የአፈፃፀም ተከሳሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 439 መሰረት በዋናው ፍርድ ላይ እንዱከፍል የተወሰነበትን እዲና ቤቱም በጨረታ ለመሸጥ የወጣውን ወጪ መክፈል እንደሚፈልግና ገንዘቡን እንደሚያሲዝ በመግለፅ የጨረታው ሑደት እንዱቆምለት እና በልላ በኩል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 430(1)፣(3) ድንጋጌን መሰረት አድርጎ በቤቱ ሽያጭ ጨረታ ላይ በአፈፃፀም ከሳሾች ተፈፅመዋል የሚላቸውን ቅን ልቦናን መሰረት ያላደረጉ እና ሕገ አቶ አቡበከር ዓሉ እና እነ አቶ ተስፊዬ እንድሪስ (2 ሰዎች) ድርጊቶች በመዘርዘር ጨረታው እንዱሰረዝለት የሚያቀርባቸው አቤቱታዎች የተለያዩ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረጉና የሚያስከትለት ውጤትም ለየቅል በመሆኑ ጉዲዩ በአግባቡ ሣይመርምር አቤቱታው በድጋሚ የቀረበ ነው፤ ጨረታው የሚሰረዝበት ምክንያት የለም በሚል አቤቱታው ውድቅ የሚደረግ ስላለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ ታሕሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ አቡበከር ዓሉ - ቀርበዋል።
ተጠሪዎች፡-
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተበል እንዱታረምለት አመልካች በመጠየቁ ነው።
ጉዲዩ የአፈፃፀም ክርክር የሚመለከት ሆኖ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር አመልካች ባለቤቴ ናት ከሚላት ሰው ጋር ሆኖ የአፈፃፀም ተከሣሽ ተጠሪዎች ደግሞ የአፈፃፀም ከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ለሰበር ክርክሩ መነሻ የሆነው የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመዝገብ በሆነው መጋቢት 21 ቀን 2013ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ነው። የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው፡- አመልካች ለተጠሪዎች እንዱከፍል በተወሰነበት እዲ ምክንያት ተጠሪዎች ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ክርክር በላለበት ታይቶ በባህር ዲር ከተማ የሚገኘው የአመልካች ቤት በጨረታ ተሸጧል። ከዚህ በኋላ አመልካች የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታው በአፈፃፀም ክሱ መጥሪያ አደራረስ፣ የጨረታው አሸናፉ ከፍርድ ባለገንዘቦች ጋር ያለውን ግንኙነት፣ ከጨረታው ሂደትና የቤቱ ስመ ንብረት የጨረታ አሸኛፉ ነው ለተባለው ሰው እንዱዞር በተሰጠው ትዕዛዝ አፈፃፀም ላይ ተፈፅሟል ያላቸውን የቅን ልቦና ጉድለትና ሕገ ወጥ ድርጊቶችን በመዘርዘር ጨረታው እንዱሰረዝለት የጠየቀ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካች ቀደም ሲል ፍርድ ቤቱ በትዕዛዝ ያለፈውን ጉዲይ በድጋሚ ያቀረበው ነው ሲል ውድቅ አድርጓል። በዚህ ትዕዛዝ ቅር የተሰኘው አመልካች የይግባኝ አቤቱታውን ለፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ስለተሰረዘበት ይህ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች ሚያዚያ 12ቀ ን 2013 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታው ቀደም ሲል ያቀረበውና ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገበት አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 439 መሰረት እዲውንና ለጨረታው የወጣውን ወጪ ለመክፈል እንደሚፈልግና የጨረታው ሂደት እንዱቋረጥለት ሆኖ ሣለ፣ ተጠሪዎች በጨረታው እንዱሳተፈ ፍርድ ቤቱ ሣይፈቅድላቸው በእጅ አዙር በጨረታው ልጃቸውን አሳትፉው ቤቱን ስለመግዛታቸው የደረስበት መሆኑን በመግለፅ ተጣርቶ ጨረታው እንዱሰረዝለት ጠይቆ ሣለ፣ የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋና የተሸጠበት ዋጋ ተቀራራቢ መሆኑ በሂደቱ ላይ የተፈፀመ ያልተገባ ድርጊት መኖሩን እያሣዬ፣ በጨረታ የተሸጠው ቤት በአመልካችና በባለቤቱ የጋብቻ ክርክር በልላ መዝገብ ታግድ ባለበት፣ ተጠሪዎች የአመልካች አድራሻ አዱስ አበባ መሆኑን እያወቁ መጥሪያ ሣያደርሱ ጉዲዩ በላለበት መታየቱ እንዱጣራለት ያቀረበውን አቤቱታ በአግባቡ ሳይመረመር በድጋሚ የቀረበ ነው ተበል ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብል እንዱታረምለት ጠይቋል።
የአመልካችን የሰበር አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልት አመልካች የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረበው አቤቱታና የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም ያቀረበው አቤቱታ ተመሣሣይነት ያለው ነው ተብልና ድጋሚ እንደቀረበ ተወስድ ውድቅ መደረጉን ተገቢነቱ ላይ ግራ ቀኙ ተከራክረውበት ተመርምሮ ውሣኔ እንዱሰጥበት ታዞ የፅሁፍ ክርክሩ ተጠናቋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካች የካቲት 15 ቀን 2013ዓ/ም እና የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም ባቀረበው አቤቱታ የጠየቀው ዲኝነት ተመሳሣይ መሆኑን፣ የሥነ ስርዓት ሕጉ ዋና ዓላማም ክርክሮችን በአጭር ጊዜ መቋጨት መሆኑን፣ በጥቅለ ተመሣሣይ ጉዲይ እንዱፈፀምለት ሁለት ጊዜ አቤቱታ ማቅረቡን በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤቶች በሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱፀናላቸው ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ ክርክሩ ተጠናቋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዲዩን አመጣጥና በዚህ ችልት የቀረበውን ክርክር ሲሆን የአመልካች ቤት ለፍርድ ማስፈጸሚያነት እንዱውል ከተሸጠ በኋላ በአፈፃፀም ክርክሩና በጨረታው ሂደት ተፈጽሟል ያላቸውን ተገቢነት የላላቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶችን በመዘርዘር ጨረታው እንዱሰረዝለት አመልካች የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም ያቀረበው አቤቱታ በድጋሚ የቀረበ ነው እንዱሁም ጨረታውን ሉያሰርዝ የሚችል ምክንያትም አልተገኘም ተብል ውድቅ በመደረጉ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር በጭብጥነት ይዘን አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ተሳታፉ ባልሆነበት የአፈፃፀም ክርክር ባህር ዲር ከተማ የሚገኘው ቤቱ ለፍርድ ማስፈፀሚያነት መሸጡን ተከትል የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ/ምና የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የተፃፈ አቤቱታ አፈፃፀሙን ለመራው ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረቡን የጉዲዩ አመጣጥ ያስገነዝባል። ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው አመልካቹ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረበውን አቤቱታ የመረመረው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለት አቤቱታ ቀደም ሲል ትዕዛዝ ሰጥበት ያለፈውን ጉዲይ መሰረት በማድረግ በድጋሚ የቀረበ ነው እንዱሁም ጨረታው የሚሰረዝበት ምክንያት የለም ሲል ውድቅ በማድረጉና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም በማፅናቱ ነው።
ሆኖም አመልካች በሁለቱ ቀናት የቀረበው አቤቱታ የተለያያ ስረ ነግርን መሰረት ያደረጉ ሆነው ሣለ ድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ምክንያትና በአቤቱታው ላይ የጠቀሳቸው ጉድለቶች መኖር አለመኖራቸው ሣይጣሩ ለማስረዝ የሚችል ምክንያት የለም በሚል ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ ይከራክራል። ተጠሪዎች በበኩላቸው በሁለቱም ቀናት የቀረቡት የአመልካች ላይ የተጠየቀው ዲኝነት ተመሣሣይ ሆኖ ሣለ የሥነ ስርዓት ሕጉን ድንጋጌ ቁጥር መቀየሩ ብቻውን የተለያየ አቤቱታ እንዲቀረበ በማስመሰል ክርክር ማቅረቡ ተገቢነት የለውም ሲለ የስር ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዱፀና ተከራክረዋል።
በቀረበልን ጉዲይ ውሣኔ ለመስጠት ለአጣሪ ችልቱ የቀረቡትን የአመልካች አቤቱታዎች ይዘት መመርመሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም መሰረት አመልካች የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረበው አቤቱታ በዋናው ፍርድ ላይ እንዱከፍል የተወሰነበትን እዲና ቤቱን ለመሸጥ የወጣውን ወጪ መክፈል እንደሚፈልግና ገንዘቡን እንደሚያሲዝ በመግለፅ የጨረታው ሑደት እንዱቆምለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 439 መሰረት መጠየቁን፤ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ፅፍ ያቀረበው አቤቱታ ደግሞ በአፈፃፀም ክርክሩ ወቅት ተጠሪዎች የአመልካች አድራሻ አዱስ አበባ መሆኑን እያወቁ ባህር ዲር ከተማ እንደሚኖር በማስመሰል መጥሪያው በባህር ዲር ከተማ አስተዲደር እንዱለጠፍ አድርገው በጋዜጣ እንዱጠራ አድርገው ክርክሩ በላለበት እንዱቀጥል መደረጉን፣ ተጠሪዎች ፍርድ ቤቱን ሣያሥፈቅደ በእጅ አዙር በልጃቸው አማካኝነት በጨረታው ተሳትፈው አመልካችን በሚጎዲና አኳኋን የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን፣ በጨረታ የተሸጠው ቤትም በልላ ክርክር ታግድ የነበረ መሆኑን በመዘርዘር ጨረታው እንዱሰረዝለት መጠየቁን ያስገነዝባለ።
እንደሚታወቀው የፍትሐ ብሓር ክርክሮች መቋጫ እንዱኖራቸው በማሰብ በሕግ ከተደነገጉ ስርዓቶች መካከል ፍርድ ወይም ውሣኔ በተሰጠበት ጉዲይ ወይም ለቀረበው ነገር መጨረሻ ውጤት የሚያስከትል ትዕዛዝ በተሰጠበት ነገር ላይ በድጋሚ ክስ ወይም አቤቱታ እንዲይቀርብ መከልከል እንደሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ይደነግጋል። አንድ ክስ ወይም በተጀመረ ክርክር ላይ የቀረበው አቤቱታ በድጋሚ የቀረበ ነው ከሚያስብለ መመዘኛዎች መካከል አንደ ደግሞ አስቀድሞ ውሣኔ ወይም የመጨረሻ ውጤት የሚያስከትል ትዕዛዝ የተሰጠበት አቤቱታ ስረ-ነገርና በድጋሚ የቀረበው ነገር ጭብጥ ተመሣሣይ መሆን አለመሆኑን መሰረት የሚያደርግ ነው።
በዚህ መርህ መሰረት የቀረበውን ጉዲይ ስንመረምረው የአሁን አመልካች የካቲት 15 ቀን 2013ዓ/ም ያቀረበው አቤቱታ ዋናውን እዲውንና ቤቱን ለመሸጥ የወጣውን ወጪ ለመክፈል የሚፈልግ መሆኑን በመግለፅ የጨረታውሂደት እንዱቋረጥ እንዱታዘዝለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 439 የቀረበ አቤቱታ ሲሆን ይህን አቤቱታ መሰረት በማድረግ የሚመረመረው ጉዲይ የአመልካቹ ቤት ሳይሸጥ እዲውን ለመክፍል የሚችል መሆኑን አለመሆኑ ጉዲይ መሆኑን መገንዝብ ይቻላል። በልላ በኩል የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም አመልካች ያቀረበው አቤቱታ በአፈፃፀም ክርክሩና በቤቱ ሽያጭ ጨረታ ላይ በተጠሪዎች ተፈፅመዋል የሚላቸውን ቅን ልቦናን መሰረት ያላደረጉ እና ሕገወጥ ድርጊቶች በመዘርዘር ጨረታው እንዱሰረዝለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 430(1)(3) ድንጋጌን መሰረት ያደረጉ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ሉጣራ የሚችለውም ጉዲይ ጉድለቶች መኖር አለመኖራቸውና ነበሩ ከተባለም በጨረታው መሰረዝ ላይ የሚያስከትለት ውጤትን የሚመለከት ነው። በዚህ ሂደትም ተጠሪዎችና የጨረታው አሸኛፉ ነው የተባለው ሰው ተሣታፉ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በሁለቱ ቀናት የቀረቡት አቤቱታዎች የተለያዩ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረጉ የሚያስከትለት ውጤትም ለየቅል መሆኑን መገንዘብ ይገባል።
በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች የካቲት 23 ቀን 2013ዓ/ም ያቀረበውን አቤቱታ ተቀብል ተጠሪዎችና የጨረታው አሸኛፉ የተባለው ሰው መልስ እንዱያቀርቡ አድርጎ ጨረታው መሰረዝ አለመሰረዝ ተገቢ ነው ያለውን ውሣኔ መስጠት ሲገባው ጉዲዩን በአግባቡ ሣይመርምር አቤቱታው በድጋሚ የቀረበ ነው፤ ጨረታው የሚሰረዝበት ምክንያት የለም ሲል ውድቅ ማድረጉ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 5 ቀን 2013ዓ/ም እና የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠ ቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረበውን አቤቱታ መርምሮ በመዝገብ መጋቢት 21 ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ የተሻረ መሆኑን አውቆ በአመልካች አቤቱታ ላይ ተጠሪዎችና የጨረታው አሸናፉ ነው የተባለው ሰው መልስ እንዱሰጡ አድርጎ ጉዲዩን አጣርቶ ተገቢ ነው ያለውን እንዱወስን ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341 መሰረት መልሰንለታል።
ይህ የሰበር ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ በሚመለከት ግራ ቀኙ የዬራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ችልት ሐምል 14ቀን 2013 ዓ/ም የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.