በግራ ቀኙ መካከል የሽያጭ ውል የላለና ረቂቅ ውል መሆኑና የሚፈጽሙት የቤት ሽያጭ ዉል የለም ከተባለ ግራ ቀኙ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ቦታ የሚመለሱና ለቤት ሽያጭ በሚል የተከፈለው ገንዘብ የሽያጭ ዋጋ ከፉል (ቅድሚያ) ክፍያ እንጂ ቀብድ አለመሆኑ አቶ ጌታሁን ኪዲነማርያም እና እነ ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ (7 ሰዎች) የተከፈለ ገንዘብ ያህል መመለስ እንጂ አጠፋታ እንዱከፍል የሚያስገደደ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1885(2) እና 1815(1)
No summary available.
መ/ቁ/211204 ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ጌታሁን ኪዲነማርያም - ጠበቃ ቴድሮስ ጌታቸው - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ/ ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ 2ኛ/ አቶ በላይነህ በቀለ 3ኛ/ ወ/ሪት የትምወርቅ በቀለ ጠበቃ ኤልያስ አበበ - ቀረቡ 4ኛ/ ወ/ሪት ሰናይት በቀለ 5ኛ/ አቶ ግሩም ከበደ 6ኛ/ ወ/ሪት መሰረት በቀለ 7ኛ/ ወ/ሮ ተዋበች በቀለ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ የካቲት 11 ቀን 2009 ዓ.ም በተደረገው የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ተጠሪዎች ከወላጅ እናታቸው ወ/ሮ አዚለች በየነ በውርስ ያገኙትን በአዱስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዲ 06 የሚገኝ ቁጥሩ 978 የሆነ ቤት በስማቸው ተዚውሮ የካርታ ቁጥር የካ/179211/05 በቀን 27/09/2005 ዓ.ም በስማቸው ተመዜግቦ የቦታ ስፊት 1396 ካ.ሜ ላይ ያረፈው ቤት በብር 11,000,000 ለአመልካች ሽጠው ውለ ሲፈረም ብር 3,000,000 የተከፈላቸው ሲሆን ቀሪው ብር የቤቱን ስመ-ሀብት ወደ አመልካች በማዚወር ቤቱን ከሙለ ሰነደ ጋር ሲያስረክቡ ለመክፈል ተስማምተናል። በመሆኑም ተጠሪዎች በውለ መሰረት ለመፈፀም ስለዘገዩ ግዳታቸዉን እንዱወጡ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻቸው ፍቃደኛ አልሆኑም፤ውለ የተደረገው በህጉ አግባብ በመሆኑ የማይፈጽምበት ምክንያት የለም፣ስለዙህ ተጠሪዎች ቤቱ እና ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድች እንዱያስረክቡ፤ሰነድች ማረጋገጫ እና ምዜገባ ጽ/ቤት እና መሬት አስተዲደደር ጽ/ቤት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት ለአመልካች እንዱያዚውሩ እና ቀሪ ገንዘቡን እንዱቀበለ፤ነገር ግን የሽያጭ ውለ ተቀባይነት የሚያጣ ከሆነ በቀብድነት የወሰደትን ገንዘብ አጠፋታ ብር 6,000,000 እንዱሁም የውል ቅጣት ብር 100,000 እና ለደላላ የተከፈለው ብር 60,000 በድምሩ ብር 6,610,000 ከተከፈለበት 11/06/2009 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ፣ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸዉ በሰጡት መልስ ከ1-6 ያለት ተጠሪዎች ለአመልካች የመኖሪያ ቤት አልሸጥንም፤ውለን አልፈረምንም፤አመልካች ከ7ኛ ተጠሪ ጋር አደረጉት የተባለው የሽያጭ ውልም ህግ በሚፈቅደው መሰረት ስርዓቱን ተከትል በውልና ማስረጃ ማረጋገጫ ምዜገባ ጽ/ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበና ገና በሂደት ላይ የነበረ በመሆኑ የሽያጭ ውለ ተፈጽሟል ለማለት የሚቻል አይደለም፤ስለዙህ ውለ በህጉ መሰረት ያልተመዘገበ በመሆኑ ውለ ፈራሽ ነው እንዱባልልን፤ ተወካይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ሲፈልግ የወካዮቹ የጥቅም ግጭት ሉፈጠር የሚችል ሁኔታ ካለ የወካዮችን ጥቅም በቅድሚያ ማሳወቅ እንዲለበት በህጉ ተመልክቷል። ስለዙህ 7ኛ ተጠሪ ብቻ በማስፈረም የተደረገው ውል የተከሳሾች መብትና ጥቅም በሚጎዲ መልኩ በማሳሳትና በህገ ወጥ የተደረገ የመንደር የቤት ሽያጭ ውል ሉፀና አይገባም እንዱባልልንና በፍ/ህ/ቁ 1815 መሰረት ወደነበሩበት እንዱመለሱ እንዱወሰን፣ አጠፋታ እንዱከፈልልኝ የተባለው አጠፋታ ክፍያ ለመክፈል ያልተስማሙ በመሆኑ ህገ ወጥ ነው፤ የደላላውም ሆነ የቅጣት ክፍያ የሚከፈልበት አግባብ የለም፣ 2ኛ ተጠሪ የአዕምሮ ህመምተኛ እና 3ኛ ተጠሪ በዕድሜ የገፈ አዚውንት እና ላልች ተጠሪዎች ከሀገር ውጭ ያለትን የወራሽነት ጉዲይም ሳይጠናቀቅ 7ኛ ተጠሪ ብቻውን ያደረገው የሽያጭ ውል ህገ ወጥ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ በማለት የተከራከሩ መሆኑን መዜገቡ ያሣያል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ የሽያጭ ውለ የተደረገው የማይንቀሳቀስ ንብረት ቤት ላይ መሆኑን፤ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስም ሆነ በክርክር ሂደት ውል መኖሩን አምነው አልተከራከሩም፣እንዱሁም ባቀረቡት መልስ ከ1 እስከ 6 ያለት ተጠሪዎች ለአመልካች መኖሪያ ቤት አልሸጥንም በማለት የተከራከሩ መሆኑን፤ ውለ የተደረገው በፍ/ህ/ቁ 1723 የተመለከተውን ድንጋጌ አሟልተው አይደለም፣ስለሆነም በህግ ፉት ሉፀና የሚችል ውል በፍ/ህ/ቁ 1678(ሐ)፣ 1719(2) እና 1723 የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተከትል የተደረገ ስምምነት ባለመሆኑ በህግ ፉት ዋጋ ያለው ሉፀና የሚችል ባለመሆኑ ቤቱን ያስረክቡኝ ወይም ስመ ሀብቱ ያዘሩልኝ በማለት ያቀረቡት ተቀባይነት የለውም።
በአማራጭ ያቀረቡትን ዲኝነት የተከፈለውን ገንዘብ ወይም ቀብድ አጠፋታ ይከፈለኝ የተባለው ውለ ረቂቅ በመሆኑ የተከፈለው ገንዘብ ቅድመ ክፍያ እንጂ ቀብድ አለመሆኑን ሰነደ ያስረዲል፤ስለዙህ ተጠሪዎች በውለ መሰረት የተቀበለትን ቅድመ ክፍያ ብር 3,000,000 ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዙህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም መዜገቡን መርምሮ ተጠሪዎች የመንደር ውለን ክደዉ የተከራከሩ መሆኑን ጠቅሶ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 የሚያሟላ ውል ስላልሆነ ውለ ፈራሽ ነው ሲል የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት መዜገቡን ዘግቶታል።
ለዙህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ላይ ነዉ።የአመልካቹ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፡ተዋዋይ ወገኖች ውል ስለመኖሩ ባልተካካደበት ሁኔታ ውለ ፍርሙን አልጠበቀም በሚል የህግ ውጤት የለውም ሲል የተሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የውለ ፍርም አልተሟላም በሚል ውል ይፍረስ የሚል ክስ ዲኝነት ተከፍል ክስ ሳይቀርብለት፣ ፍርም አልተሟላም በሚል ውል ይፍረስ ተብል የሚሰጡ ውሳኔዎች ስህተት ናቸው በሚል ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ሁኔታ እያለ የስር ፍ/ቤቶች ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል።7ኛ ተጠሪ ከላልች 6ቱ እህቶችና ወንድሞቹ ህጋዊ ውክልና መሰረት ውለን መፈፀማቸውን በግራ ቀኙ የታመነ ነው፤ተጠሪዎቹም ውክልና አልሰጠንም፣ ወኪላችን ውል አልፈፀመም፣ አልተዋዋለም የሚል ክርክር ባላቀረቡበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱሻር እና እንደ ውለ እንዱፈፀምልን በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ከ1ኛ እስከ 6ኛ የተጠቀሱት ተጠሪዎች የክርክር መነሻ የሆነውን ቤት እንዱሸጡ ለ7ኛ ተጠሪ ውክልና የሰጧቸው ስለመሆኑና በተሰጠው ውክልና መሰረት የሽያጭ ውል ስለመደረጉ ባልተካደበት ውለ ያልተመዘገበ በመሆኑ እንዱፈረስና ተጠሪዎች ከአመልካች የተቀበለትን ገንዘብ እንዱመልሱ የተወሰነበት አግባብነት ከፍ/ህ/ቁ.1723(1) እና የሰ/መ/ እንዱሁም ተያያዥ ነጥቦች መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት መዜገቡ ለሰበር ችልት ይቅረብ ተብል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዞል።
የተጠሪዎች ጠበቃ በቀን 01/02/2014ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል ተደርጓል ተብል የቀረበው የቤት ሽያጭ ውል ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትል የተደረገና የሚፀና ውል የለም፣ ምክንያቱም ከ1ኛ አስከ 6ኛ ተጠሪዎች ቤቱን ለተጠሪ አልሸጥንም፣ የሽያጭ ውልም አልተዋዋልንም፣ የሽያጭ ገንዘብም አልተቀበልንም።
አመልካች ከ7ኛ ተጠሪ ጋር አደረጉት የተባለው የቤት ሽያጭ ውልም ቢሆን ህግ በሚፈቅደው መሰረት ሥርዓቱን ተከትል በውልና ሰነድች ማረጋገጫ ምዜገባ ጽ/ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበና ገና በሂደት ላይ የነበረ በመሆኑ ውለ በህጋዊ መንገድ ተፈጽሟል ለማለት የሚቻል አይደለም።የቤት ሽያጭ የለም እንጂ አለ እንኳን ቢባል ከመጀመሪያ ህጋዊ ባለመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል መስፈርት ጠብቆ ያልቀረበ ጉድለት ያለበት በመሆኑ ውለ ፈራሽ ነው ተብል በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰጠቱ የሚነቀፍ አይደለም። ተፈጽሟል የተባለው ውል በተንኮል የተቀነባበረ የመንደር ውል ከቅን ልቦና ውጭ የተጠሪዎች መብት የሚጎዲና ህግን የሚፃረር በመሆኑ ሉፀና አይገባም።ውል እንዱፈርስ አልጠየቁም የተባለው በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ ክርክር እና ውል መኖሩም እኛ አናውቅም ግማሻችን ከሀገር ውጭ የምንኖር፣ 1ኛ ተጠሪ እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆኑ ውል ለማዋዋል የማይችለ፣ 2ኛ ተጠሪ የአእምሮ ህመምተኛ በአማኑኤል የሚታከሙ በመሆኑ መቃወሚያ ማቅረብ አልተቻለም።የስር ፍ/ቤት ውለ ፈራሽ ነው ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት የሰጠው ውሳኔ የማይነቀፍ በመሆኑ ውሳኔው እንዱፀና በማለት ተከራክረዋል። አመልካች አቤቱታቸውን በማጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዜገቡ ጋር ተያይዞል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለበትን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች እና ከሰበር ችልት ዉሳኔዎች ጋር መርምረናል።
እንደሚታወቀዉ የሰበር ስርዓት የተዘረጋበት ዋና ዓላማ በህግ አተገባበር ወይም አተረጓጎም ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም ወጥ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዱኖር ማስቻል ነዉ።የሰበር ችልቱ ስልጣንም የመጨረሻ ዉሳኔ በተሰጠባቸዉ ጉዲዮች ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ይህንኑ በማረም ላይ የተገደበ መሆኑን ከሰበር ስርዓት መሰረታዊ ዓላማ የምንገነዘበዉ ጉዲይ ነዉ።የኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ ይዘትና መንፈስ ይህንኑ የሚያመለከት ሲሆን ቀደም ሲል ሰበር ችልቱ በተለያዩ መዜገቦች መሰረታዊ የህግ ስህተት ምንነት አመላካች ዉሳኔዎች መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን ጥር 13 ቀን 2013ዓ.ም የጸደቀዉ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በሰበር ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት ማለት ምን ማለት ነዉ ወይም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚያሰኙት ሁኔታዎች ምንድናቸዉ ለሚለው ትርጉም ሰጥቷል።(አንቀጽ 2/4/ ይመለከታል)።በአዋጁ አንቀጽ 4 ስር ከሀ-ሸ እንደተዘረዘረው በሰበር ችልቱ ላታይ የሚችል የመጨረሻ ውሳኔ፣ፍርድ፣ብይን ወይም ትእዚዜ ላይ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች የሚቃረን፣ህግን አለ አግባብ የሚተረጉም ወይም ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ህግ የሚጠቅስ፤ለክርክሩ አግባብነት ያለው ጭብጥ ሳይያዜ ወይም ከክርክሩ ጋር የማይዚመድ አግባብነት የላለው ጭብጥ ተይዝ የተወሰነ፣በዲኝነት ታይቶ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ውድቅ በማድረግ የተወሰነ፣በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ከዋና ፍርድ ጋር የማይገናኝ ትእዚዜ የተሰጠበት፣ጉዲዩን አይቶ የመወሰን የዲኝነት ስልጣን ሳይኖር የተወሰነ፣ የአስተዲደር አካል ወይም ተቋም ከህግ ዉጭ የሰጠዉ ውሳኔ ወይም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን አስገዲጅ ውሳኔ በመቃረን የተወሰነ ውሳኔ ጉዲይ ስለመሆኑ ተደንግጓል።ስለዙህም ለሰበር የቀረበው ጉዲይ ከእነዙህ ቢያንስ አንደን የሚያሟላ መሆን ይጠበቅበታል።
በተያዘዉ ጉዲይ ግራቀኙን ያከራከረው በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል በፍርድ ሃይል ሉፈጸም የሚችል የቤት ሽያጭ ውል አለ ወይ? የሚለው ነው። ከስር መዜገብ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው ተጠሪዎች ቤት አልሸጥንም በማለት የተከራከሩ ሲሆን በ7ኛ ተጠሪ እና በአመልካች መካከል ተደርጓል የተባለው ውልም ተገቢውን ስርዓት ተከትል አልተደረገም፤ የጸና የቤት ሽያጭ ውል የለም በማለት በዜርዜር መከራከራቸውን ያሣያል።የስር ፍርድ ቤትም ከተጠሪዎች ክርክር በመነሳት ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ውል ክደዋል፤ ውለም የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1678፣1719(2) እና 1723 ድንጋጌዎች መሰረት የተደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።
አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪዎች ውለን አምነዋል፤ የፍርማሉቲ ጉዲይ ማንሳታቸዉ ተቀባይነት ሉኖረዉ አይገባም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰበር ችልቱ ውሳኔና ህጉን የሚቃረን ነው በማለት ነው።
ግራቀኙን ያከራከረው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል አፈጻጸም ጉዲይ ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ወይም ላልች መብቶችን ለማስተላለፍ ወይም ለማቋቋም የሚደረግ ውል በጽሁፍ እና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዜገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት መደረግ እንዲለበት የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723/1/ ድንጋጌ ይዘት ያሥገነዜባል።እንደውለታው ዓይነት ወይም በህግ የተደነገገው የጽሐፍ ውል አደራረግን ሥርዓት አስመልክቶ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678 (ሐ)፣ 1719(2) እንደተመለከተው በህግ ፉት ሉፀና የሚችል ውል አስፈላጊ የሆነውን የውል አደራረግ ሥርዓት አሟልቶ የያዘ መሆን አለበት።በዙህ አግባብ ያልተደረገ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንደረቂቅ የሚቆጠር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1720(1) እና 1723 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።የምዜገባው ሂደት ባልተሟላበት ሁኔታ ደግሞ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ሕጋዊ ነዉ ልባል እንደማይችል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ግልጽ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በላልችም መሰል ክርክሮች ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ ሰጥቷል።ሰበር መ/ቁ/34803 ቅጽ8፣ መ/ቁ/ 78398 ቅጽ14 እና ላልች መዜገቦች መመልከት ይቻላል።የሰበር ችልት ውሣኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ እና 2878 መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ በውሳኔው ላይ አስፍሯል።(መ/ቁ21448 ይመለከታል)።ይኸውም የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723/1/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በአዋዋይ አካል ወይም በፍርድ ቤት ፉት እንዱረጋገጥ (authentication) የማድረጉ አስፈላጊነት በተዋዋይ ወገኖች መካከል የፀና ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ወይም ለማስረዲት ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2878 የተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዜገባ (registration) ዓላማ ደግሞ ውለ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዱኖረዉ ለማድረግ ሲባል ነው።በልላ በኩል ሰበር ችልቱ በሰበር መ/ቁ/36887 በሰጠዉ ውሳኔ ላይ እንዲመላከተው በሰበር መ/ቁ/ 21448 ላይ የተሰጠው ትርጉም ተከራካሪ ወገኖች በመካከላቸው የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን አምነው በውልና ማስረጃ አካል ባለመመዜገቡ ብቻ ውል የለም በሚል የሚቃወሙ ተከራካሪዎችን የሚያመለከት አይደለም በማለት ውለ ተፈጻሚ ላደረግ እንደሚችል ትርጉም ሰጥቶበታል።የዉሳኔው መነሻ ምክንያት በፍ/ብ/ህግ ቁ/1723/1/ መሰረት የሚከናወነው ውለን ማረጋገጥ ዋና አላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ በማስረጃነት እንዱያገለግል በመሆኑ ነው።
ከዙህ አኳያ የተያዘዉን ክርክር ስንመለከት ተጠሪዎች በስር ፍርድ በሰጡት መልስ ‹‹ቤቱን አልሸጥንም›› ካለ በኋላ ላልች የውል ፍርማሉቲ ክርክር ማቅረባቸው የሽያጭ ውለን ማመናቸውን ያሣያል በማለት አመልካቹ የሚከራከር ቢሆንም የተጠሪዎች ዜርዜር መልስ ይዘት እንደሚያሣየው የሽያጭ ዉል የለም፤የቀረበው ሰነድም ረቂቅ ነው በማለት በግልጽ መከራከራቸዉ ውለን ማመነቸውን የሚያሳይ አይደለም።ይልቁንም የቤት ሽያጭ ውል አለመፈጸማቸውን ክደው መከራከራቸውን ያሣያል።በውክልና ስልጣን ተዋውለዋል የተባለት 7ኛ ተጠሪ ውለን በግልጽ ስለማመናቸው አያሳይም።ተጠሪዎች ቤቱን አልሸጥንም፤የቀረበው ሰነድም ረቂቅ ነው ብለው ክደው ስለተከራከሩ ውል እንዱፈጸምለት የጠየቀው አመልካች የቤት ሽያጭ ውል መኖሩን ማስረዲት የሚችለው በህጉ ቅቡልነት ያለውን በአዋዋይ ፉት የተረጋገጠ ሰነድ በማቅረብ መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723(1) እና የሰበር ችልቱ በመ/ቁ/ 21448 የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ የሚያስገነዜብ ነዉ።
ስለዙህም ይህ ሰበር አጣሪ ችልት ለጉዲዩ ተፈጻሚነት በሰበር መ/ቁ/ 36887 ላይ የሰጠው ውሳኔ እንደሆነ አድርጎ የያዘው ጭብጥ በክርክሩ የተረጋገጠውን ፍሬነገር ያገናዘበ አይደለም። በመሆኑም ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ውለን በግልጽ ባላመኑበት ሁኔታ አመልካች ውለ በጽሁፍ መደረጉን ብቻ ሳይሆን ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት የተረጋገጠ ሰነድ ባለማቅረቡ የጸና የቤት ሽያጭ ውል የለም ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት አላገኘንም።
በልላ በኩል ውለ ረቂቅ ነው አመልካቾች ተገደው የሚፈጽሙት የቤት ሽያጭ ውል የለም ከተባለ ግራ ቀኙ ከውለ በፉት ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ ተገቢ ነው።አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው አማራጭ የዲኝነት ጥያቄ ይህንኑ የሚያሳይ ነው።ይሁንና አመልካች በአማራጭ የጠየቀው ዲኝነት ተጠሪዎች የተቀበለትን ገንዘብ አጠፋታ እንዱሁም ቅጣት እና ደላላ ወጪን ጨምሮ ገንዘቡን ከተቀበለበት 11/06/2009ዓ.ም ጀምሮ ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰን በማለት የጠየቀ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ክርክራቸውን እና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪዎች የተቀበለት ሶስት ሚሉዮን ብር መሆኑንና ገንዘቡም ቀብድ ሳይሆን የሽያጭ ዋጋ ከፉል (ቅድሚያ) ክፍያ መሆኑን አረጋግጧል።አመልካቾች የተቀበለት ቀብድ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ የተቀበለትን ገንዘብ ያህል መመለስ እንጂ አጠፋታ እንዱከፍለ አይገደደም። የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1885(2) እና 1815(1) ድንጋጌ ይዘት ይህንኑ ያመላክታል።ቀብድ ነው ቢባል እንኳን ተጠሪዎች ውለ አለመደረጉን ክደው በተከራከሩበት እና ውለ መደረጉን የሚያሳይ በህግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ውለ ውጤት ሉኖረው የማይችል በመሆኑ እና ቀብድ እና ውጤቱን አስመልክቶ በህጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በህግ አግባብ የሚደረግ ውልን ታሳቢ አድርገው የተቀረጹ ከመሆናቸው አንጻር ግራቀኙ የተቀባበለትን ገንዘብ ከመመለስ ባሻገር አጠፋታ ለመመለስ አይገደደም።ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ሶስት ሚሉዮን ብር ብቻ እንዱመልሱ በማለት ወስኗል።ወለደን የማይከፍለበት ምክንያት ስለመኖሩ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ምክንያት የለም።ገንዘቡ የተከፈለው ውለ እንዱፈጸም በሚል እንደመሆኑ ምንም እንኳን ተጠሪዎች ገንዘቡን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ወለድ እንዱታሰብ አመልካች የጠየቀ ቢሆንም ገንዘብ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ወለድ ሉታሰብ የሚችልበት ምክንያት የለም፤ በመሆኑም ተጠሪዎች ገንዘቡን ይዘዉ በመቆየታቸዉ ያለአግባብ ሉበለጽጉበት ስለማይገባና ውለ ባለመፈጸሙ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ወለድ እንዱታሰብ ማድረግ ፍትሃዊ ሆኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለል የማይንቀሳቀስ ንብረት በተመለከተ የሚደረግ ውል በህግ የተወሰነውን ፍርም ተከትል እንዱደረግ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፊይዲ ወይም ጠቀሜታ እንዱሁም ባህርይ አንጻር ጥበቃ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ይታወቃል።የፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 1723 ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የተቀረጸ ነው።ስለሆነም ውለ በጽሁፍ መደረጉ ብቻ ሳይሆን በሚመለከተው አካል ዘንድ እንዱረጋገጥ ማድረግ የተዋዋይ ወገኖች ግዳታ በመሆኑ ይህ ባልተፈጸመበት ሁኔታ ውጤት ሉኖረው አይችልም። ስለዙህም ሰበር ችልት ውለ መደረጉ በግራቀኙ ከታመነ (መ/ቁ/ 36887 እና ላልች መሰል መዜገቦችን ይመለከታል) ህጋዊ ዉጤት እንደሚያስከትል ትርጉም የሰጠ ቢሆንም የትርጉሙ ወሰን የድንጋጌውን ዓላማ(አንቀጽ 1723) ያገናዘበ መሆን አለበት።የድንጋጌው ዓላማ የጸና ውል ስለመኖሩ የሚቀርብ ማስረጃ በውል አዋዋይ ፉት የተረጋገጠ ሰነድ መሆን እንዲለበት ያሣያል።ሰበር ችልቱ የሰጠው ዉሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የቤት የሽያጭ ውለ መደረጉን በግልጽ አምነው የፍርም ክርክር የቀረበ ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የውሳኔዉ ይዘት ያስገነዜባል።ከዙህ ትርጉም አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ውለ መደረግ አለመደረጉን አስመልክቶ መታየት ያለበት ጉዲይ ተከሳሽ ውለን በግልጽ አለመካደ ሳይሆን ውለን በግልጽ ማመኑ ነዉ።ስለዙህም ውለ በአንቀጽ 1723 መሰረት ስልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ ባይሆንም ውለ ህጋዊ ዉጤት የሚኖረው ተከሳሽ ውለን በግልጽ ካመነ ብቻ ላሆን ይገባል።
በዙህ ጉዲይ ተጠሪዎች ቤቱን አልሸጥንም፤ውለም ረቂቅ ነው ብለው መከራከራቸው ውለን አምነዋል የሚያሰኝ አይደለም። የስር ፍርድ ቤቶችም ተጠሪዎች ውለን ክደው መከራካራቸዉን በማረጋገጥ የሰጡት ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል አደራረግ ስርዓት በሚመለከት በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1723/1/ የተደነገገውን እና ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/ 21448 የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/ እና 10(1ለ) መሰረት ለሰበር ችልቱ ከተሰጠው መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አንጻር ሲታይ ዉሳኔው ላይ ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተገኘም።በዙሁ አግባብ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማጽናት በመ/ቁ/201863 ላይ በቀን 13/09/2013ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/ተጠሪዎች በረቂቅ ውለ መሰረት የተቀበለትን ብር ሶስት ሚሉዮን በስር ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች እንዱከፍለ ብለናል።
3ኛ/ በዚህ ችልት የተደረገውን ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
4ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በ16/11/2016 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ መዜገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።
No topics extracted.