ሰራተኛ በህመም ምክንያት ለአሰሪው ማሳወቅ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር አሰሪውን በማሳወቅ እና በመንግስት እውቅና ካለው የህክምና ተቋም የህክምና ፈቃድ በማቅረብ እረፍት የማግኘት መብት ያለው ሲሆን ሰራተኛ ለአሰሪው የሀኪም ፍቃድ ሳያቀርብ በህመም ምክንያት ፍቃድ ሲጠይቅ አሰሪው የስራው ሁኔታ አይፈቅድም በሚል ፍቃደኛ ሳይሆን ከቀረ ሰራተኛው በህግ አግባብ መብቱን ከሚያስከብር በስተቀር አሰሪው ፍቃድ እየከለከለው ሰራተኛው በራሱ ፍቃድ ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ እንደመቅረት የሚያስቆጥርና አሰሪው የስራ ውል ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፕርት ሀላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አቶ የበጋ እሸት ወልደጻዱቅ የሚያስችለው ምክንያት/ጥፊት ስለመሆኑ አሰሪ እና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/1/ለ
No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፕርት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነ/ፈ ይፈሩሀል ሙጬ - ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ የበጋ እሸት ወልደጻዱቅ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የተለያዩ ክፍያዎች ለማስከፈል የቀረበ የአሰሪ እና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ በህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ አመልካች ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም.
የተጠሪን የስራ ውል ካቋረጠ በኋላ የ15 ቀን ደመወዝ በመቅጣት ወደ ስራ እንድመለስ በማድረግ ያለአግባብ ላገኝ የሚገባኝን ክፍያ ስላሳጣኝ የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፤ የካሳ እና የአገልግልት ክፍያ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካችም ህዲር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የይርጋ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ተጠሪ በተደጋጋሚ በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ጥሪ ተደርጎላቸው ስላልቀረቡ በገንዘብ ተቀጥተው ከታለፈ በኋላ በድጋሚ በስራ ላይ ባለመገኘታቸው የስራ ውላቸው እንዱቋረጥ መደረጉ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል የተጠሪን የክፍያ ጥያቄ በከፉል ውድቅ በማድረግ ስንብቱ ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው እና በይርጋ በማይታገደ ክፍያዎች ላይ ክርክሩ እንዱቀጥል ብይን ሰጥቷል።
በመቀጠልም የፍሬ ነገር ክርክሩን መርምሮ ስንብቱ ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙት በህመም ምክንያት መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ለአመልካች በማሳወቅ ፍቃድ ያላገኙ በመሆኑ ከስራ የቀሩት በበቂ ምክንያት ነው ለማለት ስለማይቻል ስንብቱ ህጋዊ ነው። ስንብቱ ህጋዊ ሆኖ እያለ አመልካች ተጠሪን ካሰናበተ በኋላ ስንብቱን በመተው ደመወዝ በመቅጣት ወደ ስራ እንዱመለሱ ማድረጉ የስራ ዋስትናን የሚያስጠብቅ እንጂ ተጠሪ ማግኘት የሚችለትን ክፍያ ለማሳጣት አይደለም። በመሆኑም ተጠሪ የስንብት እና የካሳ ክፍያ ሉከፈላቸው አይገባም። የአመት እረፍት የ57 ቀን ብቻ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ይከፈላቸው። የፔሮቪደንት ፈንድ በተጠሪ ስም የተቀመጠ ካለም ተጠሪ ክሉራንስ አዙረው ሲጨርሱ ይከፈላቸው በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪ ለ17 ዓመት ሲያገለግለ 269 ቀናት የአመት እረፍት ነበራቸው። ተጠሪ የህክምና ፍቃድ ጨርሰው የአመት እረፍት ሲጠይቁ አመልካች ፍቃድ ከልክሎቸዋል። አመልካች የአመት እረፍት የጠየቀን ሰራተኛ አመቻችቶ እረፍት ማስወጣት እያለበት የራሱን ጥቅም ብቻ በማየት ተጠሪ ከስራ እንዱሰናበቱ ማድረጉ ስንብቱን ህገ ወጥ ያደርገዋል። በመሆኑም አመልካች የስንብት፣ የካሳ፣ ክፍያ ለዘገየበት መቀጫ ሉከፍል ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አሻሽሎል።
አመልካች ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረበው ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ሲሆን ይዘቱም ተጠሪ የአመት እረፍት ጠይቀው ተፈቅድላቸው ከጨረሱ በኋላ ተጨማሪ ፍቃድ ሲጠይቁ የድርጅቱ የስራ ሁኔታ አመቺ ባለመሆኑ ተጨማሪ ፍቃድ በመከልከላቸው ከስራ በገዛ ፍቃዲቸው ለ28 ቀን ቀርተዋል። በዚህም ምክንያት የስራ ውል መቋረጡ ተገቢ ነው። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካሳ እና የመቀጫ ክፍያ እንዱከፈላቸው መወሰኑ እንዱሁም ተጠሪ የፔሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሆነው እያለ የስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ክፍያን በተመለከተ የሰጠው ውሳኔ ሉጣራ ይገባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በሐምል 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች ህመምተኛ መሆኔን እያወቀ የአመት እረፍት ስጠይቅ መከልከለ ተገቢ አይደለም። ህመም ላይ ስለነበርኩኝ በስራ ቦታ መገኘት አልቻልኩም። አመልካች በዚህ ምክንያት ከስራ ማሰናበቱ ስንብቱን ህገ ወጥ ስለሚያደርገው ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎችን መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች በበኩለ መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የተጠሪ ስንብት ህገ ወጥ ነው የተባለበትን አግባብ እና ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ከተባለ ለተጠሪ የስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው የመወሰኑን አግባብነት ከግራ ቀኙ ክርክር፤ በማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
በመጀመሪያም የተጠሪ የስራ ስንብት ህገ ወጥ ነው የመባለን ተገቢነት ስንመለከት ተጠሪ ያልተጠቀሙበት የአመት እረፍት 259 ቀን እንዲላቸው፤ ተጠሪ በህመም ምክንያት የአመት እረፍት ሲጠይቁ የድርጅቱ የስራ ሁኔታ አይፈቅድም በሚል አመልካች ፍቃድ መከልከለን፤ ተጠሪ እረፍት በአመልካች ሳይፈቀድላቸው ለ28 ቀን በስራ ላይ ያልተገኙ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት አመልካች የስራ ውል ማቋረጡ በግራ ቀኙ የታመነ ፍሬ ነገር ነው። ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ተጠሪ በህመም ምክንያት ከአመልካች ፍቃድ ሳያገኙ ከስራ መቅረት ይችላለ ወይስ አይችለም? የሚለው ነጥብ ነው።
በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 85 ሰራተኛው በህመም ምክንያት ለአሰሪው ማሳወቅ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር አሰሪውን በማሳወቅ እና በመንግስት እውቅና ካለው የህክምና ተቋም የህክምና ፈቃድ በማቅረብ እረፍት የማግኘት መብት እንዲለው ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ የህመም ፍቃድ ማግኘት ለሰራተኛው በህግ የተጠበቀ መብት መሆኑን፤ መብቱን ለመጠቀም ግን በቅድሚያ አሰሪውን የማሳወቅ እና የህክምና ፈቃድ የማቅረብ ግዳታ እንዲለበት ያመለክታል። በልላ አባባል ህመም ከስራ ለመቅረት በቂ ምክንያት ላሆን የሚችለው አሰሪው ስለሰራተኛው ህመም በተቻለ ፍጥነት እንዱያውቅ በማድረግ እና ሰራተኛው ለአሰሪው የህክምና ፈቃድ ማቅረብ ሲችል ብቻ ነው።
ሰራተኛው የህክምና ፍቃድ ቢኖረውም አሰሪውን በተቻለ ፍጥነት ማሳወቅ ያስፈለገበት ምክንያት ሰራተኛው ከስራ ሲቀር የሚፈጠረውን የሰራተኛ ክፍተት በመሸፈን ምርት እና ምርታማነቱ ላይ አለታዊ ተጽእኖ በአሰሪው ላይ እንዲይፈጠርበት ለማድረግ ነው። በመሆኑም ሰራተኛው ካቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር የማሳወቅ ግዳታውን በመወጣት እና የሀኪም ፍቃድ በማቅረብ የሚጠበቅበትን ሁኔታ ሳያሟላ በህመም ምክንያት ቢሆንም እንኳን ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ከስራ ቢቀር በበቂ ምክንያት ከስራ እንደቀረ ስለማይቆጠር በአዋጁ አንቀጽ 27/1/ለ መሰረት ከስራ የሚያሰናብት ጥፊት ይሆናል።
በልላ በኩል በህመም ላይ የሚገኝ ሰራተኛ የሀኪም ፍቃድ ማቅረብ ባይችል አሰሪው ከተስማማ የአመት ፍቃደን በመጠቀም ከስራ ለመቅረት እንደሚችል ከአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 76 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ነገር ግን በአዋጁ አንቀጽ 78/2 መሰረት ሰራተኛው የአመት ፍቃድ መውሰድ የሚችለው አሰሪው የስራውን ባህሪ ታሳቢ አድርጎ በሚያወጣው የእረፍት ድልድል መሰረት ስለሚሆን አሰሪው ካልተስማማ ሰራተኛው በፈለገ ጊዜ ወይም መታመሙን ለአሰሪው ስለገለጸ ብቻ የአመት ፍቃድ ሉያገኝ አይችልም። በእርግጥ አንድ ሰራተኛ የታወቀ ህመም ካለበት ህመሙ በተቀሰቀሰ ጊዜ የሀኪም ፍቃድ ባይኖረውም አሰሪው ለሰራተኛው የአመት ፍቃደን በመስጠት እንዱያርፍ ቢያደርግ በአሰሪ እና ሰራተኛ መካከል መልካም ግንኙነትን በማጠናከር የኢንደስትሪ ሰላም እና የሰራተኛውን ምርታማነት የሚጨምር እንደሚሆን ይታመናል። ነገር ግን ሰራተኛው ለአሰሪው የሀኪም ፍቃድ ሳያቀርብ በህመም ምክንያት ፍቃድ ሲጠይቀው አሰሪው የስራው ሁኔታ አይፈቅድም በሚል ፍቃደኛ ሳይሆን ከቀረ ሰራተኛው በህግ አግባብ መብቱን ከሚያስከብር በስተቀር አሰሪው ፍቃድ እየከለከለው ሰራተኛው በራሱ ፍቃድ ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ እንደመቅረት ያስቆጥራል። ይህም በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 27/1/ለ ላይ በተገለጸው አግባብ አሰሪው የሰራተኛውን የስራ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለው ምክንያት/ጥፊት ይሆናል ማለት ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ በህመም ምክንያት ከስራ መቅረታቸውን የገለጹ ቢሆንም ለቀሩበት 28 ቀናት የሀኪም ፈቃድ እንዲልነበራቸው ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሲሆን ተጠሪ የህክምና ፍቃድ አለኝ በሚልም ያቀረቡት ክርክር የለም።
እንደዚሁም ተጠሪ ካላቸው የአመት ፍቃድ ላይም እረፍት እንዱሰጣቸው አመልካችን ጠይቀው ተከልክለዋል። ተጠሪ የ17 ዓመት የተጠራቀመ 269 ቀን የአመት እረፍት እንዲላቸው ሲታይ አመልካች በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጁ አንቀጽ 76/2 መሰረት ተጠሪ የአመት ፍቃዲቸውን ተጠቅመው እንዱያርፈ የማመቻቸት ግዳታውን አለመወጣቱን ያሳያል። ይህ መሆኑ ግን ተጠሪ በህግ አግባብ መብታቸውን እንዱያስከብሩ ከሚያስችላቸው በስተቀር አመልካች ሳይስማማ በገዛ ፍቃዲቸው ለ28 ቀን ከስራ ለመቅረት በቂ እና ህጋዊ ምክንያት ሉሆናቸው አይችልም። በመሆኑም ተጠሪ በአመልካች የአመት ፍቃድ ሳይሰጣቸው ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ ለ28 ቀናት ከስራ መቅረታቸው በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 27/1/ለ መሰረት ለአመልካች የስራ ውል የማቋረጥ መብት የሚሰጠው በመሆኑ የተጠሪ ስራ ስንብት ህጋዊ ነው። ስንብቱ ህጋዊ ነው ከተባለ አመልካች ከስንብት ክፍያ አንጻር የሚያቀርበውን ቅሬታ መመርመሩ አስፈላጊ ባለመሆኑ ታልፎል።
ሲጠቃለል የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪ ስንብት ህጋዊ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ ህጉን የተከተለ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ሲቀርብለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ማጽናት ሲገባው መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ. የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በየካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም.
የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
ት እ ዛ ዝ በዚህ መዝገብ
No topics extracted.