ጥፊተኛ የተባለ ተከሳሽ ላይ የሚወሰን ቅጣት እንዲይገደብ ሉያደርጉ የሚችለ በሕጉ የተቀመጡ ሁኔታዊች ውጪ በደፈናው ቅጣቱን መገደብ ጥፊተኛውን ያስተምራል ወይም ላልችንም ያስጠነቅቃል ብዬ አላመንኩበትም በሚል ቅጣት እንዲይገደብ ማድረግ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ በሕጉ ላይ የተገለፀ ባለመሆኑ የተላለፈ ቅጣት እንዲይገደብ ሉያደርጉ የሚችለ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች መኖራቸውን በውሳኔው ላይ ሳይገለጽ፣ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ቅጣት እንዲይገደብ ለማድረግ የሚያስችለ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የቅጣት ገደብ ጥያቄን ውድቅ ማድረግ አግባብ ስላለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 192 እና ተከታይ እነ ዲበረ ሆቴል ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር እና የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካቾች ጥር 02 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ሕዲር 29 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ታሕሳስ 01 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- 1ኛ አመልካች የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 131/1/ለ ድንጋጌን በመተላለፍ በአዱስአበባ ከተማ የካ ክፍለከተማ ወረዲ 08 የቤት ቁጥር 729/13/14 ተመዝግቦ በሚታወቅ የንግድ ድርጅት ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝግቦ ለሰጠው ጊዜያዊ የአልጋ አገልግልት በ3ኛ አመልካች አማካኝነት ብር 200 ተቀብል የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ባለመስጠቱ በፈጸመው ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይነት ወንጀል ተከሷዋል የሚል ነው።
2ኛ ክስ፡- 2ኛ አመልካች የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 132/1 እና 131/1/ለ የተመለከተውን በመተላለፍ በክስ 1 ላይ ለተገለጸው ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሆኖ ድርጅቱን ሲመራ የወንጀል ድርጊቱ ሲፈጸም ሕጉ የጣለበትን የመከላከል ግዳታ ባለመወጣት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
3ኛ ክስ፡- 3ኛ አመልካች የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀጽ 128 እና 131/1/ለ ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ የተመለከተው የወንጀል ድርጊት ሲፈጸም ደረሰኝ ቆርጦ መስጠት ሲገባው ባለመስጠት ተከሷል የሚል ነው።
ክሱ ለአመልካቾች ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ክደው የተከራከሩ ሲሆን 3ኛ አመልካች ግብይቱ ተከናውኗል ደረሰኝ ተቀርጦአል ነገርግን ደረሰኙን አምጥቼ እሰጣቸዋለሁ ስል በሩ ዝግ ስለነበር መስጠት አልቻልኩም በማለት የእምነት ክሕደት ቃላቸውን የሰጡ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤሕግን ምስክሮች ከሰማ በኋላ አመልካቾች በክስ አቤቱታው ላይ የተገለጸውን የወንከል ድርጊት ስለመፈጸማቸው በዓቃቤሕግ ማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል በማለት ክሱን እንዱከላከለ ሲል ብይን ሰጥቷል። አመልካቾችም መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን አስቀርበው አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካቾቸ ባቀረቡት መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤሕግ ማስረጃ የተረጋገጠባቸውን ፍሬነገር ማስተባበል አልቻለም በማለት በተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ ጥፊተኛ ብልአቸዋል። ቅጣቱንም በቅጣት አወሳስን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት አስልቶ 1ኛ አመልካች በብር 6600 / ስድስት ሺህ ስድስት መቶ / የገንዘብ መቀጮ፤ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ደግሞ እያንዲንዲቸው በአንድ ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጡ ሲል ወስኗል።
አመልካቾች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው በትዕዛዝ ተሰርዟል።
አመልካች ጥር 02 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- የዓቃቤሕግ ክስ እና ማስረጃ አይጣጣምም፤ ግብይቱ በየትኛው ስርኣት እንደተፈጸመ በግልጸ አይታወቅም፤ በቁጥጥር ሰራተኞቹ ጥድፉያ ምክንያ ከተሰጠው አገልግልት ባሕርይ አንጻር አገልግለቱ ተሰጠ ለማለት በማያስችልበት ሁኔታ የግብይት ሂደቱ በጅምር እንደቀረ እና በዚህም ምክንያት ደረሰኝ ሳይሰጠ እንደቀረ ያሳያል፤ ተከፍሎል የተባለው ገንዘብ በሚመለከተው የድርጅቱ ገንዘብ ተቀባይ ወደ ድርጅቱ ካዝና አልገባም፤ አመልካቾች ባቀረብነው መከላከያ ማስረጃ ክሱን ተከላክለናል ፤ 2ኛ እaነ 3ኛ አመልካቾች ያቀረበው የቅጣት ይገደብልኘ ጥያቄ የታለፈው በደፈናው ነው፤ ስለሆነም እነኚህ ሁኔታዎች ከግንዛቤ ሳይገቡ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ግብይት ክፍያ ካሼ ጋር ባልደረሰበት ሁኔታ በአመልካቾች ላይ የተላለፈው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 እና ከታክስ አስተዲደር ሕጉ አንቀጽ 132 እና 128 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ የሰጠው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካቾች አቤቱታ ከማስረጃ ምዘና ጋር የተያያዘ በመሆኑ አግባብነት የለውም፤ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ማስረጃዎች እንደክስ አመሰራራቱ ያስረዲ እና አመልካቾች በዓቃቤሕግ ማስረጃ የተረጋገጠባቸውን ፍሬነገር ያላስተባበለ በመሆኑ ይህንኑ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካቾች በዓቃቤሕግ ክስ ላይ የተገለጸውን የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ ስለመሆኑ እና ባቀረቡትም መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤሕግ የተረጋገጠባቸውን ፍሬነገር ማስተባበል ያልቻለ ስለመሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10/1 መሰረት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የለውም።
በያዝነው ጉዲይ አመልካቾች የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው እና ባቀረቡት መከላከያ ማስረጃም ክሱን ያላስተባበለ ስለመሆናቸው ይህንኑ የማረጋገጥ ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ ይህንኑ መሰረት በማድረግ በአመልካቾች ላይ የተላለፊው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም።
በልላ በኩል የስር ፍርድ ቤት 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ያቀረቡትን የቅጣት ይገደብልኝ ጥያቄ ቅጣቱን መገደቡ ያስተምራቸዋል ወይም ላልችንም ያስጠነቅቃል ተብል አልታመነበትም በሚል ውድቅ ማድረጉ አግባብ መሆን አለመሆኑነ እንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ ጥፊተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፉት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግድለት አመለ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፊት ከማድረግም የሚታገድ መሆኑና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ ፍርድ ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከአፈፃፀም ታግድ እንዱቆይ ሉያዝ የሚችል ስለመሆኑ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 192 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩል በጥፊተኛው ላይ የተወሰነው ቅጣት እንዲይገደብ ሉያደርጉ የሚችለ በሕጉ የተቀመጡ ሁኔታዊች ያለ መሆኑን፤እነኚህም ሁኔታዎች ጥፊተኛው ከዚህ በፉት የጽኑ እሥራት ቅጣት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ ቀላል እሥራት ቅጣት ተፈርድበት እንደሆነ እና እንደገናም በተከሰሰበት ወንጀል ከእነዚህ ቅጣቶች አንደ የሚወሰንበት እንደሆነ ወይም ጥፊተኛው ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት አመት የበለጠ የጽኑ እሥራት ቅጣት የሚፈረድበት እንደሆነ ነው በማለት የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ድንጋጌ ላይ በዝርዝር ተመልክቷል። በሕጉ ከተመለከቱት ከእነኚህ ሁኔታዎች ውጪ በደፈናው ቅጣቱን መገደብ ጥፊተኛውን ያስተምራል ወይም ላልችንም ያስጠነቅቃል ብዬ አላመንኩበትም በሚል ቅጣት እንዲይገደብ ማድረግ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ በሕጉ ላይ አልተገለጸም።
ከላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ፍ/ቤቱ በጥፊተኛው ላይ የሚጣለውን ቅጣት ለጊዜው ማገድ ለወደፉቱ ጥፊቱን ለማረም እንደሚችል ሉያምን ወይም ላያምን የሚችለውም የጥፊተኛውን የቀድሞ ታሪኩ፤ የጠባዩ እና የዓመለ አካሄድ አስመልክቶ በችልቱ የተረጋገጡትን እውነታዎች መነሻ በማድረግ ሲሆን ፍ/ቤቶች በሕግ እና በተገቢ ምክንያት የተደገፈ ውሳኔ መስጠት ያለባቸው በመሆኑ ጥፊተኛው ቅጣቱን ለማስገደብ ያቀረባቸው ምክንያቶች ፍ/ቤቱን የሚያሳምኑ ናቸው ወይም አይደለም ለማለት ሕግን መሰረት በማድረግ እና አግባብነት ያለውን ምክንያት በመስጠት ላሆን ይገባል።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት በ2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ላይ የተላለፈው ቅጣት እንዲይገደብ ሉያደርጉ የሚችለ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች መኖራቸውን በውሳኔው ላይ ሳይገልጽ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 ቅጣት እንዲይገደብ ለማድረግ የሚያስችለ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይልቁንም 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የዘወትር ባሕርያቸው መልካም እንደሆነ፤ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆናቸው፤ የተለያዩ ማሕበራዊ ሀላፉነቶችን ሲወጡ የቆዩ ስለመሆናቸው እና የጤና ችግር ያለባቸው መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት የቅጣት ገደብ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ አግባብ ሆኖ አልተገኝም። በዚህም ምክንያት ተከታዩነ ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ሕዲር 29 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ታሕሳስ 01 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ጸንቷል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት በ2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ላይ የተላለፈው የእሥራት ቅጣት አፈጻጸሙን በሚመለከት ሳይፈጸም ለሁለት ዓመት እንዱገደብ በማለት ወስነናል።
-መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ
No topics extracted.