የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ይዘት ድንጋጌዎቹን መሰረት በማድረግ የሚቀርብ ክስ ድርጊቱ የተፈጸመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ ነው የሚለውን የሕጉን መስፈርት ማሟላት በሚያስችል ሁኔታ በተከሳሽ ተፈጽሟል የተባለውን ግዙፊዊ ፍሬ ነገር /material fact/ በአግባቡ መመሥረት እና ማስረዲት በሚያስችል ሁኔታ መመሥረት የሚጠበቅበት ሲሆን ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ ተከሳሽ ክሱን እንዱከላከል ብይን ላሰጥ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ አቶ ፈለቀ ታደሰ ዘነበ እና የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411/1(ሐ) እና (2)፣ እንዱሁም አንቀጽ 407/1 (ሀ) እና (2)
No summary available.
የሰ.መ.
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ፈለቀ ታደሰ ዘነበ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - አልቀረቡም መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች የካቲት 09 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ሐምል 17 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 29 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች እና በላልች 4 ተከሳሾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች አራት ሲሆኑ አመልካችን የሚመለከቱት 1ኛ እና 3ኛ ክሶች ናቸው።
1ኛ ክስ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1(ሀ) እና 411/1(ሐ)(2) ድንጋጌን በመተላለፍ አመልካች የተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ላልቹ ደግሞ የአገዲ ተከላ እና እንክብካቤ ስራ አስኪያጅ፤
የእርሻ ኦፔሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ቡድን መሪ እና የመሬት ልማትና ዝግጅት ሱፏርቫይዘር ሆነው ከ2005 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ሲሰሩ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም የመሬት መደልደል ውል ከፊብሪካው ጋር ለተዋዋለ ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ለማስገኘት እና በፊብሪካው ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ ኮንትራክተሩ የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም እና መስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከፊብሪካው ጋር በገባው ውል መሰረት የመሬት ድልዲል ስራውን ለሸንኮራ አገዲ ተክል በሚሆን ጥራት መሰራቱን በማረጋገጥ መረከብ ሲገባቸው አመልካች የፊብሪካውን ስራ በበላይነት የመምራት እና የመቆጣጠር ሃላፉነት እያለው ባቱ ኮንስትራክሽን ለመስራት በውል የተረከበውን የመሬት መደልደል ስራ በውለ በገባው ግዳታ መሰረት ለአገዲ ተክል ልማት በሚሆን መጠን እና ጥራት ሰርቶ ማስረከብ ሲገባው ተሰርቷል ተብል ርክክብ የተደረገው የመሬት መደልደል ስራ በውለ ላይ የተገለጸው እና ለሸንኮራ አገዲ ተክል ልማት በሚፈለገው ጥራትና መጠን እንዲልሆነ እንዱሁም በፊብሪካው ማሽነሪዎች እና ወጪ የተሰራው ባቱ ኮንስትራክሽን እንደሰራው ተደርጎ ክፍያ እንዱሚፈጸምለት በፊብሪካው ሰራተኞች እየተነገረው ካለው ሃላፉነት አንጻር ስራው በአግባቡ ስለመሰራቱ በማረጋገጥ ርክክብ እንዱፈጸም ማድረግ ሲገባው ከ300 እስከ 400 ሓክታር የሚሆን የመሬት መደልደል ስራ ለሸንኮራ አገዲ ተክል ልማት በሚሆን ጥራት ሳይሰራ ርክክብ እንዱፈጸም እና በፊብሪካው ማሽነሪዎች እና ሰራተኞች በድጋሚ እንዱሰራ በማድረጉ፤ ከ2-4 ያለት ተከሳሾችም በተሰጣቸው ሃላፉነት መሰረት ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ እንዱሰራ በውል የተሰጠውን የመሬት መደልደል ስራን ሲጀምር በፊብሪካው ማሽነሪዎችና ሰራተኞች ከሚሰራው ስራ በግልጽ ተለይቶ እንዱሰጠው በማድረግ የሰራውንም ስራ በአግባቡ በመመዝገብ የሚሰራው የመሬት ዝግጅት በፊብሪካው ማሽነሪዎችና ሰራተኞች ስራው ሳይቀላቀል እንዱያከናወን ማድረግ ሲገባቸው ባለማድረጋቸው መጠኑ በግልጸ የማይታወቅና በፊብሪካው የራስ አቅም የተሰራውን ስራ ባቱ ኮንስትራክሽን ከሰራው ስራ ጋር እንዱቀላለቀል አድርገዋል፤ የመሬት ዝግጅት ስራውን ለሸንኮራ አገዲ ተክል ልማት በሚሆን ጥራት መሰረት መሰራቱን በማረጋገጥ መረከብ ሲገባቸው ከ300-400 ሓክታር መሬት በውለ ላይ በተጠቀሰው ጥራት ሳይሰራ ርክክብ አድርገው በፊብሪካው ማሽነሪዎች እና ሰራተኞች ስራው በድጋሚ እንዱሰራ ትዕዛዝ በመስጠታቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት የፊብሪካውን ጥቅም በመጉዲት የመንግስት ሥራ በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።
3ኛ ክስ፡- አመልካች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 407 /1(ሀ)(2) ድንጋጌን በመተላለፍ የተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት እና በፊብሪካው ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ ሐምል 2003 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ስኳር ኮርፕሬሽን የግዢ አፈጻጸም መመሪያ አንቀጽ 17/3 ውጪ ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ከፊብሪካው ጋር ቀደም ብል በገባው ውል መሰረት ለመስራት የተረከበውን የመሬት መደልደል ስራ ለአገዲ ተክል ልማት በሚፈለገው ጥራት እና ፍጥነት ሰርቶ ማስረከብ አለመቻለን በግልጽ እያወቀ መስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም 1000 ሓክታር የመሬት መደልደል ስራ በብር 29,691,551 እንዱሰራ ተጨማሪ ውል በመዋዋለ እና ባቱ ኮንስትራክሽንም በውል የተሰጠውን መሬት በጥራት እና በፍጥነት ባለመስራቱ ከ300-400 ሓክታር የሚሆን የመሬት ድልዲል ስራ በፊብሪካው ማሽነሪዎች እና በድጋሚ እንዱሰራ ምክንያት በመሆኑ በስልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ፈጽሟል የሚል ነው። ቀሪ ክሶች አመልካችን ስለማይመለከቱ መመዝገብ አላስፈለገም።
ተከሳሾች ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ አቅርበው በብይን ውድቅ ተደርጓል።
የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ሲጠየቁም ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ክደው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የዓቃቤሕግን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ አመልካች የፊብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ እየሰራ በነበረበት ጊዜ በባቱ ኮንስትራክሽን እንዱሰራ ውል የተገባለት የሸንኮራ አገዲ ተክል ልማት ስራ በሚፈለገው ጥራት ባለመሰራቱ ስራው በድጋሚ እንዱሰራ ማድረጉን የባቱ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎቹ ዘመናዊነት የላላቸው በመሆኑ እና የውሃ ፍሰቱን ጥራት ባለሟሟላቱ በፊብሪካው ዘመናዊ ማሽነሪዎች እንዱሁም ሰራተኞች ከ300-400 ሄክታር የማረም እና ማስተካከል ስራዎች የተሰሩ መሆኑን የዓቃቤሕግ 1ኛ፤ 2ኛ፤ 4ኛ፤ 5ኛ፤ 6ኛ፤ 8ኛ እና 10ኛ ምስክሮች አስረድተውባቸዋል፤ እነዚህ ምስክሮች በተጨማሪ 2ኛ ፤ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በፊብሪካው የራስ አቅምና በባቱ ኮንስትራክሽን የተሰራውን የመሬት ድልዲል ስራ የሚመለክት ለየብቻ የተያዘ መረጃ ባለመኖሩ መቼና በየትኛው ቦታ ምን ያህል ስራ ተሰርቷል የሚለውን ለማወቅ አለመቻለንና መጠኑ ያልታወቀ ስራ የተቀላቀለ መሆኑን እንዱሁም በስራው የጥራት ችግር ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው የመሬት መጠን በፊብሪካው ወጪ ማሽነሪና የሰው ሃይል እንደገና የማስተካከል ስራ የተሰራ መሆኑን መስክረዋል፤ 12ኛ እና 13ኛ ምስክሮች በፊብሪካው እና በባቱ ኮንስትራክሽን የተሰሩት ስራዎች ያልተለዩ የነበረ በመሆኑ የፊብሪካው የውስጥ ኦዱት ባለሙያዎች ችግሩን እንዱያስተካክለት መመሪያ ሰጥተው የተመለሱ ቢሆንም በፊብሪካው የራስ አቅም ምን ያህል በባቱ ኮንስትራክሽን ደግሞ ምን ያህል እንደተሰራ ያልተለየ ስለመሆኑ በ1ኛ፤ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ላይ መስክረውባቸውል። 3ኛ ክስን በተመለከተ አመልካች ከመስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም በፉት ፊብሪካው በገባው ውል መሰረት ባቱ ኮንስትራክሽን የሚሰራው ስራ የጥራት ችግር የነበረበት በመሆኑ በተደጋጋሚ በፊብሪካው ማሽነሪዎችና ሰራተኞች የማስተካከያ ስራዎች ሲሰሩ የነበሩ መሆኑን እያወቀ መስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚሁ ባቱ ኮንስትራክሽን ጋር ተመሳሳይ ውል መፈጸሙን ከመንግስት የልማት ድርጅት የቀጥታ ግዢ የሚፈቀደው ዔቃው ወይም አገልግልቱ በተሻለ ጥራትና ፍጥነት እንዱሁም የዋጋ ተመጣጣኝነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን ምስክሩ አስረድቷል፤ ላልች ተከሳሾችም ድርጊቱን የፈጸሙ ስለመሆኑ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል፤ ስለሆነም ተከሳሾች ክሱን ሉካለከለ ይገባል ሲል ብይን ሰጥቷል።
ተከሳሾችም መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን አስቀርበው አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አቶ ያቆብ ጨረፍ የተባለት 7ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል በ2005 ዓ.ም መጨረሻ እስከ 2006 ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ በባቱ ኮንስትራክሽን ከተሰራ በኋላ 200 ሓክተር የሚሆን መሬት በፊብሪካው ማሽነሪዎች በድጋሚ የተሰራ መሆኑን የድጋሚ ስራው ምክንያቶችም በዝናብና ነፊስ የመሬቱ ተዲፊትነት ሲበላሽ ወይም ወይም የዱዛይን ለውጥ ሲኖር እንጂ በባቱ ኮንስትራክሽን የስራ ጥራት ችግር አለመሆኑን በባቱ ኮንስትራክሽን በጥራት ተሰርቶ ርክክብ ከተደረገ በኋላ በሚመጣ ችግር ምክንያት በፊብሪካው ማሽኖች ስራዎች እየተሰሩ በየቀኑ በሱፏርቫይዘር እስከ ስኳር ኮርፕሬሽን በየደረጃው ሪፕርት የሚደረግ መሆኑን በመግለጽ ተከሳሾችን በሚጠቅም መልኩ የምስክርነት ቃል የሰጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የእኚህን ምስክር ቃል ተከሳሾቹ እንዱከላከለ በማስረጃነት ያልያዘው በመሆኑ እንዱሁም የዓቃቤ ሕግ ምስክር በሰጡት ቃል ላይ ምስክሩ አስጠቂ ምስክር በመሆናቸው መሪ ጥያቄ እንዱጠየቁ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ ፈቅድ በዋና ጥያቄ እንዱቀርብላቸው የተደረገ በመሆኑ እና በተከሳሾች በመከላከያነት ምስክርነት ተቆጥረው በችልት ያልቀረቡ ቢሆንም ተከሳሾች የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ይደግፈናል ብለው በመከራከራቸው ከቀሪ መከላከያ ምስክሮች ጋር ፍርድ ቤቱ አያይዞ የምስክርነት ቃለን መዝኖታል፤ 12ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑት አቶ አድነው ጌጤ ተፈልገው ባለመገኘታቸው ለፒሉስ የሰጡት ቃል ቀርቦ የታየ እና ፍርድ ቤቱም የእኚህን ምስክር ቃል ተከሳሾቹ የተከሰሰቡባቸውን ክሶች ማስረጃውን መዝኖ እንዱከላከለ በማስረጃነት የተጠቀመበት ቢሆንም እኚህ ምስክር ለአራቱም ተከሳሾች የጋራ መከላከያ ምስክር ሆነው በችልት ቀርበው የመሰከሩ እና ለመርማሪ ፕሉስ የሰጡት የምስክርነት ቃል በተጽእኖ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ የገለጹ እና በዓቃቤ ሕግ መስቀለኛ ጥያቄ የቀረበላቸው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች መከላከያነት የምስክርነት ቃላቸውን ተቀብል መዝኖታል፤ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ከክሱ ፍሬ ነገሮች ጋር በተገናኘ በቀጥታ አስረድተዋል፤
የተከሳሽ ምስክሮች ርክክብ የመፈጸም ሀላፉነት የለባቸውም ከሚለው ውጪ ላላውን የክሱን ፍሬነገር ለማስረዲት የሞከሩት ከመሬት ዝግጅት ጋር በተያያዘ ያለውን አሰራር ነው፤ የሑሳብ ሪፕርቱ ኦዱቱ የተሰራበትን መንገድ በዝርዝር የገለጸ እና ደጋፉ ሰነድችን ከኦዱት ሪፕርት ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን የተከሳሾች ጠበቆች በሑሳብ መርማሪው ውጤት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የቀረበውን አስተያየት ውድቅ አድርጎታል፤ በኦዱት ሪፕርቱ ላይ የተገለጹት ፍሬነገሮች እንዲለቁ ማስረጃዎች ተደርገው የማይወሰደ እና የአስረጅነታቸው ሁኔታ የሚመዘን ቢሆንም ተከሳሾች ሙያዊ በሆነ መርህ የኦዱት ስራው በትክክል ስላለመሰራቱ ያቀረቡት ማስረጃ የለም፤ ስለመሬት ርክክብ በናሙናነት የቀረበው ማስረጃ በአጠቃለይ ስለፊብሪካው አሰራር ማሳያ ተደርጎ ሉወሰድ ከሚችል በቀር ከክሱ ጋር በቀጥታ የአስረጅነት ክብደት የለውም፤ የአቶ ያዔቆብ የምሰክርነት ቃል ሲመረመር በዋናነት የድጋሚ ስራው እንዱሰራ ሲያስተባብሩ የነበሩ ስለመሆናቸው በዓቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮች የተመሰከረባቸው በመሆኑ እና ምስክሩ ራሳቸውን በሚጎዲ መልኩ ይመሰክራለ ተብል ስለማይገመት ፤
14ኛው የአመልካች የብቻ ምስክር የግዢ መመሪውን በሚመለከት ያስረደ ቢሆንም መመሪያው ሲወጣ ሐሳቡ ምን ነበር ሲለ ዳኞች ትርጓሜ የሚሰጡበት በመሆኑ የምስክርነት ቃለ ተቀባይነት የለውም፤
እኚህ ምስክር በዓቃቤ ሕግ መስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቁ የኦዱት ሪፕርቱን በዝርዝር ያላዩ እና የተመለከቱት የተሰጠውን አስተያየት ብቻ መሆኑን የመሰከሩ በመሆኑ የምስክሩ ቃል በኦዱት ሪፕርቱ አጠቃላይ ይዘት ላይ ማስተባበያ ሰጥተዋል ማለት አያስችልም፤ አድነው ጌጡ የተባለት ምስክር ሪፕርት ማድረጉ ቡድን መሪ ላይ ብቻ የሚቀር እና እስከ በኋላ ለማንም ሪፕርት የማይደረግ መሆኑን የመሰከሩ ቢሆንም የተከሳሾች ላልቹ ምስክሮች በሪፕርት መልክ በየደረጃው ላለ የስራ ሀላፉዎች የሚደረግ ስለመሆኑ ከሰጡት ምስክርት አንጻር ሲታይ የምስክርነት ቃላቸው ተአማኒ ሆኖ አልተገኘም፤
የመሬት ዝግጅት ስራው የፊብሪካው አንደ የዔቅደ አካል በመሆኑ እና ለተከሳሾች የተሰጣቸው የስራ መዘርዝር የለም ስራዎቹ የሚሰሩት በነባር ፊብሪካዎቹ የስራ ልምድ ነው ቢባል እንኳን አመልካች የፊብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ስራውን በበላይነት የመምራት እና የመቆጣጠር ዋነኛው ስራው ሆኖ የሚሰራው ስራ የጥራት ችግር ያለበት መሆኑ ተገልጾለት ሳለ ምንም ዓይነት የማስተካከያ እርምጃ የወሰደ ስለመሆኑ አላስረዲም፤ ዓቃቤ ሕግ ደረሰ የተባለው የጉዲት መጠን በገንዘብ ገምቶ እንዱያቀርብ ታዞ ክሱን አሻሽል ያቀረበ ቢሆንም የድጋሚ ስራው በፊብሪካው ማሽኖች እና በሰው ሀይል ከ300 እስከ 400 ሓክታር መሬት የማድረስ የማስተካከያ ስራ በድጋሚ ስለመሰራቱ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ዓቃቤ ሕግ በጠቀሰው የሕግ አንቀጽ ሳይሆን አመልካች በወንጀል ሕግ 411/1/ሐ በ1ኛ ክስ ጥፊተኛ ናቸው፤ 3ኛ ክስን በተመለከተ አመልካች የስኳር ኮርፕሬሽን የግዥ መመሪያ አንቀጽ 17/3 ውጪ ባቱ ኮንስትራክሽን ከዚሀ ቀደም የጥራት እና የፍጥነት ችግሮች ያለበት መሆኑን እያወቀ ድጋሚ የመሬት ዝግጅት ውል ማድረጉ ዓቃቤ ሕግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች የተረጋገጠ በመሆኑ በተከሰሰበት ድንጋጌ ሳይሆን በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ምክንያት ዓቃቤ ሕግ ጉዲቱን በገንዘብ ግምት ባለማቅረቡ ጥፊተኛ ልባል የሚገባው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 407/1/ሀ ድንጋጌ ነው በማለት ጥፊተኛ ብል በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እና በብር 7000 የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ የወሰነ ሲሆን የመጨረሻው ቅጣት ውሳኔ የሚወሰነው ግን በዚያው ፍርድ ቤት ካለው የመ. ከሆነው መዝገብ ጋር ተጣምሮ ነው በማለት ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይህንኑ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች የካቲት 09 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ሆነ ስኳር ፊብሪካ የመንግስት የልማት ድርጅቾች በመሆናቸው አመልካች አንደን ጠቅሜ እንደን ልጎዲ የምችልበት ምክንያት የላለ እና አቃቤ ህግ ይህንን የሀሳብ ክፍል በህግ ግምት የሚወሰድበትን አሳማኝ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 23(2) ድንጋጌ መስፈርትን አያሟላም፤ ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ስራው የተሰጠው የግዥ መመሪያውን መሰረት ባደረገ መልኩ ሳይሆን በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እና በስኳር ኮርፕሬሽን ዋና ዲሬክተር የፕሉሲ ውሳኔ መነሻነት መሆኑን የአመልካች መከላከያ ማስረጃዎች አስረድተዋል፤ የማሳ ርክክብ የሚፈጸመው ማሳው በትክክለኛ ጥራት መሰራቱ በቅድሚያ በሰርቬየሮች በሚወሰድ ሙያዊ ሪፕርት ብቻ ተረጋግጦ እንደሆነ እና አመልካች ጥራትን በማረጋገጥ ሂደት ላይ ምንም አይነት ሙያዊ ተሳትፍ እንደላለኝ አስረድቻለው፤
በዚህ ረገድ የዐቃቤ ህግ ምስክር የሆኑት አቶ ያእቆብ ጨረፍ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤቱ ሳይመዝን አልፍታል፤ አቃቤ ህግ በምስክርነት ቆጥሮአቸው የነበሩትን አቶ አድነው ጌጡ በአድራሻቸው የለም በማለት ሀሰተኛ አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቅርቦ ለፕሉስ የሰጡትን ቃል በማስረጃነት እንዱያያዝ ማድረጉን አመልካች የተቃወምኩ እና አቶ አድነው ጌጡም በመከላከያ ማስረጃነት ቀርበው እውነታውን ያስረደ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረጉ ተገቢነት የለውም፤ 1000 ሄክታር የመሬት መደልደል ስራ በብር 29,691,551 እንዱሰራ ተጨማሪ ውል እንዱፈረም የተደረገው በስኳር ኮርፕሬሽን ዋና ዲሬክተር እና በባቱ ኮንስትራክሽን ቦርድ ነው፤ አመልካች የተከሰስኩበት ውል መስከረም 2 ቀን 2006 ዓ.ም ሲፈረም ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ቀደም ብል በዋና ዲሬክተሩ ውሳኔ በፊብሪካው ውስጥ የመሬት ድልዲል ስራን ሲሰራ የነበረ መሆኑን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ የተወሰነ ነው፤ ሐምል 2003 ዓ.ም በወጣው የስኳር ኮርፕሬሽን የግዥ መመሪያ የአንቀጽ 17/3 ድንጋጌ መሰረት አመልካች መስከረም 2/2006 ዓ.ም በነበረው ሁኔታ የተጨማሪ ስራ ውለን እንዲይፈጸም ሉያደርግ የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለም፤ ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ በተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ በሰራቸው የመሬት ድልዲል ስራዎች ጥራት ላይ የቀረበ ቅሬታ እንደላለ በማስረጃ ተረጋግጧል፤ የድጋሚ ስራ የተሰራው በባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ የስራ ጥራት ጉድለት ጋር በተያያዘ አለመሆኑ አመልካች አስረድቷል፤ ከርክክብ በኋላ የሚፈጠሩ የማሳ ጉድለቶች ስራ ተቋራጩ የማስተካከል ኃላፉነት ስለላለበት በፊብሪካው ማሽንኖች እንዱሰራ መደረጉ ተገቢ አሰራር መሆኑን አመልካች አስረድቷል፤ በመሆኑም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የባቱ ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ ወደ ሥራው የገባበት፤ ከቆይታ የተነሳ ስራው በትክክል ስለአለመሰራቱ እና ጉድለት ያለበት ስለመሆኑ ከሙያው ባሕርይ አንጻር የተጣራበት እንደዚሁም ከአመልካች የስራ ሀላፉነት እና ላልች ተመሳሳይ ነጥቦች ጋር ታይቶ አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411/1/ሐ እና 407/ሀ በመተላለፍ የመንግስትን ሥራ በማያመች አኳሃን የመምራት እና በሥልጣን ያላግባብ መገልገል ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠበትን አግባብነት ከመሰረታዊ የክርክር አመራር ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ምዘና መርህ አንጻር ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ ጥቅምት 04 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የድርጊቱ አላማ ላላኛውን ተቋም ጥቅም እንዱያገኝ ባይሆንም እንኳ በሕገ ወጥ ተግባር ውስጥ ለራስ የሚገኝ ጥቅም የሚኖር ሲሆን በልላ በኩል የአንድን የመንግስት በጀት ለላላ የመንግስት ተቋም ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሰረት ሳይኖረው ማስተላለፍ በተቋሙ ጥቅም ላይ ጉዲት ማድረስ ነው፤ ሕገ ወጥ ትዕዛዝን መቀበል በማናቸውም መንገድ ተቀባይነት የላለው ከመሆኑም በላይ አመልካች ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ስራውን እንዱሰራ የመንግስት ፕሉሲ ነው ከማለት ውጪ ያስገደደው አካል ስለመኖሩ ያቀረበው ማስረጃ የለም፤ አመልካች ኃላፉነቱን ወደ ጎን በመተው ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ የሰራው ስራ ጥራት የጎደለው መሆኑን እያወቀ ርከክብ እዱፈጸም ያደረገ እና የድጋሚ ስራው በሙለ እውቅና ሲያሰራ የነበረ መሆኑ የአቃቤ ህግ ምስከሮች አስረድተዋል፤ በባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ኋላቀር እና ማኑዋል በመሆናቸው ስራው የጥራት ችግር የነበረበት በመሆኑ እና ይህንን ለማስተካከል በፊብሪካው ዘመናዊ መሳሪያዎች የድጋሚ ስራ መታዘዙ የተጠሪ ምስክሮች አስረድተዋል፤ አቶ ያዔቆብ ጨረፍ የተከሳሾች ተባባሪ የነበረ እና በወንጀል ድርጊቱ ላይ ተሳታፉ የነበረ በመሆኑ የሰጠው የምስክርነት ቃል ተዓማኒነት ያለው አይደለም፤ አቶ አድነው ጌጡ ለዐቃቤ ህግ በምስክርነት ተፈልጎ የጠፊ ነገር ግን በመከላከያ ምስክርነት ቀርቦ የተሰጠው ቃል እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው፤ በመሆኑም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኒ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ ከመነሻውም ቢሆን ዓቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ በሕጉ አግባብ የቀረበ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው 1ኛ ክስ አመልካች ተላልፍታል በማለት የጠቀሰው የወንጀል ሕግ 411/1(ሐ)እና(2) ድንጋጌን ነው፤ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411/1(ሐ) ማናኛውም የመንግስት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ፤ ስልጣኑን ወይም ሀላፉነቱን ተጠቅሞ በጠቅላላው በሥራው ስልጣን መሰረት በአደራ የተሰጠውን የሕዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጎዲ ተግባር በማናቸውም ዘዳ የፈጸመ እንደሆነ በድንጋጌው የተመለከተውን ቅጣት ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፤ የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 2 አክባጅ ሁኔታን የሚመለከት ነው።
በልላ በኩል ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው 3ኛ ክስ አመልካች ተላልፍታል በማለት የጠቀሰው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 407/1(ሀ)እና(2) ድንጋጌን ነው፤ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 407/1(ሀ) ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ፡- የተሰጠውን ሹመት ወይም ሥልጣን በግልጽ ተግባር ወይም በግድፈት ያለአግባብ የተገለገለበት እንደሆነ በድንጋጌው የተመለከተውን ቅጣት ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፤
የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 2 አክባጅ ሁኔታን የሚመለከት ነው።
ከላይ ከተመለከቱተ ድንጋጌዎች ይዘት በግልጽ መገንዘብ የሚቻለው ዓቃቤ ሕግ ድንጋጌዎቹን መሰረት በማድረግ ክስ ሲያቀርብ ድርጊቱ የተፈጸመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ ነው የሚለውን የሕጉን መስፈርት ማሟላት በሚያስችል ሁኔታ በተከሳሹ ተፈጽሟል ያለውን ግዙፊዊ ፍሬ ነገር / material fact / በአግባቡ መመሥረት እና ማስረዲት እንዲለበት ነው።
በያዝነው ጉዲይ ባቱ ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማሕበር የመንግስት ልማት ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት መንግስታዊ የልማት ተቋም እስከሆነ ድረስ አመልካች ፈጽሞታል በተባለው የሙስና ወንጀል ከዚሁ መንግስታዊ የልማት ተቋም የማይገባ ጥቅም ሉያገኝ ወይም ሉያስገኝ የሚችልበት ግዙፊዊ ፍሬ ነገሮች ያለ ስለመሆኑ ማሳየት በሚያስችል ሁኔታ ክሱን መመሥረት ይጠበቅበታል። ዓቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ ባቀረበው 1ኛ እና 3ኛ ክስ አመልካች ድርጊቱን የፈጸመው የተንዲሆ ስኳር ፊበሪካ ስራ አስኪያጅ ሆኖ የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም የመሬት መደልደል ውል ከፊብሪካው ጋር ለተዋዋለ ባቱ ኮንስትራክሽን አ.ማ ለማስገኘት እና በፊብሪካው ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ ድርጊቱን ፈጽሟል በማለት ከመግለጽ በቀር በእርግጥም አመልካች መንግስታዊ የልማት ድርጅት ከሆነው ባቱ ኮንስትራክሽን ላይ የማይገባ ጥቅም ሉያገኝ ወይም ሉያስገኝ የሚችልበት ግዙፊዊ ፍሬ ነገሮች / material facts / ያለ ስለመሆኑ ማሳየት በሚያስችል ሁኔታ ክሱን አልመሰረተም፤ ባቀረበው ማስረጃም ይህንኑ ማስረዲት አልቻለም። ስለሆነም ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ አመልካች ክሱን እንዱከላከል ብይን ላሰጥ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በዚህ አግባብ በማየት አመልካችን መከላከል ሳያሰፈልገው ከክሱ በነጻ ማሰናበት ሲገባቸው አመልካች ክሱን እንዱከላከል ብይን መስጠታቸው በመቀጠልም አመልካች ባቀረበው ማስረጃ ክሱን አልተከላከለም በማለት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና ሐምል 17 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 29 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት አመልካች መከላከል ሳይስፈልገው ከክሱ በነጻ ሉሰናበት ይገባል በማለት ወስነናል።
አመልካች በእስር የሚገኝ ከሆነ የሚመለከተው ማረሚያ ቤት አመልካች በልላ ጉዲይ የማይፈለግ መሆኑን አረጋግጦ ከእሥር እንዱለቀው ታዟል፡ በውሳኔው መሰረት ማስፈጸም ይቻለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ይድረሰው።
No topics extracted.