደርግ፣ እውነታን መፈለግ ላይ ውስንነት (Limited fact finding) የሚታይበት እና ጥፊተኛ አድርጎ የማስቀጣት ምጣኔ ከፍተኛ (High Rate of Conviction) እንዱሆን የሚያደርግ ውጤት የሚያስከትል ነው።
በልላ በኩል ፍትሐዊ ሂደት የመከተል ሞዳል (The Due Process Model) ቀዲሚ ትኩረቱ የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ፍትሐዊ እንዱሆንና በተሳሳተ ሂደት በመከተል ንጹሃን እንዱቀጡ ማድረግ አይገባም ብል የሚያምን ነዉ። በዚህም ምክንያት ንጹህ ሰው ያለጥፊቱ ቀጥቶ ከመጉዲት በሂደቱ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ቢያመልጡ ይሻላል ብል ያምናል።ከዚህ እምነቱ በመነሳት የወንጀል ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት ወይም ተከሳሾች በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፊተኛ ያለመገመት (Presumption of innocence)፤ ለተጠረጠሩ/ ለተከሰሱ ግለሰቦች መብት አጠባበቅ ቅድሚያ መስጠት (Priority on protecting individual rights)፣ ሂደቱን ፍትሐዊ ማድረጉ ላይ ትኩረት መስጠት (Emphasizes fairness in the process)፣እውነታን መፈለግ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ማድረግ (Emphasizes the importance of fact-finding) ፣ ማቅለያዎችንና አክባጅ ምክንያቶችን ከግምት በማስገባት እያንዲንደ ጉዲይ ላይ ፍትሃዊነት እንዱረጋገጥ ማድረግ (Individualized justice that considers mitigating and aggravating factors)፣ እንዱሁም የሚታሰሩ ሰዎች ምጣኔ አነስተኛ እንዱሆን (Lower incarceration rates) የሚያደርጉ እና እነዚህን የመሳሰለትን ላልች ሂደቶችንና አሰራሮችን መከተልን የሚመርጥ ሞዳል ነው።በዚህ አመለካከቱ የተነሳ የተጠርጣሪው ወይም የተከሳሹ መብት እንዱጠበቅ ከፍተኛ ኃላፉነት በፕሉስ እና በሕግ አስፈጻሚ ላይ ይጥላል፤በፕሉሶች ሥልጣን ላይም ገደብ ያደርጋል። የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ፕሉስ በወንጀል የጠረጠረውን ሰው እንደፈለገ አስሮ ምርመራ እንዲያደርግ የተጠረጠሩ ሰዎች ስለሚታሰረቡት አግባብ ሥርዓት ይዘረጋል ፣የተጠረጠሩ ሰዎች ስለተጠረጠሩበት ጉዲይ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ዝም የማለት መብት እንዲላቸው መርማሪ ፕሉስ እንዱነግራቸው ግዳታ ይጥላል፣ ተጠርጣሪዎችን በማስገደድ ማስረጃ እንዲይሰበስብ ማድረግና ፕሉስ ተጠርጣሪን አስገድድ የሰበሰበው ማስረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማድረግ ለአብነት ሉጠቀሱ የሚችለ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም ሞዳልች የየራሳቸዉ የሆኑ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲላቸው በዘርፈ የተጻፈ ድርሳናት ያሳያለ።እንዱሁም ሁለቱም ሞዳልች ነባራዊ ሁኔታን ችላ በማለት የየራሳቸውን ጽንፍ በመያዛቸው እና የወንጀል ተገጂዎችን (crime victims) ዘንግተዋል የሚል ትችት ይቀርብባቸዋል።
ከእዚህ የተነሳ አገራት በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሥርዓታቸው ላልች ሞዳልችን በተጨማሪነት ተግባራዊ ሲያደርጉ ይስተዋላል።በዚህ ረገድ የሚጠቀሰዉ አንደኛው በእንግሉዝኛ መጠሪያው The Punitive Model of Victims' Rights በሚል የሚታወቅ ሆኖ በግርድፈ የተጎጂዎችን መብቶች ማዔከል ያደረገ የአስቀጭነት ሞዳል ተብል ሉገለጽ የሚችል ነው። ይህ ሞዳል የወንጀል ጉዲዮች የማጥራት እና የማስቀጣት ምጣኔ ጥሩ እንዱሆን ከተፈለገ የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሥርዓቱ ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ ራሱን ማሻሻል ይኖርበታል፤የወንጀል ተጎጂዎች የተፈጸመባቸዉን የወንጀል ድርጊት ሪፕርት የሚያደርጉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደቱ በሚፈጸሙ ተግባራት የዲግም ተጠቂነት ሰለባ እንዲይሆኑ ለመከላከል( to prevent revictimization within the criminal process)የሚያስችል እርምጃ መዉሰድን፣ከወንጀል አፈጻጸም ድርድር (Conduct Plea Bargaining ) እና ከጥፊተኝነት ድርድር (Guilty Plea Bargaining) ጋር በተያያዘ ተጎጂዎችንና የወንጀል ድርጊቱን ፈጻሚ ማዔከል ማድረግ ይገባል የሚለ አመለካከቶችን የሚያራምድ ነው።
ላላዉ The Non-Punitive Model of Victims' Rights: A Circle Model በሚል የሚታወቅ ሞዳል ሲሆን ከሚያራምደው አመለካከት ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህል አንዳ ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ አጥፉውን መቅጣት ተፈጽሞ ያለፈውን ጥፊት(ያለፈ ጊዜ/ተግባር) ማዔከል ማድረጉ ላይ ስለሚያተኩርና እምብዛም የወደፉቱን ጊዜ የማመለከት እና ወደፉት ሉፈጸም የሚችልን ወንጀል የማያስቀር በመሆኑ ቅጣትን ማዔከል ከማድረግ ይልቅ የወንጀል ተጎጂዎችን መብት በጠበቀ አኳኋን እና ጉዲዩ የሚያገባቸውን በሂደቱ ማሳተፍ ላይ (የወንጀለ ድርጊትና ውጤቱ የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁለ በማሳተፍ) ትኩረት በማድረግ በወንጀለ ምክንያት የተፈጠረውን ማንኛውንም ጉዲት እና አለመግባባት መፍታት/ማከም፣ ተጎጂዉን መካስ እና ከጉዲቱ በፉት ወደነበሩበት የሚመልስ ፍትህ ማስገኘት (healing, compensation, and restorative justice) ይገባል ብል የሚያምን ነው።በዚህ መሰረት ጉዲዩ የሚመለከተው ሰው ተሳትፍ ሳያደርግ አጥፉውን ከመቅጣት ይልቅ በተፈጸመው ወንጀል ተጎጂ የሆኑ ሰዎችን፣ የእነርሱን ቤተሰቦች፣ የወንጀለን ፈጻሚዎች እና ደጋፉዎቻቸውን ሉያሳትፍ የሚችል አማራጭ የመፍትሄ ዘዳዎችን በመከተል ለአብነት አጥፉው በሂደቱ በሚያደርገው ተሳትፍ ለፈጸመው በደል በራሱ ኃላፉነቱን ወስድ ይቅርታ በመጠየቅ በደለን እንዱያክምና ተጎጂዉን እንዱክስ የሚያደርግ ሂደት መከተል ይገባል ይላል።
እንዱሁም አጥፉውን መቅጣት አስፈላጊ ከሆነም ለተጎጂው ጉዲት እውቅና ለመስጠትና ተጎጂውን ከማክበር አኳያ ታይቶ ቅጣት መወሰን ማዔከል ያደረገ ሂደት መከተል ይገባል የሚል አቋም ያለዉ ሞዳል ነው።ይህ ሞዳል በዉጤታማነት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ እና ለወደፉትም የወንጀል አፈጻጸም ምጣኔ እንዱቀንስ የማህበረሰብ እድገት (social development) የሚያመጡ ሥራዎችን በተለይም በሕጻንነት የዔድሜ ጊዜ (Early childhood) ለዚህ የሚያግዙ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ በዚህ ሞዳል ዙሪያ የተጻፈት የሕግ ድርሳናት ያሳያለ።
ከላይ ስለወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ሞዳልች ጽንሰ ሀሳባ በአጭሩ የተመለከትነዉን ከግምት በማስገባት የእኛ አገር የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ሞዳል ምን እንደሚመስል መርምረናል።
በኢፋዱሪ ሕገ መንግስት ስለተያዙ እና ስለተከሰሱ ሰዎች መብቶች፣በጥበቃ ስር ያለና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት፣የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ፣በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት ስለሚከለክል…ወዘተ መርሆዎች ከአንቀጽ 19-23 ድረስ በዝርዝር ተደንግጓል።በዚህ መልኩ በሕገ መንግስቱ እውቅና ከተሰጣቸው መብቶችና መርሆዎች ውስጥ በአንቀጽ 20 ስር የተደነገገውን የተከሰሱ ሰዎችን መብት ያየን እንደሆነ የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችልት የመሰማት መብት እንዲላቸው፣በፍርድ ሂደት ባለበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፊተኛ ያለመቆጠር፣ ክሱ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዱነገራቸው እና ክሱን በጽሁፍ የማግኘት መብት እንዲላቸው፣ የቀረቡባቸውን ማናቸዉንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት እንዲላቸው፣በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል እና የፍርደ ሂደት በሚገባቸው ቋንቋ እንዱተረጎምላቸው የመጠየቅ መብት እንዲላቸው ተደንግጓል።እነዚህ የተከሰሱ ሰዎች መብቶች ተከሳሽ በላለበት በሚታይ የፍርድ ሂደት ጭምር ክሱን በሚያቀርበው ዐቃቤ ሕግ እና መብቱን በሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት ላይ እንደ ግዳታ የሚቆጠር ቢሆንም እነዚህ መብቶች በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለት ተከሳሹ በፍርድ ቤት ቀርቦ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል በመሆኑ ሕገ መንግስቱ ተከሳሽ ባለበት የፍርድ ሂደቱ እንደሚከናወን በማሰብ እንደደነገጋቸዉ የሚቆጠሩ ናቸዉ። ይህም ተከሳሽ ባለበትም ሆነ ተከሳሽ በላለበት በሚታይ የፍርድ ሂደት የተከሰሱ ሰዎች መብቶች እንዱከበሩ ሕገ መንግስቱ እንደሚፈልግ ማሳያ ነው። ከዚህ በመነሳት ሕገ መንግስቱ በአብዛኛዉ ፍትሐዊ ሂደት የመከተል ሞዳል (The Due Process Model) በሚል ለሚታወቀው የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ሞዳል ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጥ የሚያስገነዝብ ነው።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በተቀበለችው ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ቃልኪዲን አንቀጽ 14 ላይም የተከሰሱ ሰዎች ተመሳሳይ መብቶች እንዲላቸው ተደንግጓል።በተለይ በዚህ ቃል ኪዲን አንቀጽ 14(3/መ) ላይ ተከሳሹ በአካል ችልት ቀርቦ ራሱን የመከላከል (የመዲኘት) መብት እንዲለው በግልጽ ተደንግጓል። በዚህ አግባብ በተጠቃሹ ቃል ኪዲን የተደነገገው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9/4 እና 13/2 ስር በተደነገገው መሰረት የአገራችን የሕግ አካል ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ በሕገ መንግስቱ እና በተዋረድ ባለ ሕግጋት ስለተከሰሱ ሰዎች መብቶች የተደነገገው በዚህ ቃል ኪዲን ከተደነገገው ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ሉተረጎም እና/ወይም ተግባራዊ ላደረግ ይገባል።
በ2003ዓ/ም ወጥቶ ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘዉን የኢፋዱሪ የወንጀል ፍትሕ ፕሉሲ የተመለከትን እንደሆነ በፕሉሲው ተራ ቁጥር 3.2 ላይ እንደተመለከተዉ ሕብረተሰቡ የወንጀል ሕጉን ከማስፈጸም አኳያ የወንጀል ድርጊቶችን ሪፕርት በማድረግ እና በተለያየ ደረጃ በወንጀል ምርመራ እና በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ውስጥ የሚሰሩ ሥራዎችን በማገዝ እንዱሳተፍ ማድረግ፤ ቁጥር 3.3 ላይ እንደተመለከተው የመርማሪ ፕሉሶችንና የዐቃቤያነ ሕግን የሙያ ዔውቀታቸውን፣ ክህልታቸውንና የሥነ ምግባር ደረጃቸውን እንዱያሳድጉ እና የዘመናዊ ቴክኖልጂ አጠቃቀማቸውን የሚያሳድጉ ሥራዎችን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መስራት፤በቁጥር 3.4 ላይ እንደተገለጸው የወንጀል ምርመራ ዓላማ በአጠቃላይ ስለ ወንጀል የማወቅ ፣ወንጀል እንዲይፈጸም የማስቆም፣ወንጀል ከተፈጸመ ጉዲቶችን የመቀነስ፣ የወንጀል ዑላማ የሆኑትን ሰዎች፣ንብረቶች ወይም ጥቅሞችን የመከላከል፣ወንጀል ፈጻሚዎችን ለሕግ የማቅረብ እና የወንጀል ተጎጂዎችን መብቶችና ጥቅሞችን የማስከበር ነው።
ውጤታማና ቀልጣፊ የወንጀል ምርመራ ሥራን በማከናወን የሕዝብ ጥቅም፣በወንጀል ድርጊት የተጎደ ሰዎች እና የተጠርጣሪዎች መብት እንዱጠበቅ ማድረግ እንዱቻል የወንጀል ምርማሪ የምርመራ ሥራውን ከዐቃቤ ሕግ ጋር ሉያከናውን እንደሚገባ በፕሉሲው ቁጥር 3.6 ላይ መገለጹ፤ በቁጥር 3.9 ላይ እንደተገለጸው በቀላል እስራት ወይም በሕጉ መሰረት በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ እና በግለሰብ ላይ የተፈጸሙ ወንጀልች በተበዲዩ እና በተጠርጣሪው መካከል እርቅ ከተፈጸመ ወንጀል ምርመራው ወይም የተመሰረተው ክስ እንዱቋረጥ ላደረግ እንደሚችል፤ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪውን ጥፊተኛ ለማሰኘት የሚያስችል በቂ የሆነ ማስረጃ የላለ መሆኑን የተረዲው እንደሆነ እና ተጠርጣሪው በላለበት ክሱ ላታይ የማይችል እንደሆነ…ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ አይመሰረትም በማለት መወሰን እንደሚችል በቁጥር 3.11 ላይ መገለጹ፤ የክስና የፍርድ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ ተከሳሹ ተገቢ ለሆነ አጭር ጊዜ በማረፉያ ቤት እንዱቆይ ላደረግ እንደሚችል እንዱሁም በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ ከምርመራ ወይም ከፍርድ ሂደት መጠናቀቅ ጋር በተያየዘ በእስር ላይ የሚቆዩ ተጠርጣሪዎችን ወይም ተከሳሾችን ቁጥር ለመቀነስ እንዱቻል የምርመራ ወይም የፍርድ ሂደት የሚቀላጠፍበትን ሁኔታዎች ከማመቻቸት በተጨማሪ ከእስር ውጭ ያለ ላልች አማራጮችን በሥራ ላይ ለማዋል የሚቻልባቸውን መንገድች በጥናት በመለየት ተግባራዊ ማድረግ በቁጥር 3.16.2 ስር መገለጹ፤ የምስክሮች አለመገኘትና የማስረጃ መጥፊት ምክንያት የሚፈጠረውን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ አለመሆን ለማስቀረት…ተጠርጣሪዎች ቀደም ብለው ጥፊተኝነታቸውን እንዱያምኑ ማበረታታትና የጥፊተኝነት ድርድር የሚካሄድበትን የሕግ ማዔቀፍ እንዱኖር ማድረግ፣የወንጀል ጉዲዮች ክርክር በመደበኛ የፍርድ ሂደት ዉስጥ በማለፊቸው ምክንያት በተጎጂዎች፣በምስክሮችና በተከሳሾች ሥነ ልቦና ላይ ሉደርሱ የሚችለ ጉዲቶችን ለማስቀረት የሚያስችል የጥፊተኝነት ድርድር ማድረግና ተከሳሹ ለፈጸመው ጥፊት በራሱ ነጻ ፍቃድ ኃላፉነት ወስድ ባደረገው ድርጊት ተጸጽቶ በመታረም ለወደፉቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዱኖር ማድረግ እንደሚቻል በቁጥር 4.1.፣4.5.4 ላይ መስፈሩ፤
እንዱሁም በወንጀል ጉዲይ ላይ የሚሰጡ አላስፈላጊ ቀጠሮዎችን ለመቀነስና የፍርድ ሂደቱን ቀልጣፊና ውጤታማ ለማድረግ …መርማሪዎች እና ዐቃቤያነ ሕግ ከፍርድ ቤት በሚሰጥ መጥሪያ መሰረት ተከሳሽን እና ምስክሮችን በችልት የማቅረብ ኃላፉነት ያለባቸው ስለመሆኑ በፕሉሲው ቁጥር 4.3.2 ስር መገለጹ፤ ተጠርጣሪውን ጥፊተኛ ሉያሰኝ የሚችል ማስረጃ ቢኖርም ጉዲዩ በአማራጭ የመፍትሄ እርምጃ መታየቱ የሕዝብን ጥቅምና የተጎጂውን መብቶች በተሻለ የሚያስጠብቅ ከሆነ በተጠርጣሪና በግል ተበዲይ መካከል የተፈጠረውን የወንጀል ምክንያት…ከፍርድ ሂደት ውጭ ባለ አማራጭ ዘዳዎች ተጠርጣሪው/ተከሳሹ በራሱ ፈቃድ ኃላፉነት እንዱወስድ በማድረግ፣ የግል ተበዲዩንና ወንጀል አድራጊውን በማስታረቅ እንዱሁም ተጠርጣሪው ለግል ተበዲዩ ካሳ እንዱከፍል በማድረግ ዘላቂ መፍትሓ እንዱገኝ ማድረግ፣ በተጨማሪም በወንጀለ ጉዲት የደረሰበት ማንኛውም ሰው በጉዲዩ ላይ በሚደረገው የምርመራ ፣የክስ አቀራረብ እና የፍርድ ሂደት ውስጥ ተሳትፍ እንዱያደርግ፣ጉዲዩ የደረሰበትን ደረጃ በቅርብ የመከታተል እና ስለሚሰጡት ውሳኔዎች ተገቢውን መረጃ የማግኘት…መብት እንዲለው በቁጥር 4.6.2. እና 6.2.1 ተገልጿል። በምርመራም ሆነ በክስና በክርክር ሂደት ልዩ ትኩረት የሚሰጥባቸው የወንጀል ጉዲዮች በተመለከተም በፕሉሲው ቁጥር 3.15 ላይ በሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ላይ ጉዲት ሉያስከትለ የሚችለ በሕገ መንግስትና በሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ እንደሽብርተኝነት፣ የሀገር ክህደት፣ከባድ የሰው ግድያ…የመሳሰለት ከባድ ወንጀልች ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸው ከባድ ወንጀልች እንደሆኑ ተመልክቷል።
ከዚህ በላይ በዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ፍትሕ ፕሉሲው ይዘት ከፍ ሲል የተጠቀሱትን አራቱንም የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ሞዳልችን ከግምት ያስገባ የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ተግባራዊ ማድረጉንና በሚወጡ ሕጎችም እነዚሁ ሞዳልችን ታሳቢ ያደረገ የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ተግባራዊ እንዱደረግ ፍላጎቱ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
እንዱሁም በወንጀል ሕግ አንቀጽ 1 ስር የተደነገገውን የወንጀል ሕጉን ዓላማና ግብ የተመለከትን እንደሆነ የወንጀል ሕጉ ዓላማ የአገሪቱን መንግስት፣ የሕዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት መብትና ጥቅም ማረጋገጥ ነው። ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በሚያስችል መልኩ ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ወንጀልን መከላከል፣አጥፉዎች በመቅጣት በማረም ወንጀል ከመፈጸም እንዱቆጠቡ በማድረግ እና ላልችን የማስተማር ግብ መያዙ ወንጀል የመቆጣጠር ሞዳል(The Crime Control Model) ለሚባለው የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት ሞዳል ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል።በልላ በኩል በሕጉ የመጀመሪያ ታላቅ ክፍል ስለሕጋዊነት መርህ የተደነገገው፣በሕግ ፉት እኩል ስለመሆን፣የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ፣ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትን የተሻለውን ሕግ ተፈጻሚ ስለማድረግ፣ስለይርጋ ጊዜ አፈጻጸም ደንቦች የደነገገው፣በተሻረው ሕግ መሰረት የተሰጡ ፍርድች አፈጻጸም …ወዘተ የሚመለከቱ መርሆዎች እና ስለቅጣት ማቅለያዎችና ማክበጃ ምክንያቶችና አፈጻጸማቸው እንዱሁም በሕግ በግልጽ ሲፈቀድ ፍርድ ቤት በመሰለው ቅጣት የሚያቀልበትን አግባብ መደንገጉ የወንጀል ሕጉ ፍትሐዊ ሂደት የመከተል ሞዳል (The Due Process Model) ጭምር የተንጸባረቀበት ሕግ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም በወንጀል ሕጉ በወንጀል ክስ አቅራቢነት ከሚያስከስሱ ወንጀልች በተጨማሪ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ስለሚያስቀጡ ወንጀልች (offence is punishable upon complaint) መደንገጉ በወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት የግል ተበዲይን(የተጎጂን) ተሳትፍ ማረጋገጡንና የተጎጂዎችን መብቶች ማዔከል ያደረገ የአስቀጭነት ሞዳል (The Punitive Model of Victims' Rights) ያካተተ ሕግ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
በተጨማሪም የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3/መ) ስር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥፊተኝነት ድርድር እንዱወስን፣ድርድር እንዱደረግ፣አማራጭ የመፍትሓ እርምጃ እንዱወሰድ መወሰን እንዱችል ከተሰጠው ሥልጣን መገንዘብ የሚቻለው በሕጉ የተንጸባረቀው ወንጀል የመቆጣጠር ሞዳል መከተል ብቻ ሳይሆን ቅጣትን ማዔከል ከማድረግ ይልቅ የወንጀል ተጎጂዎችን መብት በጠበቀ አኳኋንና በወንጀለ ምክንያት የተፈጠረውን ማንኛውም ጉዲት እና አለመግባባት ፣መፍታት/ማከም፣መካስ እና ከጉዲቱ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ የሚያደርስ አማራጭ ፍትህ የማግኛ መንገድችን የሚመለከተውን ሞዳል (The Non-Punitive Model of Victims' Rights) ጭምር መከተል እንዱቻል እድል የሚሰጥ የወንጀል ፍትህ አስተዲደር ሂደት መከተል እንደሚቻል መደንገጉን የሚያሳይ ሕግ ነው። በተጨማሪም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6/8 ስር ስለሰብዓዊ መብት በተመለከተ የተደነገገውም በወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት የምንከተለው ሞዳል ወንጀል የመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ፣አከበበርና ማሟላት ጋር በተያያዘም ሕጉ ትኩረት መስጠቱን ስለሚያመላክት ፍትሐዊ ሑደት የመከተል ሞዳል በሕጉ መንጸባረቁን የሚያሳይ ነው።
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉን የተመለከትን እንደሆነ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ስለሚያዝበት፣ ስለብርበራ፣የተያዘ ሰው ፍርድ ቤት መቅረብ ስላለበት ጊዜ እና ሁኔታ፣በወንጀል ምርመራ ወቅት ቃለን ለመስጠት ያለመገደድና ዝም የማለት መብት ያለው ስለመሆኑ፣የተያዘው ሰው ለምርመራ ዓላማ ተጨማሪ ጊዜ በእስር ላይ የሚቆየው በፍርድ ቤት ፈቃድ መሆኑ፣በዋስትና ወረቀት የመለቀቀ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ሲከሰስም ስለወንጀለ አፈጻጸም በቂ ዝርዝር ከያዘ የክስ ማመልከቻ ጋር መጥሪያ ደርሶት ችልት ቀርቦ በግልጽ ችልት የመዲኘት፣ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የመመርመር፣ አለኝ የሚለውን መከላከያ ማስረጃ አቅርቦ ራሱን የመከላከልና የመሰማት መብት እንዲለው በተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ መደንገጉ የተከሰሰ ሰው መብት የተጠበቀበትን ወንጀል የመቆጣጠር ሂደትን ማዔከል ያደረገ ወንጀል የመቆጣጠር እና ፍትሐዊ ሂደት የመከተል የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ሞዳልችን አጣምሮ የያዘ ሕግ መሆኑን የሚያስገነዝቡ ድንጋጌዎችን የያዘ ሕግ መሆኑን የሚያሳይ ነው።ሥነ ሥርዓት ሕጉ በዚህ መልኩ ከያዛቸው ድንጋጌዎች መካከል የተከሰሰ ሰው በላለበት ክሱ ስለሚሰማበት ሥርዓት በተመለከት በቁጥር 161 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተዘረጋው ሥነ ሥርዓት ይገኝበታል።
ከተያዘው ጉዲይ ጋር በተያያዘ ተፈጻሚነት ያለው የተከሰሰ ሰው በላለበት ነገሩ ስለሚሰማበት ሥነ ሥርዓት የሚደነግገው የወ/መ/ሥ/ሥሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) እንደሚከተለው ይነበባል፡- ‛ (2) …ከዚህ በታች በተመለከቱት ወንጀልች ካልሆነ በቀር ተከሳሹ በላለበት የወንጀል ክስ አይሰማም።(ሀ) ከአሥራ ሁለት ዓመት በታች በማያንስ ጽኑ እስራት የማያሳስር ወንጀል የሰራ … ሲሆን ነው።“ የሚል ሲሆን የዚህ ድንጋጌ የእንግሉዝኛ ቅጅ ደግሞ “(2) No accused person may be tried in his absence … unless he is charged with: (a) an offence punishable with rigorous imprisonment for not less than twelve years.”የሚል ይዘት ያለዉ ነዉ።
ከሕግ አተረጓጎም ጽንሰ ሀሳብ መገንዘብ እንደሚቻለው የተለያዩ የአተረጓጎም ስልቶችንና መርሆዎችን በመጠቀም አንድ ሕግ ወይም የሕግ ድንጋጌ ሉተረጎም የሚገባው ሕጉ ወይም የሕጉ ድንጋጌ አሻሚ፣ ግልጽነት የጎደለው፣አንደ ድንጋጌ ከላላው ጋር የሚጣረስ ሲሆንና የሕግ አውጪውን ሀሳብ በግልጽ የማያሳይ ሆኖ የሕግ አውጪውን ሀሳብ ለማግኘትና በሚተረጎመው ሕግ ወይም ድንጋጌ ለማሳካት የታቀደው ዓላማ ከግብ እንዱደርስ ለማድረግ ሕጉን/ድንጋጌውን መተርጎም የግድ የሚል ከሆነ ብቻ ነው። ከዚህ የምንገነዘበው ሕጉ/የሕጉ ድንጋጌ ግልጽ በሆነ ጊዜ በቀጥታ ተግባራዊ እንዱሆን ከማድረግ ባለፈ ትርጉም እንደማያስፈልገው ነው።
በመሰረቱ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20፣ በሲቪልና ፕለቲካ መብቶች ቃል ኪዲን አንቀጽ 14(3/መ) ፣በኢፋዱሪ የወንጀል ፍትሕ ፕሉሲ ላይ እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161 ስር ከተደነገገው መረዲት እንደሚቻለው በመርህ ደረጃ የወንጀል ክስ ተከሳሹ በላለበት አይሰማም። የዚህ መርህ ልዩ ሁኔታ ከላይ ይዘቱ የተጠቀሰው የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) እና በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ፉደል (ለ) ስር በመንግስት ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልች ሆነው በጽኑ እስራት ወይም ከብር 5,000.00 በላይ በሚያስቀጡ ከባድ ወንጀልች የተከሰሰ እንደሆነ በሚል የተገለጸው ነው። ይህም ሲባል በልላ ልዩ ሕግ ላይ በተለየ ሁኔታ የተደነገገው እንደጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። ከዚህ መረዲት የሚቻለው በወንጀል ፍትሕ ፕሉሲው እና በላልች ሕጎቻችን የመንግስትን፣እና የአገሪቱን ሕዝቦች ጥቅም እና የተጎጂዎችን መብት ለመጠበቅ በተለያየ መንገድ ያንጸባረቁት አቋሞች እንደተጠበቁ ሆነው ይህ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) የተከሰሱ ሰዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ ወንጀልን የመቆጣጠር ቅይጥ ሞዳልች የሚከተል የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት እንዲለን ማሳያ ላሆን የሚችል ድንጋጌ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም ምንም እንኳን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ሕገ መንግስቱን እና የወንጀል ፍትሕ ፕሉሲውን ቀድሞ የወጣና ከግማሽ ምዔተ ዓመት በላይ እድሜ ያለው ቢሆንም የሥነ ሥርዓት ሕጉ የተከሰሱ ሰዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ ወንጀልን የመቆጣጠር ቅይጥ ሞዳል ነጸብራቅ የሆኑ ድንጋጌዎችን በመያዝ የወጣ ነው በሚያስብል መልኩ አብዛኛዎቹ ወንጀልች የተከሰሱ ሰዎች በአካል በተገኙበት ተሰምቶ እንዱወሰን መፈለጉን እና ለተከሳሾች የመሰማትና ራስን የመከላከል መብት እዉቅና ከመስጠቱም ባሻገር ለተከሰሱ ሰዎች መብት ከፍተኛ ጥበቃ ማድረጉን ከዚህ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) ይዘት፣መንፈስና ዓለማ መገንዘብ ይቻላል።
ሕግ አውጪው የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ)ን በመደንገግ አቋም ሲወስድ ተከሳሽ በላለበት የሚታዩ የወንጀል ክሶች ማለትም በወንጀል ሕጉ(በ1949 በወጣዉ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ) መነሻ ቅጣታቸው በአስራ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ በሆነ ጽኑ እስራት የሚያስቀጡ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ውስን መሆናቸውን እና አብዛኞቹ የወንጀል ክሶች ተከሳሽ ባለበት ብቻ የሚታዩ እንደሆኑ እያወቀ ነው። ሕግ አውጪው እንዱህ አይነት አቋም የያዘው ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የሚከሰሱ ሰዎች ከፍርድ ሂደት ተሰዉረዉ የወንጀለ ተጎጂዎች ፍትህ የማግኘት መብት እንደማይጣስ ብልም የወንጀል ሕጉ ዓላማ ከግብ ሳይደርስ ቀርቶ ጠቅላላዉ ሕብረተሰብ ተገጂ እንዲይሆን ማድረግ እንደሚቻል በማመን ነው። ይህም እምነቱ እውን እንዱሆን ፕሉስ እና ላልች በሕግ ሥልጣን የተሰጣቸው ሕግ አስፈጻሚዎች የተከሰሰውን ሰው በአድራሻው ፈልገው መጥሪያ እንዱደርሰው ማድረግ እንደሚችለ እና ተከሳሹ መጥሪያ ደርሶትም ሆነ መጥሪያ ላለመቀበል ብል በመሰወሩ ምክንያት መጥሪያ ማድረስ ካልተቻለ ወይም በልላ በቂ ባልሆነ ምክንያት ተከሳሹ ፍርድ ቤት ካልቀረበ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ተይዞ እንዱቀርብ ተገቢውን ትእዛዝ እንደሚሰጥና ፕሉስ ብርቱ ጥረት አድርጎ ተከሳሹን ካለበት ፈልጎ ችልት እንዱያቀርበው ከፍተኛ ኃላፉነት በፕሉስና በላልች ሕግ አስፈጻሚ አካላት ላይ መጣለን ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 160 እና 161(1 እና 2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል።
ከላይ ይዘቱ የተጠቀሰዉ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ)ድንጋጌ ለብቻዉ ሲታይ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በላለበት ክሱ ሉሰማ የሚችለው የተከሰሰበት ወንጀል ከአስራ ሁለት ዓመት በማያንስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ (offence punishable with rigorous imprisonment for not less than twelve years) ሲሆን ብቻ ነው የሚል ግልጽ ይዘት ያለው ድንጋጌ በመሆኑ ትርጉም ሳያስፈልገው በቀጥታ ተግባራዊ ላሆን የሚገባው ነው። ይህ ድንጋጌ ትርጉም የሚሻዉ ተከሳሹ የተከሰሰበት ወንጀል የሚያስቀጣው የጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት ከአስራ ሁለት ዓመት በታች ሆኖ የጽኑ እስራት ጣሪያ ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት በላይ በሆነ የእስራት ቅጣት የሚያስቀጣ ሆኖ በተደነገገ ጊዜ ነው። እንዱህ አይነት ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) ተከሳሹ የተከሰሰበት የወንጀል ሕግ ድንጋጌ ከሚያስቀጣዉ ድንጋጌ ጋር ተገናዝቦ ከላይ በዝርዝር እንደተመለከትነው በሕጎቻችንና በወንጀል ፍትህ ፕሉስ ስለምንከተለው የወንጀል ፍትሕ አስተዲደር ሂደት ሞዳልች የተንጸባረቀውን እና የተከሰሱ ሰዎችን መብት ባገናዘበ መልኩ ሉተረጎም ይገባል።እንዱሁም ተከሳሽ በላለበት ክስ መስማት(የፍርድ ሂደት ማከናወን) ከላይ እንደገለጽነው ልዩ የሥነ ሥርዓት ሁኔታ(ድንጋጌ) በመሆኑ በሕግ አተረጓጎም ጽንሰ ሀሳብ/መርህ መሰረት በጠባቡ መተርጎም እንዲለበት ከግንዛቤ ማስገባት ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በተጠሪ ላይ የወንጀል ክስ የመሰረተው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1 እና 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተራ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ሙከራ ፈጽማለች በሚል በመሆኑ ይህ ድንጋጌ የሚያስቀጣው ከአምስት ዓመት እስከ ሃያ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ነው።የዚህ ድንጋጌ መነሻ ቅጣት ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት የሚያንስ በመሆኑ የተነሳ በተያዘው ጉዲይ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ)ን መተርጎም ያስፈልጋል። ተጠሪ በክሱ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሟ በዐቃቤ ማስረጃ ቢረጋገጥና ተጠሪ በማስተባበል መከላከል አለመቻሎ ተረጋግጦ ጥፊተኛ ብትባል ልትቀጣ የምትችለው በሕጉ አንቀጽ 540 ስር በተደነገገው እና በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ አስራ ሁለት ስር በተመለከተው ደረጃና እርከን መሰረት ነው።
በመመሪያው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 540 ለተደነገገው የእስራት ቅጣት 6 ደረጃዎች የወጣለት ሲሆን የደረጃ 1 መነሻ እርከን እርከን 21 ሲሆን ደረጃ 6 ደግሞ መነሻ ቅጣቱ እርከን 33 ላይ እንዱሆን የተደረገ ነው። በዚህ መልኩ ከወጡት 6 ደረጃዎች መካከል ሁለቱ ደረጃዎች ማለትም በደረጃ 5 እና 6 ስር የተመደበው የእስራት መነሻ ቅጣት ብቻ ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ሲሆን ቀሪዎች 4 ደረጃዎች ከአስራ ሁለት ዓመት በአነሰ ጽኑ እስራት የሚያስቀጡ መነሻ እርከኖች የያዙ ናቸው። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪ በተከሰሰችበት ወንጀል ጥፊተኛ ብትባል በአብዛኛው ልትቀጣ የምትችለው ከአስራ ሁለት ዓመት ባነሰ ጽኑ እስራት ላሆን የሚችልበት ዔድል ሰፉ መሆኑን ነው። ከዚህ በተጨማሪም ተጠሪ ፈጸመች ተብላ የተከሰሰችው ተራ የሆነ የግድያ ሙከራ ወንጀል በመሆኑ ተራ በሆነ ግድያ ሙከራ ጥፊተኛ ብትሆን ፍርድ ቤቱ ከነገሩ ሁኔታዎች በመነሳት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 540 ስር ከተደነገገው አምስት ዓመት ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት ዝቅ ብል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 179/ሐ ስር በተደነገገው መሰረት ቅጣት ሉወሰን የሚችልበት ተጨማሪ እድል በመኖሩ ይህም ተጠሪ ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት በአነሰ ልትቀጣ እንደምትችል የሚያስገነዝብ ነው።
ሲጠቃለል በተከሳሽ ላይ በቀረበው የወንጀል ክስ የተጠቀሰው ድንጋጌ የሚያስቀጣው መነሻ ቅጣት ከአስራ ሁለት ዓመት ባነሰ ጽኑ እስራት ሆኖ የድንጋጌው ጣሪያ ደግሞ ከአስራ ሁለት ዓመት በላይ ከሆነና ተከሳሹ ጥፊተኛ ሆኖ ሲገኝ ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት ያነሰ ሉቀጣ የሚችልበት አጋጣሚ ሰፉ ከሆነ ተከሳሹ በላለበት ክርክሩ ሉሰማ አይገባም። አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረተው የወንጀል ክስ ተጠሪ ጥፊተኛ ሆና ከተገኘች ከአስራ ሁለት ዓመት ጽኑ እስራት ያነሰ ቅጣት ሉወሰንባት የሚችልበት ዔድል ሰፉ መሆኑን ተገንዝበናል።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የተከሰሰችበትን ድንጋጌ እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 161(2/ሀ) ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ የፍርድ ሂደቱ ተጠሪ በላለችበት ላታይ የሚችል አይደለም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በሰጠው ትእዛዝም ሆነ በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት አመልካች ያቀረበውን ይግባኝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በትእዛዝ በመሰረዙ የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/07/2014ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 10/09/2014ዓ/ም ትዕዛዝ በሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/1 መሰረት ጸንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።ሲጠይቁ ለግራ ቀኙም ይሰጣቸው።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።