በስር ፍርድ ቤት ለቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላላው ተከራካሪ ወገን በጉዲዩ ላይ የሚያቀርበው ክርክር ከተሰማ በኋላ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ተገቢ መስል የገመተውን ማስረጃ በመመርምር የቀረበው መቃወሚያ በተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆን አለመሆኑን እነ ወ/ሮ ብርቄ ታደሰ (3 ሰዎች) እና አቶ ንጉሴ ታደሰ ነገርን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሰጠውን ውሳኔ፤ የክልል ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃውን መዝኖ፣ ከወረዲ ፍርድ ቤት እስከ ክልል ይግባኝ ሰሚ ድረስ ያለ ችልቶች አግባብነትና ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ ተቀብለው በመመዘን አረጋገጥን ከሚለት የፍሬ ነገር መደምደሚያ በመውጣት ወሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 245(1) እና (2)
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ብርቄ ታደሰ 2ኛ. ወ/ሮ የሺ ታደሰ 3ኛ. ወ/ሮ ፅጌ ታደሰ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ንጉሴ ታደሰ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች በቀን 25/09/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 03/09/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በጅልደ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ሲሆን የአሁን 3ኛ አመልካች እንዱሁም በዚህ ሰበር ክርክር የላለት አቶ ሽፈራው ግርማ እና እጅጋየሁ ታደሰ ጣልቃ ገቦች ነበሩ።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች በቀን 19/03/2012 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ አባታችን ታደሰ ተ/ጻድቅ በ2006 ዓ.ም የሞቱ ሲሆን ሰባት ልጆች አሎቸው፤ አባታችን በህይወት እያለ ይዞታው የነበረውና ከሞተ በኋላ በተከሳሽ እጅ የገቡ በሶስት ቦታ የሚገኙ ይዞታ መሬቶች የውርስ ድርሻችንን እንዱያካፍለን ይወሰንልና በማለት የመሬቱን አዋሳኝ እና መጠን ጠቅሰው ዲኝነት ጠይቀዋል። ጣ/ገቦች በበኩላቸው በቀን 11/06/2012 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ከሳሾች ያቀረቧቸውን ይዞታዎች በተመለከተ እኛም የሟች ወራሽ ስለሆን የሚገባን ድርሻ እንዱያካፍለን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሽ በቀን 06/04/2012 ዓ.ም በከሳሾች ላይ እንዱሁም በቀን 17/06/2012 ዓ.ም በጣ/ገቦች ላይ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አውራሽ የሞቱት በ2006 ዓ.ም ሳይሆን በ2005 ዓ.ም በመሆኑና በወራሾች መካከል የሚደረግ የውርስ ክርክር በ3 አመት ውስጥ መቅረብ ያለበት በመሆኑ፤
እንዱሁም የያዝኩት ይዞታ ቢኖር እንኳ ከ7 አመት በኋላ ሉጠይቁኝ ስለማይችለ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በተመለከተ ክርክር ያስነሳውን ይዞታ መሬት ወራሾች በስምምነት አካለ መጠን ያልደረሰ ወንድማቸው ትምህርቱን ተምሮ እስኪያጠናቅቅ ድረስ በተከሳሽ እጅ ይቆይ በማለት የተስማሙ መሆኑን የከሳሾች ምስክሮች ሲያረጋግጡ የተከሳሽ ምስክሮች ግን በ2006 ዓ.ም መሬቱ እጁ መግባቱን እንጂ በምን ሁኔታ እንደገባ አናውቅም ስላለ የከሳሾችን ምስክሮች ቃል አላስተባበለም። በመሆኑም የይዞታ መሬቶቹ አውራሽ ከሞተ በኋላ በስምምነት በተከሳሽ እጅ የገባ እንጂ ተከሳሽ እንደዚሁ የያዘው ስላልሆነና ስምምነቱ መኖሩ ለወደፉት እንካፈላለን በሚል በመሆኑ የይርጋ ጊዜውን ቀሪ የሚያደርግ ነው በማለት በተከሳሽ የተነሳውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል። ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም በክሱ በ3ኛ ተ.ቁ ላይ የሚገኘው ይዞታ መሬት የክርክሩ አካል ባልሆነው 3ኛ ወገን እጅ (በአቶ ደክሲሳ ገመቹ) ያለ መሆኑ ተረጋግጧል። በተ.ቁ 1 እና 2 ላይ የተገለጹት ይዞታ መሬቶች ግን የውርስ ሀብት መሆኑ ያላከራከረ በመሆኑና ይዞታ መሬቶቹን ተከሳሽ የተከራካሪዎች አባት ከሞቱ ከ2006 ዓ.ም በኋላ ውርስ ሳይካፈለ በተከሳሽ እጅ ለግዜው እንዱቆዩ በተስማሙት መሰረት የያዘ እንጂ የተከሳሽ የግለ እንዲልሆነ የከሳሾች እና የጣ/ገብ ማስረጃዎች አስረድተዋል፤ የተከሳሽ ምስክሮች ግን ይህን አላስተባበለም። በመሆኑም ተከሳሽ በእጁ ያለውን በተ.ቁ 1ኛ እና 2ኛ ላይ ከተገለጸው ይዞታ መሬት የከሳሾች እና 3ኛ ጣ/ገብ ድርሻ የሆነውን ይልቀቅ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተከሳሽ ይግባኝ ለምዔራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም አውራሽ ሲሞቱ የተከራካሪዎች ወንድም ደረጀ ታደሰ ትምህርት ላይ ስለነበር ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተከሳሽ እነሱን ረድቶ በመሬቱ እንዱጠቀምበት ወራሾች በመስማማት በተከሳሽ እጅ እንደተውት የተረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ መሬቱን ወራሾች እንዱካፈለ መወሰኑ ስህተት ያለው ሆኖ አልተገኘም በማለት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዘዋል።
በመጨረሻም ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ችልቱ ጉዲዩን መርምሮ የቀረቡት ምስክሮች ለክርክር ምክንያት የሆነውን ይዞታ መሬት ወራሾች በስምምነት ወንድማቸው ደረጀ ታደሰ እንዱማርበት በተከሳሽ እጅ ትተዋል በማለት ቃላቸውን ከመስጠታቸው ውጪ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ወራሽነታቸውን በማረጋገጥ ወንድማቸው እንዱማርበት ስለማድረጋቸው ያቀረቡት ማስረጃም ሆነ የፅሁፍ ውል የለም፤ የውርስ ይዞታ መሬት ሳይከፊፈለ እንዱቆይ መስማማታቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ባልቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች በሰው ምስክር ላይ ብቻ በመመስረት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ ያደረጉበት ሁኔታ ስህተት ነው። በአጠቃላይ አከራካሪውን መሬት ተከሳሽ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ 7 አመት የተጠቀመበት መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገበት ሁኔታ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ከሳሾች ያቀረቡት የውርስ ጥያቄ በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) መሰረት በ3 አመት ይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤቶች ያሳለፈትን ውሳኔ በመሻር በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ነው። አመልካቾች ባቀረቡት ማመልከቻ ተፈፀመ የሚለትን ስህተት ዘርዝረው የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ ተሽሮ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኜ እንዱፀና ጠይቀዋል።
ቅሬታው በአጣሪ ችልት ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት መሬቱ ወንድማቸው እንዱማርበት ብለው የቆየ መሆኑ በማስረጃ በተረጋገጠበት ሁኔታ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔውን ሽሮ በይርጋ ይታገዲል ያለበት አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 10/02/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ የስር ክርክራቸውን በማጠናከር መሬቱን ለመጠየቅ በህግ በተወሰነ ግዜ ውስጥ መጠየቅ ሲገባቸው ሳይጠይቁ ቀርተው በይርጋ መታገዲቸው አግባብነት ያለው ሆኖ ሳለ ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ ቅሬታው ውድቅ ተደርጎ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደሚታወቀው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አወሳሰንን በተመለከተ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 245(1) እና (2) እንደተደነገገው ተከሳሽ ለክሱ መቃወሚያ ባቀረበ ጊዜ ፍርድ ቤቱ መቃወሚያውን ተቀብል ላላው ተከራካሪ ወገን በጉዲዩ ላይ የሚያቀርበውን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ተገቢ መስል የሚገምተውን ማስረጃ በመመርምር የቀረበው መቃወሚያ በተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆን አለመሆኑን ፍሬ ነገርን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በማረጋገጥ ይወስናል።
በተያዘው ጉዲይ የወረዲው ፍርድ ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ካሳለፈት ውሳኔና ትዕዛዝ መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ ለክሱ ባቀረቡት መቃወሚያ ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል በማለት የተከራከሩ ሲሆን የስር ፍርድ ቤትም በመቃወሚያው ላይ ግራቀኙ ያደረጉትን ክርክር ተመልክቶ ለጉዲዩ አወሳሰን ይረዲል ያለውን ለጉዲዩ አግባብነት ያለው በህጉም ተቀባይት የለውም ያልተባለን ማስረጃ ተቀብል መርምሮና መዝኖ የግራቀኙ አውራሽ እንደሞቱ ወራሾች ስምምነት በማድረግ ወንድማቸው ደረጀ ታደሰ ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተጠሪ እየረዲው በውርስ መሬቱ እንዱጠቀምበት በመስማማት በተጠሪ እጅ መሬቱን እንደተዉት በማረጋገጥ የይርጋ ክርክሩን ውድቅ በማድረግ ወስኗል። ይህን ተከትል በውርስ የሚተላለፍ መሆኑ ያላከራከረውን ይዞታ መሬት ወራሾች እንዱካፈለት ወስኗል። ይህ የፍሬ ነገር መደምደሚያ እና ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ችልቶችም ተቀባይነት አግኝቷል።
በአንጻሩ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃውን መዝኖ ከወረዲው ፍርድ ቤት እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ድረስ ያለ ችልቶች አግባብነትና ተቀባይነት ያለው በማስረጃ ተቀብለው በመመዘን አረጋገጥን ከሚለት የፍሬ ነገር መደምደሚያ በመውጣት አመልካቾች ወራሽነታቸውን በማረጋገጥ ወንድማቸው እንዱማርበት ስለመስማማታቸው ያቀረቡት ማስረጃም የለም፤
የውርስ ይዞታ መሬት ሳይከፊፈለ እንዱቆይ መስማማታቸውን የሚያሳይ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ስለላለ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ማስረጃውን በተመለከተ ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በመጨረሻ ተቀብለው የሰጡትን ውሳኔ ሽሯል።
እንደሚታወቀው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን እንዲለው በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ለ) እንዱሁም በክልለ ህገ መንግስት እና በክልለ ፍርድ ቤቶች አዋጅ በግልጽ ተመልክቷል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ማስረጃ በመመርመር ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ከማረም ስልጣኑ ውጭ በመሆኑ የሚነቀፍ ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 03/09/2013 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የጀልደ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 26/05/2013 ዓ.ም፤ የምዔራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 02/06/2013 ዓ.ም፤ እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 21/07/2013 ያሳለፈት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ስለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.