የሁከት ይወገድልኝ የክስ አቤቱታ ቀርቧል ለማለት የሚቻለው ለክርክሩ መንስዓ የሆነው ንብረት በእጅ አድርጎ የሚገኝ እና ንብረቱ ላይ በእውነት ለማዘዝ እንዱችል የንብረቱ አያያዝ ያልተጭበረበረና በማናቸውም መንገድ ሕገ ወጥ በሆነ ሁኔታ ያልተያዘ መሆኑ ሲረጋገጥ እና ተከሣሽ ድርጊቱን እንዱፈፅም የተፈቀደለት መብት ወይም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በማይታበይ ሁኔታ ማስረዲት የሚጠበቅ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1140ና 1149
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ቄስ ቀፀላጊዮርጊስ ደስታ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደደር የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታሕሳስ 7ቀን 2014 ዓ/ም በሰጠው ትእዛዝ የስር ፍርድ ቤቶች በሰጡት ውሣኔ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ሲል የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብል እንዱታረምላቸው አመልካች ስለጠየቁ ነው።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጀመረው የሁከት ክርክር የሰበር አመልካች ከሣሽ፣ የሰበር አንደኛ ተጠሪ ተከሣሽ፣የሰበር ሁለተኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች ግንቦት 2ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ ክሣቸው በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 የቤት ቁጥር 648 የሚታወቀው ቤት የግል ቤታቸው መሆኑን፤ የቤት ቁጥር 649 ደግሞ የአስተዲደሩ ሆኖ አመልካች የግል ቤታቸው ስለጠበባቸው በኪራይ እንዱሰጣቸው ሕዲር 21ቀን 1985 ዓ/ም ጠይቀው በቃለ-ጉባኤ ተሰጥቷቸው እንዱሁም ቤቱ ወንዝ ዲር በመሆኑ በወንዙ የተወሰደውን የቤቱን ክፍል በራሣቸው ወጪ አድሰው ኪራይ እየከፈለ በይዞታቸው አድርገው እስካሁን እየተጠቀሙበት መሆኑንና ውል እንዱይዝላቸው ኪራይም እንዱቀበላቸው ሲጠይቁት ይጠብቁ ሲላቸው ከቆየ በኋላ ሚያዚያ 28ቀን 2013ዓ/ም የግል ቤታቸውን ጨምሮ ማሸጉን ዘርዝረው የፈጠረባቸው ሁከት እንዱቆም የቤቱንም ኪራይ እንዱቀበል እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አመልካች የቀበላው አስተዲደር አከራካሪውን ቤት የሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል የተባለ ቃለ-ጉባኤ፣ በመዝገብ ቁጥር 648/91 የተሰጠ ውሣኔና የአፈፃፀም ችልቱ የሰጠውን ትዕዛዝ በማስረጃነት ስለማቅረባቸው የስር ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ያስገነዝባል።
አንደኛ ተጠሪ የመልስ ክርክሩን እንዱያቀርብ ታዞ አላቀረበም። ሁለተኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ሆኖ ለክርክሩ መንስዓ የሆነውን ቤት ማሸጉን ሣይክድ ነገር ግን አመልካች በክፍለ ከተማው ወረዲ 03 ውስጥ የግል ቤት ያላቸው ስለሆነና የግል ቤት እያላቸው የመንግስት ቤትን በኪራይ መያዝ ስለማይችለ ቤቱ መታሸጉ በሕግ የተሰጣቸውን ሀላፉነት መወጣታቸውን እንጅ ሁከት ባለመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዱሆን ተከራክሯል። አመልካች በበኩላቸው የግል ቤታቸውና ግማሹ በጎርፍ የተወሰደው የተጠሪው ቤት በአንድ ጣራ ስር መሆናቸውን በ1985 ዓ/ም ስራ ላይ የነበረው የቀበላ አስተዲደር ቤቱን በኪራይ የሰጣቸው የግል ቤታቸው በመጥበቡ መሆኑን፣ ቀደም ሲል በፍርድ ቤት ሲከራከሩ ቆይተው ስለተወሰነላቸው መረከባቸውን በመጥቀስ ለዚህ ጉዲይ መመሪያው ተፈፀሚነት ሉኖረው አይገባም ሲለ ተከራክረዋል።
የስር ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ክስና የመልስ ክርክር ከሰነድ ማስረጃ ጋር አጣምሮ ከመረመረ በኋላ አመልካች የግል ቤት ያላቸው ስለመሆኑ አለመካደን በመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 10(8) መሰረት የግል ቤት ያለው ሰው የቀበላ ቤት የያዘ ከሆነ የቀበላ ቤቱን መመለስ እንደሚገባው የሚደነግግ በመሆኑ ተጠሪው የፈፀመው ድርጊት ሁከት አይደለም ሲል የአመልካችን ክስ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2) ድንጋጌን በመጥቀስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኙት አመልካች የይግባኝና የሰበር አቤቱታቸውን በየደረጃው ለሚገኙት የከተማ አስተዲደሩ ፍርድ ቤቶች ያቀረቡ ቢሆንም ስለተሰረዘባቸው ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
አመልካች ታሕሳስ 16ቀን 2014ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታቸው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ከቀድሞው ወረዲ 6 ቀበላ 13 አስተደደር ፅ/ቤት መጀመሪያም በቃለጉባኤ ተሰጥቷቸው በኋላም በፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 648/2011 በተደረገው ክርክር ውሣኔ አግኝቶ ውሳኔው እንዱፈፀም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ግንቦት 27 ቀን 1994ዓ/ም ስለመረከባቸው በሰነድ ማስረጃ በተረጋገጠበት፤ የቤት ቁጥር 649 የሆነውን የተከራዩት የግል ቤት እያላቸው ነገር ግን ችግራቸው ታይቶ ከ17 ዓመት በፉት መሆኑ በተረጋገጠበት የግል ቤት ሣይኖራቸው የተከራዩት በማስመሰልና በመገንዘብ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራውን መመሪያ ቁጥር 5/2011 በመጥቀስ ተጠሪው ሁከት አልፈጠረም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብል እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሣኔ የቤት ቁጥር 648ን በሚመለከት የቀረበውን ክርክር መሰረት ያደረገ መሆን ያለመሆኑን፤እንዱሁም የቤት ቁጥር 649ን በሚመለከት የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 820/94 መጋቢት 9ቀን 1994 ዓ/ም የሰጠውን የአፈፃጸም ትዕዛዝ ያገናዘበ መሆን አለመሆኑ እንዱመረመር ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪው በበኩለ የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ አመልካች የቤት ቁጥር 648 ተብል የሚታወቅ የግል ቤት ያላቸው ስለመሆኑ ባለመካደ መመሪያ ቁጥር 5/2011 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የተሰጠ ውሣኔ መሆኑን፤ በወረዲ አስተዲደር ለዚያውም መመሪያን በመጣስ የግል ቤት ላለው ሰው የመንግስት ቤት መስጠትም ሆነ መያዝ ሕገ ወጥ መሆኑን ገልፆ የስር ፍርድ ቤቱ ውሣኔ እንዱፀና ተከራክሯል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥና የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ሲሆን የስር ፍርድ ቤቱ ተጠሪው ቤቱን ማሸጉ ሁከት አይደለም ሲል በመወሰኑና በየደረጃው የሚገኙት ፍርድ ቤቶችም ይህን ውሣኔ በማፅናታቸው የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር ያለመኖሩን በጭብጥነት ተይዞ ጉዲዩ ተመርምሯል።
እንደተመረመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ ይዘት በወቅቱ የቀበላን ቤት ያስተዲድር በነበረው የመንግስት አካል የቤት ቁጥር 648 የግል ቤታቸው መሆኑን እያወቀ ነገር ግን ቤታቸው በመጥበቡ ችግራቸውን ለማቃለል ሲባል የመንግስት ቤት የሆነውን 649 በኪራይ እየከፈለ እንዱኖሩበት የተሰጣቸው መሆኑን በኋላም በዚሁ ቤት ላይ በፍርድ ቤት በተደረገ ክርክር ቤቱ ለአመልካች እንደሚገባ ተወስኖላቸው በአፈፃፀም ከተረከቡ በኋላ በራሳቸው ወጪ አድሰው ኪራይ እየከፈለ እስካሁን ድረስ ሲጠቀሙ የቆዩ ቢሆንም ሚያዚያ 28ቀን 2013ዓ/ም አንደኛ ተጠሪው የግል ቤታቸውን ጨምሮ ቤቱን በማሸጉ ሁከት ነው ተብል ሁከቱ እንዱወገድ የቤቱን የኪራይ ዋጋም እንዱቀበላቸው እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ በጣልቃ ገብነት ቀርቦ የከተማ አስተዲደሩን የመንግስት ቤቶች ለማስተዲደር የወጣው መመሪያ ቁጥር 5/2011 በሚደነግገው መሰረት አመልካች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው የመንግስትን ቤት በኪራይ መያዝ ስለማይችለ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ማሸጉ ሁከት አይደለም ሲል መከራካሩን የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ያስገነዝባል።
እንደሚታወቀው ከሣሽ የሆነ ወገን ተገቢነት ያለው የሁከት ይወገድልኝ የክስ አቤቱታ አቅርቧል ለማለት የሚቻለው ለክርክሩ መንስዓ የሆነው ንብረት በእጅ አድርጎ የሚገኝ እና ንብረቱ ላይ በእውነት ለማዘዝ እንዱችል የንብረቱ አያያዝ ያልተጭበረበረና በማኛቸውም መንገድ ሕገወጥ በሆነ ሁኔታ ያልያዘው መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ በዚህ መሰረት ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ድርጊቱን እንዱፈፅም የተፈቀደለት መብት ወይም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በማይታበይ ሁኔታ ማስረዲት የሚጠበቅበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1140ና 1149 ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ።
በቀረበልን ጉዲይ ክሱ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት በኪራይ የያዙት የአዱስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዲደር ቢሮ ያወጣውን መመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀፅ 10(8) ድንጋጌን በመጣስ የግል ቤት እያላቸው ነው ካለ በኋላ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2) ጠቅሶ ውደቅ አድርጓል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33 በከሣሽነት ወይም በተከሣሽነት የሙግት ተካፊይ ስለመሆን በሚደነግግው የስነ ስርዓት ሕጉ ሁለተኛ መፅሐፍ ስር የሚገኝ ሲሆን ማንም ሰው ክስ ሉያቀርብ የሚችለው ወይም የሚገባው ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ሀብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ መረጋገጥን ከከሣሽነት መመዘኛዎች መካከል አንደ እንደሆነ ተደንግጓል። የዚህ ድንጋጌ ዓላማም በአከራካሪው ንብረቱ ወይም መብት ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ጥቅም የላለው ሰው ክስ እያቀረበ የተከራካሪ ወገኖችን እና የፍርድ ቤቱን ጊዜ እንዲያባክን፣ ተገቢነት ለላለው የገንዘብ ወጪ ምክንያት እንዲይሆን ታስቦ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
በልላ በኩል የስር ፍርድ ቤቱ ለሰጠው ውሣኔ መሰረት ያደረገው የከተማ አስተደደሩን መመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀፅ 10(8) ድንጋጌን ነው። ይህ አንቀፅ ንብረትነታቸው የቀበላ ወይም የመንግስት የሆኑ መኖሪያ ቤቶች ለተከራይ ነዋሪዎች የሚሰጡበትን መመዘኛዎች የሚደነግግ ነው። ከእነዚህ መመዘኛዎች መካከል የግል ቤት ወይም ላላ በማናቸውም ምክንያት የተገኘ መኖሪያ ቤት አለመኖር አንደ ላሆን እንደሚገባና የግል ወይም በማኛቸውም መንገድ የተገኘ መኖሪያ ቤት ያለው ሰው የቀበላ ቤት የያዘ ከሆነ የቀበላውን ቤት ሉመልስ እንደሚገባ የአንቀፁ ንዐስ አንቀፅ 8 ይደነግጋል። የመመሪያው ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት ከነሐሴ 10ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ አንቀፅ 60 ይደነግጋል።
በዚህ አንቀፅ ላይ የተደነገገው የተፈፃሚት ጊዜና የመመሪያውን አስፈላጊነት ለማስገንዘብ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ጣምራ ንባብ መመሪያው ተግባራዊ እንዱሆን ከተገለፀው ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዱውል ታስቦ የወጣ መሆኑን ያስገነዝባለ። ይህም ማለት ይህ መመሪያ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ንብረትነቱ የመንግስት የሆነን መኖሪያ ቤት ለግሰቦች በኪራይ መስጠትም ሆነ መያዝ የሚቻለው ተከራዩ የግል ወይም በማናቸውም መንገድ የተገኘ ላላ መኖሪያ ቤት የላለው መሆነን በማረጋገጥ ላሆን እንደሚገባ የሚደነግግ ነው።
በያዝነው ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች የግል ቤት ያላቸው መሆኑ እየታወቀ ቤቱን ሲያስተዲድር በነበረው የመንግስት አካል በ1985 ዓ/ም በሕጋዊ መንገድ የተሰጣቸው ስለመሆኑ፤
ከዚህ በኋላም በፍርድ ቤት ውሣኔ ቤቱን መረከባቸውን፤ ከ1985 ዓ/ም ጀምሮ ኪራይ እየከፈለ በይዞታቸው አድርገው ሲጠቀሙበት መቆየታቸው በመዘርዘር የሚያቀርቡትን ክርክር ተጠሪው በግልጽና በዝርዝር ክድ የተከራከረ መሆኑን መዝገቡ አያመላክትም። ተከሣሽ የተከሰሰበትን ነገር መካድ የሚችለው በከሣሹ የቀረቡትን ነገሮች ሁለ በዝርዝርና በግልጽ ክድ በመቃወም ላሆን እንደሚገባና የቀረበውን ነገር በዝርዝርና በግልጽ ያለመካድ ያልተካደውን ነገር በከፉልም ሆነ በሙለ አምኖ እንደመቀበል የሚያስቆጥር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 83 ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አመልካች አከራካሪውን ቤት ያገኙት የግል ቤት ያላቸው ስለመሆኑ በአስተዲደር አካለ ታውቆና ችግራቸው ታምኖበት ተሰጥቷቸው በኋላም በፍርድ ቤት ውሣኔ አፈፃፀም ቤቱን ተረክበው ኪራይ እየከፈለ ሲገለገለበት መቆየታቸው ካልተካደ አመልካቹ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1140 በሚደነግገው መሰረት ተከራይ ባለይዞታ መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም በወቅቱ አከራካሪውን ቤት ሲያስተዲድር በነበረው የመንግስት አካል የቤቱን ኪራይ እየከፈለ አመልካች እንዱኖሩበት በሰጣቸው ጊዜ የግል መኖሪያ ቤት እንዲላቸው እውቅና አልነበረም የሚል ክርክር ባልቀረበበትና ባልተረጋገጠበት፤ እንዱሁም ቤቱ ለአመልካች በተሰጠበት ወቅት በማናቸውም መንገድ የተገኘ ላላ መኖሪያ ቤት እያለው የመንግስት ቤት በኪራይ መስጠትም ሆነ መያዝ ክልከላ የነበረ ስለመሆኑ በተጠሪው ክርክር ባልቀረበበት ከነሐሴ 10ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ እንዱሆን ታስቦ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 5/2011 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የተጠሪው ድርጊት ሁከት አይደለም ተብል መወሰኑ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረት ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታሕሳስ 7ቀን 2014ዓ/ም እና በመዝገብ ህዲር 22ቀን 2014ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጣቸው ትዔዛዞች እንዱሁም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ሕዲር 6ቀን 2014ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ከግል ቤታቸው ጋር የተያያዘውን ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የቀበላ ቤት አመልካች ኪራይ እየከፈለ እንዱኖሩበት መጀመሪያ በአስተዲደሩ ተወስኖ ተሰጥቷቸው በኋላም በፍርድ ቤት ውሣኔ አፈፃፀም የተረከቡትን የመኖሪያ ቤት ከነሐሴ 10ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ እንዱሆን ታስቦ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 5/2011 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ተጠሪው ማሸጉ የሁከት ድርጊት በመሆኑ እንዱወገድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተወስኗል።
ይህ ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.