ከሕግ-ዉጭ የሥራ ዉል ተቋርጦብኛል የሚል ሰራተኛ በአሰሪዉ የሥራ ዉለ ከሕግ አግባብ ዉጭ በሆነ አኳኋን እንደተቋረጠበት ማስረዲት የሚጠበቅበትና ሰራተኛው የሚሰራውን ስራ አሰሪው መቀበለን፣ ሥራን መስራት እንዲይቻል ወይም ሥራ መከልከልን በክርክር ማስረዲት አሰሪው ከሕግ አግባብ ዉጭ የሥራ ዉል አቋርጧል ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ ስላለመሆኑ አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 12(1-3) እና 32 (1/መ እና 2)
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 05 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ጋራንባ ቦትሉንግ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር- የጠበቃ ረዲት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ንጉሴ ፊሲል መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ነዉ። ተጠሪ በአመልካች ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ በአመልካች ድርጅት በከባድ መኪና አሽከርካሪነት የሥራ መደብ ላይ በወር ብር9900.00 ደመወዝ እየተከፈለኝ ከቀን 26/06/2012ዓ/ም ጀምሮ እየሰራሁ እያለሁ ለሥራ የሚሰጠኝ ነዲጅ በቂ ስላልሆነ በቂ ነዲጅ እንዱሰጠኝ ጥያቄ በማቅረቤ አመልካች የማሽከረክረዉን መኪና ለላላ ሹፋር በመስጠት የሥራ ዉላን አቋርጦብኛል። በመሆኑም ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ እንዱባልልኝና የሥንብት ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ቅጣት እና ያልተከፈለኝ የአንድ ወር ደመወዝ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠዉ መልስ አመልካች ላላ በርካታ ተሽከርካሪዎች ስላለኝ ተጠሪ ያነሱትን የነዲጅ ይጨመርልኝ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ላላ ተሽከርካሪ በመስጠት ለማሰራት ብፈልግም ተጠሪ ከቀን 18/10/2012ዓ/ም ጀምሮ በሥራ ገበታቸዉ ላይ አልተገኙም። በዚሁ ምክንያት ተጠሪ ከሥራ የቀሩበትን ምክንያት ይዘዉ እንዱቀርቡ ማስጠንቀቂያ ቢለጠፍም ተጠሪ ሉቀርቡ አልቻለም። በመሆኑም የሥራ ዉለን ተጠሪ በገዛ ፈቃዲቸዉ ያቋረጡ በመሆኑ እና የሰኔ ወር ደመወዝ ቀርበዉ ያልወሰደ በመሆኑ ክሳቸዉ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች መርምሮ በቀን 27/05/2013 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ነዲጅ ይጨመርልኝ ጥያቄ በማቅረባቸዉ ምክንያት አመልካች በቀን 09/10/2012ዓ/ም ተጠሪ የሚያሽከረክሩትን መኪና እንዱያስረክቡ ማድረጉን፤ተጠሪ በተደጋጋሚ ሥራ ይሰጠኝ እንዱሁም ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት ላቀረቡት ጥያቄ አመልካች መልስ ሳይሰጣቸዉ መቆየቱን ምስክሮች ከመሰከሩት መረዲት ተችሎል።የተጠሪ ጥያቄ ነዲጅ ያንሰኛል የሚል በመሆኑ አመልካች ጉዲዩን አጣርቶ መጨመር ወይም ባለዉ እንዱቀጥለ ማድረግ ሲገባዉ ወይም በመልሱ ላይ እንደገለጸዉ ላላ መኪና መቀየር ሲገባዉ መኪናዉን እንዱያሰረክቡ አድርጎ ሥራ በመከልከል የሥራ ዉል ማቋረጡን የተጠሪ ምስክሮች አስረድተዋል።የአመልካች ምስክሮች ቃል ይህንን የሚያስተባብል አይደለም።
በመሆኑም አመልካች ሥራ በመከልከል የሥራ ዉለን በማቋረጡ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ።ስለሆነም የስንብት ክፍያ ብር 3300.00፣ካሳ ብር 59,400.00፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ብር 9900.00፣ ያልተከፈለ ደመወዝ ብር 9900.00 እንዱሁም ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት ብር 9900.00 አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 23/07/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞበታል።
አመልካች በቀን 28/07/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ፡-ተጠሪ ከቀን 18/10/2012 ዓ/ም ጀምሮ በሥራ ገበታቸዉ ላይ አልተገኙም።በማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎላቸዉም ሉገኙ አልቻለም።ይህንን የሚያረጋግጥ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦለት እያለ የሥር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1/ለ) መሰረት የተቋረጠዉን የሥራ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጧል በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም ተጠሪ እንኳን በክርክራቸዉ ላይ ያላነሱትን ተጠሪ ሥራ ተከልክለዋል በሚል ምክንያት ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም።ይህ ፍሬ ነገ ሀሰት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሰራተኛ ከሥራ እስካልተሰናበተ ድረስ ሥራ ወይም ደመወዝ ተከልክያለሁ ቢል እንኳን ደመወዝ እንዱከፈለዉ ክስ ይመሰርታል እንጂ እራሱ ጥል የሄደዉን ሥራ አለአግባብ እንደተሰናበት ተቆጥሮ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸዉ የሚሰጥ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች አላሰናበትኩም ብል እየተከራከረ ይህ ሳይጣራ አመልካች ከተጠሪ ላይ መኪና በመረከቡ ብቻ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ በማለት የወሰነበትን አግባብነት ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 09/09/2013 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።ተጠሪ የማሽከረክረዉን ተሽከርካሪ በሥራ ኃላፉዎቹ አማካኝነት በቀን 09/09/2012ዓ/ም ለላላ ሹፋር እንዲስረክብ ትእዛዝ ሰጥቶኝ አስረክቤ ላላ ተሽከርካሪ እንዱሰጠኝ በተደጋጋሚ ጠይቄ አመልካች አትመላለስ በሚል ተሽከርካሪ ሉሰጠኝ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን በማስረጃ አስረድቻለሁ።በገዛ ፈቃዳ ከሥራ አለመቅረቴንም በማስረጃ አስረድቻለሁ።ስለሆነም አመልካች በሕገ-ወጥ መንገድ የአመልካችን የሥራ ዉል አቋርጧል ተብል መወሰኑና ይህንን ተከትል አመልካች የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍለኝ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 27/09/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅርብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ተጠሪ በአመልካች ዘንድ በአሽከርካሪነት ተቀጥረዉ ለሚያሽከረክሩት ተሽከርካሪ በቂ ነዲጅ እንዱሰጣቸዉ አመልካችን በመጠየቃቸዉ አመልካች የሚያሽከረክሩትን ተሽከርካሪ ለላላ አሽከርካሪ በመስጠት የሥራ ዉላቸዉን እንዲቋረጠባቸዉ በመገልጽ የሥራ ዉላቸዉ ከሕግ ዉጭ እንደተቋረጠባቸዉ በመግለጽ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸዉ ጠይቀዋል።አመልካች ደግሞ አመልካች ላላ በርካታ ተሽከርካሪዎች ስላለኝ ተጠሪ ያነሱትን የነዲጅ ይጨመርልኝ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ላላ ተሽከርካሪ በመስጠት ለማሰራት ብፈልግም ተጠሪ ከቀን 18/10/2012ዓ/ም ጀምሮ በሥራ ገበታቸዉ ላይ ባለመገኘት በገዛ ፈቃዲቸዉ የሥራ ዉለን አቋረጡ እንጂ የሥራ ዉላቸዉን አላቋረጥኩም በማለት ተከራክረዋል።የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን በመመርመር አመልካች ተጠሪ ሲያሽከረክሩ የነበረዉን ተሽከርካሪ በመቀበል ሥራ በመከልከል የሥራ ዉላቸዉን ከሕግ-ዉጭ በሆነ አኳኋን አቋርጦ አሰናብቷቸዋል በማለት አመልካች የተለያዩ ክፍያዎችን ለተጠሪ እንዱከፍል የወሰነ ሲሆን የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻዉም አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ከሕግ ዉጭ አቋርጧል ተብል የመወሰኑን የሕግ አግባብ የሚመለከት ነዉ።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 12(1-3) ስር እንደተደነገገዉ ማንኛዉም አሰሪ፣በሥራ ዉለ ከተመለከቱት ልዩ ግዳታዎች በተጨማሪ ለሰራተኛዉ በሥራ ዉለ መሰረት ሥራ የመስጠት፣በሥራ ዉለ በልላ አኳኋን የተወሰነዉ ካለ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሥራ የሚያስፈልገዉን መሳሪያና ጥሬ ዔቃ ለሰራተኛዉ የማቅረብ እና ለሰራተኛዉ ደመወዝና ላልች ክፍያዎችን በዚህ አዋጅ ወይም በኅብረት ስምምነት መሰረት የመክፈል ግዳታ አለበት።ሰራተኛም በአዋጁ አንቀጽ 13 ስር የተመለከቱትን ላልች ግዳታዎችን የመፈጸም ግዳታ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሥራዉ ብቁ በሆነ የአእምሮና የአካል ሁኔታ በሥራ ላይ የመገኘት ግዳታ አለበት።
በያዝነዉ ጉዲይ ተጠሪ ለሚያሽከረክሩት ተሽከርካሪ በቂ ነዲጅ እንዱሰጣቸዉ መጠየቃቸዉና አመልካችም ይህንን ጥያቄ ተከትል ተጠሪ ሲያሽከረክሩ የነበረዉን ተሽከርካሪ የተረከቧቸዉ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።ከዚህ በኋላ አመልካች ተጠሪ በሥራ ቦታ እንዲይገኙ በማድረግ ያሰናበቷቸዉ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል።አመልካች ተጠሪ ሲያሽከረክሩ የነበረዉን ተሽከርካሪ የተረከበዉ ተጠሪ ያቀረቡትን የነዲጅ ጥያቄ መሰረት በማድረግ በልላ ተሽከርካሪ ለመለወጥ እንደሆነ ገልጸዉ ተከራክረዋል።ከሕግ-ዉጭ የሥራ ዉላ ተቋርጦብኛል የሚል ተከራካሪ ወገን በአሰሪዉ የሥራ ዉለ ከሕግ አግባብ ዉጭ በሆነ አኳኋን እንደተቋረጠበት ማስረዲት ይጠበቅበታል።በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ የሚያሽከረክሩትን ተሽከርካሪ አመልካች ስለተቀበላቸዉ የማሽከርካር ሥራቸዉን መስራት እንዲልቻለ በልላ አነጋገር አመልካች ሥራ እንደከለከላቸዉ ያስረደ ቢሆንም በዚህ ደረጃ ያስረደት አመልካች ተጠሪን ከሕግ አግባብ ዉጭ የሥራ ዉላቸዉን አቋርጧል ወደሚል ድምዲሜ የሚያደረስ አይደለም።
ተጠሪ አመልካች የማሽከረክረዉን ተሽከርካሪ በመረከብ ሥራ ከልክልኛል የሚለ ከሆነ ሥራ እንዱሰጣቸዉ በመጠየቅና ምክንያታዊ ለሆነ ጊዜ አመልካች ላላ ተሽከርካሪ እስከሚሰጣቸዉ በመጠበቅ በሚሰጣቸዉ ተሽከርካሪ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል እንጂ ያለአመልካች ፈቃድ ከሥራ የመቅረት መብት የላቸዉም። በመቀጠልም አመልካች ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ሥራ ካልሰጣቸዉ በአዋጁ አንቀጽ 32(1/መ እና 2) ስር በተደነገገዉ መሰረት አመልካች በአዋጁ አንቀጽ 12/1 ስር የተደነገገዉን ሥራ የመስጠትና አሰርቶ ደመወዝ የመክፈል ግዳታ በመደጋገም አለመፈጸሙን በማረጋገጥ እና ይህንንም በጽሁፍ ለአሰሪዉ በማሳወቅ የሥራ ዉለን ማቋረጥ ከሚችለ በስተቀር አመልካች ከሕግ-ዉጭ የሥራ ዉላ ተቋርጦብኛል በማለት ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ብል እንዱወሰን ለመጠየቅ የሚችለበት የሕግ መሰረት የለም። የሥራ ክርክር የሚወሰን አካልም በአዋጁ አንቀጽ 32(1/መ እና 2) ስር የተደነገገዉ መስፈርት ሲሟላ የሥራ ዉለ በሕግ አግባብ ተቋርጧል ብል የሚወስንበት ሁኔታ ቢኖርም አሰሪ ሥራ ከልክሎል በሚል ምክንያት ብቻ የሥራ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጧል ብል ለመወሰን የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም።
በመሆኑም አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ከሕግ-ዉጭ በማቋረጥ እንዲሰናበታቸዉ ተጠሪ ካለማስረዲታቸዉም በተጨማሪ አመልካች ሥራ መከልከለ ከሕግ-ዉጭ ተጠሪን አሰናብቷል የሚያሰኝ ምክንያት ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች የሥራ ዉለ ከሕግ ዉጭ ተቋርጧል በማለት የሰጡት ዉሳኔ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/05/2013 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 23/07/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ከሕግ-ዉጭ በሆነ አኳኋን ማቋረጡን ተጠሪ ያላስረደ በመሆኑ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ከሕግ-ዉጭ አቋርጧል ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ እና ለተጠሪ ካልተከፈላቸዉ የ1 ወር ደመወዝ በስተቀር የወሰነዉ የተለያዩ ክፍያዎች ተሽረዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.