በባልና ሚስት ንብረት ክርክር የጋራ ንብረት የሆነውን የግል የሚያደርግ፤ የግል የሆነውን ንብረት የጋራ የሚያደርግ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ህጋዊነት የላለው ስለመሆኑ የአማራ ብ/ክ/መ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 97(1) እና አንቀጽ 101
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 24/5/2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች- ወ/ሮ አሰለፈች ዘነበ - ጠበቃ ግርማ ጌታቸው ተጠሪ- አቶ ቀጸላ አበበ - ቀረቡ መዜገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዙህ የሰበር መዜገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03- 91413 የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው። ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዜርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የምትለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር በጋራ ያፈራሁትን የጋራ ንብረት የተጠሪ የግል ንብረት የሚያደርገውንና የግል ንብረቴን የጋራ የሚያደርገውን በወረዲ ፍ/ቤት የጸደቀው ስምምነት መብቴን የሚጎዲ ለህሉናና ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ እያለ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 3316 መሰረት ፈራሽ መሆን ሲገባ ስምምነቱ መፍረስ የለበትም ብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሁም የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/3 እና 03-94947 ላይ በአንድ ጉዲይ የተለያዩ ውሳኔዎች በመስጠቱ ውሳኔዎቹ የሚቃረኑና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ባቀረበችው አቤቱታ ከአሁን ተጠሪ ጋር የነበረን ጋብቻ ፈርሶ በ8/4/2010 ዓ/ም ያደረግነው ስምምነት በ12/4/2010 ዓ/ም በዋለው ችልት የጸደቀው 1. በክሴ ላይ ያልጠየኩትን ከጋብቻ በፉት በግላ ያፈራሁትን ንብረት ዲኝነት ሳይጠየቅበት በስምምነቱ የጋራ ንብረት እንዱሆን የተደረገ በመሆኑ 2. በክሴ ላይ የገለጽኩትን ንብረቶች ላይ ምንም ሳይባል ፍ/ቤቱ የእርቅ ስምምነቱን በማጽደቅ መዜገቡን መዜጋቱ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ስለሆነ ይፍረስልኝ ስትል በ25/10/2010 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ ጠይቃለች። የአሁን ተጠሪም በ8/4/2010 ዓ/ም ፈቅደን በመረጥነው ሽማግላዎች የንብረት ከፍፍል ተደርጎ ስምምነቱ የጸደቀ በመሆኑ እና ይህ የጸደቀው ስምምነት ባልተሻረበት ሁኔታ የጸደቀ ስምምነት ይሻርልኝ ስትል ያቀረበችው አቤቱታ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ።
በጅምር ላይ ያለ ቤት ተጠናቆ እንድንካፈል የተስማማነው ህጋዊ አይደለም የሚያስብል ባለመሆኑ አቤቱታዋ ውድቅ ይሁንልኝ ሲል መልስ ሰጥቷል። የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት አከራክሮ በ19/2/2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በግራ ቀኙ ቀርቦ የጸደቀው ስምምነት ሉፈርስ አይገባም ሲል የአሁን አመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። የአሁን አመልካች ለሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ አከራክሮ በመ/4 ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የወረዲ ፍ/ቤት በ19/2/2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር በ8/4/2010 ዓ/ም በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል ተደርጓል የተባለው ስምምነት ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ አጣርቶ እንዱወስን ለወረዲ ፍ/ቤት መልሶታል። የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/7/10 ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ በ8/4/2010 ዓ.ም ግራ ቀኙ ያደረጉት ስምምነት የጋራ ንብረት ነው በማለት የተማመኑበትን ቤት ተጠሪ የጋራ ንብረታቸው የሆኑትን 3 ፈረሶች ሸጦ ቤቱን በመጨረስ በ30/4/2011 ዓ/ም ሉካፈለት ነው። እንዱሁም ተጠሪ የጋራ ንብረት ናቸው ብላ ዘርዜራ ያቀረበችውንና የልጅ አስተዲደግ ላይም ምንም ሳይልበት መዜገቡ ተዘግቷል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 274(2) እርቅ ወይም ግልግል ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻልና የፍ/ብ/ህግ 3307 እስከ 3324 የተደነገጉት ካልተሟላ እርቅ ወይም ግልግል መፍረስ የሚችል መሆኑን ነው። የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 3309 መብት መተው የሚዲርጉ የግልግል ቃልች በጠባቡ ሉተረጎሙ እንደሚገባ ይደነግጋል። የአማራ ብ/ክ/መ. የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 101(1) የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለእኩል መካፈል አንዲለበት ይደንግጋል። ተጠሪ በመልሱ የጋራ ንብረት መሆኑን ያመነውን ከጋራ ንብረት ውጪ ማድረጉ የሴቶችን ህገ መንግስታዊ የእኩልነት መብት የሚጋፊ ነው። በመሆኑም በ8/4/2010 ዓ/ም የተደረገው ስምምነት ከፍትህ አንጻር ለህግና ለሞራል የሚቃረን በመሆኑ ፈራሽ ነው። ግራ ቀኙ በቀድሞ ክስ መሰረት ክርክር እንዱቀጥለ ሲል ወስኗል። የአሁን ተጠሪ ለሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/8 መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ትእዚዜ የወረዲ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል። የአሁን ተጠሪ ለአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ አከራክሮ በመ/ቁጥር 03-91413 የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኙ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 3309 እና ተከታዮቹ መሰረት በሽማግላ የእርቅ ስምምነት ውለን ከመጽደቁ በፉት ለህግና ለሞራል ተቃራኒ መሆን አለመሆኑ መመርመር ሲገባ ታልፎል የሚል ሆኖ በወረዲ ፍ/ቤት የጸደቀ የእርቅ ስምምነት ሉሻር አይገባም ሲል መጀመሪያ ሰጥቶ የነበረው ብይን በአግባቡ ነው። ነገር ግን የዝኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ቀርቦለት ተመላሽ ማድረጉና የወረዲ ፍ/ቤት ሉፈርስ ይገባል ሲል የሰጠው ውሳኔ እና የከፍተኛው ፍ/ቤት አያስቀርብም ማለቱ ህጉን የተከተለ አይደለም። የአሁን አመልካች ያደረኩት ስምምነት መጽደቁና መዜገቡ መዘጋቱ ተገቢ አይደለም ካለች ይግባኝ በማለት ማሳረም አንጂ የጸደቀ እርቅ እንደ ውሳኔ ስለሆነ በእራሱ ሉሽረው ስለማይገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዚዜ እና የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል። በወረዲ ፍ/ቤት በ8/4/2010 ዓ/ም የጸደቀው እርቅ ሉሻር አይገባም ሲል ወስኗል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርባለች። መዜገቡም ተመርምሮ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአመልካችና ተጠሪ መካከል የተፈጸመው የእርቅ ስምምነት በፍ/ቤት የጸደቀ በመሆኑ በይግባኝ ከማሻር በስተቀር ሉፈርስ አይችልም ሲል የወሰነበትን አግባብ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታዋን በማጠናከር ተከራክራለች።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ቀደም ብል ከአሁን ተጠሪ ጋር በነበራቸው የባልና ሚስት ንብረት ክርክር በ8/4/2010 ዓ/ም የተጻፈ የንብረት ክፍፍል ስምምነት በአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ በ12/4/2010 ዓ/ም በዋለው ችልት አጽድቋል። የአሁን አመልካች ይህን የወረዲው ፍ/ቤት በ12/4/2010 ዓ/ም በዋለው ችልት ስምምነታቸውን በማጽደቅ የሰጠውን ትእዚዜ ይፍረስልኝ ስትል በ25/10/2010 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ ጠይቃለች። የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤትም በ19/2/2011 ዓ/ም በዋለው ችልት አቤቱታዋን ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል። የአሁን አመልካች ይህን የወረዲ ፍ/ቤት ውሳኔ ለሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባበት አከራክሮ በመ/4 ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት በ19/2/2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔን በመሻር በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል በ8/4/2010 ዓ/ም የተደረገው የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ስምምነት ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ ይዝ አከራክሮ እንዱወስን ለወረዲ ፍ/ቤት መልሶታል። አንድ ፍ/ቤት የሰጠውን ትእዚዜ ወይም ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 6፣ 78፣ 358 ውጪ ውሳኔው ፍትሐዊ አይደለም በሚል በሚቀርብለት አቤቱታ የራሱን ትእዚዜ ወይም ውሳኔ የሚሽርበት የህግ አግባብ የለም። ይሁንና ይህን የሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ የአሁን ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦበት ያላሻረውና ውሳኔው እንደጸና የሚገኝ፣ የአሁን ተጠሪ ይህን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ተቀብል አንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት ተመልሶ የከፍተኛ ፍ/ቤት በመለሰው ጭብጥ መሰረት ተከራክሮ ወረዲው ፍ/ቤትም በተመለሰለት ጭብጥ መሰረት አከራክሮ ውሳኔ ሰጥቶበታል። ከዙህ በኋላ ያለው ክርክር የአሁን አመልካችና ተጠሪ ያደረጉትን የንብረት ክፍፍል ስምምነት ተቀብል የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት በማጽደቅ የሰጠው ውሳኔ ሉሻር ይገባል ወይስ አይገባም የሚል ሳይሆን በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል የተደረገው ስምምነት ተቀባይነት ሉኖረው ይገባል ወይስ አይገባም የሚል ክርክር ነው። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ብል የሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/4 ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በፍሬ ነገር አከራክሮ የሰጠውን ውሳኔና ይግባኝ ባልተባለበት ባለቀ ጉዲይ ተጠቅሞ በኋላ የከፍተኛ ፍ/ቤት ጭብጥ ይዝ በመለሰው መሰረት ተጣርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መሻሩ ሥነ ሥረዓታዊ ሆኖ ባለመገኘቱ ሉታረም የሚገባው ነው። በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል ታህሳስ 8 ቀን 2010 ዓ/ም በተጻፈ ስምምነት የተደረገውን የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል በተመለከተ የአማራ ብ/ክ/መ. የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 97(1) ባል ወይም ሚስት የግለ መሆኑን በማስረዲት የግል ሀብቱ የሆነውን ንብረት መልሶ የመውሰድ መብት እንዲለው ይደነግጋል። የአማራ ብ/ክ/መ. የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 101 ከዙህ በላይ የተመለከቱት የባልና ሚስት ሀብትን በስምምነት ስለመከፊፈል የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም ተጋቢዎች እኩል የሚከፊፈል እንደሚሆን ደንግጓል። በዙህ መሰረት የአሁን አመለካችና ተጠሪ ያደረጉት ስምምነት የጋራ ንብረት የሆነውን የግል የሚያደርግና የግል የሆነውን ንብረት የጋራ የሚያደርግ ስምምነት በክልለ የቤተሰብ ህግ በተጠቀሰው መሰረት ለህጉ ተቃራኒ ሆኖ የሚገኝ ነው። በመሆኑም የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል ታህሳስ 8 ቀን 2010 ዓ/ም የተጻፈ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ስምምነት ውድቅ ማደረጉ ተገቢ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-91413 የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሰሜን ሸዋ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/8 መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዚዜ እና የአንጎለላና ጠራ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/7 ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በዙህ መዜገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዙህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዜገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.