የቤት ሽያጭ ዉል ስለመደረጉ ክርክር በቀረበበት ሁኔታ ዉለ በጽሁፍ መደረጉን ብቻ ሳይሆን ስርዓቱን ተከትል ዉል ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ አካል ፉት የተረጋገጠ የቤት ሽያጭ ዉል ባልቀረበበትና ይህም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሆኖ፤ ረቂቅ ነዉ የተባለ ሰነድ ላይ እነ አቶ ጳውልስ ኦርጂኖ (2 ሰዎች) እና አቶ ተስፊዬ ኤጌድ ፊርማ እና የምስክሮች ቃል መሰረት በማድረግ በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ ሉረጋገጥ የሚችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1720(1) እና 1723/1/፣ 1678 (ሐ)፣ 1719(2) የቤት ሽያጭ ዉል የለም ከተባለ ግራ ቀኙ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ቦታ ሲመለሱ ለቤት መግዣ በሚል የተከለፈ ገንዘብ ቀብድ ሳይሆን የሽያጭ ዋጋ ከፉል ክፍያ መሆኑ ከተረጋገጠ የተከፈለው ገንዘብ ያህል የሚመለስ እንጂ አጠፋታ እንዱከፍል በሚል የሚያስገድድ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1885(2) እና 1815(1)
No summary available.
መ/ቁ/215762 ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡- 1ኛ/ አቶ ጳውልስ ኦርጂኖ 2ኛ/ ወ/ሮ አመለወርቅ ሁሴን አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ኤጌድ- ተወካይ ታደሰ ኤጌድ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዙህ ሰበር አቤቱታ የቀረበዉ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በዙህ ችልት እንዱታረም በሚል ነዉ።
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዲይ ነዉ።የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዝን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በደራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዱሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበለ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውለ መሰረት ቤቱን እንዱያስረክቡ እንዱወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበለትን ቀብድ አጠፋታ እና ገንዘቡ ተከፍል እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰን በማለት ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸዉ ባቀረቡት መልስ የቤት ሽያጭ ውል ሲደረግ ቀብድ መሆኑ በውለ ስላልተገለጸ ቀብድ ነው በሚል አጠፋታ መጠየቅ ተገቢ ስላለመሆኑ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ አስገዲጅ የህግ ትርጉም መስጠቱን፤በውልም ሆነ በወኪላቸው ገንዘብ ያልተቀበለ ከመሆኑም በላይ የሽያጭ ውለ በሚመለከተው አካል ፉት ያልተደረገ እና ያልተመዘገበ የማይፀና ረቂቅ ውል በመሆኑ ቤቱን የማስረከብ ግዳታ የለብንም፣የቀብድ ውል የላለና የባንክ ሰነድ ቀብድ መሆኑን የሚገልጽ አይደለም፣ክሱ ውድቅ እንዱደረግ በማለት መከራካራቸዉን መዜገቡ ያሣያል።
የዝኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል በቀን 24/01/2012 ዓ.ም የቤት ሽያጭ ውል የተደረገ መሆኑን፤1,000,000.00 ብር ቀብድ ሳይሆን ለቤቱ ሽያጭ የተከፈለ መሆኑን፤ብር 800,000ለቤት ሽያጭ የተከፈለ አለመሆኑን፤በሽያጭ ከተዋዋለበት ዋጋ ቀሪውን ብር ተጠሪ ለአመልካቾች ከፍል አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች በዙህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ጉዲዩ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዝታል።
አመልካቾች በውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል እንዱታረምልኝ በማለት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት ከመረመረ በኋላ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካቾች ለዙህ ሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይህንን ዉሳኔ ለማስለወጥ ነው።የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ፡-የሽያጭ ውል ነዉ የተባለዉ 2ኛ አመልካች በላለሁበት እና ባልፈረምኩበት ድርሻዬን በሚመለከት ልዩ ጥንቃቄ አድርጎ መወሰን ሲገባው እና ተጠሪ የጠየቀው የቀብድ አጠፋታ እንዱመለስ የሚል ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ ከተጠየቀው የዲኝነት ውጪ የቀብድ ውል የለም ካለ በኋላ የሽያጭ ውል አለ በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ስህተት ነዉ፤ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል የቤት ሽያጭ ውል የለም፤የስር ፍ/ቤት ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ፉት ተመዜግቦ ማረጋገጫ ያገኘ መሆን አለመሆኑን ሳያረጋግጥ የውለ ሰነድ ከረቂቅ ያለፈ የህግ ጥበቃ የሚያገኝ ሰነድ ስለመሆኑ ሳይመረምር ውል አለ በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዱሻር በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ አመልካቾች የቤት ሽያጭ ውለን በግልፅ ክደው ተከራክረው እያለ የስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ውል አለ፤ተጠሪ ቀሪውን ገንዘብ ከፍል ቤቱን ይረከብ በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለማጣራት ጉዲዩ በአዋጅ ቀ/1234/2013 አንቀጽ 28(3) መሰረት ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞል።
ተጠሪ በቀን 15/04/2014ዓ.ም ባቀረበው መልስ በቀብድ ሰነድ ላይ ያለው ፊርማ የአመልካቾች አይደለም በማለት ክደው የተከራከሩትን የስር ፍ/ቤት በፍረንሲክ ምርመራ ፊርማው የአመልካቾች መሆኑ ከማረጋገጡ በተጨማሪም የቤት ሽያጭ ውል መኖሩና በእማኞች ፉት ገንዘብ የተቀበለ መሆኑ አሳማኝ እና በቂ በሆነ መልኩ በሰውና በሰነድ ተረጋግጦ ይህንን ሉያስተባብል የሚችል ማስረጃ አመልካቾች ስላላቀረቡ የተወሰነ እንጂ አንዲችም መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ስለሆነ ውሳኔው እንዱፀና በማለት ተከራክሯል።አመልካቾች አቤቱታቸውን በማጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዜገቡ ጋር ተያይዞል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለበትን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።እንደመረመርነዉ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ አመልካቾች የተቀበለትን ቀብድ አጠፋታ እንዱመልሱ ወይም በዉለ መሰረት የሸጡትን ቤት እንዱያስረክቡ የሚል ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸዉ ቤት ሽያጭ ዉል የለም፤ቀብድ አልተቀበልንም በማለት መከራከራቸዉን መዜገቡ ያሣያል። የስር ፍርድ ቤት የሽያጭ ዉል መደረጉን ያስረዲል የተባለዉ ሰነድ ላይ ያለዉን ፊርማ በባለሙያ አስመርምሮ እና ዉለ ሲደረግ እማኝ ነበሩ የተባለትን ሰዎች ምስክርነት ቃል ሰምቶ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ ተረጋግጧል በማለት አመልካቾች ቀሪ ገንዘብ ተቀብለዉ ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በቅደም ተከተል በይግባኝ ሰሚ ችልት እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጸንቷል።ለዙህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ላይ በመሆኑ በዉሳኔዉ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለሰበር ችልቱ ከተሰጠዉ ስልጣን ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደሚታወቀዉ የሰበር ስርዓት በህግ አተገባበር ወይም አተረጓጎም ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዱኖር ማስቻል ነዉ።የሰበር ችልቱ ስልጣንም የመጨረሻ ዉሳኔ በተሰጠባቸዉ ጉዲዮች ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ይህንኑ በማረም ላይ የተገደበ መሆኑን ከሰበር ስርዓት መሰረታዊ ዓላማ የምንገነዘበዉ ጉዲይ ነዉ።የኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ ይዘትና መንፈስ ይህንኑ የሚያመለከት ሲሆን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በሰበር ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚያሰኙት ሁኔታዎች ምንድናቸዉ ለሚለዉ ትርጉም መሰጠቱ (አንቀጽ 2/4/ ይመለከታል) ሰበር ሰሚ ችልት የተቋቋመበትን ዓላማ ማለትም ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዱኖር እና የዉሳኔዎችን ተገማችነት በማረጋገጥ ረገድ አገራዊ ፊይዲ ያላቸዉ ጉዲዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እንዱሰራ የሚያስችል ነዉ ተብል ይታሰባል።
በተለይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ ዉሳኔ/ትዕዚዜ/ብይን ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታዉን ተቀብል በሰበር የማየት ስልጣን የሚኖረዉ ዉሳኔዉ/ትዕዚዘ/ብይኑ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን አስገዲጅ ዉሳኔ የሚቃረን ሲሆን እንዱሁም አግባብነት የላለዉን ህግ በመጥቀስ ወይም ህግን ያላግባብ በመተርጎም የተሰጠ ዉሳኔ/ትዕዚዜ/ብይን ሆኖ ጉዲዩም አገራዊ ፊይዲን የሚመለከት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ድንጋጌዎች ያስገነዜባለ።ከዙህም የምንረዲዉ የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ ከእነዙህ ሦስቱ ሁኔታዎች ዉጪ ባለት ሁኔታዎች፣ መሰረታዊ የህግ ስህተትን መስፈርት አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ዉስጥ አንደን የሚያሟላ ሆኖ ቢገኝ እንኳን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በሰበር የማረም ስልጣን የላለዉ መሆኑን ነዉ።ስለሆነም ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን ዉሳኔ/ትዕዚዜ/ብይን በመቃወም የቀረበለት አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ከሆነ ዉሳኔዉ/ትዕዚዘ/ብይኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ እነዙህኑ ልዩ ሁኔታዎች ማለትም በአዋጁ አንቀጽ 10(1/ሐ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከግምት ዉስጥ የማስገባት ኃላፉነት ይኖርበታል።
በተያዘዉ ጉዲይ ግራቀኙን ያከራከረዉ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል በፍርድ ሃይል ሉፈጸም የሚችል የቤት ሽየጭ ዉል አለ ወይስ የለም የሚለዉ ነዉ።አመልካቾች አጥብቀዉ የሚከራከሩት የቤት ሽያጭ ዉል የለም፤የቀረበዉ ሰነድም ረቂቅ ነዉ በማለት በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር ታልፍ ዉል መኖሩ ተረጋግጧል፤ተገደዉ ሉፈጽሙ ይገባል ተብል በየደረጃዉ ባለት የክልለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ የሰበር ችልቱ ዉሳኔና ህጉን የሚቃረን ነዉ በማለት ነዉ።
በመሰረቱ የዉለታዉ ጉዲይ የሚቻል፣ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ካልሆነ እና ተዋዋይ ወገኖች ፈቅድ ወይም ችልታ ጉድለት የላለበት እንዱሁም በህግ የተደነገገዉን የዉል አደራረግ ስርዓት ተከትል ተዋዋይ ወገኖች ወደዉና ፈቅደዉ የሚያደርጉት ዉል ህግ ሆኖ የሚያስገድዲቸዉ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር1678 እና 1731/1 ድንጋጌ ያስገነዜባል። እንደዉለ ያልተፈጸመለት ወገን አንድም ዉለ እንዱፈጸምለት ወይም ዉለ እንዱሰረዜና ኪሳራ እንዱከፈለዉ መጠየቅ ይችላል።የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1771 ይመለከታል። ዉለ እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዜ የሚደረገዉ አንድም በህግ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱና የዉለ አደራረግ ጉድለት ያለበት ሲሆን ወይም ዉለ እንዲይፈጸም የሚያደርግ መሰናክል ሲፈጠር አሉያም አንደኛዉ ተዋዋይ ወገን ግዳታዉን ለመወጣት የማይችል መሆኑ በማያጠራጥር ሁኔታ ሲረጋገጥ ወይም የዉለ አይነተኛ ጉዲይ የተነካ ከሆነ ወይም በልላ ምክንያት በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት የተደረሰበት ከሆነ ነዉ።(የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808፣1784 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች ይመለከታል)።
የተያዘዉ ጉዲይ ግራ ቀኙን ያከራከረዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል አፈጻጸም የሚመለከት ነዉ።የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ወይም ላልች መብቶችን ለማስተላለፍ ወይም ለማቋቋም የሚደረግ ዉል በጽሁፍ እና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዜገብ ወይም ዉል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት መደረግ እንዲለበት የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723/1/ ድንጋጌ ይዘት ያሥገነዜባል።እንደውለታው ዓይነት ወይም በህግ የተደነገገዉ የጽሐፍ ውል አደራረግን ሥርዓት አስመልክቶ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678 (ሐ)፣ 1719(2) እንደተመለከተው በህግ ፉት ሉፀና የሚችል ውል አስፈላጊ የሆነውን የውል አደራረግ ሥርዓት አሟልቶ የያዘ መሆን አለበት።በዙህ አግባብ ያልተደረገ የሽያጭ ዉል እንደረቂቅ የሚቆጠር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1720(1) እና 1723 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።የምዜገባው ሂደት ባልተሟላበት ሁኔታ ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ሕጋዊ ነዉ ልባል እንደማይችል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በሰጠው ግልጽ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በላልችም መሰል ክርክሮች ላይ ተመሳሳይ ዉሳኔ ሰጥቷል።ሰበር መ/ቁ/34803 ቅጽ8፣መ/ቁ/ 78398 ቅጽ14 እና ላልች መዜገቦች መመልከት ይቻላል።የሰበር ችልት ውሣኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ እና 2878 ያላቸውን ልዩነት በግልጽ አስፍሯል።(መ/ቁ21448 ይመለከታል)፡ይኸውም የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በአዋዋይ አካል ወይም በፍርድ ቤት ፉት እንዱረጋገጥ (authentication) ሂደት የማድረጉ አስፈላጊነት በተዋዋይ ወገኖቹ መካከል የፀና ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 የተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዜገባ (registration) ዓላማ ደግሞ ውለ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዱኖረዉ ለማድረግ ሲባል ነው።በልላ በኩል ሰበር ችልቱ በሰበር መ/ቁ/36887 በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ እንዲመላከተዉ በሰበር መ/ቁ/ 21448 ላይ የተሰጠዉ ትርጉም በመካከላቸው የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን አምነው በውልና ማስረጃ አካል ባለመመዜገቡ ብቻ ውል የለም በሚል የሚቃወሙ ተከራካሪዎችን የሚያጠቃልል አይደለም ምክንያቱም በፍ/ብ/ህግ ቁ/1723/1/ መሰረት የሚከናወነው የምዜገባ ዋና አላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የቤት ሽያጭ ውል ለመኖሩ በማስረጃነት እንዱያገለግል በመሆኑ ነዉ።
በተያዘዉ ክርክር አመልካቾች በስር ፍርድ በሰጡት መልስ የቤት ሽያጭ ዉል የለም፤የቀረበዉ ሰነድም ረቂቅ ነዉ በማለት በግልጽ ተከራክረዋል።ይህ ከሆነ ደግሞ የቤት ሽያጭ ዉል አለመፈጸማቸዉን ክደዉ መከራከራቸዉን ያሣያል።አመልካቾች የቤት ሽያጭ ዉል አልፈጸምንም ብለዉ ክደዉ ስለተከራከሩ ዉል እንዱፈጸምለት የጠየቀዉ ተጠሪ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩን ማስረዲት የሚችለዉ በህጉ ቅቡልነት ያለውን ሰነድ በማቅረብ መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723(1) እና ከላይ የተጠቀሱት የሰበር ችልቱ የሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ ያስገነዜባል።ይህ ከሆነ ደግሞ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/ 36887 ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ሳይሆን በመ/ቁ/ 21448 እና ላልች መሰል ዉሳኔዎች ናቸዉ።በመሆኑም አመልካቾች የቤት ሽያጭ ዉለን ክደዉ በመከራከራቸዉ ተጠሪ በበኩለ ዉለ በጽሁፍ መደረጉን ብቻ ሳይሆን ዉል ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ አካል ፉት የተረጋገጠ ዉል በማቅረብ ማስረዲት ይጠበቅበታል።ተጠሪ ያቀረበዉ ሰነድ በዙህ አግባብ የተረጋገጠ አለመሆኑ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።በዙህ አግባብ ስርዓቱን ተከትል የተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል ባልቀረበበት ሁኔታ ረቂቅ ነዉ የተባለዉ ሰነድ ላይ ያለዉን ፊርማ እና የምስክሮች ቃል መሰረት አድርጎ በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ ተረጋግጧል በሚል የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ መታረም የሚገባዉ ሆኖ አግኝተናል።
በልላ በኩል ዉለ ረቂቅ ነዉ አመልካቾች ተገደዉ የሚፈጽሙት የቤት ሽያጭ ዉል የለም ከተባለ ግራ ቀኙ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ ተገቢ ነዉ።ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ አማራጭ የዲኝነት ጥያቄ ይህንኑ የሚያሳይ ነዉ።ይሁንና ተጠሪ በአማራጭ የጠየቀዉ ዲኝነት አመልካቾች የተቀበለትን ገንዘብ አጠፋታ እንዱከፍለ እንዱወሰን በማለት ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ክርክራቸዉንና ማስረጃ መርምሮ አመልካቾች የተቀበለት አንድ ሚሉዮን ብር መሆኑንና ገንዘቡም ቀብድ ሳይሆን የሽያጭ ዋጋ ከፉል ክፍያ መሆኑን አረጋግጧል።አመልካቾች የተቀበለት ቀብድ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ የተቀበለትን ገንዘብ ያህል መመለስ እንጂ አጠፋታ እንዱከፍለ አይገደደም።የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1885(2) እና 1815(1) ድንጋጌ ይዘት ይህንኑ ያመላክታል።
ሲጠቃለል አመልካቾች የቤት ሽያጭ ዉል ክደዉ ተከራክረዉ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ሽያጭ ዉል መደረጉ ተረጋግጧል በሚል አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት የሰጡት ዉሳኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል አደራረግ ስርዓት በሚመለከት በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723/1/ የተደነገገዉን እና ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/ 21448 የሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4-ሸ/ እና 10(1ሐ) ድንጋጌዎች መሰረት ለሰበር ችልቱ ከተሰጠዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አንጻር ሲታይ ዉሳኔዉ ላይ ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።በዙሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በማጽናት በመ/ቁ/17102 ላይ በቀን 10/02/2014ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/በግራ ቀኙ መካከል የተደረገዉ ዉል ረቂቅ ዉል እንጂ አመልካቾች ቤት እንዱያስረክቡ የሚገደደበት በህግ አግባብ የተቋቋመ የቤት ሽያጭ ዉል የለም ብለናል።
3ኛ/አመልካቾች በረቂቅ ዉለ መሰረት የተቀበለትን ብር አንድ ሚሉዮን ክሱ በስር ፍርድ ቤት ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ኪሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍለ ብለናል።
4ኛ/በዙህ ችልት የተደረገዉን ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
5ኛ/በዙህ መዜገብ ላይ በ22/03/2014ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ እግድ ትእዚዜ ተነስቷል።ይጻፍ መዜገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።