ተከሳሽ ወንጀል የፈፀመው ከላልች ሰዎች ጋር መሆኑ ቢረጋገጥም ግብረ አበሮች የወንበዳ ቡድን አባል ስለመሆናቸው የቀረበ ክርክርና ማስረጃ በላለበት በስምምነት ከላልች ሰዎች ጋር የተፈፀመ ወንጀል ሁለ ከባድ ውንብድና ወንጀል ማቋቋሚያ የሆነውን መመዘኛ የማያሟላና ተከሳሽ ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 የተከለከለውን የውንብድና ድርጊት ተላልፍ በፈፀመው የውንብድና ወንጀል እንጂ በከባድ ውንብድና ወንጀል ስላለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 እና 671(1)(ለ)ና (ሐ) በተከሳሽና በግብረ አበሮቹ የተፈፀመ የማስፈራራትም ሆነ የሐይል ድርጊት በኑሮ ልማድ እና በወንጀል ሕግ አንቀፅ 671 ማቋቋሚያ መርሆዎች መሰረት ሲመዘን ከፍ ያለ ፍርሀትን ወይም ሞትን በሚያስከትል መሳሪያ ስለመፈፀሙ ካልተረጋገጠ የተፈፀመው የሐይል ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 ስር የሚሸፈን ዮናታን ጎንቴ ዋልኮ እና የፋ/ጠ/ዐ/ሕግ
No summary available.
የሰ/መ/ ታሕሳስ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ዮናታን ጎንቴ ዋልኮ ተጠሪ፡- የፋ/ጠ/ዐ/ሕግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል እንዱታረምለት አመልካች በመጠየቁ ነው።
ጉዲዩ አመልካች ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈፅሟል በሚል የቀረበበትን ክስ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ ሕዲር 4ቀን 2012 ዓ/ም በተፃፈ ክሱ አመልካች ከላልች አራት ተከሣሾች ጋር በመሆን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 671(1)(ለ)ና (ሐ) የሚደነግገውን በመተላለፍ ጥቅምት 20ቀን 2012ዓ/ም ከላለቱ 10፡30 ሲሆን በቦላ ከፍለ ከተማ ወረዲ 06 ልዩ ቦታው ገርጅ መብራት ሀይል አካባቢ ንብረትነቱ የግል ተበዲይ የአቶ ተስፊዬ ብርሐኔ የሆነውን ሱቅ ተንጠልጣይ ቁልፍ በብረት መቁረጫ በመቁረጥ የገጠማቸውን ተቃውሞ ለማስቀረት ሲለ በምስክሮች አይን ላይ የፒውዛ (ከፍተኛ ብርሃን የሚያመነጭ) መብራት በማብራት፣ እፈጭሃለሁ የሚል ማስፈራሪያ ቃል በመናገር እንዱሁም ከቦታው በማባረር ግምታቸው 239,500.00 ብር የሚያወጡ ለሽያጭ የተዘጋጁ ጥቅል የኤላክትክ ገመድ በመውሰዲቸው ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸው ክደው ተከራክረዋል።
የተጠሪ ምስክሮች ተደምጠው አመልካች በክሱ በተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ መከላከል እንዱጀምር ታዞ መከላከያው ከተደመጠ በኋላ ጥፊተኛ ተብል በዘጠኝ አመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ተወስኖበታል።
በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኘው አመልካች የይግባኝ አቤቱታውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ስለፀናው ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች ሰኔ 7ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታው ፈፅሟል የተባለው የወንጀል ድርጊት በክሱ ላይ የተጠቀሰውን አንቀፅ ማቋቋሚያ የሚያሟላ አይደለም ሲል ያቀረበው መቃወሚያ ታልፍ ከባድ ውንብድና ወንጀል ስለመፈፀሙ ተጠሪ ባቀረበው ማስረጃ በአግባቡ ሣይረጋገጥ ባቀረበው መከላኪያ ማስረጃም አስተባብል ሣለ ጥፊተኛ ተብል ከባድ ቅጣት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተበል እንዱታረምለት ጠይቋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በተጠሪ በኩል ቀርበው ከተደመጡት ምስክሮች መካከል 3ኛ ምስክር በተከሳሾች የተፈፀመበት የሀይል ድርጊት ስለመኖሩ ሣያረጋግጥ በወንጀል ሕግ አንቀፅ 671(1)(ለ) (ሐ) ድንጋጌ ስር የጥፊተኝት ፍርድ የመሰጠቱን አግባብት ከድንጋጌው ማቋቋሚያ ፍሬ ነገር አኳያ እንዱመረመር በመታዘዙ ክርክራቸውን በፅሁፍ ተለዋውጠዋል።
ተጠሪ በበኩለ ማስረጃን የመመዝን የዲኝነት ስልጣን ለሰበር ሰሚ ችልት ያልተሰጠው መሆኑን ሆኖም በስር ፍርድ ቤቱ የተፈፀመ ማስረጃ ምዘና አለመኖሩን፣ ከባድ ውንብድና ወንጀልን ለመቋቋም የሀይል ድርጊት መኖር ብቸኛ መመዘኛ አለመሆኑን፣ አመልካችም የሐይል ድርጊት መፈፀሙን በማስረጃ መረጋገጡን በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤቶች የፈፀሙት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተበል የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግለት ክርክሩን አቅርቧል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር ተጠናቋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥና የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀፅ 671(1)(ለ)ና (ሐ) የተመለከተውን በመተላለፍ ከባድ ውንብድና ወንጀል ፈፅሟል ተብል በእስራት እንዱቀጣ በተሰጠው ውሣኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በጭብጥነት ይዘን የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። እንደመረመርነው አመልካች ከባድ የውብድና ወንጀል ፈፅሟል የሚል ክስ እንዱቀርብበት ምክንያት የሆነው በአመልካችና በግብረ አበሮቹ የተፈፀመው የሃይል ድርጊት ስለመሆኑ የክሱ አቀራረብ ያስገነዝባል።
አንድ ሰው ከባድ ውንብድና ወንጀል ፈፅሟል ተብል ቅጣት ሉወሰንበት የሚችለው የውንብድና ወንጀል የተፈፀመው በሰዎች ላይ ወይም በንብረት ላይ የሐይል ተግባር ለመፈፀም በተቋቋመ የወንበዳ ቡድን አባል በመሆን ሲሆን ወይም ተበዲዩን እገድልሃለሁ ብል እርግጠኛ የሞት አደጋ እንደሚያደርስበት በመቃጣት ይልቁንም በጦር መሳሪያ ወይም በተለይም አደገኛ በሆነ ላላ አይነት መሣሪያ በማስፈራራት ወይም ስቃይ በሚያደርስ ሁኔታ በማንገላታት ወይም ከባድ አካል ጉዲት በማደርስ ሲሆን ወይም በተለይም አደገኝነቱን በሚያሣይ በማናቸውም ላላ ሁኔታ ሲሆን እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከባድ ውንብድና ወንጀልን ከውንብድና ወንጀል የሚለየው የሐይል ድርጊቱ የተፈፀመው ለዚሁ ተግባር በተቋቋመ የወንበዳ ቡድን ከሆነ ወይም የተፈፀመው ድርጊት ከፍ ያለ መንግላታትን ያስከተለ ወይም በጦር መሣሪያ በመጠቀም እርግጠኛ የሞት አደጋ እንደሚያደርስበት በማስፈራራት በተፈፀመ ጊዜ እንደሆነ ይደነግጋል። በመሆኑም አመልካቹ የፈፀመው የውንብድና ወንጀል ነው ወይስ ከባድ ውንብድና የሚለው አከራካሪ ነጥብ የዚህን ችልት መልስ የሚሻ ነጥብ ነው።
በዚህም መሰረት በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀረበው ማስረጃ አመልካች ወንጀለን የፈፀመው ከላልች ሰዎች ጋራ መሆኑ ቢረጋገጥም አመልካችም ሆነ ላልች ግብረ አበሮች የወንበዳ ቡድን አባል ስለመሆናቸው የቀረበ ክርክርና ማስረጃ የለም። በመሆኑም በስምምነት ከላልች ሰዎች ጋር የተፈፀመ ወንጀል ሁለ ከባድ ውንብድና ወንጀል ማቋቋሚያ የሆነውን መመዘኛ የሚያሟላ አይሆንም።
በልላ በኩል አመልካችና ግብረ አበሮቹ የፈፀሙት የሀይል ድርጊት በወጀል ሕግ አንቀፅ 670 ድንጋጌ የሚጠቃለለ ናቸው ወይስ አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት የወንጀል ሕግ እንቀጽ 671 የሚለው ጉዲይ መልስ ማግኘት ይኖርበታል። በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካችና ጓደኞቹ የፈፀሙት የሐይል ድርጊት ምስክሮች ወንጀለን እንዲይከላከለ በአይናቸው ላይ ፒውዛ ማብራትና ማስፈራራት እንደሆነ በምስክሮች ተረጋግጧል። ይህ የማስፈራራቱም ሆነ የሐይል ድርጊቱ በኑሮ ልማድ እና በወንጀል ሕግ አንቀፅ 671 ማቋቋሚያ መርሆዎች መሰረት ሲመዘን ከፍ ያለ መንገላታትን ወይም ፍርሀት አስከትለዋል የሚያስብል ካለመሆኑም ባሻገር ሲፈፀሙም ከፍ ያለ ፍርህትን ወይም ሞትን በሚያስከትል መሳሪያ የተፈፀሙ ስለመሆናቸውም በማስረጃ ያልተረጋገጠ ስለሆነ የአመልካችና ግብረ አበሮቹ የፈፀሙት የሐይል ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 ስር የሚሸፈን ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም አመልካች ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 የተከለከለውን የውንብድና ድርጊት ተላልፍ በፈፀመው የውንብድና ወንጀል እንጅ በከባድ ውንብድና ወንጀል አለመሆኑን ስለተገነዘብን ተከታዩን ውሣኔ ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራለ ከተፍኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 29 እና 30 ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ፣ እንዱሁም በመዝገብ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195(2)(ለ)(2) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 670 የተመለከተውን ተላልፍ የውንብድና ወንጀል የፈፀመ በመሆኑ ይሕ ጥፊቱ በወንጀል ቅጣቶች አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀፅ 17 መሰረት መመሪያ የወጣለት በመሆኑ ደረጃው 5 የእስራት ቅጣቱ እርከን 19 በመነሻነት ተይዞ ወንጀለ በስምምነት የተፈፀመ መሆኑን በማክበጃነት ተይዞ በስር ፍርድ ቤት የተያዙለትን ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘውለት እርከን 28 እንዱያርፍ ተድርጎ በዚህ ጉዲይ የታሰረው ሁለ ታሣቢ ሆኖለት በሶስት ዓመት ከሰባት ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ተወስኖበታል።
ት ዔ ዛ ዝ
የአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት በዚህ ችልት የተወሰነውን የሶስት ዓመት ከሰባት ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተከታትል እንዱያስፈፅም ታዟል፤ ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.