የመድን ሽፊን ለተሰጠው ከቀረጥ ነጻ የገባ ተሽከርካሪ ጉዲት ሲደርስበት የመድን ሽፊን ሰጪው ከደንበኛው ጋር በገባው የመድን ውል ላይ ስለቀረጥ እና ታክስ የመድህን ሽፊን ለመስጠቱ በውለ ላይ ቢገለጽም ባይገለጽም፤ የመድን ሽፊን ሰጪው ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ቀረጥ እና ታክስ ለሚመለከተው ለመንግስት አካል፤ ቀረውን ለደንበኛው መክፈለ በህግ የተጣለበትን ግዳታ መወጣቱን የሚያሳይ እና ይህ እስከተረጋገጠ ድረስ ለጉዲቱ ሀላፉነት ያለበት ወገን የተከፈለውን ቀረጥ እና ታክስ ለመተካት ከህግ የመነጨ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 129 እና 130/3 እንዱሁም ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ጉዲት የደረሰባቸውን ተሸከርካሪዎችን የቀረጥ እና ታክስ አከፊፈል ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 52/2003 አንቀጽ 5/1 እና አንቀጽ 14/1 የአደጋ መነሻ ክፍያን በሚመለከት የአደጋ መነሻ መሰላት ያለበት የመድን ሽፊን ከተሰጠው አጠቃላይ የተሽከርካሪ ዋጋ ላይ ነው ወይስ አደጋው በደረሰ ወቅት ባለው የተሽከርካሪ ዋጋ ላይ ነው በሚል ለሚነሳ ክርክር እልባት ለመስጠት የውለን ይዘት መሰረት በማድረግ ውሳኔ የሚሰጥ ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክስዮን ማህበር እና አቶ ገ/ስላሴ በየነ
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክስዮን ማህበር - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ገ/ስላሴ በየነ - ጠበቃ ብርሃኑ ተሻገር **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በዋነኛነት የመድን ሽፊን ለተሰጠው ከቀረጥ ነጻ የገባ ተሽከርካሪ ጉዲት ሲደርስበት የመድን ሽፊን ሰጪው ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ቀረጥ እና ታክስ ለመንግስት ቢከፍል የከፈለውን ቀረጥ በጉዲቱ ኃላፉነት ያለበት ወገን እንዱተካለት መጠየቅ የሚችል መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ፤ አቶ ተስፊዬ ገብረመድህን 2ኛ ተከሳሽ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት 3ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. አሻሽል ባቀረበው ክስ ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በነበሩት በ2ኛ ተከሳሽ ጥፊት በደንበኛዬ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት ደርሷል። የጉዲቱ መጠን በባለሙያ ሲገመት 57.62 በመቶ የነበረ በመሆኑ ተሽከርካሪው ሙለ ውድመት(total loss) እንደደረሰበት በመቁጠር መድን ከተገባለት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ብር 1,300,000 የአደጋ ተቀናሽ ብር 65,000 ሲቀነስ የካሳው መጠን ብር 1,235,000 ይሆናል። አመልካች ካሳውን ከተሽከርካሪው ለሚፈለግ ቀረጥ እና ታክስ ብር 283,363.43 ለኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን እንዱሁም ብር 951,636.57 ደንበኛዬ ለሆነው ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ ባለቤት ከፍያለሁ። የተሽከርካሪው ቅሪተ አካል ብር 489,288.67 የተሸጠ በመሆኑ ይህ ገንዘብ ለካሳ ከተከፈለው ገንዘብ ላይ ሲቀነስ የሚቀረው ብር 745,711.33 ይሆናል። በመሆኑም ለጉዲት ገማች የተከፈለ ብር 2,593.25 እና ለመኪናው ከአደጋ ቦታ ማስነሻ የተከፈለ ብር 1,545 ጨምሮ በድምሩ ብር 749,849.58 ተጠሪ ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድነት እና በነጠላ እንዱከፍለ የስር 3ኛ ተከሳሽም ለተጠሪ ተሸከርካሪ በሰጠው የሶስተኛ ወገን መድን ሽፊን መጠን ልክ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ በግንቦት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ ጉዲቱ የደረሰው በ2ኛ ተከሳሽ ጥፊት መሆኑ በማስረጃ አልተረጋገጠም። የጉዲት መጠኑ ተጠሪን ሳያሳትፍ መሰራቱ ከህግ ውጪ ነው። ካሳ መከፈል ያለበት አደጋው በደረሰ ወቅት ባለው የተሽከርካሪ ዋጋ ልክ ነው። ተሽከርካሪው ጉዲት በደረሰበት ወቅት ከቀረጥ ነጻ የገባ በመሆኑ እና አመልካች ሉከፍል የማይገባውን ቀረጥ እና ታክስ የከፈለ በመሆኑ ተጠሪ ለቀረጥ እና ታክስ የተከፈለውን ገንዘብ የመተካት ግዳታ የለብኝም። የአደጋ ተቀናሽም አጠቃላይ የመድን ሽፊን ከተሰጠው 1,400,000 ብር 5 በመቶ 70,000 ላሆን ሲገባ አመልካች ብር 65,000 ብቻ ተቀናሽ ማድረጉ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የስር 2ኛ ተከሳሽ በጋዜጣ ተጠርተው ያልቀረቡ በመሆኑ ክርክሩ በላለበት ታይቷል። 3ኛ ተከሳሽ በበኩለ ለተጠሪ ተሽከርካሪ እስከ ብር 200,000 የመድን ሽፊን መስጠቱን፤ ከዚህ ላይ ብር 8,406 ለኢትዮ ቴላኮም መክፈለን እና የሚቀረው ብር 191,593.66 ብቻ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ጉዲቱ የደረሰው በ2ኛ ተከሳሽ ጥፊት መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ለደረሰው ጉዲት ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሻሽ በአንድነት እና በነጠላ ኃላፉነት አለባቸው። አመልካች የመድን ሽፊን የሰጠው ተሽከርካሪ አደጋ በደረሰበት ወቅት የገበያ ዋጋው ግምት በባለሙያ ተሰልቶ በቀረበው መሰረት ካሳው ብር 1,275,000 ላሆን ይገባል። አደጋ መነሻ መሰላት ያለበት አጠቃላይ የመድን ሽፊን በተሰጠው የገንዘብ መጠን ላይ ላሆን ስለሚገባ ተቀናሽ ላደረግ የሚገባው ብር 70,000 ነው። አመልካች የተሽከርካሪውን ቀረጥና ታክስ ለመንግስት እንዱከፍል ግዳታ የሚጥልበት ህግም ሆነ ውል በላለበት የከፈለ በመሆኑ ይህ ገንዘብ ለአመልካች ሉተካ አይገባም። አመልካች ለጉዲት ገማች እና ለተሽከርካሪው ማስነሻ የከፈለው ገንዘብ ሉተካለት ይገባል። በመሆኑም ከተሸከርካሪው የገበያ ዋጋ ብር 1,275,000 ላይ የአደጋ ተቀናሽ ብር 70,000፤ ቅሪተ አካል በመሸጥ የተገኘው ብር 489,288.67 እና አመልካች ለግብር የከፈለው ብር 283,363.43 በድምሩ ብር 842,652,10 ተቀናሽ ተደርጎ ብር 436,486.48 ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ በአንድነትና በነጠላ ለአመልካች ይክፈለ። የስር 3ኛ ተከሳሽም 191,593.66 ተጠሪን ተክቶ ለአመልካች ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች ለቀረጥ እና ታክስ የከፈለው ገንዘብ ሉተካለት አይገባም መባለን እና የአደጋ ተቀናሽ ብር 70,000 ላሆን ይገባል መባለን በመቃወም ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ቀረጥና ታክስን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 52/2003 አንቀጽ 5/1 ማንኛውም መድህን ሰጪ ከቀረጥ ነጻ ለገባ ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና ሲሰጥ የተገባው ዋስትና ለቀረጡ ጭምር መሆኑን ማረጋገጥ እንዲለበት እና የመድን ውለ የማያረጋግጥ ከሆነ ግን ለቀረጥ እና ታክሱ አከፊፈል መድህን ሰጪው ተጠያቂ እንደሚሆን ተመልክቷል። አመልካች ታክስን ጨምሮ የመድህን ሽፊን ለመስጠቱ በውለ ላይ ያላረጋገጠ በመሆኑ ቀረጥና ታክስ መክፈለ ተገቢ አይደለም። አደጋ ተቀናሽም በመድን ፕሉሲው መሰረት መታሰብ ያለበት የመድን ሽፊን ከተገባለት አጠቃላይ ዋጋ ላይ ላሆን ስለሚገባ ተቀናሽ መደረግ ያለበት 70,000 ነው መባለ ተገቢ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም የሚከተለውን የሰበር ቅሬታ አቅርቧል።
አመልካች በነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ጽፍ ባቀረበው የሰበር ቅሬታ በመድን ውለ ላይ ሽፊን የሰጠሁት የተሽከርካሪውን ቀረጥ እና ታክስ ጨምሮ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የአደጋ ተቀናሽም በመድን ውለ መሰረት ሉታሰብ የሚገባው ከሚከፈለው የካሳ መጠን ላይ በመሆኑ ብር 65,000 ተቀናሽ ማድረጌ ተገቢ ሆኖ እያለ ብር 70,000 ሉቀነስ ይገባል መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት ጠይቋል።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ አመልካች ለደንበኛው ካሳ የከፈለው የመድህን ፕሉሲውን ተከትል ነው አይደለም? የሚለውን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች የመድን ውለ የተሽከርካሪውን ቀረጥ ይጨምራል በማለት ያቀረበው ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የኢንሹራንስ ፕሉሲው የተሽከርካሪው ግምት የመለዋወጫ እቃን የሚጨምር መሆኑን ከመግለጹ ውጪ ቀረጥና ታክስን የሚጨምር ስለመሆኑ አያመለክትም። አደጋ ተቀናሽም ሉሰላ የሚገባው የመድን ሽፊን ከተሰጠው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ላይ ላሆን ይገባል መባለ የመድን ውለን የተከተለ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም በጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው ጉዲት የደረሰበት የአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ከቀረጥ ነጻ የገባ መሆኑ፤
ተሽከርካሪው ጉዲት ከደረሰበት በኋላ አመልካች ለደንበኛው ከሚከፍለው የካሳ መጠን ላይ ተቀናሽ በማድረግ ለመንግስት ቀረጥ እና ታክስ የከፈለ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ይህ ከቀረጥ ነጻ የገባ ተሽከርካሪ ጉዲት ሲደርስበት ቀረጥና ታክሱ በአመልካች ለመንግስት መከፈል ነበረበት ወይስ አልነበረበትም የሚለው ነው? ለዚህ ነጥብ ምላሽ ለመስጠት ከቀረጥ ነጻ መብት ያስፈለገበትን አላማ እና የመብቱ ተጠቃሚ ማን እንደሆነ መመርመሩ ተገቢ ነው። በጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 129 እና 130 ስለቀረጥና ታክስ ነጻ መብት አሰጣጥ እና ከቀረጥ ነጻ በገባ ተሽከርካሪ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ከቀረጥ ነጻ እንዱያስገባ የተፈቀደለት አካል ብቻ መሆኑን ተደንግጓል። እንደዚሁም ከቀረጥ ነጻ የገባ እቃ የጠፊ ወይም ጉዲት የደረሰበት እንደሆነ አስመጪው ለባለስልጣኑ ይህንኑ ማሳወቅ እንዲለበት በአዋጁ አንቀጽ 130/3 ላይ ተመልክቷል። ይህ የማሳወቅ ግዳታ በአስመጪው ላይ የተጣለበት አላማ ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ የገባ ተሽከርካሪ ጠቅላላ ጉዲት ደርሶበት ከጉዲት አድራሹ ወይም ከመድን ሰጪው ካሳ ሲከፈለው የሚከፈለው ካሳ ቀረጥ እና ታክስን ጨምሮ የተሽከርካሪውን የገበያ ዋጋ ይከፈለዋል ተብል ስለሚታሰብ በቀረጥ ነጻ መብት ተሽከርካሪውን ያስገባው ሰው በካሳ መልክ ቀረጥ እና ታክስን አብሮ በመቀበል አላግባብ እንዲይበለጽግ ለመከላከል ብልም ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ መብት ከታለመለት አላማ ውጪ እንዲይውል ለማድረግ ነው። ስለዚህ አስመጪው ከቀረጥ ነጻ የገባው ተሽከራካሪ ጉዲት ደርሶበት ከመድን ሰጪው ካሳን ሲቀበል የካሳው መጠን ግብር እና ታክሱንም የሚጨምር በመሆኑ ለጉዲት ኃላፉ የሆነ ወገን ቀረጥ እና ታክሱን ለመድህን ሰጪው ለመተካት ከህግ የመነጨ ኃላፉነት ይኖርበታል።
በተጨማሪም ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ጉዲት የደረሰባቸውን ተሸከርካሪዎች የቀረጥ እና ታክስ አከፊፈል ሁኔታ ለመወሰን በሚኒስቴሩ መመሪያ ቁጥር 52/2003 ወጥቶ በስራ ላይ ውሎል። በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5/1 ከቀረጥ ነጻ ለገባ ተሽከርካሪ የመድን ሽፊን ሲሰጥ የመድን ሽፊን ዋስትናው ቀረጥ እና ታክሱን የሚጨምር መሆኑን በመድን ውለ ላይ መገለጽ እንዲለበት እና በመድን ውለ ላይ ካልተገለጸ የመድን ሽፊን ሰጪው ለተሽከርካሪው ቀረጥ እና ታክስ ኃላፉ እንደሚሆን ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው የመድን ሽፊን ውለ በተሽከርካሪው ባለቤት እና በኢንሹራንስ ዋስትና ሰጪው መካከል የሚደረግ በመሆኑ ስለቀረጥና ታክሱ በመድን ውለ ላይ ሳይገለጽ በመቅረቱ ኢንሹራንሱ የተሽከርካሪውን ቀረጥ እና ታክስ ከጉዲት ካሳ ወይም ከተሽከርካሪው ዋጋ ላይ ተቀናሽ ሳያደርግ ለደንበኛው ቢከፍል ለቀረጥ እና ታክሱ መድን ሰጪው ለመንግስት ተጠያቂ እንደሚሆን አመላካች ነው። መድን ሰጪው ለደንበኛው ከሚከፍለው የካሳ መጠን ላይ ግብር እና ታክሱን ተቀናሽ አድርጎ ለመንግስት ከከፈለ በመድን ውለ ላይ ስለቀረጥ እና ታክስ መጠቀስ አለመጠቀሱ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። በልላ አባባል በመድን ውለ ላይ የመድን ሽፊኑ የተሽከርካሪውን ቀረጥ እና ታክስ የሚጨምር መሆኑን መግለጽ ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ግብር ሰብሳቢው አካል በቀላለ ከተሽከርካሪው የሚፈለገውን ግብር ካሳ በሚከፈልበት ጊዜ ከመድን ሰጪው መሰብሰብ እንዱያስችለው እንጂ በመድን ውለ ላይ ካልተገለጸ በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰው ጉዲት ሃላፉነት ያለበት ወገን ለመድን ሰጪው ግብር እና ታክሱን የመተካት ግዳታ ያስቀርለታል ማለት አይደለም። በተጠቀሰው መመሪያ አንቀጽ 14/1 ከቀረጥ ነጻ የገባ ተሽከርካሪ ሙለ ለሙለ እንዱወድም ምክንያት የሚሆነው ሰው ለቀረጥ እና ታክሱ ኃላፉነት እንዲለበት መገለጹ ለቀረጥ እና ታክሱ ክፍያ የመጨረሻ ኃላፉነት ያለበት ለጉዲቱ ኃላፉ የሆነው ሰው መሆኑን የሚያመላክት ነው። በመሆኑም በመድን ውለ ላይ ስለቀረጥ እና ታክስ ባይገለጽም እንኳን የመድን ዋስትና ሰጪው ከቀረጥ ነጻ ለገባው ተሽከርካሪ ቀረጥ እና ታክሱን ጉዲት ከደረሰበት ተሽከርካሪ የገበያ ዋጋ ላይ በመቀነስ መክፈለ እስከተረጋገጠ ድረስ ለጉዲቱ ኃላፉነት ያለበት ወገን መድህን ሰጪው የከፈለውን ቀረጥ እና ታክስ የማይተካበት የህግ አግባብ የለም።
በተያዘው ጉዲይ ጉዲት የደረሰበት የአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አደጋ በደረሰበት ወቅት የገበያ ዋጋው ምን ያክል እንደሆነ ታክስን ጨምሮ እና ታክስን ሳይጨምር ተገምቶ ቀርቧል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ታክስን ጨምሮ የቀረበውን ግምት ብር 1,235,000 መቀበለን የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል። ከዚህ የተሽከርካሪው አጠቃላይ ግምት ላይ አመልካች ግብር እና ታክሱን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ቀረውን ለደንበኛው መክፈለ ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ የተጣለበትን ግዳታ መወጣቱን ከሚያሳይ በስተቀር ግዳታ ሳይኖርበት ከፍሎል የሚያስብል አይደለም።
አመልካች ከደንበኛው ጋር በገባው የመድን ውል ላይ ስለቀረጥ እና ታክሱ ቢገለጽም ባይገለጽም አመልካች ቀረጥ እና ታክሱን መክፈለ መረጋገጡ በቂ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠሪ የመድን ውለ ቀረጥ እና ታክስ ይጨምራል የሚል ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያላነሳው በመሆኑ በዚህ ሰበር ደረጃ ሉነሳ አይችልም በማለት ተከራክረዋል። በእርግጥ በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ የፍሬ ነገር ክርክር በይግባኝ ወይም በሰበር ደረጃ ሉነሳ እንደማይችል በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 329/1 ላይ ተመልክቷል። ነገር ግን ከላይ እንደተገለጸው በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበት ወገን ለቀረጥ እና ታክሱም ኃላፉነት እንዲለበት በጉምሩክ አዋጁ እና በመመሪያ የተደነገገ በመሆኑ በመድን ውለ መገለጽ አለመገለጹ ከጉዲት አድራሹ አንጻር የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ቀረጥ እና ታክስ የመክፈል ግዳታ ሳይኖርበት የከፈለ በመሆኑ በተጠሪ ሉተካለት አይገባም ማለታቸው መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ላላው የአመልካች የቅሬታ ነጥብ የአደጋ መነሻ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው 5 በመቶ የአደጋ መነሻ መሰላት ያለበት የመድን ሽፊን ከተሰጠው አጠቃላይ የተሽከርካሪ ዋጋ ላይ ነው ወይስ አደጋው በደረሰ ወቅት ባለው የተሽከርካሪ ዋጋ ላይ ነው የሚለው ነው። ለዚህ ነጥብ እልባት ለመስጠት የውለን ይዘት መመልከት ተገቢ ነው። የአደጋ መነሻ ክፍያን በተመለከተ በመድን ውለ ላይ ‛birr 5000 or 5/100 0f the repair cost in the case of partial loss or 5/100 of the sum insured or the market value in case of total loss, whichever is higher“ በሚል ተቀምጧል።
ይህም ማለት ተሽከርካሪው አጠቃላይ ውድመት(total loss) ከደረሰበት የአደጋ መነሻ 5/100 የሚታሰበው የመድን ሽፊን በተሰጠው አጠቃላይ ገንዘብ እና አደጋው በደረሰ ሰአት በተገመተው የተሸከርካሪ የገበያ ዋጋ መካከል ከፍተኛ ከሆነው ላይ እንደሆነ አመላካች ነው። ይህም ማለት በተያዘው ጉዲይ የመድን ሽፊን የተሰጠው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ብር 1,400,000 ከተሽከርካሪው የገበያ ዋጋ የሚበልጥ በመሆኑ የተቀናሽ ክፍያው መታሰብ ያለበት ከዚሁ ከአጠቃላይ የገንዘብ መጠን ላይ ነው።
በዚህ የገንዘብ መጠን ላይ ሲታሰብ 5/100 ብር 70,000 ይሆናል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የአደጋ መነሻ ብር 70,000 መቀነስ ነበረበት በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የመድን ውለን መሰረት ያደረገ ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ12/04/2011 ዓ.ም. እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ29/07/2012 ዓ.ም. የሰጡት ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽለዋል።
2ኛ. አመልካች ጉዲት ለደረሰበት ተሽከርካሪ የከፈለውን ቀረጥ እና ታክስ ብር 283,363.43 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺ ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከአርባ ሶስት ሳንቲም) ተጠሪ ለአመልካች ሉተኩ ይገባል ብለናል። ላላው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አልተነካም።
3ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.