በቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኟቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀሩ በተደገነገገበት ሁኔታ በጋብቻ ወቅት ባልና ሚስት በፍ/ቤት ወይም ስልጣን ባለው አካል ባልፀደቀ ውል ከውርስ የሚገኝ ንብረት የጋራ ነው በሚል ቢዋዋለም ውለ በፍርድ ቤት ካልተረጋገጠ በቀር ውጤት ስለላለው በጋብቻ ወቅት በውርስ የተገኘ ንብረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ሆኖ የሚቀጥል ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 አንቀጽ 73 እና 89
No summary available.
የሰ.መ.
ቀን፡- ጥቅምት 2 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ ተሾመ ቶላ - ጠበቃ ገናነው ተሾመ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሰጉ ፈዬ - ጠበቃ ሀ/ማርያም አበበ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በ26/2/13ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. በ9/3/13ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ14/3/13ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ ተጠሪ በስር የደገም ወረዲ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ከፍቺ በኋላ የንብረት ክፍፍል ክስ ከአመልካች ጋር የጋራችን የሆነ አከራካሪውን በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኝ በ200 ቆርቆሮ የተሰራ 8 ክፍል ቤት ግምቱ ብር 2‚000‚000.00 የሆነ በ600ካ.ሜ ላይ ያለ አዋሳኞቹ በክሱ ውስጥ የተጠቀሱ አመልካች በ9/4/09ዓ.ም በፈረመልኝ ውል መሰረት እንዱያካፍለኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች ባቀረቡት መልስ ተጠሪ ከቤቱ ጋር በተገናኘ የገለጸችው ውል በጋብቻ ውስጥ የተፈረመ ሲሆን ይህ የኦሮሚያ ቤተሰብ ህግ አ/ቁ 69/95 እና 83/96 አንቀጽ 89 ከደነገገው አንጻር በፍርድ ቤት ያልጸደቀ እና ስልጣን ባለው አካል ስላልተረጋገጠ በህግ ተቀባይነት ስለላለው ክሱ ውድቅ እንዱደረግ፤ ይህን ቤት ከእህቴ ወ/ሮ አሰፋ ቶላ የወረስኩት በመሆኑ የኦሮሚያ ቤተሰብ ህግ አ/ቁ 69/95 እና 83/96 አንቀጽ 73 በውርስ የተገኘ ንብረት ከክርክር ውስጥ እንዱወጣ የደነገገ በመሆኑ ከዚሁ ንብረት ጋር በተያያዘ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዱሆንልኝ። በ9/4/09ዓ.ም የተደረገው ውል በደፈናው በውርስ ያገኘሁትን ቤት በጋራ ተጠቀምንበት የሚል እንጂ ቤቱ እንዳት አይነት እንደሆነ፤ ስፊቱ፤ አዋሳኞቹ እነማን እንደሆኑ ግልጽ ባለመሆኑ ውለ በህግ ተቀባይነት የለውም። ስለሆነም ክሱ ውድቅ እንዱደረግ በማለት ጠይቀዋል። አመልካች በበኩላቸው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበው ተጠሪ ለዚሁ ክስ መልስ ሰጥተዋል።
ፍ/ቤቱም ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው ያላቸውን ጭብጦች በመያዝ የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ባልና ሚስት ጋብቻ ሲፈጽሙ በግላቸው ያለውን ንብረት ወይም ከዚያ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በግላቸው ያገኙትን የግላቸው ሆኖ እንደሚቀር የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አ/ቁ 69/85 እና 83/96 አንቀጽ 73 ደንግጓል። በሀምቢሶ ከተማ የሚገኘውን ከላይ የተገለጸውን ተጠሪ በ2009ዓ.ም አመልካች ፈረመልኝ በማለት የገለጸችው ቤት አመልካች ከእህቱ ወ/ሮ አሰፋ ቶላ በውርስ ያገኘ ስለመሆኑ የቀረበው ክርክር እና የግራቀኙ ማስረጃ የሚያስረዲ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ባልና ሚስት ተጋብተው አብረው በሚኖሩበት ግዜ በመካከላቸው ያደረጉት ውል በፍርድ ቤት ካልተረጋገጠ በቀር ውጤት እንደላለው በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 89 ተደንግጓል። አመልካች እና ተጠሪ በሽማግላዎች ተስማምተው በውርስ የተገኘውን ይዞታ መሬት እና ንብረት ስለመፈራረማቸው ከቀረበው ክርክር እና ከግራቀኙ ምስክሮች ለመረዲት የሚቻል ነው። ሆኖም ይህ ውል በፍርድ ቤት የተረጋገጠ ስለመሆኑ የቀረበ የሰውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃ የለም። ስለሆነም በተጠሪ ክስ የቀረበበት በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኘውን በ600ካ.ሜ ላይ ያረፈውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰውን ቤት በተመለከተ በ9/4/09ዓ.ም የተደረገው ውል ያልጸደቀ እና በውርስ የተገኘ ንብረት ነው በማለት በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 73 እና 89 መሰረት የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። በአመልካች የቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ ክስ ባቀረቡበት በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 የሚገኘውን ቤት በተመለከተ ከላይ በተገለጸው በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል። በዚሁ ላይ ተጠሪ ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ በሀምቢሶ ከተማ የሚገኘውን ቤት በተመለከተ ግራቀኙ በባልና ሚስትነት በመኖር ላይ ሳለ አመልካች በውርስ ያገኘ መሆኑን ግራቀኙ አልተካካደም። በጋብቻ ውስጥ በውርስ ንብረት ያገኘው ወገን ንብረቱ የግለ እንደሚሆን የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 73 የደነገገ ሲሆን፤ በግለ ወረሰ የሚባለው በስጦታ ውል ወይም በኑዛዜ ቃል ወይም በልላ ሁኔታ ካልተገለጸ በቀር በውርስ የተገኘ ንብረት የተጋቢዎች ነው። አመልካች ለብቻው መውረሱን የሚገልጽ የስጦታ ውል ወይም በኑዛዜ ቃል የወረሰበትን አላቀረበም። አመልካች እና ተጠሪ በ9/4/09ዓ.ም በፈጸሙት ውል ክርክር ያስነሳውን ቤት የጋራቸው ንብረት አድርገው ነበር። ይህ ውል የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 89 በደነገገው መሰረት ስላልተመዘገበ ተቀባይነት ቢያጣም ተጠሪ አስቀድማ በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 78(3) መሰረት ያገኘችውን መብት የሚያሳጣት አይደለም። በግለሰቦች መካከል የተደረገ ውል በአዋጅ የተሰጠውን መብት የሚከለክል አይደለም በማለት በስር ፍ/ቤት ቤቱን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር ቤቱን ተጠሪ ከአመልካች ጋር እንድትካፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች ከላይ በተገለጸው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ውሳኔውን አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከላይ የተገለጹትን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡትን ውሳኔ እና ትእዛዝ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ አከራካሪውን በሀምቢሶ ከተማ የሚገኘውን ቤት ያገኘሁት ያለኑዛዜ ከወንድሞቼ ጋር ተከራክሬ በፍ/ቤት ውሳኔ በውርስ ነው። አመልካች ቤቱን ያለኑዛዜ በፍ/ቤት ውሳኔ መውረሴን በስር የወረዲው ፍ/ቤት ባቀረበችው ክስ ባልካደችበት፤ ቤቱን በኑዛዜ ወይም በስጦታ ውል መውረሴን ተጠሪ ባልተከራከረችበት እና በማስረጃም ባላስረዲችበት የስር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች አመልካች ቤቱን በግለ ስለመውረሱ ማስረጃ አላቀረበም በማለት የስር የወረዲውን እና የከፍተኛውን ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ትእዛዝ በመሻር የሰጡት ውሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተሽሮ የስር የወረዲው እና የከፍተኛው ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ትእዛዝ እንዱጸናልኝ፤ ወጪና ኪሳራም እንዱከፈለኝ እንዱወሰንልኝ የሚል ነው።
ይህ አቤቱታቸው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አከራካሪው በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኝ 600ካ.ሜ የሆነው ቤት እና ይዞታ አመልካች በውርስ ያገኘው ንብረት ሆኖ ሳለ በጋብቻ ውስጥ የተገኘ ውርስ ነው በሚል የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ተጠሪ ልትካፈል የሚገባው የጋራ ንብረት ነው ያለውን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ያጸናበት ከኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አ/ቁ 69/95 አንቀጽ 73 አንጻር ለመመርመር ለሰበር ችልቱ ይቅረብ ተብል በ18/3/13ዓ.ም በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ በ9/4/13ዓ.ም በተጻፈ ባቀረቡት መልስ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም የሚለበትን ምክንያቶች በመዘርዘር አቤቱታው ውድቅ ተደርጎ ውሳኔው እና ትእዛዙ እንዱጸና፤ ወጪና ኪሳራም እንዱከፈላቸው እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል።
አመልካች በ23/4/13ዓ.ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ይህ የሰበር ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ፤ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢዎቹ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር የስር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምሯል።
ተጠሪ በስር የደገም ወረዲ ፍ/ቤት ክስ ያቀረቡበት አከራካሪውን በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኘውን በ200 ቆርቆሮ የተሰራ ባለ 8 ክፍል ግምቱ፤ ስፊቱ እና አዋሳኞቹ በክሱ ውስጥ የተጠቀሱትን ቤት አመልካች እና ተጠሪ በጋብቻ ውስጥ እያለ አመልካች ከእህቱ ከወ/ሮ አሰፋ ቶላ በውርስ ያገኘው ስለመሆኑ አመልካች እና ተጠሪ ያልተካካደት እና በስር የደገም ወረዲ ፍ/ቤት እንዱሁም በይግባኝ ሰሚው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬጉዲይ ነው።
የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 73 ባልና ሚስት ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው ያገኟቸው ንብረቶች የግል ንብረቶቻቸው ሆነው እንደሚቀሩ ደንግጓል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች አከራካሪውን በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 የሚገኘውን ቤት ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ውስጥ እያለ ከእህቱ ወ/ሮ አሰፋ ቶላ በውርስ ያገኘው ስለመሆኑ ያላከራከረ እና የተረጋገጠም ጭምር በመሆኑ ይህ ከሆነ ደግሞ ከላይ በተገለጸው የህግ ድንጋጌ መሰረት ቤቱ የአመልካች የግል ንብረት ሆኖ የሚቀር ነው። ከዚህ አንጻር የስር የደገም ወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪ በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኘውን ቤት አመልካች ያካፍለኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ እና በዚሁ ውሳኔ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረዝ የሰጠውን ትእዛዝ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመሻር ቤቱን ተጠሪ ከአመልካች ጋር እንድትካፈል በማለት የሰጠውን ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በማጽናት የሰጠውን ትእዛዝ ይህ የሰበር ችልት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝቶታል።
ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በ26/2/13ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. በ9/3/13ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የደገም ወረዲ ፍ/ቤት በመ. በ7/5/12ዓ.ም በሀምቢሶ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኘው በ200 ቆርቆሮ የተሰራ 8 ክፍል የሆነ ግምቱ ፤ ስፊቱ እና አዋሳኞቹ በክሱ ውስጥ የተገለጹትን ቤት አመልካች ያካፍለኝ ሲለ ተጠሪ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም በዚሁ ውሳኔ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.
በ10/6/12ዓ.ም በመሰረዝ የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
ከላይ በውሳኔው ክፍል ተራ ቁጥር 2 ስር ከተገለጸው ነጥብ ውጪ የደገም ወረዲ ፍ/ቤት በመ. በ7/5/12ዓ.ም በሀረርጌ ዞን ድባ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኘውን ግምቱ፤ መጠኑ እና አዋሳኞቹ በአመልካች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውስጥ የተገለጸውን ቤት በተመለከተ የሰጠው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
በዚህ የሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.