በፍርድ አፈጻጸም ጊዜ ፍርድ ቤቶች ሉያስፈጽሙ የሚገባው በተሰጠው ፍርድ መሰረትና በህግ አግባብ ከተዘረጋው ስርአት ውጪ የአፈጻጸም ችልት የፍርደን ይዘት በሚቀይር መልኩ ወይም ፍርድ ያልተሰጠበትን ነገር የሚያስፈጸም ስላለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 378 እና ተከታይ አቶ በቀለ ድሪብሳ እና አቶ የምክር በሪሁን
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ በቀለ ድሪብሳ - ጠበቃ ዘነበ ጥላሁን ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ የምክር በሪሁን - ጠበቃ ግሩም አየለ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን የአፈጻጸም ክርክሩ በተጀመረበት የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች የፍርድ ባለእዲ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለመብት በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩን አመጣጥ ስንመለከት ተጠሪ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ አመልካችን ጨምሮ በ5 ሰዎች ላይ በቀድሞ ወረዲ 17 ቀበላ 21 የሚገኝ የቤት ቁጥር 552 እንዱያስረክቡኝ እና ስመሀብት እንዱያዛውሩልኝ ይወሰንልኝ የሚል ክስ አቅርበው መስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም. አመልካችን ጨምሮ 4 ተከሳሾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ ተወስኗል። ተጠሪም ይህንን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በአፈጻጸም መዝገብ የአፈጻጸም አቤቱታ አቅርበው ቤቱን ከተረከቡ በኋላ አመልካች እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ ተጠሪ ቤቱን እንዱረከቡ በተሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ውሳኔውን አሽረዋል። የውሳኔውን መሻር ተከትል አመልካች እና ባለቤታቸው ተጠሪ በአፈጻጸም የተረከቡትን ቤት መልሰው እንዱያስረክቧቸው አቤቱታ አቅርበው ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እና ለባለቤታቸው ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ አስረክበው አፈጻጸሙ በመጠናቀቁ የአፈጻጸም መዝገቡ ተዘግቷል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ አጠቃላይ ይዞታዬ 391 ካ.ሜ. የነበረ ሲሆን ከዚህ ላይ ለአመልካች እና ባለቤታቸው ቤቱን ከ200 ካ.ሜ. ይዞታ ጋር ሳስረክብ 191 ካ.ሜ.
ይዞታ ይቀረኛል። ስለዚህ በቀሪው 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት የይዞታ ምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ እንዱሰጠኝ ይታዘዝልኝ በማለት በተዘጋው የአፈጻጸም መዝገብ ላይ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በተጠሪ አቤቱታ መሰረት የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቶ ለተጠሪ እንዱሰጥ አዟል። አመልካች በዚህ ትእዛዝ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ቅሬታው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
አመልካች በ06/05/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት በስር ፍርድ ቤት በተሰጠው የአፈጻጸም ትእዛዝ ተፈጽሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ለማሳረም ሲሆን የቅሬታው ይዘት በ191 ካ.ሜ.
ይዞታ ላይ ለተጠሪ ካርታ እንዱሰጥ ፍርድ አልተሰጠም። የአፈጻጸም ትእዛዙ ሲሰጥም አመልካች አስተያየት እንድሰጥ አልተደረገም። ይዞታው ለ15 ዓመት ግብር የገበርኩበት ስለሆነ ለተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ይሰጥ መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ የተሰጠው የአፈጻጸም ትእዛዝ ፍርደን የተከተለ ነው አይደለም? የሚለውን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በ01/07/2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ የአፈጻጸም ትእዛዙ የተሰጠው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም. በተሰጠ ፍርድ መሰረት ነው። በዚህ ውሳኔ ቤት እንድረከብ የተወሰነ ቢሆንም አመልካች እና ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ በውሳኔው ላይ የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቤት እንድረከብ የተሰጠውን ውሳኔ ክፍል በመሻሩ ከአመልካች እና ከባለቤታቸው በአፈጻጸም የተረከብኩትን ቤት ከ200 ካ.ሜ. ቦታ ጋር መልሼ አስረክቤአለሁ። አመልካች በውሳኔው መሰረት ሳይረከቡ የቀረ ነገር የለም። በተጨማሪም የይዞታ የምስክር ወረቀት ተሰርቶ እንዱሰጠኝ የታዘዘው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፋደራል ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ እንዱሁም በፋደራል ፍርድ ቤት መዝገብ የተሰጡ ውሳኔዎች ታይተው በመሆኑ በተሰጠው የአፈጻጸም ትእዛዝ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካችም በ16/07/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን አጠናክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ትእዛዝ እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው ለቅሬታ መነሻ የሆነው የአፈጻጸም ትእዛዝ ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የሚመለከተው የአስተዲደር አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ሰርቶ ይስጥ የሚል ነው። አመልካች ይህንን ትእዛዝ የሚቃወሙት ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዱሰራላቸው የተሰጠ ውሳኔ የለም በሚል ነው። ተጠሪ በበኩላቸው በመዝገብ እና በላልች መዝገቦች ላይ በተሰጠ ውሳኔ መሰረት የአፈጻጸም ትእዛዙ የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ትእዛዙ ተገቢ መሆኑን ተከራክረዋል። በመሆኑም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻው ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ተሰርቶ እንዱሰጣቸው የተሰጠ ፍርድ አለ ወይስ የለም? የሚለው ይሆናል።
በፍርድ አፈጻጸም ጊዜ ፍርድ ቤቶች ሉያስፈጽሙ የሚገባው በተሰጠው ፍርድ መሰረት መሆን እንዲለበት የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በነዚህ ድንጋጌዎች አግባብ ከተዘረጋው ስርአት ውጪ የአፈጻጸም ችልት የፍርደን ይዘት በሚቀይር መልኩ ወይም ፍርድ ያልተሰጠበትን ነገር ማስፈጸም አይችልም። የፍርድ አፈጻጸም ስርአት አንድ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በራሱ አማካኝነት በህጉ የተዘረጋውን የአፈጻጸም ስርአት በመከተል ወደውጤት የሚቀይርበት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አፈጻጸሙ ፍርደን የተከተለ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት አለበት።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታን በተመለከተ ፍርድ ተሰጥቶበታል የሚለት አንድም በመዝገብ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም.
የተሰጠውን ፍርድ በመጥቀስ ሲሆን እኛም የዚህን ፍርድ ይዘት ተመልክተናል። የፍርደ ይዘት ተጠሪ አመልካችን ጨምሮ በአራት ሰዎች እና በአዱስ አበባ መስተዲድር የስራ ከተማ ልማት ቢሮ ላይ በቀድሞ ወረዲ 17 ቀበላ 21 በካርታ የተመዘገበውን የቤት ቁጥር 552 የሆነውን ቤት ለመረከብ እና ስመ ሀብት እንዱዛወርላቸው ክስ አቅርበው አራቱ ተከሳሾች የተጠቀሰውን ቤት ለተጠሪ እንዱያስረክቡ የተወሰነ መሆኑን ያሳያል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት የአመልካች ባለቤት ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ተጠሪ ቤት እንዱረከቡ የተሰጠው ውሳኔ መሻሩን የፍርደ ግልባጭ የሚያመለክት ሲሆን በተጠሪም የታመነ ጉዲይ ነው። ይህም ማለት ተጠሪ በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ በግልጽ ቤት ይረከቡ በሚል የተፈረደላቸው ፍርድ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሰጠው ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ በመዝገብ በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ መሰረት ለተጠሪ ሉፈጸምላቸው የሚችል ነገር የለም ማለት ነው። የስር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ትእዛዙን ሲሰጥ በምክንያትነት የጠቀሰው የተጠሪ አጠቃላይ ይዞታ 391 ካ.ሜ. ሲሆን ከዚህ ይዞታ ላይ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 349 መሰረት 200 ካ.ሜ. ቦታ ተቀንሶ አመልካች እና ባለቤታቸው ሲረከቡ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ለተጠሪ ይቀራል በሚል ነው። ነገር ግን ተጠሪ ክስ ያቀረቡበት የመዝገብ ላይ ተጠሪ ቤት እንዱረከቡ የተሰጠው ውሳኔ በተሻረበት ሁኔታ ለተጠሪ ምን ያክል ይዞታ እንደሚቀር እና በሚቀረው ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዱሰራ በአፈጻጸም ችልት ሉታዘዝ የሚችልበት የህግ አግባብ የለም። ይህ ማለት ግን ተጠሪ ከፍርድ ቤት የአፈጻጸም ትእዛዝ ውጪ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ ማረጋገጫ እንዱሰጣቸው መጠየቅ አይችለም ማለት አይደለም። ስለዚህ ተጠሪ ይዞታው ላይ በሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዱሰጣቸው ከሚጠይቁ እና ይህ አካል በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካላቸው በተገቢው የህግ አግባብ አለኝ የሚለትን መብት ክስ በማቅረብ ከሚያስከብሩ በስተቀር ተጠሪ በጠቀሱት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ የተሰጠው ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ ለተጠሪ የይዞታ የምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በማድረግ የሚፈጸም ፍርድ የለም።
ላላው ተጠሪ ከአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፋደራል ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ እንዱሁም በፋደራል ፍርድ ቤት መዝገብ የተሰጡ ውሳኔዎች ታይተው ነው የአፈጻጸም ትእዛዝ የተሰጠው በማለት የሚያነሱትን ክርክር ስንመለከት በነዚህ በውሳኔዎች ላይም ቢሆን አመልካች የቤት ቁጥር 552 ን በተመለከተ ሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅርበው ውድቅ የተደረገበት እንጂ ተጠሪ የሚገባቸው ይዞታ ምንያክል እንደሆነ ተረጋግጦ ፍርድ ያረፈበት አይደለም።
ሲጠቃለል የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ተሰርቶ እንዱሰጥ በማለት የአፈጻጸም ትእዛዝ የሰጠው ተጠሪ መብት አግኝቻለሁ የሚለበት ቤት እንዱረከቡ የተሰጠው ውሳኔ በተሻረበት እና ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ መብት ያላቸው መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠ ፍርድ በላለበት በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህጉ የተዘረጋውን የአፈጻጸም ስርአት የሚቃረን እና ከአፈጻጸም ችልት ስልጣን ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር109006 በ10/03/2012 ዓ.ም. እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ22/04/2013 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
2ኛ. ተጠሪ ቤት እንዱረከቡ የተሰጠው ውሳኔ በተሻረበት እና 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ተሰርቶ እንዱሰጣቸው የተሰጠ ፍርድ በላለበት የአፈጻጸም ትእዛዝ መሰጠቱ ተገቢ አይደለም ብለናል።
3ኛ. ይህ ውሳኔ ተጠሪ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚያግድ አይደለም።
4ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገ ክርክር ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.