ሁከት እንዱወገድ በሚል በቀረበ ክስ ሁከት ተፈጠረበት የተባለው ቤት ባለቤትነት አከራካሪ፣ ከሳሽም ቤቱ በውርስ የተገኘና ባለቤት እንደሆነ የገለጽ ከሆነ፤ ተከሳሽ የሚያነሳው ባለቤትነትን የተመለከተ ክርክር አግባብነት ያለውና ቤቱ የከሳሽ የግል ሀብት አለመሆኑ ተጣርቶ የሚሰጥ ውሳኔ ከሳሽ ለጠየቁት ዲኝነት ምላሽ የሰጠ እና በአግባቡ የተሰጠ ፍርድ ነው ከሚባል በቀር፤ፍርድ ቤት ከቀረበለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ጭብጥ ወጥቶ የቤት ባለቤትነት ጉዲይ ላይ ፍርድ ሰጥቷል የሚያስብል እነ አቶ ብርሃኑ ሻይ (4 ሰዎች) እና የአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ አስተዲደር የሽግግር ጊዜ አገልግልት ፔሮጀክት ጽ/ቤት (2 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 01/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የከተማ ቤት ሁከት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡በቀድሞ አጠራር ወረዲ 05 ቀበላ 15 በአሁኑ በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዲ 02 የሚገኝ ቁጥሩ 1141 የሆነ ቤት ከወላጆቻቸው በውርስ የተላለፈላቸው እና በቀን 24/05/2008 ዓ.ም በስማቸው ካርታ የተሰጣቸው መሆኑን፤ በዚሁ ቤት ግቢ ውስጥ አውራሾቻቸው በሕይወት እያለ የዋናው ቤት አካል ሆኖ የሚጠቀሙበትን ማድቤት እና መጸዲጃ ቤት ያለ መሆኑን፤ ወላጆቻቸው በሕይወት እያለ ማድቤቱን በችግር ላይ ለነበረች ሴት ለጊዜው ሰጥተዋት የነበሩ መሆኑን፤ ሆኖም አዋጁ ሲታወጅ የሴትየዋ ልጅ በወቅቱ ቀበላ ይሰራ ስለነበር ስልጣኑን ተጠቅሞ ቤቱን እንደተከራየ አድርጎ ቁጥር 1140 የሚል ቁጥር ያሰጠው መሆኑን፤ ግለሰቧም ቤቱን ለቃ ለአውራሻቸው ሳታስረክብ የሄደች መሆኑን፤
አመልካቾች በይዞታቸው ስር አድርገው ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑን፤ ሆኖም 1ኛው ተጠሪ በሰጣቸው ካርታ ላይ ይህንኑ ማድቤት እና መጸዲጃ ቤት የመንግስት ብል በመስራት፤ 2ኛ ተጠሪም ቤቱ የራሴ ነው በማለት ሁከት እየፈጠሩባቸው የሚገኙ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪዎች የፈጠሩት ሁከት እንዱወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁን ተጠሪዎች በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጡት መልስ የአመልካቾች አውራሾች ክስ የቀረበበትን ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 አስረክበዋል፤ 2ኛ ተጠሪ ቀደም ሲል ቤቱን ለአቶ ወርጃ አበዙ አከራይቶ ኪራይ ሲሰበስብበት የቆየ ነው፤ ተከራይ ቤቱን በምን አግባብ እንደለቀቀ ሳይታወቅ አመልካቾች ክስ የቀረበበትን ቤት ቀላቅለው ይዘዋል፤ ስለሆነም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ፤ ቁጥራቸው 1140 እና 1141 የሆኑትን ቤቶች ማሕደሮች አስቀርቦ ከተመለከተ እና ከሚመለከተው የአስተዲደር አካል ስለጉዲዩ ተጣርቶ እንዱላክለት ካደረገ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካቾች ካርታ ያቀረቡ ቢሆንም አከራካሪው መጸዲጃ ቤት እና ማዔድ ቤት በይዞታ ማረጋገጫ ካርታው ውስጥ የማይካተት መሆኑ ተረጋግጧል፤ የሚመለከተው የአስተዲደር አካል በሰጠው መልስ ቁጥሩ 1140 የሆነው ቤት መጸዲጃ ቤት እንደሆነ እና አመልካቾች የያዙት ቢሆንም በሲአይኤስ ላይ የቀበላ ቤት በሚል የተገለጸ ነው የሚል ምላሽ ልኳል፤ 2ኛ ተጠሪ የመንግስት ነው የሚለው ቤት አመልካቾች ለመጸዲጃ ቤት የሚገለገለበት እና 2ኛ ተጠሪም ይህን ቤት እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ሲያከራየው የነበረ ነው፤ 2ኛ ተጠሪ ቤቱ በምን አግባብ ከእጁ ሉወጣ እንደቻለ አላስረዲም፤ የአመልካቾች ምስክሮች አመልካቾች ቤቱን ሲገለገለበት እንደነበረ ያስረደ ቢሆንም ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ስለላለ አከራካሪው ቤት የአመልካቾች አይደለም በማለት ወስኗል። ይህ ውሳኔ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- የስር ፍርድ ቤት ከቀረበለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ጭብጥ ወጥቶ የባለቤትነት ፍርድ መስጠቱ አግባብ አይደለም፤ ሁከት እንዱወገድ በሚል በሚቀርብ ክስ ላይ ተከሳሽ የሚያነሳው ባለቤትነትን የተመለከተ ክርክር አግባብነት የለውም፤ አመልካቾች ወደፉት ለክርክሩ መነሻ በሆነው መኖሪያ ቤት ላይ የምናነሳውን የባለይዞታነት ክርክር በሚገድብ መልኩ የተሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድ የሚል ክስ አቅርበው ሳለ አከራካሪው ቤት የአመልካቾች የግል ሀብት አይደለም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች የአመልካቾች መሆን አለመሆናቸው ጭብጥ ተይዞ ውሳኔ የተሰጠው አመልካቾች የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ስላቀረቡ ነው፤ የስር ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አስፈላጊ የሆነውን ጭብጥ በመያዝ እና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በማስቀረብ ጉዲዩን መርምሮ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ ውሳኔው ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የቻልነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት 1ኛው ተጠሪ በሰጣቸው ካርታ ላይ አከራካሪ የሆነውን ማድቤት እና መጸዲጃ ቤት የመንግስት ብል በመስራት፤
2ኛ ተጠሪም ይህንኑ ቤት የራሴ ነው በማለት ሁከት የፈጠሩብን በመሆኑ ሁከቱ እንዱወገድልን የሚል ነው። ሆኖም የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄ ሁከት ይወገድልን የሚል ቢሆንም ይህንኑ ዲኝነት ሉጠይቁ የቻለት አከራካሪ የሆነው ማድቤት እና መጸዲጃ ቤት ከአውራሾቻቸው የወረሱት ቤት አካል መሆኑን በመግለጽ ነው። ይህም አመልካቾች የአከራካሪው ማዔድ ቤት እና መጸዲጃ ቤት ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ በዚሁ ቤት ላይ ተፈጠረ የሚለት ሁከት እንዱወገድ ክስ ያቀረቡ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች አከራካሪ የሆነው ማዔድ ቤት እና መጸዲጃ ቤት የቀበላ ቤት መሆኑ እና 2ኛ ተጠሪም እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ሲያከራየው የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10/1 መሰረት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የለውም።
በያዝነው ጉዲይ አመልካቾች ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት በአከራካሪው ማዔድ ቤት እና መጸዲጃ ቤት ላይ በተጠሪዎች ተፈጥሯል የሚለት ሁከት እንዱወገድ የሚል ቢሆንም ይህንኑ ዲኝነት ሉጠይቁ የቻለት አከራካሪ የሆነው ማድቤት እና መጸዲጃ ቤት ከአውራሾቻቸው የወረሱት ቤት አካል መሆኑን እና የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ በመሆኑ ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን አጣርቶ አመልካቾች የአከራካሪው ማዔድ ቤት እና መጸዲጃ ቤት የአመልካቾች የግል ሐብት አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ አመልካቾች ለጠየቁት ዲኝነት ምላሽ የሰጠ እና በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 01/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
No topics extracted.