ጋብቻ በህጋዊ መንገድ ሳይቋረጥ ላላ ትዲር ከተመሰረተ በኋላ በተፈራ ቤት ላይ የበፉት/የመጀመሪያው ተጋቢ በቤት ማፍራቱ ላይ አስተዋፅኦ የላለው ስለመሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም ቤቱ በተፈራበት ወቅት የቀደመው ጋብቻ ያልተቋረጠ የነበረ በመሆኑ በቤቱ መፈራአት ላይ አስተዋጽኦ የላለው ተጋቢ የቤቱ ቀሪ ግማሽ ድርሻ(50%) ከሆነው ከቀድሞ ተጋቢ ድርሻ ውስጥ ግማሹን (25%) ድርሻ የማያሳጣውና የሁለተኛው ጋብቻ ባል/ሚስት ቤቱ የተፈራው በጋብቻ ውስጥ ባለበት ወቅት በመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 62(2) መሰረት የቤቱ ግማሽ (50%) ድርሻ ባለመብት ሃዱያ ያሲን ሸዩቦ እና ሁሴን ሰኒ ኢብራሂም
No summary available.
የሰ.መ.
ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ሃዱያ ያሲን ሸዩቦ - ጠበቃ በቃለ ለማ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሁሴን ሰኒ ኢብራሂም - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ የቀረበው አመልካች የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኮ/ቀ/ምድብ 2ኛ ቤተሰብ ችልት በመ. በ24/7/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ. በ14/11/12ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ9/2/13ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 በተጠሪ ስም የተገዛ በሻጭ አቶ ደረጀ ደበበ ስም የተመዘገበ ቤት እንዱሁም የቤት ቁሳቁሶችን በመዘርዘር እንድንከፊፈል እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ማስረጃዎችንም አቅርበዋል። ተጠሪ ባቀረቡት መልስ አመልካች የጋራ ሀብት ነው በማለት የጠቀሱት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነው ቤት አመልካች ትዲራቸውን ጥለው በሄደበት ከ1996ዓ.ም እስከ 2008ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ ከሁለተኛ ባለቤቴ ጋር ያፈራሁት ነው።
አመልካች የጋራ ነው ባለበት ቤት ላይ ያደረጉት አስተዋጽኦ የላለ ስለሆነ ድርሻ ሉኖራቸው አይገባም በማለት እንዱሁም የቤት ቁሳቁሶችንም በተመለከተ መልስ ከሰጡ በኋላ በአመልካች አቤቱታ ውስጥ ያልተካተቱ በማለት የቤት ቁሳቁሶችን በመዘርዘር እንድንካፈል እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኘነት ጠይቀዋል። የምስክሮችንም ዝርዝር አቅርበዋል።
አመልካች ተጠሪ ዘርዝረው ያቀረቡትን የቤት ቁሳቁሶች በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በፍሬ ጉዲዩ ላይ መልስ አቅርበዋል። መቃወሚያው በብይን ታልፎል።
በስር ጣልቃገብ (አሁን ሰበር ክርክሩ ላይ የላለት ወ/ሮ ነፉሳ ስሩር) ባቀረቡት የጣልቃገብነት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር በ2001ዓ.ም ጋብቻ ከመሰረትን በኋላ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነ ቤት ተጠሪ በ29/1/03ዓ.ም ገዝተዋል። ቤቱ የተፈራው ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሳስረን ባለንበት ግዜ ስለሆነ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያፈሩት ንብረት አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ለጉዲዩ አግባብ ናቸው ያላቸውን ጭብጦች በመያዝ አከራካሪውን በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን ቤት በተመለከተ በክስ መሰማት ወቅት አመልካች ይህ ቤት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 ወይራ በሚባል ቦታ የነበረን የጋራ ቤት በመሸጥ ከተገኘው ገንዘብ ላይ ተጠሪ ብር 200‚000.00 ሰጥተው እንዱሁም አመልካች ከውጭ ሀገር ብር 130‚000.00 በመላክ ከወንድማቸው ብር 30‚000.00 ተበድረው በመጨመር የተገዛ ስለሆነ የጋራ ነው፤ ገንዘቡን የላኩት በእህቴ በኩል ነው ሲለ መከራከራቸውን እንዱሁም ተጠሪ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 ወይራ በሚባል ቦታ የነበረንን ቤት የሸጡት የአመልካች እህት ናቸው፤ ከሽያጩ ገንዘብ ላይ የደረሰኝ የለም። አመልካች ከ1996ዓ.ም እስከ 2008ዓ.ም ድረስ ባህር ማድ የነበሩ በመሆናቸው በቤቱ ላይ ምንም አስተዋጽኦ አላደረጉም፤ ስለሆነም ድርሻ የላቸውም በማለት መከራከራቸውን በመግለጽ እንዱሁም አመልካች ከ1996ዓ.ም እስከ 2008ዓ.ም ድረስ ባህር ማድ የነበሩ ስለመሆናቸው ክርክር ያልተነሳበት መሆኑን ከገለጸ እና አከራካሪውን ቤት በተመለከተ የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ እንዱሁም የግራቀኙ የጋራ ሀብት እንደነበረ የተገለጸው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 ውስጥ በአመልካች ስም ተመዝግቦ ይገኝ የነበረው ቤት ማህደር ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዱረዲ እንዱቀርብ በተደጋጋሚ ትእዛዝ ሰጥቶ ትእዛዙ ለተገቢው አካል ባለመድረሱ ማህደሩ ላቀርብ ባለመቻለ በማለት ትእዛዙን ካለፈ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች አከራካሪው በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 በሆነው ቤት ላይ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን በሰውም ሆነ በሰነድ ማስረጃ አላረጋገጡም በማለት ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ እንዱሁም የቤት ቁሳቁሶችን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች ከላይ በተገለጸው አከራካሪውን በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን ቤት በተመለከተ በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው እንዱሁም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 327(3) መሰረት ተጨማሪ ማስረጃ ለማቅረብ እንዱፈቀድላቸው ጠይቀው ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ስህተት የላለው መሆኑን እንዱሁም የተጨማሪ ማስረጃ ላቅርብ ጥያቄን በተመለከተ አመልካች የጠየቁትን ማስረጃ በስር ፍ/ቤት አቅርበው ተቀባይነት ስላለማግኘቱ አልተረጋገጠም በማለት፤ ማስረጃውም ለተያዘው ጉዲይ ተገቢ ሆኖ አለመገኘቱን በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከላይ የተገለጹትን ውሳኔዎች በመቃወም ሲሆን ይዘቱም አከራካሪውን በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን ቤት በተመለከተ በአመልካች በኩል የቀረቡት ምስክሮች ቤቱ የተገዛው ቀደም ሲል አመልካች እና ተጠሪ በትዲር እያለን ያፈራነው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 ልዩ ስሙ ወይራ ሰፈር በተባለው የነበረንን ቤት በብር 280‚000.00 ሸጠን ብር 80‚000.00 ተጠሪ አጥፍቶ ቀሪው ብር 200‚000.00፤ አመልካች ከውጭ ሀገር ብር 130‚000.00 ልኬ ብር 37‚000.00 ከአመልካች ወንድም ተወስድ በብር 367‚000.00 የተገዛ መሆኑን በተመሳሳይ ሁኔታ አስረድተዋል። ተጠሪ የአመልካችን ማስረጃ አላስተባበለም። አመልካች በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 የቤ.ቁ አዱስ የሆነውን ቤት የሸጥን መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ከኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 አስተዲደር እንዱቀርብልኝ ትእዛዝ ተሰጥቶ የወረዲው አስተዲደርም ፊይለን አላገኘሁም ግዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዱረዲ የስር ፍ/ቤቱ ለኮ/ቀ/ክ/ከተማ ይዞታና አስተዲደር የሽግግር ግዜ አገልግልት ፔሮጀክት ዳስክ ትእዛዝ እንዱሰጥልኝ አቤቱታ አቅርቤ አቤቱታውን ባለመቀበል አልፍታል።
የአመልካች ምስክሮች በበቂ ሁኔታ ያስረደ መሆኑን የስር ፍ/ቤቱ በውሳኔው ላይ አትቶ እና ከባንክ የቀረበለትን ማስረጃ ባለመመልከት አመልካች በቤቱ ላይ አስተዋጽኦ አላደረገችም በማለት የሰጠው ውሳኔ እና ይህንንም የይግባኝ ሰሚው የፋ/ከ/ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ማጽናቱ የቤተሰብ ህግ አ/ቁ 213/92 አንቀጽ 62(2) ድንጋጌ ውጪ ስለሆነ ሉታረም ይገባል። ተጠሪ የአመልካችን ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆኑ አመልካች የጋራ የሆነው ንብረት ላይ አስተዋጽኦ አላደረገችም በማለት በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ አመልካች አከራካሪውን በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን ቤት በጋራ አፍርታለች፤ ጋብቻው ጸንቶ ባለበት ግዜ የተፈራ ነው ተብል እንዱወሰንልኝ፤ ወጪና ኪሳራም እንዱከፈለኝ እንዱወሰንልኝ የሚል ነው።
ይህ አቤቱታቸው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት ተከራካሪ ወገኖች በትዲር ውስጥ ባለበት ግዜ የነበራቸው የጋራ ቤት ተሽጦ የተገዛ ስለመሆኑ በተገለጸበት አመልካች በቤቱ ላይ አስተዋጽኦ ያላቸው ስለመሆኑ በማስረጃ አልተረጋገጠም በሚል የተወሰነበትን አግባብነት ለማጣራት ለሰበር ችልቱ ይቅረብ ተብል በ4/8/13ዓ.ም በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ በ2/9/13ዓ.ም በተጻፈ ባቀረቡት መልስ አመልካች አቤቱታ ያቀረበችበት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን የመኖሪያ ቤት አመልካች ትዲሯን ጥላ በሄደችበት ከ1996ዓ.ም እስከ 2008ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ ከሁለተኛ ባለቤቴ(በስር ፍ/ቤት ጣልቃገብ የነበሩት ወ/ሮ ነፉሳ ስሩር) ጋር በጋራ ጥረታችን ያፈራነው ንብረት እንጂ አመልካች ምንም አይነት አስተዋጽኦ ያላደረገችበት እና ትዲሩን ጥላው በሄደችበት ግዜ ያፈራነው ንብረት ነው። አንድ ተጋቢ ጥል በሄደበት እና ምንም አስተዋጽኦ ያላደረገበትን ንብረት በተመለከተ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. (ቅጽ 11) ላይ ከሰጠው አስገዲጅ ትርጉም አንጻር አመልካች በቤቱ ላይ ያደረገችው አስተዋጽኦ የላለ እና በሰነድም ሆነ በሰው ማስረጃ ያላስረዲች በመሆኑ ከዚህ አንጻር በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ አቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል።
አመልካች በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 6 የቤ.ቁ አዱስ የሆነውን ቤት በተመለከተ በስር ፍ/ቤት እንዲያቀርቡ የተከለከለት ማስረጃ የለም። ይልቁንም አመልካች ማስረጃውን ከሚመለከተው አካል እንዱያቀርቡ በችልት በተደጋጋሚ ግዜ ታዘው ትእዛዙን ወደ ጎን በመተው ትእዛዝ ላልተጻፈለት አካል በማድረሳቸው ችልቱ ትእዛዙን ማለፈ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ማስረጃው ለተያዘው ጉዲይ ተገቢነት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም። ስለሆነም የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግ፤ ወጪና ኪሳራም እንዱከፈለኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
አመልካች በ19/9/13ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ይህ የሰበር ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ፤ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢዎቹ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር የስር ፍ/ቤቶች አከራካሪውን በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነውን ቤት በተመለከተ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምሯል።
አከራካሪው በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነው ቤት የተገዛው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያልተቋረጠ ጋብቻ በነበረበት ወቅት እንዱሁም ተጠሪ እና በስር ክርክር ጣልቃገብ የነበሩት ወ/ሮ ነፉሳ ስሩር በጋብቻ ውስጥ ባለበት ወቅት ስለመሆኑ የክርክሩ ይዘት የሚያስገንዝብ ነው። በዚህ አከራካሪው ቤት ላይ አመልካች አስተዋጽኦ የላላቸው ስለመሆኑ ማስረጃዎችን የመስማት፤ የመመርመር እና የመመዘን በህግ ስልጣን የተሰጠው የስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍሬነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ ነው።
እዚህ ላይ ላታይ የሚገባው ነጥብ አመልካች ከላይ በተገለጸው ቤት መፈራት ላይ አስተዋጽኦ የለሽም መባላቸው ቤቱን በተመለከተ በአመልካች ላይ የሚያመጣው ውጤት ምንድን ነው? የሚለው ነው።
በስር ክርክር ጣልቃገብ ሆና የተከራከረችው የተጠሪ ባለቤት ወ/ሮ ነፉሳ ስሩር የተጠሪ ሚስት በመሆኗ እና አከራካሪው ቤት የተገዛው ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ውስጥ ባለበት ወቅት በመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አ/ቁ 213/92 አንቀጽ 62(2) ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁለ የጋራ ሀብታቸው እንደሚሆን ከደነገገው አንጻር የቤቱ ግማሽ (50%) ድርሻ ባለመብት የምትሆን ሲሆን አመልካች ደግሞ ቤቱ በተፈራበት ወቅት ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ ያልተቋረጠ የነበረ በመሆኑ በቤቱ መፈራት ላይ አስተዋጽኦ የላትም መባለ የቤቱ ቀሪ ግማሽ ድርሻ(50%) ከሆነው የተጠሪ ድርሻ ውስጥ ግማሹን (25%) ድርሻዋን የሚያሳጣት አይሆንም።
ስለሆነም ከላይ በተገለጸው ምክንያት የስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች ከተጠሪ የቤቱ ግማሽ ድርሻ(50%) ላይ ግማሽ ድርሻ(25%) አላት በማለት ውሳኔ መስጠት ሲገባው አመልካች በቤቱ ላይ ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የስር የፋ/ከ/ፍ/ቤት ከላይ በተገለጸው መልኩ ሉያርም ሲገባው ውሳኔውን በማጽናት የሰጠውን ውሳኔ ይህ የሰበር ሰሚ ችልት ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኮ/ቀ/ምድብ ችልት 2ኛ ቤተሰብ ችልት በመ. በ24/7/11ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኮ/ቀ/ምድብ ችልት 2ኛ ቤተሰብ ችልት በመ. በ24/7/11ዓ.ም አመልካች በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 በሆነው ቤት ላይ ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም ይህንኑ ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ. በ14/11/12ዓ.ም በማጽናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 4 የቤ.ቁ 327 የሆነው ቤት ግማሽ (50%) የተጠሪ ድርሻ ላይ ግማሹ (25%) የአመልካች በመሆኑ ከተቻለ የቤቱ 25% ለአመልካች በአይነት ሉሰጣቸው፤ ካልተቻለ የቤቱ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ በባለሙያ ተገምቶ የግምቱን 25 % ለአመልካች ሉሰጣቸው እና ተጠሪ ቤቱን እንዱያስቀሩ፤ይህ ካልተቻለ ቤቱን አመልካች እና ተጠሪ በስምምነት ሸጠው ከሽያጩ ገንዘብ ውስጥ 25% ለአመልካች ላሰጥ፤ ይህም ካልተቻለ ቤቱ በሀራጅ ተሽጦ ከሽያጩ ገንዘብ ውስጥ 25% ለአመልካች ሉከፈላቸው ይገባል በማለት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተወስኗል።
ከላይ በውሳኔው ክፍል ተራ ቁጥር 1፤2 እና 3 ላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውጪ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኮ/ቀ/ምድብ 2ኛ ቤተሰብ ችልት በመ. በ24/7/11ዓ.ም በላልች ንብረቶች ላይ የሰጠው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
በዚህ የሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.