የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረውና ይህንኑ በሀይል ሲነጠቅ ወይም በይዞታዉ ስር ባለ ንብረት ላይ የመጠቀም መብቱን የሚያዉክ ተግባር ሲፈጸም እንዱሁም ንብረቱ በሕግ አግባብ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የሀይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር ንብረቱን እንደወሰደበት ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1149/1
No summary available.
የሰ.መ.
ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ደበርማዊ ቅደስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ቤተክርስቲያን ነሐሴ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በተወካይዋ አማካኝነት ተጽፍ በቀረበ የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቧ ነው።
ጉዲዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት መነሲቦ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን 1ኛ ተጠሪ እና በዚህ የሰበር ክርክር የላለ አላዛር ተረፈ የተባለ ግለሰብ እንደቅደምተከተላቸው ተከሳሾች፤
የአሁን 2ኛ ተጠሪ እና አረጋሽ ነጋሳ የተባለ ግለሰብ ደግሞ ጣልቃ ገቦች ነበሩ። አመልካች ቤተክርስቲያን በሥር ፍ/ቤት ያቀረበችው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኙ በክሱ የተገለጸው እና በመንዱ ከተማ 04 ቀበላ ውስጥ የሚገኘው ይዞታ ለጥምቀት አገልግልት ስትጠቀምበት የነበረ መሆኑን፤ 1ኛው ተጠሪ ከዚህ በፉት ይዞታዋን አልፍ ግንባታ በመፈጸሙ ምክንያት ጉዲያቸው በሽማግላ ታይቶ በቀን 23/05/2010 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት በሕገ-ወጥ መንገድ የሰራው ግንባታ ተትቶለት ሁለተኛ ወደ አመልካች ይዞታ አልፍ እንዲይገባ የተስማሙ መሆኑን፤ ሆኖም 1ኛ ተጠሪ ስምምነቱን በማፍረስ በምስራቅ በኩል ሰርቶ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት በማለፍ በግምት 400 ካ.ሜ የሚሆን ይዞታ ላይ በፍልጥ ቤት የሰራ መሆኑን፤ አስተዲደሩ አላግባብ የሰራውን ቤት እንዱያነሳው ደብዲቤ የጻፈለት ቢሆንም ፈቃደኛ አለመሆኑን፤ የስር 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ በምስራቅ አቅጣጫ ወደ ምንጭ ውሃ አካባቢ የሚገኘውን በግምት 600 ካ.ሜ የሚሆን ይዞታ በመያዝ አጥር የሰራበት መሆኑን በመግለጽ አላግባብ የሰሩትን ግንባታ አፍርሰው ይዞታውን እንዱለቁ ይወሰንላት ዘንድ ዲኝነት መጠየቋን የሚያሳይ ነው።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች የመሬቱ ባለይዞታ መሆንዋን የሚያሳይ የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ አላቀረበችም፤ በቀን 23/05/2010 ዓ.ም ተፈጸመ የተባለው የውል ስምምነት የቦታውን አዋሳኝ ለይቶ አይገልጽም፤ ከአመልካች ጋር ከዚህ በፉት ይዞታውን በሚመለከት አለመግባባት ተፈጥሮ መታረቃችን አይካድም፤ ቤት የተሰራበት መሬት ለአቶ ጆብር አለማየሁ በሕጋዊ መንገድ የተሰጠው ይዞታ ሲሆን ለሕዝብ ተከልል ከሚገኘው ይዞታ ውጪ በመሆኑ ክሱ ወድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የስር 2ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ፡- የአሁን 2ኛ ተጠሪ በቡና ችግኝ አጥር ስራልኝ ብላኝ አጥር መስራት ስጀምር አመልካች ሰዎችን ልኮ ከቦታው አባሮኛል በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩለት ጠይቋል።
የአሁን 2ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የጣልቃ ገብነት ክርክር አከራካሪ የሆነው ይዞታ የመንግስት ግብር የሚከፍለበት ይዞታቸው መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል። በልላ በኩል የስር 2ኛ ጣልቃ ገብ ክርክሩ የሚመለከታቸው መሆኑን በመግለጽ ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን የጣልቃ ገብነት አቤቱታ ውድቅ ያደረገው መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች እና ተጨማሪ ምስክሮች ከሰማ እና የሚመለከተው የአስተዲደር አካል ስለጉዲዩ አጥርቶ እንዱልክለት ካደረገ በኋላ ክርክር ያስነሳው መሬት በቀን 23/05/2010 ዓ.ም በተፈጸመው የእርቅ ውል ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠ አይደለም፤ 1ኛ ተጠሪ የጆብር አለማየሁ ይዞታ ነው በማለት ቤት የሰራበት መሬት በአመልካች ክስ ላይ በተጠቀሰው አዋሳኝ የሚካተት ሲሆን አመልካች ክስ ያቀረበችበት ይዞታ የአመልካች ይዞታ ስለመሆኑ ከተሰጣት የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ላይ መገንዘብ ተችሎል፤ 1ኛ ተጠሪ ከልጁ ጆብር አለማየሁ ሕጋዊ ውክልና ሳይሰጠው ጆብር አለማየሁን በመወከል ለመከራከርም ሆነ እላዩ ላይ ቤት ለመስራት አይችልም፤ ለአቶ ጆብር አለማየሁ የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነው በአመልካች እና በአቶ ጆብር አለማየሁ መካከል ክርክር ቢነሳ ኖሮ ነበር፤ 1ኛ ተጠሪ በአከራካሪው መሬት ላይ ቤት መስራቱን ያልካደ እና ቤት የሰራውም ከአቶ ጆብር አለማየሁ ሕጋዊ ውክልና ሳይወስድ እና አመልካች ቤተክርስቲያን የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ በወሰደችበት ይዞታ ላይ አመልካች እየተቃወመችው የሰራ በመሆኑ ግምቱን የመጠየቅ መብት ሳይኖረው በራሱ ወጪ አፍርሶ መሬቱን ለአመልካች ሉለቅ ይገባል፤
በልላ በኩል 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ የገባቸው ከባለቤትዋ በውርስ እየተላለፍ መጥቶ በባለቤትዋ ተስፊዬ ቶልሳ ላይ በደረሰ ይዞታ ላይ ነው፤ የከተማው አስተዲደር ይህን ይዞታ ለአመልካች ቤተክርስቲያን ሰጥቷል፤ ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ የባለቤትዋ ልጆች ሕጋዊ ውክልና ሳይሰጥዋት እንደግል ንብረትዋ ለመከራከር መብት የላትም፤ መብት አላት ቢባል እንኳን አግባብነት ባላቸው መመሪዎች መሰረት አስተዲደሩን በመጠየቅ መብቷን ከምታስከብር በቀር ጣልቃ ገብታ መከራከርዋ አግባብ አይደለም በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን በትዕዛዝ ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪዎች በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል።
ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አከራካሪው ይዞታ ከድሮ ጀምሮ የ1ኛ ተጠሪ ቤተሰብ እንደሆነ እና በኋላ ላይ የ1ኛ ተጠሪ ልጅ ለሆነው ጆብር አለማየሁ ለተባለ ሰው እንደተሰጠ፤
2ኛ ተጠሪም ይዞታውን ከባለቤቷ ቤተሰብ በውርስ እንዲገኘች እና ከእጇ ወጥቶ እንደማያውቅ በስር ፍርድ ቤት ከቀረቡት ማስረጃዎች መገንዘብ ተችሎል፤ አመልካች ሳይት ፔላን አለኝ ከማለት በቀር ይዞታው በሕጋዊ መንገድ ከባለይዞታው ተወስድ የተሰጣት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፤ ስለሆነም ይዞታው የአመልካች መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪዎች ይዞታውን እንዱለቁ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም ሲል ሽሮታል።
አመልካች በተራዋ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበች ቢሆንም አቤቱታዋ በትዕዛዝ ውድቅ ተደርጓል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ነሐሴ 17 ቀን 2012 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ይዘቱም፡- አከራካሪ የሆነው ይዞታ ከ2003 ዓ.ም በፉት ለጥምቀት በዓል ስጠቀምበት የነበረ ሲሆን በ 2003 ዓ.ም ደግሞ በከተማው መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሳይት ፔላን ተሰጥቶኛል፤ 1ኛ ተጠሪ በሕገ ወጥ መንገድ ይዞታዬ ውስጥ በመግባቱ ጉዲያችን በሽማግላ ታይቶ 400 ካ.ሜ ተትቶለታል፤ 1ኛ ተጠሪ እንደገና በግምት 400 ካ.ሜ የሆነ ይዞታ የልጄ የጆብር አለማየሁ ነው በማለት በሕገ ወጥ መንገድ ቤት የገነባበት ስለመሆኑ እና 2ኛ ተጠሪም 600 ካ.ሜ የሆነ ይዞታ በመያዝ አጥር ያጠረችበት ስለመሆኑ በወረዲው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል፤ ስለሆነም ይህ ታልፍ ተጠሪዎች ይዞታውን ሉለቁ አይገባም በማለት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ የተሰጣት መሆኑን መሰረት በማድረግ 1ኛ ተጠሪ በይዞታው ላይ የሰሩትን ቤት እንዱያፈርሱ በከተማ አስተዲደሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ባለበት እና 2ኛ ተጠሪ ባለይዞታ ስለመሆናቸው ባልተገለጸበት ተጠሪዎች ይዞታውን ሉለቁ አይገባም በሚል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪዎች ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- 1ኛ ተጠሪ የተከሰስኩበት ይዞታ የቤተሰቦቻችን ነባር ይዞታ ሲሆን ልጄ ጆብር አለማየሁ በ1998 ዓ.ም ከመንዱ ከተማ አስተዲደር በሕጋዊ መንገድ ያገኘው እና የግንባታ ፈቃድ የወሰደበት ነው፤ አከራካሪው መሬት በአመልካች ሳይት ፔላን ውስጥ እንደማይገኝም ተረጋግጧል፤ 2ኛ ተጠሪም ስፊቱ 600 ካ.ሜ የሆነ ይዞታ በውርስ ወደ ባለቤቴ ተስፊዬ ቶልሳ ተላልፍ የቡና ተክል እንዲለኝ እና የመንግስት ግብር እንደምገብርበት ተረጋግጧል፤ ስለሆነም ይህን መሰረት በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
በመሰረቱ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈፀምን ማናቸውም ድርጊት እንዱቆም ወይም ተገቢው መብት እንዱመለስለት ሕጉ ከዘረጋቸው መንገድች አንደ የይዞታ ክስ ስለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1149/1 ድንጋጌ የሚያስገነዝብ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረውና ይህንኑ በሀይል ሲነጠቅ ወይም በይዞታዉ ስር ባለ ንብረት ላይ የመጠቀም መብቱን የሚያዉክ ተግባር ሲፈጸም ሲሆን ማረጋገጥ ያለበትም ንብረቱ በሕግ አግባብ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የሀይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው።
በያዝነው ጉዲይ ለአመልካች ቤተክርስቲያን በአከራካሪው ይዞታ ላይ ሳይት ፔላን የተሰጣት መሆኑን፤
1ኛ ተጠሪ የልጄ የአቶ ጆብር አለማየሁ ይዞታ ነው በማለት ቤት የሰራበት ይዞታ ለአመልካች በተሰጣት ሳይት ፔላን ውስጥ የሚገኝ መሆኑን፤ በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል ቀደም ሲል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በቀን 23/05/2010 ዓ.ም በተፈጸመው የእርቅ ስምምነት አከራካሪው ይዞታ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠ አለመሆኑ፤ 1ኛ ተጠሪ ከልጁ ጆብር አለማየሁ ይዞታውን በሚመለከት የተሰጠው ውክልና አለመኖሩ፤ 2ኛ ተጠሪ አጥራ የያዘችው ይዞታም ለአመልካች በተሰጣት ሳይት ፔላን ውስጥ የሚገኝ መሆኑን በወረዲው ፍርድ ቤት ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር መገንዘብ ችለናል።
1ኛ ተጠሪ ቤት የሰራበት እና 2ኛ ተጠሪም አጥራ የያዘችው አከራካሪ የሆነው ይዞታ ለአመልካች ቤተክርስቲያን በተሰጣት ሳይት ፔላን ውስጥ የሚገኝ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካች በዚሁ ይዞታ ውስጥ ተፈጥሯል የምትለው የሁከት ተግባር እንዱወገድ ያቀረበችው ክስ በሕጉ አግባብ የቀረበ ነው። ስለሆነም አመልካች በሳይት ፔላን ተረጋግጦ በተሰጣት ይዞታ ውስጥ የተፈጠረው የሁከት ተግባር እንዱወገድ እና ተጠሪዎች ይዞታውን እንዱለቁ በወረዲው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ሆኖ ሳለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ይዞታው በሕጋዊ መንገድ ከባለይዞታው ተወስድ የተሰጣት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት የሰጡት ውሳኔ ስለሁከት ክስ አቀራረብና ሁከት እንዱወገድለት ክስ የሚያቀርብ ወገን ማስረዲት ስለሚጠበቅበት ፍሬ ነገር አስመልክቶ የተደነገጉትን የፍትሐብሕር ሕጉን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ. የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የመነሲቦ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 06/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የምዔራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ጥር 05 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.