ስለ ጋብቻ መፍረስ በተመለከተ ውሳኔ የመስጠት ወይም የማጽደቅ ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ቢሆንም ባልና ሚስት ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የራሳቸውን ህይወት በየፉናቸው በመኖራቸው ጋብቻው የተቋረጠ በመሆኑ ተለያይተው ስለኖሩ ብቻ ጋብቻ በሁኔታ የለም በሚል ከፍርድ ቤት አቶ ፍቃደ ገብሬ እና ወ/ሮ እመቤት ኃይለ 253 ውጪ የጋብቻ ፍቺ አለ በሚል የሚስጥ ውሳኔ ተፈጻሚነት የላለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 75 እና የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የፋደሬሽን ም/ቤት በመ/ቁጥር 50/10 ኛ የፒርላማ ዘመን፣ አምስተኛ ዓመት፣ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ የተሰጠ ውሳኔ
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 25/4/2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ ፍቃደ ገብሬ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ እመቤት ኃይለ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው። ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የሚለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በአመልካችና ተጠሪ መሀል በህግ የሚታወቅ ጋብቻ እያለ በመንግስት ሥራ ምክንያት ወደ ሀዋሳ የሄድኩና ከማገኘው ደሞዝ ቤተሰቦቼን እየረዲሁ የቆየሁ ሆኖ ሳለ በከሳሽና ተከሳሽ መሀከል ጋብቻ የለም ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የአሁን አመልካች ባቀረበው ክስ ከተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ጋር በ1990 ዓ/ም ተጋብተናል። በትዲር ውስጥ በጋራ ያፈራናቸው ንብረቶች አለን። ይሁንና ተከሳሽ በመሀላችን በተፈጠረ አለመግባባት ከቤት ያስወጣችን በመሆኑ ጋብቻችን ፈርሶ በጋራ ያፈራነው ንብረቶችን ታካፍለኝ ሲል ጠይቋል። ተከሳሽም ከከሳሽ ጋር ተጋብተን 3 ልጆች መውለዲችን እውነት ነው። ይሁንና ከሳሽ 2000 ዓ/ም ትቶን ሄዶል። አድራሻው እንኳ አይታወቅም። ልጆቻችንን ምንም ሳይረዲኝ ያሳደኩት እኔ ነኝ። አሁን ንብረት ለመካፈል ፍለጋ የመጣና ከሄደ ከ12 ዓመት በኋላ የመጣ በመሆኑ ጋብቻቻን ፈርሷል። ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥታለች። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ የኢፋዳሪ የተሻሸለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 53(1 እና 2) ተጋቢዎች አብረው የመኖርና መደበኛውን የጋብቻ ግዳታ መፈጸም እንዲለባቸው ይደነግጋል። ይሁንና ከሳሽና ተከሳሽ በ2000 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች በመኖር ላይ ያለ መሆኑ የተሰሙት ምስክሮች ያስረደና የጋብቻ ግዳታዎችን ከሳሽ አለመወጣቱን የሚያሳይ ነው። የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተጋቢዎች ተለያይተው ለረጅም ጊዜ መኖር እና በየፉናቸው የየራሳቸውን ህይወት መምራት በህጋዊ መንገድ ጋብቻ ተቋርጧል የሚያስብል መሆኑን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ከሳሽና ተከሳሽ ለረጅም ጊዜ ተለያይተው በመኖር በየፉናቸው የየራሳቸውን ህይወት መኖራቸው በምስከሮች የተረጋገጠ በመሆኑ እና ጋብቻቸው የተቋረጠ በመሆኑ በዚህ ፍ/ቤት የሚፈርስ ጋብቻ የለም ሲል የከሳሽን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። ከሳሽ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ትእዛዝ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል። መዝገቡም ተመርምሮ በአመልካችና ተጠሪ መካከል ያለው ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል በማለት የተወሰነበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ቀርቧል።
መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ሐምል 23 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ስትል ተከራክራለች።
አመልካችም መስከረም ወር 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 75 ስለ ጋብቻ መፍረስ በተመለከተ ውሳኔ የመስጠት ወይም የማጽደቅ ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ እንደሆነ ደንግጎ ይገኛል። በስር ፍ/ቤቶች በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለን ጋብቻ እንዱፈርስልኝ ሲል ላቀረበው ክስ ተጠሪ ለረጅም ጊዜ ከአመልካች ጋር ተለያይተው የኖሩ በመሆኑ ጋብቻችን ፈርሷል ስትል ላቀረበችው ክርክር የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካችና ተጠሪ ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የየራሳቸውን ኑሮ መስርተው ይኖሩ የነበሩ መሆኑ በመረጋገጡ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ባልና ሚስት በመለያየት ሀሳብ ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የየራሳቸውን ኑሮ መስርተው የሚኖሩ ከሆነ ጋብቻ በሁኔታ የፈረሰ መሆኑን አስገዲጅ የህግ ትርጉም በሰጠው መሰረት የአሁን አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሲል ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም አያስቀረብም ብልታል። የስር ፍ/ቤቶች በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሲለ ውሳኔ የሰጡት የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ እና ላልችም መዝገቦች ላይ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት አድርገው ቢሆንም የኢፋዱሪ የፋደሬሽን ም/ቤት በመ/ቁጥር 50/10 መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ/ም 5ኛ የፒርላማ ዘመን፣ አምስተኛ ዓመት፣ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ይህን ውሳኔ ህገ መንግስታዊ ባለመሆኑ ተፈጻሚነት እንዲይኖረው ውሳኔ ሰጥቶበታል። በመሆኑም ባልና ሚስት ተለያይተው ስለኖሩ ብቻ ከፍ/ቤት ውሳኔ ውጪ የጋብቻ ፍቺ አለ ለማለት የህግ መስረት ያለው አይደለም። በተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ ድንጋጌ መሰረት በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ ስለመፍረሱ የቀረበ ማስረጃ ሳይኖር የስር ፍ/ቤቶች በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሲለ የሰጡት ውሳኔ ሉታረም የሚገባው ነው ብለናል።
ት እ ዛ ዝ
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአሁን አመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብል የተሰጠው ውሳኔ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተሻረ በመሆኑ የአሁን አመልካች ባቀረበው የጋብቻ ፍቺ ክስ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.