ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ውድቅ በማድረግ በዋናው ፍሬ ጉዲይ ላይ ክርክር ለመስማት ቀጠሮ መለወጡ ብቻ ከስረ-ነገሩ ፍርድ በፉት ይግባኝ ላቀርብበት የማይችልና በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ወይም እልባት የተሰጠበት ባለመሆኑ በዚህ ሁኔታ ቅሬታ ካለ በስረ-ነገሩ ጉዲይ እነ ወ/ሮ አታሬ አሳላ (3 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ ሹምቡቤ ሻሬቾ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ መቃወሚያው በመታለፈም ያለውን ቅሬታ ጨምሮ በአንድ ላይ በማጠቃለል ይግባኙን/የሰበር አቤቱታው የሚቀርብ እንጂ ክርክሩ ቀጥል ባለበት ሁኔታ በመቃወሚያ በተሰጠ ብይን ላይ ይግባኝ የሚቀርብ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ሰ/ህ/ቁ 320(3) (7 ሰዎች)
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡- 1ኛ. ወ/ሮ አታሬ አሳላ 2ኛ አመልካች በራሳቸውና ስለላልችም ቀረቡ 2ኛ. አቶ አይዱቆ ዋና 3ኛ. አቶ መንግስቱ ዋና ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ሹምቡቤ ሻሬቾ 2ኛ. አቶ ዋድል ዋና 3ኛ. አቶ ቹቹ ዋና 4ኛ. ወ/ሮ አንድነት ዋና አልቀረቡም 5ኛ. ወ/ሮ አስቴር ዋና 6ኛ. አቶ ደሳለኝ ዋና 7ኛ. ወ/ሮ ጥሩወርቅ ዋና **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 19/04/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የቦዱቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/05/2012 ዓ.ም፣ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 12/06/12 ዓ.ም፣ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 02/07/2012 ዓ.ም፤ እንዱሁም የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ በቀን 28/03/2011 ዓ.ም የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው ጉዲዩ የውርስና የባልና ሚስት ንብረት ክርክርን መሰረት ያደረገ ሲሆን የቦዱቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበለትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ሰጥቷል። በሰጠው ብይን ከተራ ቁጥር 2-7 ያለት ተጠሪዎች የሟች ዋና ሆንችል ልጆች በመሆናቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ናቸው፤ በመሆኑም የውርሱ ሀብት ከዘር የወረደ እርስት በመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1000(2) ድንጋጌ መሰረት አቤቱታቸው ይርጋ አያግደውም፤ የሟች አባታቸው የውርስ ሀብት ላይ መብት ያላቸው በመሆኑ እና የውርስ ተጠቃሚ በመሆናቸውም በዚህ ረገድ የቀረበው መቃወሚያም ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጓል። የ1ኛ ተጠሪን በተመለከተም የሟች ሚስት በመሆነቸውና ሟች ስንት ሚስቶች እንደነበሩት፣ የትና እንዳት ባለ ሁኔታ እንዲኖራቸው በፍሬ ነገር ደረጃ በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ጠቅሶ የአሁን አመልካቾች ያቀረቧቸውን መቃወሚያዎች ውድቅ አድርጓል። ይህን ተከትልም በዋናው ፍሬ ጉዲይ ላይ ለማከራከር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት እንዱሁም ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈው ብይን ጉድለት የለውም ተብል ቅሬታቸው ውድቅ ተደርጓል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካቾች በቀን 19/04/2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ አባታችን ከሞተበት ከ1983 ዓ.ም እስካሁን ድረስ 30 አመት ሙለ ቆይተው ያቀረቡት የወራሽነት አቤቱታ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ እያለ የቦዱቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(2) የተደነገገውን ያለአግባብ በመተርጎም ከዘር ሀረግ የወረደ ርስት ይርጋ የለውም በማለት ያቀረብነውን መቃወሚያ በብይን ውድቅ ማድረጉ፤ ይህን ብይን የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ አቅርበን መጽናቱ ስህተት በመሆኑ እንዱሻርልን በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ክርክሩ ንብረት የርስት ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(2) በይርጋ የሚታገድ አይደለም ተብል የተሰጠው ውሳኔ ርስት የሚለው ሀሳብ በአሁኑ ሰአት ተግባራዊ ላደረግ የሚቻል ነው ወይ የሚለውን ነጥብ ተጠሪዎች ባለበት መጣራት ያለበት መሆኑ ታምኖበታል ተብል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪዎች በቀን 18/08/2013 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ክርክር ውሳኔ ባልተሰጠበት እና ጉዲዩን የያዘው የስር ቦዱቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ማስረጃ ቃል ለመስማት በመዝገቡ ላይ ቀጠሮ ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ በዋናው ጉዲይ ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት አመልካቾች በብይኑ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ህጉን ያልተከተለ በመሆኑ ወድቅ እንዱደረግ፤ በልላም በኩል ሟች ከሞቱ በኋላ የሟች መኖሪያ ቤት እና ቤቱ ያለበት ይዞታ አመልካቾች እና ተጠሪዎች በጋራ ስናስተዲድር ቆይተን አሁን የድርሻ ድርሻችንን ለማስተዲደር የወስን ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ያቀረብን ስለሆነና የክርክሩ ንብረት የዘር ሀረግ ተከትል የመጣ በመሆኑ የአመልካቾች የይርጋ መከራከሪያ በብይን በመታለፈ የህግ ስህተት ያልተፈጸመ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱጸናልን በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾችም በመልስ መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር አቅርበዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። እንደመረመርነው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በተሰጠ ብይን ከስረ ነገሩ ፍርድ በፉት ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ የመቅረቡን ስነ ስርዓታዊነት በቅድሚያ መመልከቱ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ይህንኑ መርምረናል።
በመሰረቱ በህጉ በልላ ሁኔታ እንዱፈፀም የሚያዝ ድንጋጌ ከላለ በቀር ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በተወሰነበት የመጨረሻ ፍርድ ላይ ይግባኝ ማለት የሚችል ሲሆን በልላ በኩል ፍርድ ቤቱ ክርክሩን በሚሰማበት ጊዜ በጉዲዩ ላይ ጊዜያዊ አገልግልት ያለው ትዕዛዝ ሲሰጥ፣ በመጀመሪያ ደረጃ በሚቀርብ መቃወሚያ ላይ ተገቢ መስል የታየውን ብይን ሲሰጥና ከስረ ነገሩ ፍርድ በፉት በሚሰጠው በማናቸውም ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማለት ወይም የሰበር አቤቱታ ማቅረብ አይቻልም። ይኸው የሥነ ሥርዓት ህግ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320 (1) (3) እና (4) ስር ተመልክቷል።
በተያዘውም ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ያሳለፈው ብይን ላይ ዋናው ክርክር ሳያልቅ ይግባኝ/የሰበር አቤቱታ ላቀርብበት አይገባም ተብል ይግባኙ/የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ሲገባ ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጀምሮ ባለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ መታየቱ እና በዚህ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪም የይርጋ መቃወሚያው ውድቅ የመደረጉ ጉዲይ በጭብጥነት ተይዞ ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ መደረጉ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ሥነ ሥርዓታዊ ድንጋጌ የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ውድቅ በማድረግ በዋናው ፍሬ ጉዲይ ላይ ክርክር ለመስማት ቀጠሮ መለወጡ ብቻ ከስረነገሩ ፍርድ በፉት ይግባኝ ላቀርብበት የሚችል አይደለም። በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ወይም እልባት ተሰጥቷል ልባል የሚችልም አይደለም። በዚህ ሁኔታ ደግሞ አመልካቾች ቅሬታ ካላቸው በስረ-ነገሩ ጉዲይ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ መቃወሚያው በመታለፈም ያላቸውን ቅሬታ ጨምረው በአንድ ላይ በማጠቃለል ይግባኙን/የሰበር አቤቱታውን ያቀርባለ እንጂ ክርክሩ ቀጥል ባለበት ሁኔታ በመቃወሚያ በተሰጠ ብይን ላይ ይግባኝ ማቅረብ እነደማይችለ ከሥነ ሥርዓት ህግ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ እንዱሁም በፍ/ብ/ስ/ሰ/ህ/ቁ 320(3) ሥር በግልጽ ከተመለከተው ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ይግባኝ ሰሚ እንዱሁም ሰበር ሰሚ ችልቶች ቅሬታ የቀረበበት ጉዲይ ዋናው ክርክር ሳያልቅ ይግባኝ የማይፈቀድበት ነው በማለት ቅሬታውን ውድቅ ማድረግ ሲገባቸው መርምረው ትዕዛዝና ውሳኔ ማሳለፊቸው የህግ ስህተት ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 12/06/12 ዓ.ም፤ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 02/07/2012 ዓ.ም፤ እንዱሁም የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ በቀን 28/03/2011 ዓ.ም የሰጡት ትዕዛዝና ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾች የቦዱቲ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/05/2012 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ባሳለፈው ብይን ያላቸውን ቅሬታ በስረ-ነገሩ ጉዲይ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ መቃወሚያው በመታለፈም ያላቸውን ቅሬታ ጨምረው በአንድ ላይ በማጠቃለል ይግባኙ/የሰበር አቤቱታቸውን ሉያቀርቡ ይችላለ ብለናል።
በስር ፍርድ ቤት የተጀመረው ክርክር ታግድ እንዱቆይ ሰኔ 2/2013 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.