ከብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በላይ ለመበደር ወይም ለማበደር ወይም ለላላ ሰዉ ዋስ ለመሆን የተጋቢዎቹ ስምምነት የሕግ ግዳታን ባለማክበር አንደ ተጋቢ የውል ግዳታ ገብቶ ሲገኝ ላላኛው ተጋቢ ግዳታው እንዱፈርስ ክስ ሲያቀርብ የውል ግዳታ የገባው ተጋቢ ላላኛው ተጋቢ ግዳታ መገባቱን ያውቃል በሚል በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 ስር የተደነገገዉን የ6 ወር የይርጋ ጊዜ በመቃወሚያ የሚያቀርብ ተከራካሪ (ተጋቢ) ላላኛዉ ተጋቢ ግዳታዉ መገባቱን እንዳትና መቼ እንዲወቀ ማስረዲት የሚጠበቅበት ስለመሆኑ በአንደኛዉ ተጋቢ የዉል ግዳታ ሲገባ በስምምነቱ ተሳታፉ ያልሆነ[ዉ]ችዉ ተጋቢ ዉል ይፍረስልኝ ክስ ለማቅረብ በሚያስችል ልክ ስለዉለ መኖር የተሟላ እዉቀት ሉኖረዉ(ልኖራት) ስለሚገባ በአንደኛዉ ተጋቢ የተደረገ የገንዘብ ብድር ዉል መኖሩን ላላዉ/ዋ ተጋቢ አወቀ/አወቀች ልባል/ልትባል የሚችለዉ/የምትችለዉ ቢያንስ የገንዘብ ብድር ዉለ ከማን ጋር እንደተደረገ፣ የምን ያህል ገንዘብ ብድር ዉል እንደሆነ፣ መቼ የተደረገ የብድር ዉል እንደሆነ ማወቅ ሲችል/ስትችል ስለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) ፣ 80(2-4)፣85 እና 222/1፣ 258-260 እንዱሁም የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001/1 የጋብቻ ፍቺ ተከትል በሚደረገዉ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጊዜ ካልሆነ በቀር በተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 68/መ እና 69/1 መሰረት የገንዘብ ብድር ዉል ሲደረግ ያልተሳተፈ ተጋቢ የብድር ዉለ እንዱፈርስ ለመጠየቅ ምክንያት ሉያደርግ የሚገባዉና ዉለ እንዱፈርስ ከመወሰኑ በፉት በፍሬ ነገር ደረጃ ሉረጋገጥ የሚገባዉ በገንዘብ ብድር ዉል ግዳታዉ በተዋዋይነት አለመሳተፈን ብቻ እንጂ ከዚህ ዉጭ ዉል ይፍረስልኝ በሚል ከሚቀርብ ክስ ጋር በተያያዘ በብድር ተገኘ የተባለዉ ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ዉሎል ወይስ አልዋለም በሚለዉ ጭብጥ ላይ በማከራከር ዉሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ
No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ዓለማየሁ አባተ(ዶ/ር)፡- ጠበቃ ዘፊኒያህ ዓለሙ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መፅሄት ዓይነኩለ፡ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለው የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አንደኛው ተጋቢ የፈጸመውን የብድር ውል ላላኛዉ ተጋቢ አውቋል ልባል የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ተጠሪ በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ በመሰረቱት ክስ ከአመልካች ጋር ተጋብተው እየኖሩ ቆይተዉ በቀን 03/06/2009ዓ/ም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ ጋብቻዉ ፈርሷል። አመልካች በጋራ ንብረት ክፍፍል ክርክር መልሳቸው ላይ በአማራ ክልል ባህር ዲር ከተማ በካርታ /97 በአመልካች ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት የተሰራው ከስር 2ኛ ተከሳሽ በተገኘ ብድር እና እዲውም አልተከፈለም በማለት መልስ የሰጠ ቢሆንም የብድር ውለ ተጠሪ ሳያውቁት የተደረገ ነው። በቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 68(1/መ) መሰረት ከብር 500 በላይ ለማበደርም ሆነ ለመበደር የተጋቢዎች የጋራ ስምምነት ያስፈልጋል። ተጠሪ የብድር ውል ስለመኖሩ አላውቅም። በብድር ተገኘ የተባለውም ገንዘብም ለትዲር ጥቅም አልዋለም።
ውለ ከቅን ልቦና ውጪ ተጠሪን ለመጉዲት የተደረገ በመሆኑ የብድር ውለ ሉፈርስ ይገባል እንዱሁም የብድር ውለ ተጠሪ ላይ የሚያመጣው ግዳታ የለም ተብል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ለክሱ በሰጡት መልስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለውም።ተጠሪ ክስ የመሰረቱበት የብድር ውል ስለመኖሩ ስለሚያውቁ ውለ መኖሩን ካወቁ ከስድስት ወር በኋላ ያቀረቡት ክስ በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብታቸው በይርጋ ቀሪ የሆነ ነው በማለት ተቃውመዋል።ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ባህርዲር ከተማ ያለ ቤት ስሰራ የገንዘብ ችግር ገጥሞኝ ተጠሪ ብድር ማግኘት ባለመቻሎ የብድር ገንዘብ ፈልገን እኔ እንድበደር ተነጋግረን ተበድሬ ቤቱን ሰርቻለሁ። በዚህ አግባብ የተገኘው ገንዘብ በባህርዲር ከተማ ያለውን መኖሪያ ቤት መስሪያ መዋለንና የብድር ውል መኖሩን ተጠሪ ታውቃለች። ከተበደርነው ገንዘብ ብር 110,000.00 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ከፍዬ ብር 340,000.00 እንደሚቀር ተጠሪ ያውቃለ። ስለሆነም ተጠሪ የብድር ውለ እሷን ለመጉዲት በማስመሰል እንደተደረገ አድርገው ውለ እንዱፈርስ ያቀረቡት ክስ በማስረጃ ያልተደገፈ እና የሕግ መሰረት የላለው ስለሆነ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 10/03/2011ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስመልክቶ በሰጠው ብይን ይርጋን በሚመለከት የቀረበውን መቃወሚያ በተመለከተ ተጠሪ ብድሩ መኖሩን ካወቀች 6 ወር አልፎል የሚለውን አመልካች ባቀረቡት ማስረጃ በተሻለ ሁኔታ አስረድተዋል። ሆኖም የብድር ውል የተደረገው በቀን 07/10/2007ዓ/ም ሲሆን ተጠሪ ክስ የመሰረቱት ደግሞ የብድር ውል ግዳታ ከተገባ ሁለት አመት ሳይሞላው በቀን 28/09/2009ዓ/ም ነው። በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 69/2 ስር በተደነገገው የሁለት አመት አማራጭ ይርጋ መሰረት የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ አልሆነም በሚል በዚህ ረገድ የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። በመቀጠልም ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ምስክሮች ሰምቶና መርምሮ በቀን 17/04/2012ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ በብድሩ ላይ አልፈረሙም።አመልካች ባቀረቧቸው ምስክሮች ብድር ስለመኖሩ እንደተነገራቸው ከመመስከራቸው ዉጪ ስለብድሩ እዉቅና ያላቸው ስለመሆኑ አላስረደም። በልላ በኩል ተጠሪ በምስክርነት ቃላቸው ቤቱ የተሰራው ከአመልካች ጋር ባፈሩት የጋራ ገንዘብ መሆኑን አስረድተዋል።በተጨማሪም መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት እየሰሩ ደመወዝ በወር 80,000.00 ሲከፈላቸዉ እንደነበር ገልጸው ቤቱ የተሰራው በዚህ ገንዘብ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል።
የአመልካች ምስክሮች ብድር ስለመኖሩም አመልካች ነግሮናል በማለት ውለ ሲፈጸምም ሆነ አመልካች ብሩን ሲበደሩ እንዲላዩ አስረድተዋል።በመሆኑም አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 71/ሐ በክሱ ላይ የተደረገው ውል ተጠሪ የማያዉቁትና ገንዘቡም ለትዲር ጥቅም ያልዋለ በመሆኑ በአመልካችና በስር 2ኛ ተከሳሽ መካከል የተደረገው የብድር ዉል በአንቀጽ 69/1 መሰረት ፈርሷል ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 06/06/2013ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የአመልካች ምስክሮች ቃል ላይ እንደተመለከተው አመልካች ብድሩን እንደወሰደ እንደነገራቸው እንጂ በእርግጥ የብድር ውለ መኖሩን በግልጽ አላስረደም። በመሆኑም በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 ስር የተመለከተውን የይርጋ ጥያቄን ለማንሳት ተጠሪ ስለብድሩ እውቅና እንዲላቸው በግልጽ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በ6 ወር ዉስጥ ክሱ አልቀረበም ብል በይርጋ ውድቅ ማድረግ ተገቢ ስለማይሆን የስር ፍርድ ቤት ከዚህ አንጻር የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው። እንዱሁም ባህርዲር ከተማ ውስጥ ያላቸው ቤት የተሰራዉ ተጠሪ ገንዘብ እየላኩ በጋራ ገንዘባቸው እንደሆነ ተጠሪ አስረድተዋል። አመልካች ደግሞ ቤቱ የተሰራው በግራ ቀኙ የጋራ ገንዘብ እንዲልሆነ በማስተባበል አላስረደም። በመሆኑም የብድር ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም አልዋለም በማለት የስር ፍርድ ቤት የብድር ውለ እንዱፈርስ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ሲል አጽንቷል።
አመልካች በቀን 23/09/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከላይ በተመለከተው መሰረት በተሰጠ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸው ይዘት በአጭሩ፡የብድር ውል ግዳታ የተገባው በ07/10/2007 ዓ/ም ነዉ። ተጠሪ በቀን 28/09/2009ዓ/ም ክስ የመሰረቱት ብድሩ መኖሩን ካወቁ ከስድስት ወር በኋላ መሆኑን አመልካች ከተጠሪ የተሻለ ማስረጃ በማቅረብ አስረድቻለሁ። የስር የፋዳራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 ስር የተደነገገዉ የ6 ወር ይርጋ ራሱን ችል የቆመ ይርጋ እንጂ ከሁለት አመት ፍጹማዊ ይርጋ ጋር ግንኙነት የላለው ሆኖ እያለ ጉዲዩን ከሁለት አመት ይርጋ አንጻር በማየት የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ አልታገደም በሚል አለአግባብ የአመልካችን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ስህተት ማረም ሲገባው አለአግባብ ማስረጃ ምዘና ዉስጥ በመግባት ብድር ዉል ግዳታ መገባቱን ተጠሪ ልታዉቅ አትችልም የሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የሰጠው ውሳኔ የክርክር አመራር በተመለከተ በሰ/መ/ የተሰጠውን የሕግ ትርጉም የሚቀረን ነዉ። በብድር ውለ ላይ በግልጽ ገንዘቡ በብድር የተወሰደው በባህር ዲር ከተማ ለምናስገነባው ቤት ለማዋል እንደሆነ ተመልክቷል። በዚህ አግባብ በብድር ውለ ላይ ተመልክቶ እያለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2006/1 ስር የተደነገገውን በሚቃረን አኳኋን በምስክሮች ለማረጋገጥ የተደረገው የክርክር አመራር ስህተት ቢሆንም አመልካች በምስክሮች ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ አስረድቻለሁ። ተጠሪ ግን ገንዘብ ለትዲር ጥቅም አለመዋለን በማስረጃ ማስረዲት አልቻለም። የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የብድር ውለ መኖሩን አታዉቅም የሚል ድምዲሜ ላይ የደረሱት በማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ወደጎን በመተው በመሆኑ ገንዘቡ ለጋራ ጥቅም ዉሎል ተብል እንዱወስንላቸው እና የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ የሆነ ነው ተብል የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመጠየቅ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ያደረጉት የገንዘብ ብድር ውል መኖሩን ተጠሪ ካወቁ ከስድስት ወር በኋላ የብድር ውለ እንዱፈርስ ክስ እንዲቀረቡ የስር ፍርድ ቤት በቀን 10/03/2011 ዓ/ም በሰጠው ብይን ላይ በገለፀበት ሁኔታ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ከቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀፅ 69/2 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 07/03/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
የቀረበውን የይርጋ ክርክር በተመለከተ ግራ ቀኙ በነበራቸው የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክስ ወቅት ለዚህ ክስ መነሻ የሆነውን የብድር ውል አመልካች የባልና የሚስት የጋራ እዲ መሆኑ ተረጋግጦ እንዱወሰንላቸው ክርክሩን ሲመለከት ለነበረው የስር ፍርድ ቤት በሚያዚያ 18/2009 ዓ/ም አቅርበው ተጠሪም የጋራ እዲ እንዱባል የቀረበው የብድር ውል ስለመደረጉ የሚያውቁት ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት የብድር ውል መደረጉን ባወቁ በስድስት ወር ውስጥ ውለ እንዱፈርስ በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃ መዝነዉ የብድር ዉል መደረጉን እንደማላውቅ ድምዲሜ ላይ የደረሱ ስለሆነ በሰበር ሰሚ ችልቱ የሚታይ አይደለም። እንዱሁም የብድር ውል መደረጉን ዉለ በተደረገ በስድስት ወራት ውስጥ አውቅ እንደነበር አመልካች አላረጋገጡም። የገንዘብ ብድሩ ለትዲር ጥቅም አለመዋለ በስር ፍርድ ቤት በቀረቡት ማስረጃዎች ተረጋግጠዋል። እንዱሁም በቤተሰብ ጉዲይ ችልት በብድር የተወሰደው ገንዘብ የጋራ እዲ እንዱባልላቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ እዲው የጋራ እዲ ነዉ ተብል የተሰጠ ውሳኔ የለም። በዚህ አግባብ ብድሩ ለትዲር ጥቅም የዋለ ነው ተብል እንዱወሰንላቸው የጠየቁት ተቀባይነት ባላገኘበት ተጠሪ የብድር ውለ እንዱፈርስ ዲኝነት በጠየቁበት መዝገብ ላይ ብድሩ ለትዲር ጥቅም የዋለ ነዉ ተብል እንዱወሰንላቸው ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም በቀን 01/04/2014 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ውሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘውን ማስቀረቢያ ጭብጥ ከግምት በማስገባት በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 68/መ ስር እንደተደነገገው በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር ከብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በላይ ለመበደር ወይም ለማበደር ወይም ለላላ ሰዉ ዋስ ለመሆን የተጋቢዎቹ ስምምነት ያስፈልጋል። ይህንኑ የሕግ ግዳታ ባለማክበር አንደ ተጋቢ የውል ግዳታ ገብቶ የተገኘ እንደሆነም ላላኛው ተጋቢ ግዳታው እንዱፈርስ ክስ የማቅረብ መብት ያለው መሆኑን በሕጉ አንቀጽ 69/1 ላይ ተመልክቷል። የክስ ማቅረቢያ ጊዜም ግዳታው መገባቱን ከአወቀበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ መሆን እንዲለበት ወይም በልላ በማንናቸውም ሁኔታ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ከሆነ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ በአንቀጽ 6 በንዐስ አንቀጽ 2 ላይ ተደንግጎ ይገኛል። በዚህ አንቀጽ ላይ የተመለከተው ሁለቱም አይነት የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚነቱ ያለአንደኛው ተጋቢ ተሳትፍ በልላኛው ተጋቢ የተገባ ግዳታ እንዱፈርስ በስምምነቱ ተካፊይ ያልሆነዉ ተጋቢ ሲጠይቅ ነዉ። እንዱሁም በዚህ ድንጋጌ ላይ የተመለከተው ሁለት አይነት የይርጋ ጊዜ ሲሆን አንደኛዉ የስድስት ወር የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚነቱ በሕጉ ከአንቀጽ 68(ሀ-መ) ስር የተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት ያስፈልጋል ተብለው በተዘረዘሩት ጉዲዮች ላይ አንዲኛው ተጋቢ የላላኛው ተጋቢ ስምምነት ሳይኖር የውል ግዳታ መገባቱን ያወቀ ተጋቢ ውለ እንዱፈርስ ክስ ማቅረብ ያለበትን ጊዜ የሚመለከት ነው። ሁለተኛው በዚሁ ድንጋጌ የተመለከተው የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ደግሞ በማንኛውም ላላ ምክንያት በሕጉ ከአንቀጽ 68(ሀ-መ) ስር የተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት ያስፈልጋል ተብለው በተዘረዘሩት ጉዲዮች ላይ አንዲኛው ተጋቢ የላላኛው ተጋቢ ስምምነት ሳይኖር የውል ግዳታ መገባቱን በመቃወም ውለ እንዱፈርስ ክስ የሚያቀርብበትን ፍጹማዊ(absolute) የሆነ የይርጋ ጊዜ የሚመለከት ነው። በዚህ አግባብ የይርጋ ጊዜያትና ለእያንዲንደ የይርጋ ጊዜ መሰረት ሉሆኑ የሚችለ አመላካች ምክንያቶች ተለይቶ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር ከተመለከተው በተለየ ሁኔታ የተደነገገበት ምክንያት የተጋቢዎችን ልዩ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ጥቅማቸውን ለማስከበር እና በዉል ግንኙነት ለተፈጠረዉ ግብይት ጥበቃ (security of transaction) በማድረግ ተወዲዲሪ ጥቅሞችን ለማስከበር ነው።
ላላው የዚህን ችልት ትርጉም የሚሻው ነጥብ በአንደኛው ተጋቢ የውል ግዳታ ሲገባ ተካፊይ ያልሆነ ተጋቢ ግዳታው መገባቱን አወቀ የሚባለው መቼ ነው? የሚለውን የሚመለከት ነው። ከላይ እንደተመለከተው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69/2 ስር የተጠቀሰው የ6 ወር የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው የውል ግዳታ በአንደኛው ተጋቢ መገባቱን ለሚያውቅ ተጋቢ ነው። ጊዜውም ያጠረበት ምክንያትም ያለእሱ ተሳትፍ ግዳታ መገባቱን እስካወቀ ድረስ ሁለት ዓመት እስኪሆን መጠበቅ ሳያስፈልግ ግዳታ ያመጣው ውል እንዱፈርስ መጠየቅ ይችላል በሚል እምነት ነው። እንግዱህ ይህ ይርጋ ውል ይፍረስልኝ በሚል ክስ የማቅረብ መብት ቀሪ የሚያደርግ እስከሆነ ድረስ በስምምነቱ ተሳታፉ ያልሆነ[ው]ችው ተጋቢ ውል ይፍረስልኝ ክስ ለማቅረብ በሚያስችል ልክ ስለውለ መኖር የተሟላ እዉቀት ሉኖረው(ልኖራት) ይገባል። በዚህ መሰረት በአንደኛው ተጋቢ የተደረገ የገንዘብ ብድር ውል መኖሩን ላላው/ዋ ተጋቢ አወቀ/አወቀች ልባል/ልትባል የሚችለው/የምትችለው ቢያንስ የገንዘብ ብድር ውለ ከማን ጋር እንደተደረገ፣ የምን ያህል ገንዘብ ብድር ውል እንደሆነ፣ መቼ የተደረገ የብድር ውል እንደሆነ ማወቅ ሲችል/ስትችል ነው። እነዚህን ፍሬ ነገሮች ያላወቀ ተጋቢ የገንዘብ ብድር ዉለ ይፍረስልኝ ክስ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ይቸገራል። ምክንያቱም የገንዘብ ብድር ውል ይፍረስልኝ ዲኝነት በመጠየቅ ክስ የሚያቀርበው ተጋቢ በልላኛው ተጋቢ የብድር ውል ግዳታ መገባቱን በጥቅለ ከማወቅ ባለፈ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በቁጥር 33(2 እና 3) ፣ 80(2-4)፣85 እና 222/1 እንደተደነገገው የተከሳሹን ማንነት እና የክሱን ምክንያት (ለክሱ አስፈላጊ የሆኑ ፍሬ ነገሮችን) በክሱ እንዱገልጽ ሕጉ ስለሚያስገድደው ላላኛው ተጋቢ ከማን ጋር የምን ያህል ገንዘብ ብድር ውል እንደተዋዋለ እና የብድር ውለ መቼ እንደተደረገ ማወቅና በክስ አቤቱታዉ ላይ በፍሬ ነገር ደረጃ መግለጽ ስለሚኖርበት እና ሥልጣን ያለዉን ፍርድ ቤት ከብድሩ ገንዘብ መጠን አንጻር ለይቶ ገልጾ ክሱን ማቅረብ ስለሚኖርበት ነው።
እንዱሁም አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክምን ከሚመለከተው መሰረታዊው መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዲት እንደሚቻለው አንድ አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ብል የሚከራከር ሰው ፍሬ ነገሩ መኖሩን በማስረጃ የማስረዲት ሸክም(ግዳታ) አለበት። (የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 258-260 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001/1 ይመለከቷል)። በዚህ መሰረት ግዳታ መገባቱን አውቋል ብል በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 ስር የተደነገገውን የ6 ወር የይርጋ ጊዜ አንስቶ የሚከራከር ተከራካሪ (ተጋቢ) ላላኛው ተጋቢ ግዳታው መገባቱን እንዳትና መቼ እንዲወቀ ማስረዲት ይኖርበታል።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ይፈርስ ዘንድ ዲኝነት በመጠየቅ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ ክስ የመሰረቱበት የገንዘብ ብድር ውል አመልካች ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ዉስጥ ተሳስረው በነበሩበት ጊዜ ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር ተዋውለዋል የተባለውን ውል ነው። በዚህ የብድር ውል ላይ ተጠሪ በተዋዋይነት አለመሳተፊቸው እና ከክርክሩ እንደተገነዘብነውም የብድር ግዳታ የተገባበት የገንዘብ መጠን ብር 450,000.00 መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። አመልካች የገንዘብ ብድር ውል ግዳታ መገባቱን ተጠሪ ክሱ ከመቅረቡ ከ6 ወር በፉት ታውቅ ነበር ያለትን ለማስረዲት ያቀረቧቸው ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት ቃል አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ብድር እንደተበደሩ ለተጠሪ ነግረዋቸዋል የሚል እንደነበር የስር ፍርድ ቤቶች በሕግ የተሰጣቸውን የምስክሮችን ቃል የመመዘን ሥልጣን በመጠቀም ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነው። በዚህ መልኩ አመልካች በምስክሮቻቸዉ በጥቅለ ያስረደት አመልካች ከማን ጋር ምን ያህል ገንዘብ ለመበደር መቼ በተደረገ የብድር ውል እንደተዋዋለ ተጠሪ ውል ይፍረስልኝ ክስ ለመመስረት በሚያስችላቸው በተሟላ መልኩ አውቀዋል የሚያሰኝ ማስረጃ ወይም ምስክርነት ቃል አይደለም።
እንደሚታወቀው በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) ስር እንደተመለከተው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ እንዱያርም ነው። ችልቱ በዚህ ሥልጣኑ ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ ለመቀበል፣ ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን ለተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ያቀረቡትን ማስረጃዎች የመመዘን ጉዲይ ውስጥ በመግባት ማስረጃዎችን በመመርመርና በመመዘን አከራካሪ የሆነው የፍሬ ነገር ጭብጥ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጣን ለችልቱ አልተሰጠውም። ሆኖም የማስረጃ አቀራረብን፣ አግባብነትን፣ ተቀባይነትን እና ማስረጃ አቅርቦ አንድን ፍሬ ነገር የማስረዲት ሸክም መርህ (Production, relevancy, admissibility and burden of proof of evidence)እንዱሁም የማስረጃ ምዘናን ወይም የማስረዲት ደረጃን (standard of proof or weight of evidence) የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆዎች ተጥሶ የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ሲኖር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሚሆን በሰበር ሰሚ ችልት የሚታረም ይሆናል። በዚህ በያዝነው ጉዲይ ከላይ እንደተመለከተው ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕግ የተሰጠውን ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን በመጠቀም የግራ ቀኙን ማስረጃዎች መዝኖ አመልካች በምስክሮቻቸው ቃል ብድሩን እንደወሰደ ለተጠሪ እንደነገራቸው እንጂ በእርግጥ የብድር ውለ መኖሩን በግልጽ ለተጠሪ አላስረደም በማለት የደረሰበት የፍሬ ነገር ድምዲሜ ከማስረጃ ምዘና መሰረታዊ መርህ አተገባበር አንጻር ጉድለት ያለበት አይደለም። አንደኛው ተጋቢ ገንዘብ ተበድሬያለሁ ብል ለላላኛው ተጋቢ ተናግሯል መባለ ብቻ መብት ለማስከበር በሚያስችል ሁኔታ የብድር ውል ግዳታ መገባቱን ላላኛው ተጋቢ አውቋል ብል ለመደምደም አያስችልም።
በልላ በኩል የስር ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ አልሆነም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ከውጤት አንጻር ተገቢ ቢሆንም ተጠሪ የብድር ውል መገባቱን ከ6 ወር በፉት እንደሚያውቁ አመልካች በማስረጃ አስረድተዋል ካለ በኋላ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 መሰረት የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜን እንደአማራጭ ይርጋ ጊዜ በመቁጠር የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ አልታገደም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ በድንጋጌው የተመለከተውን የይርጋ ጊዜያት ትክክለኛ አፈጻጸም ያላገናዘበ ሆኖ እያለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የታየውን የይርጋ ጊዜያት አተገባበር ጉድለት አለማረሙ ስህተት ነው። እንዱሁም በቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 68/መ እና 69/1 መሰረት የገንዘብ ብድር ውል ሲደረግ ያልተሳተፈ ተጋቢ የብድር ውለ እንዱፈርስ ለመጠየቅ ምክንያት ሉያደርግ የሚገባውና ውለ እንዱፈርስ ከመወሰኑ በፉት በፍሬ ነገር ደረጃ ሉረጋገጥ የሚገባው በገንዘብ ብድር ውል ግዳታዉ በተዋዋይነት አለመሳተፈን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ውል ይፍረስልኝ በሚል ከሚቀርብ ክስ ጋር በተያያዘ በብድር ተገኘ የተባለው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ዉሎል ወይስ አልዋለም በሚለው ጭብጥ ላይ ማከራከርና ውሳኔ መስጠት አይቻልም። ይህ አይነት ክርክር ላቀርብ የሚገባው የጋብቻ ፍቺ ተከትል በሚደረገው የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጊዜ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የብድር ውል ይፍረስልኝ ተብል በቀረበ ክስ ክርክር ላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነው በብድር ተገኘ የተባለዉ ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ውሎል ወይስ አልዋለም የሚለውን ጭብጥ ላይ ግራ ቀኙን አከራክረው መወሰናቸው ሉታረም የሚገባው የክርክር አመራር ጉድለት ነው ብለናል።
ሲጠቃለል ለክሱ መነሻ የሆነው የገንዘብ ብድር ውል የተደረገዉ በቀን 07/10/2007ዓ/ም ሲሆን ተጠሪ ክስ የመሰረቱት ደግሞ የብድር ውል ግዳታ ከተገባ ሁለት አመት ሳይሞላው በቀን 28/09/2009ዓ/ም ነው። አመልካች ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር የገንዘብ ብድር ውል ሲያደርጉ ተጠሪ በተዋዋይነት እንዲልተሳተፈ ከመረጋገጡም በተጨማሪ ተጠሪ ክስ ከማቅረባቸው ከ6 ወር በፉት የገንዘብ ብድር ውል ግዳታ መገባቱን ተጠሪ ከላይ በተመለከተው አግባብ በተሟላ መልኩ እንደሚያውቁ አመልካች አለማስረዲታቸው ተረጋግጧል። ስለሆነም የ6 ወር ይርጋ ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት የለውም።
በመሆኑም ከላይ እንደተመለከተው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ የተለያዩ ጉድለቶች ቢኖሩም ተጠሪ ክስ የመሰረቱት በተዋዋይነት ያልተሳተፈት ወይም ፈቃዲቸውን ያልገለጹበት ውል እንዱፈርስላቸው ከመሆኑ አንጻር ሲታይ እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 69/2 መሰረት የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ መሰረት በማድረግ ሲታይ የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ አልሆነም በማለት በሰጡት ውሳኔም ሆነ ከተጠሪ አንጻር የብድር ውለ እንዱፈርስ (ተጠሪን አይመለከታቸዉም ሲለ) በሰጡት ውሳኔ ከውጤት አንጻር ሲታይ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 10/03/2011ዓ/ም የሰጠው ብይን እና በቀን 17/04/2012ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 06/06/2013ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጪ የየራሳቸውን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸው።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.