በጣልቃ ገብነት ይርጋን በመቃወሚያነት በማንሳት ለሚቀርብ ክርክር የላላኛው ተከራካሪ ወገን ከሚያቀርበው መከራከሪያ ጋር አከራክሮ ውሳኔ መስጠት ሲገባ ጣልቃ ገብቶ የሚከራከር ወገን ይርጋን እንደመቃወሚያ አንስቶ ሉከራከር አይችልም በሚል የይርጋ መቃወሚያ ክርክር ውድቅ የሚደረግ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358-360
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 25/4/2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካችቸ፡- ወ/ሮ ክላሪስ ዳኒስ ቶምሰን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ት ቤቴልሄም አስራት - ጠበቃ መላኩ አድነው - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የቀረበው አመልካች መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው። ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችልት በኩል ላታይልኝ ይገባል የምትለውን ዲኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ የይርጋ መቃወምያዬን ውድቅ ያደረገው ይርጋ የሚያነሳው የመቃወሚያ ተጠሪ እንጂ የመቃወሚያ አመልካች አይደለችም በሚል አረዲድ ሲሆን የመቃወሚያ አመልካች በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ጣልቃ ገብታ ስትከራከር የመቃወሚያ ተጠሪን አቤቱታ በመቃወም በመሆኑ አመልካች እንደሚቀርብባት አቤቱታ መወሰድ ነበረበት። የመቃወሚያ ተጠሪ ማስረጃውን የወሰደችው ከ3 ዓመት በኋላ በመሆኑ ማስረጃዋ በይርጋ ሉሰረዝ ሲገባ መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የመቃወሚያ አመልካች (የአሁን አመልካች) ባቀረበችው አቤቱታ የመቃወሚያ ተጠሪ (የአሁን ተጠሪ) በመ/7 ላይ የተሰጣት የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝልኝ። ይሄውም የመቃወሚያ ተጠሪ ማስረጃውን ለማግኘት አቤቱታ ያቀረበችው አቶ አስራት ግዛው ከሞተ ከ4 ዓመት በኋላ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል። የመቃወሚያ ተጠሪ የሟች አቶ አስራት ግዛው ልጅ አይደለችም። ልጅነቷንም አልተቀበለም ማስረጃዋ ውድቅ ይሁንልኝ ስትል ጠይቃለች። የመቃወሚያ ተጠሪም ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታዋን በቀጥታ ተቀብል ማስተናገድ አይችልም።
የከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ ማየት እንጂ ጉዲዩን በቀጥታ ማየት የማይችልና ጉዲዩን ማየት የሚችለው ማስረጃውን የሰጠው ፍ/ቤት ነው። አመልካች አቤቱታዋን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የላትም። ጉዲዩ በልላ ፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ አቤቱታዋ ውድቅ ይሁንልኝ። የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠኝ ልጅነቴን አረጋግጬ ነው። በውርስ በሚደርሰኝ ንብረቶችም እየተጠቀምኩበት በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። የመቃወሚያ አመልካች የሟች አቶ አስራት ልጅ አይደለችም። ከሟች እህቶቹና ወንድሞቹ ጋር ተከራክራ የሀሰት ልጅነት ማስረጃ ወስዲለች። የወሰደችው የልጅነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ በሚል መልስ ሰጥታለች። የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/5 ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ የመቃወሚያ አመልካች ያቀረበችውን የመቃወሚያ ተጠሪ የሟች አቶ አስራት ግዛው ልጅ አይደለችም፣ የወራሽነት ማስረጃዋ ይሰረዝልኝ አቤቱታ በማስረጃ ያላስረዲች በመሆኑ የመቃወሚያ አቤቱታዋ ውድቅ ነው ሲል ወስኗል። የመቃወሚያ አመልካች ለአማራ ብ/ክ/መ.
ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ አከራክሮ በመ/ቁጥር 01-19572 የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ሟች አቶ አስራት ግዛው የሞተው በ15/4/2003 ዓ/ም ሲሆን የመቃወሚያ ተጠሪ የወራሽት ማስረጃ ይሰጠኝ አቤቱታ ለወረዲ ፍ/ቤት ያቀረበችው በ7/8/2007 ዓ/ም ነው። ማስረጃው የተሰጣት በ9/8/2007 ዓ/ም ነው። የመቃወሚያ ተጠሪ ጥያቄውን ያቀረበችው ከ3 ዓመት ከ4 ወር በኋላ ነው። በመሆኑም በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ማስረጃ የወሰደችው ከ3 ዓመት በኋላ በመሆኑ አቤቱታዋ በይርጋ ውድቅ የሚሆን ነው። የወሰደችው የወራሽነት ማስረጃዋ ተሰርዟል ሲል የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ወስኗል። የመቃወሚያ ተጠሪ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ አከራክሮ በመ/ ሰኔ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ የመቃወሚያ ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ አቤቱታ ያቀረበችው የመቃወሚያ አመልካች አንጂ የመቃወሚያ ተጠሪ አይደለችም። የይርጋ መቃወሚያ የሚታየው ከእውነተኛ የወራሽነት ጥያቄ አንጻር አንጂ የመቃወሚያ ተጠሪ አስቀድማ ከወሰደችው የወራሽነት ማስረጃ ላይ ባለመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የመ/ተጠሪን አቤቱታ በይርጋ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ሲል የክልለን ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሮ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍሬ ነገሩ ላይ አከራክሮ አንዱወስን ሲል መልሶለታል።
የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርባለች። መዝገቡም ተመርምሮ በፍርድ ቤት አስቀድሞ በተሰጠው የወራሽነት ማስረጃ ላይ ተቃውሞ በሚያቀርብ አመልካች በኩል ይርጋ ሉነሳ አይገባም ተብል በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተወሰነበትን አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 1000 እና 999 አንጻር ለመመርመር ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዲልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ስትል ተከራክራለች። አመልካችም መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታዋን በማጠናከር ተከራክራለች።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልሱን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር አሁን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት መዝገብ ምክንያት የሆነው የይርጋ ክርክር በተመለከተ የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ባቀረበችው አቤቱታ ተጠሪ የሟች አቶ አስራት የወራሽነት ማስረጃ የወሰደችው ከ3 ዓመት በኋላ በመሆኑ አቤቱታዋ በይርጋ ውድቅ መሆን ሲገባ ወራሽ ነች ተብል መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ ማስረጃዋ ይሰረዝልኝ ስትል የጠየቀች ሲሆን ተጠሪም የአሁን አመልካች ላቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ በውርስ በሚደርሰኝ ንብረቶች እየተጠቀምኩበት በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ስትል መልስ ሰጥታለች። የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ያቀረበችውን የይርጋ መቃወሚያ በተመለከተ የሰጠው ብይን ስለመኖሩ ውሳኔው አያመለክትም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5(3) በቀድሞው ክርክርና ሙግት ላይ በግልጽ ዲኝነት ተጠይቆበት ጥያቄው ተቀባይነትን ሳያገኝ የታለፈ እንደሆነ በዚህ ቁጥር አግባብ የተጠየቀው ዲኝነት እንደተከለከለ እንደሚቆጠር ደንግጎ ይገኛል። የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በሰጠው ውሳኔም ትርጉም ሰጥቶበታል። የአሁን አመልካች ይርጋን በመቃወሚያነት ያቀረበችውን ክርክር የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ምንም ሳይል በማለፈ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባበት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአሁን አመልካች ያቀረበችውን ይርጋ መቃወሚያ አከራክሮ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ የአሁን ተጠሪ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባበት የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አከራክሮ የአሁን አመልካች ተከሳሽ ሆና ካልቀረበች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ባቀረበችው አቤቱታ ይርጋን እንደመቃወሚያ ልታነሳ አትችልም በሚል ትርጉም የአሁን አመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 በክርክር ውስጥ ተካፊይ መሆን የሚገባው ወይም በክርክሩ ውስጥ ለመግባት የሚችልና እንዱሁም ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸውም ሰው ራሱ ወይም ጠበቃው ወይም ነገረ ፈጁ ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ ከመፈጸሙ በፉት መቃወሚያውን ላማቅረብ እንደሚችል ይደነግጋል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 360(2) የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሰማበት ሥነ ሥረዓት መሰረት ሆኖ ፍርድ ቤቱ ነገሩን ካጣራ በኋላ መቃወሚያ የቀረበበትን ፍርድ ለማጽደቅ ለማሻሻል ወይም ለመለወጥ ወይም ለመሰረዝ እንደሚችል ደንግጎ ይገኛል። ፍ/ቤቶች ክርክሩን በመደበኛው ሥነ ሥረዓት ግራ ቀኙን ሲያከራክሩ በተሰጠው ውሳኔ መብቴ ተነክቶብኛል ሲል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ጣልቃ ገብቶ የሚከራከር ወገን መብቱ የሚነካበትን ምክንያት እና ውሳኔውን ለማስለወጥ ቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ክርክር ውስጥ ተካፊይ ቢሆን ኖሮ ሉያነሳቸው የሚገባቸውን ክርክሮች ሁለ አንስቶ መከራከር ይጠበቅበታል። በዚህ ጉዲይ የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ጣልቃ ገብታ የምትከራከረው የአሁን ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ተጠሪ የሟች ወራሽ ነች ተብል የተሰጠው ውሳኔ መብቷን የሚነካበትን ሁኔታ ቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተከራካሪ ብትሆን ኖሮ ሉታነሳ የምትችለውን መከራከሪያዎች፣ የተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ሉሰረዝላት የሚገባበትን ምክንያቶች ሁለ አንስታ መከራከር የሚገባትና የአሁን ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ የወሰደችው አቤቱታዋን ማቅረብ በሚገባት ጊዜ ውስጥ አይደለም አቤቱታዋ በይርጋ ቀሪ መሆን ነበረበት የሚል መቃወሚያንም ጨምሮ አንስታ መከራከር የምትችል፣ ፍ/ቤቶችም አከራክረው ውሳኔ መስጠት የሚገባቸው ነው። የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአሁን አመልካች ይርጋን በመቃወሚያነት ያቀረበችውን ክርክር የአሁን ተጠሪም በውርስ ንብረቱ እየተጠቀምኩበት በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ስትል ካቀረበችው መከራከሪያ ጋር አከራክሮ መወሰን ሲገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ጣልቃ ገብቶ የሚከራከር ወገን ይርጋን እንደመቃወሚያ አንስቶ ሉከራከር አይችልም ሲል የአሁን አመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ክርክር ውድቅ ማድረጉ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358-360 ድንጋጌዎች ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአሁን አመልካች ይርጋን በመቃወሚያነት ያቀረበችውን ክርክር እና የአሁን ተጠሪም በውርስ ንብረቱ እየተጠቀምኩበት በመሆኑ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ስትል ካቀረበችው መከራከሪያ ጋር አከራክሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 341(1) መልሰንለታል።
በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ከስር ፍ/ቤት የመጣው መዝገብ በመጣበት ሁኔታ ይመለስ ብለናል።
በሰበር ሰሚ ችልት ጥር 20 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የመ/ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል።
የአሁን ተጠሪ ያቀረበችው የመስቀለኛ አቤቱታ በዚህ ውሳኔ እልባት ያገኘ በመሆኑ ታልፎል።
የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.