በአንድ የንግድ ማህበር ውስጥ አብሮ የመስራት ፍላጎት ባልጠፊበት፣ የማህበሩ አባላት ተስማምተው ለመስራት ፍላጎት እያላቸው፣ ማህበር አባላትን ለማሰናበት የሚያስችል በቂና አሳማኝ ምክንያት በላለበት ህግ ካስቀመጣቸው አማራጮች መካከል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውንና ለተፈጠረ አነስተኛ ጥፊት፣ የማህበሩን ህልውና ለማስቀጠል እንደማይችል ተደርጎ ከማህበሩ እንዱሰናበቱ መወሰኑ የንግድ ህጉንም ሆነ የማህበሩን ደንብ መሰረት ያላደረገና ተቀባይነት የላለው እነ አቶ ሰለሞን እሸቱ (3 ሰዎች) እና ሰዓዲ ጌቱ እና ጓደኞቻቸው ሻወርና መፀዲጃ ህ/ሽ/ማህበር
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ ሰለሞን እሸቱ 2ኛ. አቶ ብርሃኑ ወርቅነህ ቀረቡ 3ኛ. ወ/ሮ አብዮት ደሳለኝ ተጠሪ፡- ሰዓዲ ጌቱ እና ጓደኞቻቸው ሻወርና መፀዲጃ ህ/ሽ/ማህበር - ስራ አስኪያጅ ፍሬህይወት ጉርሜሳ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 09/03/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 01/10/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/02/2014 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው በስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ የተጠሪ ማህበር መስራች አባል መሆናቸውን ገልፀው ነገር ግን ማህበሩ 1ኛ አመልካችን የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ፣ 2ኛ አመልካችን መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም እንዱሁም 3ኛ አመልካችን የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ከማህበር አባልነት አሰናብቷል:: በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ እንዱሁም ውስጠ ደንብ መሰረት ማህበሩ ፈጽማችኋል ያላቸውን ተግባሮች ያልፈፀምን ሲሆን ተፈጽመዋል ቢባል እንኳን ከአባልነት እንደሚያሰናበቱ አልተደነገገም። በመሆኑም ስንብቱ ህገወጥ በመሆኑ ተከሳሽ ማህበር ወደ አባልነታችን እንዱመልሰን እንዱወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ በሰጠው መልስ በአመልካቾች ላይ የተወሰደው እርምጃ የማህበሩን መመስረቻ እና መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ያደረገ ነው። 1ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በ29/08/2011 ዓ.ም በላልች የማህበሩ አባላት ላይ የስድብ፣ ዛቻና ማስፈራራት እንዱሁም የማህበሩን ስራ ትተው የመሄድ ተግባር ፈጽመዋል፤
ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁከትና ዛቻ በመፍጠራቸው ለፕሉስ ቀርቦ ጉዲዩ በይቅርታ ተፈቷል። 3ኛ አመልካች በማህበሩ ውስጥ ዝቅተኛ የስራ ተነሳሽነት ያላቸው እንዱሁም ያለ በቂ ምክንያት ለረጅም ግዜ ከስራ ጠፍተው በመምጣት ጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። 2ኛ አመልካችም በአባላት ስብሰባ የማይገኙ እና የተለያዩ ጥፊቶችን የሚፈጽሙ በመሆናቸው የገንዘብ ቅጣት ተጥልባቸዋል። ከዚህ ባለፈ 2ኛ አመልካች ለ 2 ወራት ሙለ የሰአት መቆጣጠሪያ ላይ ሳይፈርሙና የማህበሩን ገንዘብ ገቢ ሳያደርጉ እየሰሩ የሚገኙ በመሆናቸው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እና የ 2 ወር ደሞዝ ቅጣት ተላልፍባቸዋል። በዚህም ስራቸው ሉታረሙ ባለመቻላቸው 1ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የማህበሩን ገንዘብ ብር 6050.00 ገቢ ሳያደርጉ በመቅረታቸው እና ሲጠየቁም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንዱሁም 2ኛ አመልካች ከማህበሩ አባላት ብር 450 ነጥቀው በመውሰዲቸው ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ አሰናብቷቸዋል። የማባረር እርምጃ መወሰደ የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍና መተዲደሪያ ደንብ ተከትል የተደረገ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የተጠሪ ማህበር ውስጠ ደንብ አንቀጽ 24 ማንኛውም አባል የማህበሩን ንብረት በአግባቡ መያዝ እንዲለበት የሚደነግግ ሲሆን በአንቀጽ 20 መሰረት ተከሳሽ ማህበር አባላቱን የማባረር ስልጣን አለው። የተከሳሽ ምስክሮች በተመሳሳይ ቃል ከሳሾች የማህበሩን ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ አለማድረጋቸውን አስረድተዋል። ከሳሾች በምስክርነት ቃላቸው ገንዘቡን ገቢ ያላደረጉት በወቅቱ የማህበሩ ገንዘብ ያዥ ባለመኖሩ መሆኑን ቢያስረደም የማህበሩን ገንዘብ በማግስቱም ሆነ በቀጣዮቹ ጊዜ ገቢ ማድረግ የነበረባቸው እና የመብት ጥያቄ ካላቸውም ማህበሩን ከሚጠይቁ በቀር ገንዘቡን ለራሳቸው ለማድረግም ሆነ ለመብት ማስከበሪያ መጠቀም አይችለም። በምስክርነታቸው ከሳሾች ገንዘቡን ለግላቸው አለማዋላቸው ቢገለጽም ገንዘብ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑ በእጃቸው ካደረጉ በህግ ንብረታቸው እንደሆነ የሚቆጠር ሲሆን ለማህበሩ ገቢ አለማድረጋቸው ለግላቸው በማዋል ሀሳብ ስለመሆኑ ፍ/ቤቱ ተገንዝቧል። ከዚህ ባለፈ ተከሳሽ በመልሱ የጠቀሳቸውን ተግባራት ሲፈጽሙ እንደነበር የተከሳሽ ምስክሮች በአግባቡ ሲያስረደ ከሳሾች ግን ይህን አላስተባበለም። በመሆኑም ከሳሾች በውስጠ ደንቡ እንዱሁም በንግድ ህግ አንቀጽ 292 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የማህበሩን ጥቅም ለራሳቸው በማድረጋቸው፣ በማህበሩ ጥቅም ላይ ጉዲት በማድረሳቸው እንዱሁም አባላት ስራቸውን በአግባቡ እንዲይሰሩ ሁከት መፍጠራቸው በመረጋገጡ በውስጠ ደንቡ አንቀጽ 20 መሰረት ማህበሩ ለማባረር ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ ከሳሾች ጥር 22 እና መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረጉ ጠቅላላ ጉባኤዎች መሰናበታቸው በአግባቡ በመሆኑ ማህበሩ ያስተላለፈው የስንብት ውሳኔ እንዱነሳ በሚል የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካቾች ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ አመልካቾች በተጠሪ ማህበር ውስጥ የማህበሩ መስራችና አባል ስንሆን ተጠሪም ምንም የህግ ምክንያት ሳይኖረው ከማህበሩ አባልነታችን በማሰናበቱ በስር ፍ/ቤት ወደ አባልነታችን እንዱመልሰን ክስ አቅርበን በሰጠነው ምስክርነት አመልካቾች የሰበሰብነውን ገንዘብ ወደ አካውንቱ ልናስገባ ስንሄድ በባንኩ ማስገባት አትችለም በመባላችን ምክንያት ያላስገባን ስለመሆኑና ገንዘቡም በ1ኛ ከሳሽ ሂሳብ ውስጥ የሚገኝና ለግል ጥቅማችን ያላዋልነው ስለመሆኑ እንዱሁም ተከሳሽ የጠቀሰውን ተግባር ያልፈጸምን ስለመሆኑ በማስረጃ አስረድተን እያለና የማህበሩ ውስጠ ደንብ አንቀጽ 20 በግልጽ ያስቀመጠው ጉዲይ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ የተያዘን የሚመለከት በመሆኑ ተከሳሽ በዚህ ረገድ ክርክር ባላቀረበበትና በቀረቡት ምስክሮችም ይኸው ስለመሆኑ ሳይረጋገጥብን ከውስጠ ደንቡ ውጭ ገንዘቡ በእጃችን ያለና ለግል ጥቅማችን ያላዋልን ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት በፍርደ ሀተታ ላይም ተመልክቶ እያለ ገንዘቡ በእጃቸው መሆኑ ንብረታቸው እንደሆነ የሚቆጠር ስለሆነና ለማህበሩ ገቢ አለማድረጋቸው ለግላቸው ለማዋል ሀሳብ እንዲላቸው የሚያሳይ ነው በማለት ፍርድ ቤቱ የተሳሳተ ግምት በመውሰድ በውስጠ ደንቡ አንቀጽ 20 ን ተላልፈዋል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዘናና የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል። አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ባቀረብነው ምስክር በፈረቃ እንደማንገናኝ በመልሳቸው ላይ ጠቅሰው ያቀረቡትን ተግባር ያልፈጸምን ስለመሆኑ አስረድተን እያለ በተጠሪ የተመሰከረባቸውን አላስተባበለም በማለት የደረሰበት መደምደሚያም የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ተጠሪ ያለውን ተግባር ያልፈጸምን ስለመሆኑ በአግባቡ ያስረዲን ከመሆኑም በላይ የማህበሩ ውስጠ ደንብ አንቀጽ 20 በዚህ ምክንያት ሉያሰናብት እንደሚችል ባልተደነገገበት ሁኔታና የተጠሪ ምስክሮች ይህን ባላስረደበት ሁኔታ ከአባልነታችን ማሰናበቱ ተገቢ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የህግም ሆነ የማስረጃ ድጋፍ የላለው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምልን በማለት ቅሬታቸው አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ መተዲደሪያ ደንቡ የማህበሩ ገንዘብ ስርቆት መፈጸም እንደሚያሰናብት የሚገልጽ ሲሆን የአሁን አመልካቾች የማህበሩ ገንዘብ ያዥ እንዱቀበላቸው ጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ በእጃቸው መቆየቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት ለግላቸው ለማዋል ሀሳብ እንዲላቸው ተገንዝቤያለሁ በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 10/06/2014 ዓ.ም ባቀረበው መልስ አመልካቾች የተጠሪ ማህበርን ህልውና የሚጎዲ ተግባር በየግዜው ከመፈጸማቸው በተጨማሪ 1ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ከጥር 01 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሰበሰቡትን ብር 6050.00 ለተጠሪ ገንዘብ ያዥ ገቢ እንዱያደርጉ እየጠየቅናቸው በእንቢተኛነት ወደ ራሳቸው አካውንት ገቢ ለማድረግ ጠይቀው ባንኩ ስላልተቀበላቸው 1ኛ አመልካች አካውንት ውስጥ ማስገባታቸው ለግል ጥቅማቸው ያዋለ መሆኑን ስለሚያረጋግጥ፤ 2ኛ አመልካች ደግሞ የማህበሩን ብር 450.00 ከማህበሩ አባላት ነጥቆ መውሰደ በተጠሪ የውስጥ ደንብ አንቀጽ 20 መሰረት ከስራ ስለሚያሰናብት ተጠሪ የወሰደው የስንብት እርምጃ በአግባቡ ነው፤ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔም መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም ተብል የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግ በማለት አቅርበዋል። አመልካቾችም በመልስ መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካቾች ክስ ለማቅረባቸው ቀዲሚ ምክንያት የሆነው የተጠሪ ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፈው የስንብት ውሳኔ ሲሆን ለውሳኔውም ምክንያት የሆነው 1ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የማህበሩን ገንዘብ ብር 6050.00 ገቢ ሳያደርጉ መቅረታቸው እንዱሁም 2ኛ አመልካች ከማህበሩ አባላት ብር 450.00 ወስደዋል መባለ ነው። ከዚያ በፉት በአመልካቾች ተፈጽመዋል ለተባለ የተለያዩ ግድፈቶች የተሰጡ አስተዲደራዊ ውሳኔዎችም ተያይዘው በመከራከሪያነት ቀርበዋል።
የማህበሩ ውስጠ ደንብ አንቀጽ 24 ማንኛውም አባል የማህበሩን ንብረት በአግባቡ መያዝ እንዲለበት የሚደነግግ መሆኑ ግራቀኙን አላከራከረም። ማህበሩም በደንቡ አንቀጽ 20 መሰረት አባላትን የማባረር ስልጣን ቢኖረውም ይኸው ስልጣን በበቂ ምክንያትና ማስረጃ ላይ ተደግፍ ሉተገበር የሚገባ ነው።
ለስንብት ምክንያት የሆነውን የማህበሩን ገንዘብ አመልካቾች ገቢ ያላደረጉት በወቅቱ የማህበሩ ገንዘብ ያዥ ባለመኖሩ መሆኑን፤ በባንክም ሄደው በአካውንት ለማስገባት ሞክረው በባንኩ ማስገባት አትችለም በመባላቸው ምክንያት ገቢ ስላለመሆኑና ገንዘቡም ተጠቃል በ1ኛ አመልካች የሚገኝና ለግል ጥቅማቸው ያላዋለት ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር በማስረጃዎቻቸው የተደገፈ ስለሆኑ የስር ፍርድ ቤት ካሳለፈው ውሳኔ መገንዘብ ይቻላል። የስር ፍርድ ቤት ይህን ፍሬ ነገርና ማስረጃ ተቀብል ነገር ግን ገንዘብ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑ በእጃቸው ካደረጉ በህግ ንብረታቸው እንደሆነ የሚቆጠር ነው ለግላቸው ለማዋል ሀሳብ እንዲላቸውም ግንዛቤ ይወሰዲል በማለት የደረሰበት የግምት መደምደሚያ የግራቀኙን ክርክርና ህጉን መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላም በኩል ተጠሪ በተለያየ ጊዜ በአመልካቾች ተፈፀሙ ለሚላቸው ቀላል ጥፊቶች በይቅርታ መታለፊቸውን እንዱሁም በማህበሩ መመስረቻ እና መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ማስጠንቀቂያና የገንዘብ ቅጣት ተጥልባቸው መታለፊቸውን ከተጠሪም ክርክር መገንዘብ ይቻላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ አሁን ላደረገው ስንብት ህጋዊነት በድጋሚ በመከራከሪያነት ማቅረቡ እንዱሁም የስር ፍርድ ቤትም አስቀድሞ ማስጠንቀቂያና መሰል ቅጣት ተሰጥቶባቸው የታለፈ ጉዲዮችን ለስንብቱ እንደምክንያት ተቀብል መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ አመልካቾችን ከተጠሪ ሕብረት ሽርክና ማህበር ለማሰናበት የሚያስችል በቂና አሳማኝ ምክንያት የለም። አመልካቾች ከማህበሩ አባላት ጋር ተስማምተው ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ከክርክሩ ሂደት መረዲት የሚቻል ሲሆን በአንድ የንግድ ማህበር ውስጥ አብሮ የመስራት ፍላጎት ባልጠፊበት ህጉ ካስቀመጣቸው አማራጮች መካከል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን ከማህበር ማሰናበት መወሰን ተቀባይነት የለውም። የሕብረት ሽርክና ማህበር የሚመሰረተው በአባላት መካከል ባለው መተማመን እና አብሮ የመስራት ፍላጎት ላይ ሲሆን ይህ ማለት ግን በሁለም የማህበሩ አባላት መካከል ያለመስማማት አይፈጠርም ወይም አነስተኛ ጥፊቶች ሁለ ለስንብት ያበቃለ ማለት አይደለም።
ስለሆነም የአመልካቾች ተግባር የማህበሩን ህልውና ለማስቀጠል እንደማይችል ተደርጎ ከማህበሩ እንዱሰናበቱ መወሰኑ የንግድ ህጉንም ሆነ የማህበሩን ደንብ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል። ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 01/10/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/02/2014 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ማህበር አመልካቾችን ወደ አባልነታቸው እንዱመልስ ወስነናል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።