ፍርድ የተፈረደለት ሰዉ ማመልከቻ በማቅረብ የፍርድ አፈጸጻም ሲጠይቅ ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት እንዱፈጸም የተጠየቀዉን ፍርድ መሰረት በማድረግ ፍርደን ለማስፈጸም በሚል የሚሰጠዉ ትእዛዝ፤ ፍርደን ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንና የተወሰነላቸዉ ሰዎች የተወሰነላቸዉን ነገር እንዱያገኙ ለማድረግ የሚችል ተስማሚ ትእዛዝ መሆኑን መረጋገጥ ያለበትና ራሱን ችል ክርክር ባልተደረገበት ጉዲይ ላይ ትዕዛዝ የሚሰጥበት አቶ ፀጋዬ አለሙ እና አቶ ያሲን ኑሩ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 378 እና 392/1
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 05 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ፀጋዬ አለሙ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ያሲን ኑሩ - ጠበቃ ሲራጅ አብደላ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የፍርድ አፈጻጸም የሚመለከት ነዉ።ተጠሪ በአመልካችና በላልች 6 የፍርድ ባለእዲ በሆኑ ሰዎች ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ የፍርድ ባለእዲዎች በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዲ 25 ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን የቤት ቁጥር 529 የሆነ ቤት ስፊቱ 521 ከሆነ ካሬ ሜትር ቦታ ጋር እንዱያስረክቡኝ ተወስኗል።በፍርድ አፈጻጸም በተሰጠ ትእዛዝ በፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በኩል 412 ካሬ ሜትር ቦታ እና ቤቱን ተረክቤያለሁ።ነገር ግን ቀሪዉን 106 ካሬ ሜትር ቦታ የአሁን አመልካች የቤት ቁጥር 529/2 ከሆነዉ ቤታቸዉ ጋር ቀላቅለዉ ስለያዙት ሳልረከብ ቀርቻለሁ። አመልካች 106 ካሬ ሜትር ቦታ ከራሳቸዉ ቦታ ቀላቅለዉ ካርታ የወሰደ ቢሆንም ካርታቸዉ መክኗል። እንዱሁም ሁከት ይወገድልኝ በማለት የመሰረቱት ክስ ዉድቅ ተደርጎ የያዙትን 106 ካሬ ሜትር ቤት እንዱለቁ ተወስኖባቸዋል። አስቀድሞ ለፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት የተሰጠዉ ትእዛዝ የቤት ቁጥር 529 ላይ ብቻ ፍርደ እንዱፈጸም የሚል ስለነበር ሉፈጸምልኝ ስላልቻለ በፍርደ መሰረት ቀሪዉን 106 ካሬ ሜትር ጭምር እንዱያስረክቡኝ ትእዛዙ ተስተካክል ይታዘዝልኝ በማለት ጠይቀዋል።
አመልካች በሰጡት መልስ ዉሳኔ የተሰጠዉ በቤት ቁጥር 529 ላይ እንጂ በቤት ቁጥር 529/2 ላይ አይደለም። ስለሆነም መፈጸም ያለበት በዉሳኔዉ መሰረት ስለሆነ አቤቱታዉ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም። ዉሳኔዉ የቤት ቁጥር 529/2ን የሚመለከት ቢሆን ኖሮ በወቅቱ ተጠሪ መረከብ ይችለ ነበር። እነዚህ ሁለት ቤቶች በአጥር እንኳን የማይገናኙ ኩታ ገጠም ያልሆኑ ቤቶች ናቸዉ። በሁከት ይወገድልኝ ክርክር ላይ 106 ካሬ ሜትር ቦታ እንዲስረክብ የተወሰነ ቢሆንም ይህ የዉሳኔ ክፍል በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ተሽሯል። ቦታቸዉን ወስጄ ከሆነ ክስ በመመስረት ሉጠይቁ ከሚችለ በስተቀር በአፈጻጸም የሚረከቡበት አግባብ የለም። ካርታ መከነ የተባለዉም ስህተት ነዉ በማለት የተጠሪ ጥያቄ ዉድቅ እንዱደረግ አስተያየታቸዉን በመስጠት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ዉሳኔዎችን እንዱሁም ከተለያዩ አስተዲደር አካላት የተጻፈ ሰነድችን መርምሮ በቀን 27/02/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ዉሳኔ የተሰጠበት ቤት የቤት ቁጥር 529 የሚል ቢሆንም ቤቱ ግን በመሬት ላይ 529 እና 529/2 ሆኖ ተገኝቷል።
በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 392/1 መሰረት ፍርድ መፈጸም ያለበት ለአፈጻጸሙ ተስማሚ በሆነ መንገድ ላሆን ይገባል። ለአመልካች አባት አቶ አለሙ አጋ በቀን 27/07/2004ዓ/ም የተሰጠዉ ቁጥሩ አከ/10/08/1/4976 የሆነዉ ካርታ ለተጠሪ በሽያጭ የተላለፈዉን ይዞታ ጭምር በማካተት የተሰጠ መሆኑ ተረጋግጦ መክኗል። አመልካች በግል ይዞታቸዉ ላይ እንዱፈጸም በማድረግ ሁከት እንደተፈጠረባቸዉ በመግለጽ በመሰረቱት ክስ መነሻ ክርክር አድርገዉ ሁከት አልተፈጠረም ተብል ተወስኖባቸዋል። ስለሆነም እንዱፈጸም በተጠየቀዉ ዉሳኔ ላይ ተጠሪ እንዱረከቡ የተወሰነዉ የቤት ቁጥር 529 የሆነ ቤት ከ521 ካሬ ሜትር ቦታ ጋር በመሆኑና 521 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የቤት ቁጥር 529/2 ጭምር ስለሚገኝ አስቀድሞ በመዝገቡ ላይ በተሰጡ ትእዛዛት መሰረት ለተጠሪ 521 ካሬ ሜትር እስኪሆን ድረስ ርክክብ እንዱፈጸም ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች ይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 09/04/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፍርድ ያላረፈበትንና ክርክር ያልተደረገበትን የቤት ቁጥር 529/2 የሆነ ቤት እና ይዞታዉን አመልካች ለተጠሪ ያስረክቡ የሚል እንድምታ ያለዉ አይደለም። ይልቁንም ፍርድ ካረፈበት በቤት ቁጥር 529 ከሚታወቀዉ 521 ካሬ ሜትር ይዞታ ዉስጥ የፍርድ ባለመብት ያልተረከቡት ቀሪ ይዞታ አመልካች ከቤት ቁጥር 529/2 ጋር ቀላቅለዉ የያዙ ስለሆነ ይህንኑ ቀሪ ይዞታ ሉያስረክቡ ይገባል የሚል ነዉ። በዚህ አግባብ የተሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 392/1 መሰረት ለፍርድ አፈጻጸም ተስማሚ ትእዛዝ እንደተሰጠ የሚቆጠር ነዉ። ስለሆነም የተሰጠዉ ትእዛዝ ለተጠሪ የተወሰነላቸዉን ይዞታ አመልካች ከቤት ቁጥር 529/2 ይዞታ ጋር ቀላቅለዉ እንደያዙ ተጣርቶ የተወሰነ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አጽንቷል።
አመልካች በቀን 14/04/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡እንዱፈጸም በተጠየቀዉ ዋናዉ ዉሳኔ ላይም ሆነ በየትኛዉም ጊዜ በተሰጠ የአፈጻጸም ትእዛዝ ላይ አመልካች የቤት ቁጥር 529/2 የሆነዉን ቤት እንዲስረክብ የተሰጠ ዉሳኔ የለም። ሁከት እንዱወገድ በመሰረትኩት ክስ መነሻ 106 ካሬ ሜትር እንዲስረክብ ተሰጥቶ የነበረዉን ዉሳኔ በይግባኝ አሽሬያለሁ።
የቤት ቁጥር 529/2 የሆነ ቤት በስሜ ተመዝግቦ ካርታ ተሰጥቶኛል። ካርታዉ መክኖ የነበረዉ ከተጠሪ ይዞታ ጋር በመቀላቀል ካርታ ስላሰራሁበት አይደለም።106 ካሬ ሜትር የተባለዉ ቦታ የእኔ ቤት ቁጥር 529/2 የሆነዉ የሚገኝበት ስለሆነና የቤት ቁጥር 529/2 እንዲስረክብ ዉሳኔ ባልተሰጠበት በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘዉን ቤት እንዲስረክብ ዉሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች እንዱለቁ የአፈጻጸም ትእዛዝ የተሰጠበት ይዞታ በፍርደ የተመለከተ መሆን አለመሆኑ ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 15/06/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
አመልካች ለተጠሪ ከተወሰነዉ 521 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተወሰነዉን ቦታ ወደራሳቸዉ ጨምረዉ ካርታ ማስወጣታቸዉ ተረጋግጦ ካርታዉ መክኗል። አመልካች ፍርድ ያረፈበትን ቁጥሩ 529 የሆነዉን ቤት አለአግባብ አስቀይረዉ 529/1 የራሳቸዉን ቤት ደግሞ 529/2 አስደርገዉ የተገኙ በመሆኑ እንዱረከብ የተባለዉ ቀሪዉ ቦታ የቤት ቁጥር 529/2 ከሆነዉ የአመልካች ይዞታ ተቀንሶ እንዱሰጠኝ በቀን 07/10/2009ዓ/ም በተሰጠዉ ተእዛዝ መሰረት የተወሰነ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።
የተወሰነልኝ አጠቃላይ ይዞታ ስፊት 521 ካሬ ሜትር ቦታ በመሆኑና ቀሪዉ 106ካሬ ሜትር ቦታ ደግሞ አመልካች ከይዞታቸዉ ጋር ቀላቅለዉ ይዘዉ እንደሚገኙ ተረጋግጦ ስፊቱ 521 ካሬ ሜትር የሆነ ቦታ ከነቤቱ እንዱያስረክቡኝ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት ስለላለ የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በቀን 30/06/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካችና የስር የፍርድ ባለእዲዎች ለተጠሪ እንዱያስረክቡ የተወሰነላቸዉ የቤት ቁጥር 529 የሆነ ቤት ከ521 ካሬ ሜትር ቦታ ጋር እንደሆነ በግራ ቀኙ የታመነና የስር ፍርድ ቤቶችም ያረጋገጡት ይሄዉ ነዉ። ፍርደን ለማስፈጸም በተደረገዉ ሂደት ተጠሪ የቤት ቁጥር 529 የሆነ ቤት ከ412 ካሬ ሜትር ቦታ ጋር ተረክበዋል። ግራ ቀኙን ያከራከረዉ ቀሪዉ 106 ካሬ ሜትር ቦታ አመልካች ሉያስረክቡ ይገባል በማለት የተወሰነበት አግባብ ነዉ።
በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ስለ ፍርድ አፈጻጸም በሚደነግገዉ ሰባተኛ መጽሐፍ ስር ካለ ድንጋጌዎች እንደምንረዲዉ የተፈረደለት ሰዉ ማመልከቻ በማቅረብ የፍርድ አፈጸጻም ሲጠይቅ ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት እንዱፈጸም የተጠየቀዉን ፍርድ መሰረት በማድረግ እና በዚህ መጽሐፍ ስር ባለ ድንጋጌዎች የተዘረጋዉን ሥርዓት ተከትል ማስፈጸም ይኖርበታል። በዚህ መሰረት ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት ፍርደን ለማስፈጸም በሚል የሚሰጠዉ ትእዛዝ ፍርደን ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንና የተወሰነላቸዉ ሰዎች የተወሰነላቸዉን ነገር እንዱያገኙ ለማድረግ የሚችል ተስማሚ ትእዛዝ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 378 እና 392/1 ስር የተደነገገዉ ያሳያል። በዚህ አግባብ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን ሥርዓት ተከትል ፍርደን ተግባራዊ ማድረግ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ዉሳኔ ማስፈጸም ስለመቻላቸዉ ዋነኛ ማረጋገጫ ከመሆኑም በተጨማሪ ነጻነቱ የተጠበቀ እና የሕዝብ አመኔታ ያለዉ ፍርድ ቤት ለመኖሩ ማሳያ ሆኖ የሚያገለግል የዲኝነት ሥራ ተግባር ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ ከላይ እንደተመለከተዉ ተጠሪ በፍርደ መሰረት የመረከብ መብት የሚኖራቸዉ የቤት ቁጥር 529 ተብል የሚታወቅ አንድ ቤት ከ521 ካሬ ሜትር ቦታ ጋር ነዉ። ከዚህ ዉጭ ከመነሻዉም የቤት ቁጥር 529/2 የተባለ ቤት የቤት ቁጥር 529 አካል ነዉ በሚል ወይም ራሱን ችል ክርክር ተደርጎበት አመልካችና የስር የፍርድ ባለእዲዎች ለተጠሪ እንዱያስረክቡ አልተወሰነም። እንዱሁም ተጠሪ ለስር ፍርድ ቤቶች ባቀረቡት ክርክር ላይ እንደገለጹት የቤት ቁጥር 529/2 ተብል የሚታወቅ ቤት የመረከብ መብት የላቸዉም። ስለሆነም የቤት ቁጥር 529/2 የሆነ ቤት የሚገኘዉ ተጠሪ እንዱረከቡ በተወሰነዉ 521 ካሬ ሜትር ቦታ ክልል ዉስጥ የሚገኝ መሆን አለመሆኑ፤ተጠሪ በአመልካችና በስር የፍርድ ባለእዲዎች ላይ ክስ ሲመሰርቱ የቤት ቁጥር 529/2 የሆነዉ ቤት በ521 ካሬ ሜትር ቦታ ክልል ዉስጥ ተሰርቶ የነበረ ነዉ ወይስ ክርክር ከተደረገና ዋናዉ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ለተጠሪ በተወሰነላቸዉ 521 ካሬ ሜትር ክልል ዉስጥ የተሰራ ነዉ የሚለዉን ከቤቶቹ ማህደር፣ ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ በማስቀረብና በባለሙያ በማረጋገጥ ሉፈጸም የሚችል የፍርድ ክፍል ካለ ሉፈጸም የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ተስማሚ ትእዛዝ መስጠት ይገባል። ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ሲታይ በደፈናዉ አመልካች 106 ካሬ ሜትር ለተጠሪ ያስረክቡ የሚል ብቻ በመሆኑ በዚህ 106 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ፍርድ ያላረፈበት የቤት ቁጥር 529/2 የሚገኝ ከሆነ አፈጻጸሙ ምን ይሆናል ለሚለዉ እልባት ያልሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ ለፍርድ አፈጻጸሙ የማያዲግም ተስማሚ ትእዛዝ ሰጥተዋል የሚያሰኝ ስላልሆነ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። ስለሆነም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/02/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 09/04/2013 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ የቤት ቁጥር 529/2 የሆነ ቤት የሚገኘዉ ተጠሪ እንዱረከቡ በተወሰነዉ 521 ካሬ ሜትር ቦታ ክልል ዉስጥ የሚገኝ መሆን አለመሆኑ፤ተጠሪ በአመልካችና በስር የፍርድ ባለእዲዎች ላይ ክስ ሲመሰርቱ የቤት ቁጥር 529/2 የሆነዉ ቤት በ521 ካሬ ሜትር ቦታ ክልል ዉስጥ ተሰርቶ የነበረ ነዉ ወይስ ክርክር ከተደረገና ዋናዉ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ለተጠሪ በተወሰነላቸዉ 521 ካሬ ሜትር ክልል ዉስጥ የተሰራ ነዉ የሚለዉን ከቤቶቹ ማህደር፣ ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ በማስቀረብና በባለሙያ በማረጋገጥ የ521 ካሬ ሜትር አካል የሆነ 106 ካሬ ሜትር ቦታ ባድ ቦታ ከሆነ በፍርደ መሰረት እንዱያስፈጽም፤ በዚህ 106 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የቤት ቁጥር 529/2 የሚገኝ ከሆነ ሉፈጸም የሚችል የፍርድ ክፍል መኖር አለመኖሩን አረጋግጦ ለጉዲዩ ተገቢዉን እልባት እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት ወስነናል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.