በባል ወይም በሚስት ስም ተመዜግቦ የሚገኝ ቤት በጋብቻ ወቅት በጋራ ጥቅም ላይ የዋለ በመሆኑ የጋራ ነው በሚል የንብረት ክፍፍል ዲኝነት ሲቀርብ የጋራ ንብረት ነው የተባለበት ምክንያት በትዲር ውስጥ ስላፈሩት ነው ወይስ የግል ንብረት የነበረውን በጋብቻቸው ጊዛ የጋራ ያደረጉት የሚለውን በመለየት ውሳኔ የሚሰጥበትና ቤቱ የግላ ነው በሚል የሚቀርብ ክርክር የግል ስለመሆኑ ማስረዲት የሚጠበቅበትና የግል ንብረት መሆኑን ካሳየ የግል ንብረቱ የጋራ ሆኗል የሚል ተከራካሪም ይህንን ማስረዲት የሚጠበቅበት ስለመሆኑ ቤት በባል ወይም በሚስት ስም ተመዜግቦ ያለ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በትዲር ባለበት ጊዛ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ ባልተካደበት የጋራ ንብረት ስለመሆኑ የተቀመጠውን የህግ ግምት ቤቱ በስሙ የተመዘገበው ተጋቢ የግል ንብረቱ መሆኑን በማስረጃ ማስረዲት እየተገባ የጋራ ንብረት መሆኑን አላስረዲም/አላስረዲችም ልባል የሚችል ስላለመሆኑ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 63(1)
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 22/9/2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ገነት ገለቱ ከጠበቃ ተስፊዬ አድማሱ ጋር - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዮሀንስ ዚቲ ጠበቃ ጌትነት ገሰሰ - ቀረቡ መዜገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዙህ የሰበር መዜገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዚዜ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው። ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዜርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የምትለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤቶች በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው ቤት የጋራ ንብረታችን ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ የጋራ ንብረት አይደለም ተብል መወሰኑ፣ 3 ቀርጥ መሬት የጋራ ንብረት ልባል እንደሚገባ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ አምኖ መልስ ሰጥቶ እያለ በልማት ምክንያት በመንግስት ተወስዶል ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የአሁን አመልካች ባቀረበችው ክስ በከሳሽ እና ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በ21/7/2009 ዓ/ም በፍቺ ቀሪ ተደርጓል። በመሆኑም ከተከሳሽ ጋር በጋራ ያፈራነው 1. በተከሳሽ ስም ተመዜግቦ የሚገኝ በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ በቀድሞ አጠራር ፈጨ ቀበላ በኋላ ወረዲ 13 ውስጥ የሚገኝ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈ ቤት 2. የእርሻ መሬታችን ለልማት በመወሰደ ምክንያት መንግስት የሰጠን የመሬት ካሳ ተጣርቶ ድርሻ ይካፈለኝ 3. በአመልካችና ተጠሪ ስም ተመዜግቦ የሚገኝ 3 ቀርጥ የእርሻ መሬት ግማሹን እንዱያካፍለኝ 4. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዲሸን ባንክ አቃቂ ቅርንጫፍ፣ በህብረት ባንክ፣ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በአቢሲኒያ ባንክ በተከሳሽ ስም ያለ ገንዘብ ተጣርቶ ድርሻዬ ይካፈለኝ 5. የእርሻ መሬታችን በመንግስት በመወሰደ በምትክ የተሰጠን ባለ 3 መኝታ ኮንድሚኒየም እና ለቤት ማደሻ የሚሰጠው ገንዘብ ድርሻዬን ያካፍለኝ 6. የሲሚንቶ ማቡኪያ፣ ጋሪ ከነ ፈረሱ ድረሻዬን ያካፍለኝ ስትል ጠይቃለች። ተከሳሽም ከሳሽ ትዲራዋን ትታ የሄደችው በ1992 ዓ/ም ሲሆን እስከ ሄደችበት ጊዛ ድረስ በጋራ ያፈራነው የቤት ቁሳቁስ ብቻ ነው። አንድ ተጋቢ የትዲር ግንኙነት ትቶ በሄደበት ወቅት የተፈራ ንብረት ለመካፈል መብት የላለው ስለመሆኑ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በተከሳሽ ስም የሚገኝ በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈው የመኖሪያ ቤት ከወላጅ አባቴ በውርስ ያገኘሁትና ካርታ ፕላን የተሰጠኝ በ2001 ዓ/ም ሲሆን የግል ንብረቴ ነው። የእርሻ መሬታችን በልማት በመወሰደ የተከፈለ ካሳ ድርሻዬ ይከፈለኝ ያለችው መሬቱን በውርስ ያገኘሁት ነው። ከሳውም የተከፈለው በ1992 ዓ/ም ነው። አሁን ያለው መሬት 2 ቀርጥ ሲሆን በወታደርነት ባበረከትኩት አገልግልት የተሰጠኝ ነው። ያገኘሁትም ከከሳሽ ጋር ሳንጋባ በፉት በ1983 ዓ/ም ነው። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለው የሂሳብ ቁጥር የተከፈተው ከሳሽ በ1992 ዓ/ም ትዲርዋን ትታ ከሄደች በኋላ በ1997 ዓ/ም ነው። የአቢሲኒያ ባንክ የተከፈተው በ2011 ዓ/ም ነው። ባለ 3 መኝታ ኮንድሚኒየም ቤት ከቤት ማደሻ ገንዘብ ጋር የጠየቀችውን በተመለከተ ከወላጆቼ በውርስ ባገኘሁት መሬት የተሰጠ ካሳ በመሆኑ ልትካፈል አይገባም። የሲሚንቶ ማቡኪያ እና የፈረስ ጋሪ የለም፣ አለ ከተባለም ደርሻ የላትም በሚል መልስ ሰጥተዋል። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው ቤት ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በጋራ ያፈሩት ስለመሆኑ አላስረዲችም ተከሳሽ ይዝታው የአባቱ፣ ቤቱ የወንድሙ መሆኑን አስመስክሯል በመሆኑም የጋራ ንብረት አይደለም። 2 ቀርጥ መሬት በተመለከተ ተከሳሽ ከውትድርና ስመለስ የተሰጠው መሆኑ የተከሳሽ ምስክሮች አስረድተዋል። ይሁንና በትዲር ባለ ጊዛ የተገኘ በመሆኑ የጋራ ንብረት ነው። ይህ መሬት በልማት ምክንያት የተወሰደ በመሆኑ የሚካፈለት መሬት የለም።
በልማት ምክንያት ለተጠሪ የተከፈለ ካሳ ከጽ/ቤቱ የቀረበው ሪፖርት የተከፈለው ካሳ ተነሽ አርሶ አደሩ ከ3 ልጆቹ ጋር ተመዜግቦ የተከፈለ ሲሆን ከሳሽ በባለቤትነት ያልተመዘገበችና ተከሳሽ ጋብቻ የላለው መሆኑ ማስረጃ ቀርቦ ኮንድሚኒየም የተሰጠው ሲሆን በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት በመሆኑ የካሳ ገንዘቡና ኮንድሚኒየም ቤቱ የጋራ ንብረት ነው። ከሳሽና ተከሳሽ ፍቺ የፈጸሙት በ21/7/2009 ዓ/ም ሲሆን ከሳሽ አረብ ሀገር የሄደችና እየመጣች የጋራ ኑሮዋቸውን የምትደግፍ መሆኑ የተመሰከረ ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለው ገንዘብ ፍቺ እስከተፈጸመበት 2009 ዓ/ም ያለው የጋራ ንብረታቸው ነው። በልላ ባንክ የተቀመጠ ገንዘብ የለም። የሲሚኒቶ ማቡኪያ እና የጋሪ ፈረስ ስለመኖራቸው በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ታልፎል ሲል ወስኗል። ከሳሽ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ በመ/ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ትእዚዜ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኝዋን ውድቅ አድርጎል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርባለች። መዜገቡም ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የአሁን አመልካች በማስረጃ ዜርዜር መግለጫ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 145 እንዱቀርብላት የጠየቀችው ማስረጃ አስቀርቦ ሳያጣራ እንዱሁም መሬት ልማት ማኔጅመንት በ21/5/2013 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ 500 ካ/ሜ ይዝታ በተጠሪ ስም የተመዘገበ መሆኑ እየተገለጸ በማስረጃ አላስረዲችም በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል።
አመልካችም ሚያዜያ 18 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታዋን በማጠናከር ተከራክራለች።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። እንደመረመርነውም አሁን ለዙህ ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ምክንያት የሆነው በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው ቤት እና በአመልካችና ተጠሪ ስም ተመዜግቦ የሚገኝ ከሳሽ 3 መሬት ቀርጥ የምትለው ተከሳሽ 2 ቀርጥ መሬት ከውትድርና ስመለስ የተሰጠኝ ነው የሚለው የእርሻ መሬት በተመለከተ በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ባቀረበችው ክስ በተከሳሽ ስም ተመዜግቦ ያለና በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ በቀድሞ አጠራር ፈጨ ቀበላ በኋላ ወረዲ 13 ውስጥ የሚገኝ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈ ቤት 2.
የእርሻ መሬታችን ለልማት በመወሰደ ምክንያት መንግስት የሰጠን የመሬት ካሳ 3. በአመልካችና ተጠሪ ስም ተመዜግቦ የሚገኝ 3 ቀረጥ የእርሻ መሬት ድርሻዬን ያካፍለኝ የሚል ሲሆን ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ ደግሞ በተከሳሽ ስም የሚገኝ በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈው የመኖሪያ ቤት ከወላጅ አባቴ በውርስ ያገኘሁትና በ2001 ዓ/ም ካርታ ፕላን የተሰጠኝ የግል ንብረቴ ነው። የእርሻ መሬታችን በልማት በመወሰደ የተከፈለ ካሳ ድርሻዬ ይከፈለኝ ያለችው መሬቱን በውርስ ያገኘሁትና ከሳውም የተከፈለው በ1992 ዓ/ም በመሆኑ የሚካፈላት ካሳ የለም። አሁን ያለው መሬት 2 ቀርጥ ሲሆን በወታደርነት ባበረከትኩት አገልግልት የተሰጠኝ በመሆኑ ልትካፈል አይገባም ሲል ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤቶችም በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው ቤት ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በጋራ ያፈሩት ስለመሆኑ አላስረዲችም ተከሳሽ ይዝታው የአባቱ፣ ቤቱ የወንድሙ መሆኑን አስመስክሯል በመሆኑም የጋራ ንብረት አይደለም። 2 ቀርጥ መሬት በተመለከተ ተከሳሽ ከውትድርና ስመለስ የተሰጠው መሆኑ የተከሳሽ ምስክሮች አስረድተዋል። ይሁንና በትዲር ባለ ጊዛ የተገኘ በመሆኑ የጋራ ንብረት ነው። ይህ መሬት በልማት ምክንያት የተወሰደ በመሆኑ የሚካፈለት መሬት የለም ሲል ወስኗል። የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በሰጠው ውሳኔ በግልጽ የቀረበን ክርክር በተቆጠረ ማስረጃ ወይም አግባብነት ባለው መንገድ እንዱጣራ ሳይደረግ የሚሰጥ ውሳኔ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበት ይገኛል። ግራ ቀኙን ያከራከራቸው በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈ ቤት በተመለከተ የአሁን አመልካች በጠየቀችው ዲኝነት በአሁን ተጠሪ ስም ተመዜግቦ የሚገኝ፣ የአሁን አመልካችና ተጠሪ በትዲር እያለ ሲጠቀሙበት የነበር መሆኑን በመጥቀስ የጋራ ንብረት ስለሆነ ያካፍለኝ ብላለች። ከሳሽ ይህን ቤት የጋራ ንብረት ነው ስትል ላቀረበችው ዲኝነት፣ ያጋራ ንብረት ነው ያለችበት ምክንያት በትዲር ውስጥ ስላፈሩት ነው ወይስ የግል ንብረት የነበረውን በጋብቻቸው ጊዛ የጋራ ያደረጉት ስለመሆኑ መለየት ያለበት ጭብጥ ነው። የጋራ ንብረት ነው ያለችበት ምክንያት በትዲራችን ወቅት አፍርተናል የሚል ከሆነ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ድንጋጌ አንጻር የአሁን አመልካች የጋራ ንብረት ስለመሆኑ የህግ ግምት የሚወሰድ እና የአሁን ተጠሪ የግል ንብረት ነው የሚል ክርክር ያለው በመሆኑ የግል ንብረቱ ስለመሆኑ ማስረዲት ያለበት ነው። ከሳሽ የአሁን አመልካች የግል ንብረቱ የነበረውን በጋብቻቸው የጋራ ንብረት ሆኗል የሚል ምክንያት ካላት ደግሞ ከሳሽ የግል ንብረት የጋራ ሆኗል የምትልበት ክርክር የማስረዲት ግዳታ የሚጠበቅባት ነው። የፍደራል የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 63(1) አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዲ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት አንደሆነ ይቆጠራል ሲል ይደነግጋል። እንዱሁም ይሄው አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 86(1) ባልና ሚስት የግለ መሆኑን በማስረዲት የግል ሀብቱ የሆነውን መልሶ የመውሰድ መብት እንደሚኖረው ይደነግጋል። በመሆኑም ያከራከረው በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው ቤት ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ የግላ ነው ሲል ላቀረበው ክርክር የግለ ስለመሆኑ ማስረዲት የሚጠበቅበትና የግል ንብረት መሆኑን ካሳየ ከሳሽ የአሁን አመልካች የግል ንብረቱ የጋራ ሆኗል ክርክር ካላት ይህን ለማስረዲት የሚጠበቅባት ነው። ይሁንና የስር ፍ/ቤቶች ያከራከረው ቤት በተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ስም ተመዜግቦ ያለ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በትዲር ባለበት ጊዛ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ ባልተካደበት የጋራ ንብረት ስለመሆኑ የተቀመጠውን የህግ ግምት የአሁን ተጠሪ የግል ንብረቱ መሆኑን በማስረጃ ማስረዲት እየተገባው ከሳሽ የአሁን አመልካች የጋራ ንብረት መሆኑን አላስረዲችም መባለ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ተከሳሽ ከወላጆቼ በውርስ ያገኘሁት ነው የሚል ክርክር አቀርቦም እያለ የአባቱና የወንድሙ ንብረት መሆኑ ተመስክሯል በሚል የተሰጠው ውሳኔ የግራ ቀኙን ክርክርና የባልና ሚስት ንብረት የቤተሰብ ህግ ደንጋጌን ያልተከተለ ግልጽ ያልሆነ ውሳኔ መሆኑን መረዲት የሚቻል ነው።
ላላው የአሁን አመልካች የጋራ ንብረታቸን ነው ስትል እንዱከፈላት የጠየቀችው ካሳ የተከፈለበት የመሬት ይዝታ እና በክርክራቸው ወቅት የነበረ የእርሻ መሬትን የሚመለከት ነው። የአሁን ተጠሪም ካሳ የተከፈለበት የእርሻ መሬት በውርስ ያገኘሁት ነው፣ ይካፈለኝ ያለችው የመሬት ይዝታ ደግሞ ከውትድርና ስመለስ ላደረኩት አገልግልት የተሰጠኝ የግል ንብረቴ ነው የሚል ክርክር አቅርቧል።
ከግራ ቀኙ ክርክር የምንረዲው ሁለት ቦታ ያለ የመሬት ይዝታዎች አንደ ካሳ የተከፈለበት አንደ ደግሞ በክርክራቸው ወቅት ያለ መሆኑን ነው። ይሁንና የስር ፍ/ቤቶች በነዙህ የመሬት ይዝታዎች ላይ ግልጽ የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክር በተገቢው ማስረጃ ሳያጣሩ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ከውትድርና ስመለስ ተሰጠኝ የሚለውንና መኖሩን የገለጸውን የመሬት ይዝታ ካሳ ተከፍልበታል ከተባለው መሬት ጋር አንድ በማድረግ ካሳ ተከፍልበት በመንግስት በመወሰደ የምትካፈለው መሬት የለም ሲል የሰጠው ውሳኔ ተገቢውን ማጣራት ሳያደርግ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዚዜ እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 1. በአቃቂ ቃሉቲ ክ/ከተማ ወረዲ 13 ውስጥ የሚገኝ በ500 ካ/ሜ ላይ ያረፈውን ቤት በተመለከተ ከሳሽ የጋራ ንብረት ነው ስትል ላቀረበችው ዲኝነት የጋራ ንብረት ነው ያለችበት ምክንያት በትዲር ውስጥ አፍርተናል ነው ወይስ የግል ንብረት የጋራ ሆኗል የሚል ስለመሆን አለመሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር በመለየት፣ የጋራ ንብረት ነው ያለችበት ምክንያት በትዲራችን ወቅት አፍርተናል የሚል ከሆነ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ድንጋጌ አንጻር የአሁን አመልካች የጋራ ንብረት ስለመሆኑ የህግ ግምት የሚወሰድ እና የአሁን ተጠሪ የግል ንብረት ነው የሚል ክርክር ያለው በመሆኑ የግል ንብረቱ ስለመሆኑ ባቀረበው ማስረጃ እንዱያስረዲ በማድረግ፣ ከሳሽ የአሁን አመልካች የግል ንብረቱ የጋራ ንብረት ሆኗል የሚል ምክንያት ክርክር ካላት ደግሞ ከሳሽ የግል ንብረት የጋራ ሆኗል የምትልበት ክርክሯን ባቀረበችው ማስረጃ እንድታስረዲ በማድረግ እንዱሁም ተገቢውን ማስረጃ በማስቀረብ አጣርቶ እንዱወስን፣ 2. የአሁን አመልካች የጋራ ንብረታቸን ነው ስትል እንዱካፈላት የጠየቀችው ሁለት ቦታዎች ያለ ካሳ የተከፈለበት የመሬት ይዝታ እና በክርክራቸው ወቅት የነበር የእርሻ መሬት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን የአሁን ተጠሪም ካሳ የተከፈለበት የእርሻ መሬት በውርስ ያገኘሁት ነው፣ ይካፈለኝ ያለችው የመሬት ይዝታ ደግሞ ከውትድርና ስመለስ ላደረኩት አገልግልት የተሰጠኝ የግል ንብረቴ ነው የሚል ክርክር ያለው በመሆኑ እነዙህን የመሬት ይዝታዎች በመለየት ባቀረቡት ማስረጃና ከተገቢው አካል በማጣራት ካሳ የተከፈለበት የመሬት ይዝታ በተመለከተም ግልጽ ውሳኔ መስጠት እንዱሁም በክርክራቸው ውቅት አለ የተባለውንም የመሬት ይዝታ በተመለከተም እንዱሁ አጣርቶ ግልጽ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰናል። ላላው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
በዙህ መዜገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የዙህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዜገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።