በቤት ሽያጭ ውል ሻጭ የሆነው አካል ቤቱን ገዝቻለሁ ከማለት ውጪ ለገዥ ለማስተላለፍ በስሙ ያስመዘገበበት ሁኔታ ስለመኖሩ የሚገልጽ ማስረጃ ወይም ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል ላላ ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ የሚያስረዲ ማስረጃ በላለበት የቤቱ ስመ ሀብት በገዥ ስም በመመዝገቡ ብቻ ሻጭ ቤቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ ከዉል ወይም ከህግ የመነጨ መብት ያለዉ መሆኑን የማስረዲት ሸክም ባልተወጣበትና የራስ ባልሆነ ቤት ላይ የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ተፈፃሚነት የላለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808፣1784 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች፣የፍ/ብ/ህ/ቁ 2281 እና 2282፣ እንዱሁም 1195 እና 1196
No summary available.
መ/ቁ/208266 ሚያዝያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ስሜነህ ዘሪሁን - ጠበቃ አለባቸው - ቀረቡ ተጠሪዎች፡ 1ኛ/ አቶ ጀማል ሰይድ 2ኛ/ አቶ ወንደ ጣፉያ አልቀረቡም 3ኛ/ ወ/ሮ ኤደጋ ድምና መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በዚህ ችልት እንዱታረም በሚል ነው።
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደተመለከትነው ክርክሩ የተጀመረው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ ሲሆን የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ ገቦች ሲሆኑ የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።1ኛ ተጠሪ ባቀረበው ክስ አመልካች በ225 ካ.ሜ ላይ የተሰራውን ቤት በብር 150,000 ሽጦልኝ የስመ ንብረት የዞረልኝ ቢሆንም የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ቤቱን አለቅም ስላለ ቤቱን አስለቅቆ እንዱያስረክበኝ ወይም ውለ ፈርሶ ገንዘቡን ከነቅጣቱ እንዱከፍል እንዱወሰን ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስ እኔ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ የሸጥኩት እና ስመ ሀብቱም የተላለፈለት በመሆኑ ቤቱን ያለአግባብ የያዙት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን ተገደው እንዱወጡ ክስ ከማቅረብ ውጭ እኔ ልጠየቅ አይገባም፤ ቤቱን የገዛው ስም ሳይዞር ነው፤አሁን ስም ስለዞረለት ሉጠይቀኝ አይችልም በማለት የተከራከረ ሲሆን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ቤቱን አልሸጥንም፤ 1ኛ ተጠሪም ለመሸጥ የሚያስችለው መብት የለውም፤በስሙ የተመዘገበው ከማዘጋጃ ቤት ሰራተኛ ጋር በመመሳጠር ነው በማለት ቤቱን ለማስረከብ አንገደድም ሲለ መከራከራቸውን መዝገቡ ያሣያል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የሸጠውን ቤት በአመልካች ስም ያልተመዘገበ እና የራሱ ያልሆነውን የሸጠ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1715(2) መሰረት ውለ ፈራሽ ስለሆነ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ የተቀበለውን ገንዘብ ብር 150,000 የመመለስ ግዳታ አለበት በማለት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1815 ምርኩዝ በማድረግ ወስኗል።በ1ኛ ተጠሪ እና በጣልቃ ገቦች (2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች) መካከል ያለው የቤት ሽያጭ ውል የፀና ነው የሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱን መዝገቡ ያሣያል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ጉዲዩ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞበታል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አያስቀርብም በማለት አቤቱታውን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችልት ያቀረበው ይህንኑ ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፡- ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት በሚመለከት አመልካች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ ጥቅምት 10/2009 ዓ.ም በተፃፈው ውል ብር 70,000 መግዛቱን፤ይህንኑ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ ብር 150,000 ጥር 14 ቀን 2009 ዓ.ም በተፃፈ ውል በሽያጭ ማስተላለፈን ፤ስመ ሀብቱ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱዞር አመልክቼ ተቃዋሚ እንዱቀርብ ማስታወቂያ ተለጥፍ ስመ ሀብቱ ለ1ኛ ተጠሪ ተላልፎል፤ይህም በስር ፍ/ቤት በተከራካሪዎች የታመነ እና ስም የተዛወረበት ሰነድም መቅረቡን፤
ስለሆነም በህጉ መሰረት የተፈፀመ ሽያጭ ውል እና ስመ ሀብቱ የዞረ እና አከራይቶ ሲጠቀም የቆየው ውለ ይፍረስ ማለቱ ከፍተኛ መሰናክል የሚፈጥር እና የሰበር ሰሚ ውሳኔ በሰ/መ/ እንዱሁም በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 36(4) የተደነገገውን የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ጥሰት ተፈፅሟል። 1ኛ ተጠሪ በስሙ የተላለፈውን ቤት በተመለከተ ይፀናል በማለት መወሰኑ፣ በልላ በኩል ደግሞ አመልካች የተቀበለውን ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱመለስ መወሰኑ አመልካች ሁለት ጊዜ እንዱቀጣ የሚያደርግ እና 1ኛ ተጠሪ ሁለቴ እንዱጠቀም የሚያደርግ በመሆኑ ተከራካሪዎች በህግ ዘንድ እኩል የመታየት እና ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ በመሆኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አላግባብ ቤቱን ይዘው የሚገኙ ከሆነ በህግ እንዱለቁ ክስ ከማቅረብ ውጭ አመልካች የሚጠየቅበት እና ውለ ከተፈፀመ ከ4 ዓመት በኋላ እንዱፈርስ እና ገንዘብ እንዱመለስ የሚደረግበት አግባብ የላለ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል እንዱታረም የሚል ነው።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ስመ ሀብት ወደ 1ኛ ተጠሪ በዞረበት እና ቀሪ ገንዘቡንም ለአመልካች የከፈላቸው ስለመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታቸው ላይ ጠቅሰው እያለ የቤት ሽያጭ ውለ እንዱፈርስ አመልካች የተቀበለትን ገንዘብ እንዱመልሱና የሚፈፀም የስም ዝውውር አይኖርም በሚል የተወሰነበት እንዱሁም ላልች ተያያዥ ነጥቦች መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዟል።
1ኛ ተጠሪ ባቀረበው መልስ አመልካች ይህንን ቤት ለ1ኛ ተጠሪ መሸጡንና ገንዘብ መቀበለ እና የስም ዝውውር ለ1ኛ ተጠሪ መደረጉ ያልተካካደ ጉዲይ መሆኑን ነገር ግን አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የሸጠው ቤት ላይ ህጋዊ መብት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለው በስር ፍ/ቤት በጭብጥነት ተይዞ በማስረጃ ሲጣራ ተጠሪ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ በሚሸጥበት ጊዜ ቤቱ በራሱ ስም ያልተመዘገበ የንብረቱ ባለቤት በ2ኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበ እና 2ኛ ተጠሪም ሆነ ባለቤታቸው 3ኛ ተጠሪ ቤቱን እንዱሸጡ ውክልና ያልሰጧቸው መሆኑ ተረጋግጧል፤አመልካች ይህንን ለማስተባበል በቂ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ አመልካች መብት ሳይኖረው በአየር ላይ በቀን 14/05/2009 ዓ.ም የፈፀመው የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ መደረጉ የህግ ስህተት የለውም። ውለ ሉፈርስ አይገባም ከተባለ በስር ፍ/ቤት በአማራጭ የጠየኩትን ዲኝነት አመልካች ቤቱን ከማንኛውም 3ኛ ወገን ነፃ በማድረግ እንዱያስረክበኝ ውሳኔ እንዱሰጥ በማለት ተከራክረዋል።1ኛ ተጠሪ ባቀረበው መልስ ላይ አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች መጥሪያ የደረሳቸው ቢሆንም መልስ ያላቀረቡ በመሆኑ የፅሁፍ መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለበት ጭብጥ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብ ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበነው 1ኛ ተጠሪ ዲኝነት የጠየቀው አመልካች የሸጠለትን ቤት ነፃ በማድረግ እንዱያስረክብ ወይም ውል እንዱፈርስ የሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ ቤቱን ያለአግባብ የያዙ ሰዎችን ከሚጠይቅ በስተቀር ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የተከራከረ ሲሆን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ክርክር የተነሳበት ቤት በሽያጭ አለማስተላለፊቸውን እንዱሁም አመልካች ለመሸጥ የሚያስችለው መብት እንደላለው እና ቤቱ የግል ንብረታቸው መሆኑን ገልጸው መከራከራቸውን መዝገቡ ያሣያል። ፍርድ ቤቱም የቤት ሽያጭ ውለ ሉፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም አሉያም ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለ ጭብጦችን በመያዝ በማስረጃ አጣርቶ አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል መብት እንደላለው በማረጋገጥ ውለ ፈርሶ ከውለ በፉት ወደ ነበሩበት እንዱመለሱ የሰጠው ውሳኔ በክልለ ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት ጸንቷል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ያጸና በመሆኑ በዚህ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለሰበር ችልቱ ከተሰጠው ስልጣን ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደሚታወቀው የሰበር ስርዓት በህግ አተገባበር ወይም አተረጓጎም ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዱኖር ማስቻል ነው። የሰበር ችልቱ ስልጣንም የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠባቸው ጉዲዮች ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ይህንኑ በማረም ላይ የተገደበ መሆኑን ከሰበር ስርዓት መሰረታዊ ዓላማ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ ይዘትና መንፈስ ይህንኑ የሚያመልከት ሲሆን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በሰበር ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚያሰኙት ሁኔታዎች ምንድናቸዉ ለሚለው ትርጉም መሰጠቱ (አንቀጽ 2/4/ ይመለከታል) ሰበር ሰሚ ችልት የተቋቋመበትን ዓላማ ማለትም ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዱኖር እና የውሳኔዎችን ተገማችነት በማረጋገጥ ረገድ አገራዊ ፊይዲ ያላቸው ጉዲዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እንዱሰራ የሚያስችል ነው ተብል ይታሰባል።
በተለይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠ ውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ተቀብል በሰበር የማየት ስልጣን የሚኖረዉ ውሳኔው/ትዔዛዙ/ብይኑ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን አስገዲጅ ውሳኔ የሚቃረን ሲሆን እንዱሁም አግባብነት የላለውን ህግ በመጥቀስ ወይም ህግን ያላግባብ በመተርጎም የተሰጠ ውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ሆኖ ጉዲዩም አገራዊ ፊይዲን የሚመለከት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ከዚህም የምንረዲው የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ከእነዚህ ሦስቱ ሁኔታዎች ውጪ ባለት ሁኔታዎች፣ መሰረታዊ የህግ ስህተትን መስፈርት አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ውስጥ አንደን የሚያሟላ ሆኖ ቢገኝ እንኳን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በሰበር የማረም ስልጣን የላለው መሆኑን ነው።ስለሆነም ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትን ውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን በመቃወም የቀረበለት አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ከሆነ ውሳኔዉ/ትዔዛዙ/ብይኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ እነዚህኑ ልዩ ሁኔታዎች ማለትም በአዋጁ አንቀጽ 10(1/ሐ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከግምት ዉስጥ የማስገባት ኃላፉነት ይኖርበታል።
በተያዘዉ ጉዲይ ግራቀኙን ያከራከረው በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ሉፈርስ ይገባል ተብል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን አለመሆኑ ጉዲይ ነው።
በመሰረቱ የውለታዉ ጉዲይ የሚቻል፣ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ካልሆነ እና ተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ ወይም ችልታ ጉድለት የላለበት እንዱሁም በህግ የተደነገገውን የውል አደራረግ ስርዓት ተከትል ተዋዋይ ወገኖች ወደውና ፈቅደው የሚያደርጉት ውል ህግ ሆኖ የሚያስገድዲቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1678 እና 1731/1 ድንጋጌ ያስገነዝባል። እንደውለ ያልተፈጸመለት ወገን አንድም ውለ እንዱፈጸምለት ወይም ውለ እንዱሰረዝና ኪሳራ እንዱከፈለዉ መጠየቅ ይችላል።የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1771 ይመለከታል። ዉለ እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዝ የሚደረገው አንድም በህግ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱና የዉለ አደራረግ ጉድለት ያለበት ሲሆን ወይም ውለ እንዲይፈጸም የሚያደርግ መሰናክል ሲፈጠር አሉያም አንደኛዉ ተዋዋይ ወገን ግዳታውን ለመወጣት የማይችል መሆኑ በማያጠራጥር ሁኔታ ሲረጋገጥ ወይም የውለ አይነተኛ ጉዲይ የተነካ ከሆነ ወይም በልላ ምክንያት በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት የተደረሰበት ከሆነ ነው።(የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808፣1784 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች ይመለከታል)። በህግ አግባብ የተቋቋመ ውል በተቻለ መጠን እንዱፈጸም ማድረግ የፍርድ ቤቶች ኃላፉነት ነዉ።
በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በ14/05/09ዓ.ም የቤት ሽያጭ ውል መደረጉ አላከራከረም።
ይሁንና ቤቱ በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ይዞታ ስር መሆኑ ብቻ ሳይሆን አመልካቹም ቤቱን ከእነዚህ ተጠሪዎች የገዛ መሆኑንና ስመ ሀብቱ በስሙ ሳይመዘገብ ለ1ኛ ተጠሪ አሳልፍ የሸጠ መሆኑን ገልጾ የተከራከረ ሲሆን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው ቤቱን ለአመልካች አለመሸጣቸውን ይልቁንም ቤቱን ሳይጨምር ከመሬት ይዞታቸዉ ላይ ቆርሰው መሸጣቸውን ገልጸው በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል ሉፈጸም እንደማይችል ተከራክረዋል።ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች አከራካሪውን ቤት በሽያጭ ለማስተላለፍ መብት ያለው መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል።፡በፍ/ብ/ህ/ቁ 2281 እና 2282 መሰረት ሻጭ ለገዥው የሸጠውን ነገር የማያስነካ መብት ለገዥው ማስተላለፍ እና የእኔ ነው ባይ ሲመጣ ዋቢ የመሆን ግዳታ ያለበት መሆኑን ይደንግጋል። ቤቱ የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ንብረት እንደነበር ያላከራከረ እና አመልካችም ቤቱን ከእነዚሁ ገዝቻለሁ ከማለት ውጪ ቤቱን በስሙ ያስመዘገበበት ሁኔታ ስለመኖሩ የሚገልጽ ማስረጃ ወይም ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል ላላ ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ የሚያስረዲ ማስረጃ አለማቅረቡን የስር ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ፍሬ ነገር ጉዲይ ነው።
አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረው የቤቱ ስመ ሀብት በ1ኛ ተጠሪ መመዝገቡ ተረጋግጦ እያለ ውለ ሉፈጸም አይችልም ተብል መወሰኑ ስህተት ነው በማለት ነው። በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195 ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በማወቅ በአስተዲደር አካል ማስረጃ የተሰጠው ሰው የዚሁ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ የህግ ግምት የሚወሰድ ቢሆንም ይህ የህግ ግምት ሉስተባበል እንደሚችል የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1196 ድንጋጌ ይዘት ያመላክታል። አመልካች እና ተጠሪን ያከራከረው ጉዲይ በሽያጭ የተላለፈው ቤት ስመሀብት በተጠሪው ስም የተመዘገበ ቢሆንም ቤቱን በይዞታቸው ስር አድርገው እየተጠቀሙበት ያለት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የሽያጭ ውለንም ሆነ ስመ ሀብቱ በ1ኛ ተጠሪ የተመዘገበበት ሁኔታ ተገቢነት እንደላለዉ የበኩላቸውን ክርክር በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱም የተረጋገጠው ፍሬ ነገር የቤቱ ስመ ሀብት በአመልካች ባልታወቀበት ሁኔታ አመልካች ግዳታውን ለመፈጸም እንደማይችል በማረጋገጥ ውለ እንዱፈርስ የሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱን መገንዘብ ችለናል። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ቤቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ ከውል ወይም ከህግ የመነጨ መብት ያለው መሆኑን የማስረዲት ሸክም ባልተወጣበት ሁኔታ ስመ ሀብቱ በ1ኛ ተጠሪ ስም መመዝገቡን ብቻ መሰረት አድርጎ ያቀረበው ክርክር ውድቅ መደረጉ ስህተት ነው የሚባልበት ምክንያት የለም።
ላላኛው የአመልካች አቤቱታ ነጥብ የስር ፍርድ ቤት በአንድ በኩል ውለ ፈራሽ ነው ገንዘቡን ለ1ኛ ተጠሪ እንዱመልስ ወስኖ እያለ ቤቱ በ1ኛ ተጠሪ ስም እንደተመዘገበ ይጸናል ማለቱ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጭ እና ተጠሪው ሁለቴ እንዱጠቀም ያደረገ ነው የሚል ነው። ዲኝነት ላሰጥ የሚገባው በተጠየቀው ልክ እና አግባብብ ብቻ መሆን እንዲለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 182 በግልጽ ደንግጓል። በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ችልት በተለያዩ መዝገቦች የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔም ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነው። ሰበር መ/ቁ/86510 ቅጽ 15 እና ላልች መዝገቦችን መመልከት ይቻላል። መዝገቡ እንደሚያሣየው የ1ኛ ተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ አመልካች ቤቱን እንዱያስረክብ ይህ ካልተቻለ ውለ ፈርሶ ገንዘቡን እንዱመልስለት የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱ አመልካች የራሱ ያልሆነ ቤት መሸጡን በማረጋገጥ ውለ ሉፈጸም ስለማይችል አመልካች ገንዘቡን ለ1ኛ ተጠሪ ይመልስ ካለ በኋላ የቤቱ ስመ ሀብት በ1ኛ ተጠሪ ስም እንደተመዘገበ ይጸናል ማለቱ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጪ መሆኑን ያሣያል። ከዚህም ላላ በክርክሩ ሂደት እንደተገለጸው 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የሸጡት ቤቱን ሳይሆን ከይዞታቸዉ ላይ መሬት ቆርሰው መሸጣቸውን ገልጸው ተከራክረዋል። በተለይም በቀን 13/02/08ዓ.ም እና በ10/02/09 የተደረጉ ውልች ለስር ፍርድ ቤት ስለማቅረባቸዉ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ተጠቅሷል።
ይሁንና 1ኛ ተጠሪን እና አመልካችን ያከራከረው በቀን 14/05/2009ዓ.ም የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም እና ውለ የሚፈርስ ከሆነ የሚኖረው ህጋዊ ውጤት እንጂ ላልቹን ውልች በሚመለከት የተጠየቀ ዲኝነት ስለመኖሩ መዝገቡ አያሣይም። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካችም ሆነ ተጠሪዎች በልላ አግባብ ያላቸውን የውል ወይም ላላ የህግ ምክንያት መሰረት አድርገው የሚጠይቁትን መብት በማይነካ ሁኔታ መወሰን ሲገባው የቤቱ ስመ ሀብት በ1ኛ ተጠሪ እንደተመዘገበ ይቀራል ማለቱ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጭ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለል በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በቀን 14/05/2009ዓ.ም የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል መብት የላለው መሆኑን በማረጋገጥ ውለ ሉፈጸም የማይቻል ነው በማለት እንዱፈርስ እና አመልካች ገንዘቡን ለ1ኛ ተጠሪ እንዱመልስ ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ጉድለት ያልተገኘበት ሲሆን በልላ በኩል ግን የቤቱ ስመ ሀብት በ1ኛ ተጠሪ እንደተመዘገበ ይረጋል በማለት የሰጠው ውሳኔ ክፍል ዲኝነት ያልተጠየቀበት በመሆኑ እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 182 እንዱሁም የሰበር ችልቱን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/ሸ/ እና 10/1/ሐ መሰረት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል። በዚሁ አግባብ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማጽናት በመ/ቁ/11260 ላይ በቀን በ15/08/2013ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/ በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በቀን 14/05/2009ዓ.ም የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ እና አመልካች ገንዘቡን ለተጠሪ እንዱመልስ የተሰጠው ፍርድ ክፍል ባለበት ጸንቷል።
3ኛ/ የቤቱ ስመ ሀብት በ1ኛ ተጠሪ እንደተመዘገበ ይረጋል በማለት የተወሰነው ከተጠየቀው ዲኝነት ዉጭ ስለሆነ ተሽሯል።
4ኛ/ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
5ኛ/ በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 11/10/2013ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
No topics extracted.