የአስተዲደር ተቋም በዔለት ተዔለት ተግባሩ በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ በሰጠው የአስተዲደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው የክለሳ አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከዚህ በቀር የአስተዲደር ውሳኔው የተሰጠው አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ከተሰጠ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በመሆኑ የክለሳ አቤቱታ ላቀርብበት አይችልም እንዱሁም በእንዱህ አይነት ሁኔታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስልጣን አይኖረውም የሚባልበት የህግ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሕግ ስለ አስተዲደር ክፍልች አንቀጽ ሶስት ምዔራፍ አንድ ቁጥር 401(1) እና 402(1) እንዱሁም የአስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 48(2) እና 49(1) በአስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጁ መሰረት በሚከናወኑ የክለሳ ክርክሮች በአዋጁ የተመለከቱ ሥነ ሥርዓት ነክ ድንጋጌዎች የሚፈፀሙ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የክለሳ ስነ ስርዓት ጉዲዮች ላይ አግባብነት ያላቸው የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸው ስለመሆኑ አስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 58
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ዲሽን ባንክ አክስዮን ማህበር - ጠበቃ ፔ/ር ጥላሁን ተሾመ እና ነ/ፈጅ አበራ በቀለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዱት ቦርድ - ነ/ፈጅ ሰለሞን ነጋሽ - ቀረቡ 2ኛ. የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ - ነ/ፈጅ ታፈሰ ኩሳ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 28/03/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 05/01/2014 ዓ.ም ተዘጋጅቶ በቀን 01/02/2014 ዓ.ም ለባለጉዲዮች ተነቧል የተባለው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቀ ነው። ክርክሩ በፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ጣ/ገብቶ ተከራክሯል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው ከሳሽ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ/ም እና በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 48 መሰረት ውሳኔው እንዱከለስ በማለት ጠይቋል።
ተከሳሽ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችንና የፍሬ ነገር ክርክሩን አቅርቧል።
ባቀረበው መቃወሚያ ተከሳሽ ለጣ/ገብ በ04/02/2013 ዓ.ም የጻፈው ደብዲቤ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በጉዲዩ ላይ ቋሚ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ በማለት የሰጠውን መመሪያ ለማብራራት የተጻፈ ደብዲቤ እንጂ አስተዲደራዊ ውሳኔ አይደለም። በቀን 19/02/2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1183/12 ከመውጣቱ በፉት የወጣ ስለሆነ አዋጁ በመመሪያው ላይ ተፈጻሚ ላሆን አይገባም። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም። በተጨማሪም ከሳሽ ተከሳሽ በሰጠው ውሳኔ ቅሬታውን በአዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 51 መሰረት ለተከሳሽ ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ያላቀረበ ስለሆነ ከሳሽ የተከሳሽን አስተዲደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ ያልጨረሰ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ተከራክሯል።
ጣ/ገብ በበኩለ ወደ ክርክሩ ገብቶ ባቀረበው መቃወሚያ በቀን 04/02/2013 ዓ.ም በተከሳሽ የተጻፈው ደብዲቤ ጣ/ገብ ለተከሳሽ ለጻፈው ደብዲቤ ምላሽ ለመስጠት ሲሆን በግልባጭ ከሳሽ እንዱያውቀው ተደርጓል። ሆኖም ከሳሽ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 መሰረት ለተከሳሽ ምንም ቅሬታ ያላቀረበ ስለሆነ በአዋጁ መሰረት አስተዲደራዊ መፍትሄዎችን አሟጦ ያልጨረሰ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል። ከሳሽ በአዋጁ መሰረት የአስተዲደር ውሳኔው በተወሰነ 30 ቀናት ውስጥ ክስ ማቅረብ ሲኖርበት ግዜው ካለፈ በኋላ በማቅረቡ በይርጋ ይታገዲል። እንዱሁም በራሱ 22ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነው ውሳኔ በ23ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የተሻረ ስለሆነ ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለውም በማለት ተከራክሯል።
ለመቃወሚያ ክርክሩ ከሳሽ በሰጠው መልስ መቃወሚያዎቹ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244(2) መሰረት የቀረቡ አይደለም፤ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ ተከሳሽ እንደሚለው ቋሚም ሆነ ግዜያዊ መመሪያ አይደለም፤ የቦርድ ሰብሳቢ መመሪያም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የለውም፤ ስልጣን ያለው የዲይሬክተሮች ቦርድ ነው፤ እነዚህ ደብዲቤዎች የአስተዲደር መመሪያዎች እንዱሁም የአስተዲደር ውሳኔዎች አይደለም። መብታችን በመነካቱ ነው ፍ/ቤት የመጣነው። በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተከሳሽ በተጻፈው ደብዲቤ መነሻ ላቀረብነው ቅሬታ ምላሽ የተሰጠን አዋጅ ቁጥር 1183/12 ከወጣ በኋላ በቀን 04/02/2013 ዓ.ም ስለሆነ ይህንኑ መሰረት አድርገን ነው ክስ ያቀረብነው። በአስተዲደር ተቋም ውስጥ ያለውን መፍትሄ አሟጦ መጨረስን በተመለከተ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በቦርድ ሰብሳቢ የተጻፈው ደብዲቤ እንደደረሰን በ26/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በውሳኔው ላይ ቅሬታችንን በመግለጽ ለቦርደ ሰብሳቢ ለራሳቸው አመልክተናል፤ በግልባጭም ለጣ/ገብ አሳውቀናል። ጣ/ገብም በጉዲዩ ላይ ማብራሪያ እንዱሰጥበት ጠይቋል። ቦርደ በቀን 04/02/2013 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ አቤቱታችንን እንዲልተቀበለ በግልባጭ አሳውቆናል፤ ደብዲቤው በአድራሻ የተጻፈው ለጣ/ገብ ነው። ተከሳሽ ቅሬታ ስናቀርብ ወደ ቅሬታ ሰሚ ሂደ ብል አልመራንም፤ አሁንም ቢሆን ተከሳሽ ቅሬታ ሰሚ አካል ያቋቋመ ስለመሆኑ ይፊ አላደረገም። በመሆኑም መቃወሚያው ውድቅ ላደረግ ይገባል። ይርጋ መቃወሚያውን በተመለከተ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ እንደደረሰን በ26/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በውሳኔው ላይ ቅሬታችንን አቅርበን ቦርደ በቀን 04/02/2013 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ አቤቱታችንን እንዲልተቀበለው በመግለጽ ይርጋ ጊዜውን አቋርጦታል። መብትና ጥቅም የለውም የተባለውን በተመለከተም በክሱ መሰረት ከተወሰነልን በ22ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነው ውሳኔ ደግሞ ለመወሰን የሚያስችለን ስለሆነ ክስ የማቅረብ መብትና ጥቅም አለን በማለት ተከራክሯል።
የመቃወሚያ ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ ከሳሽ ደብዲቤዎቹ የአስተዲደር መመሪያዎች አይደለም እንዱሁም የአስተዲደር ውሳኔዎች አይደለም፤ መብታችን ስለተነካ ነው ፍ/ቤት የመጣነው በማለት ለመቃወሚያው ክርክር ቢያቀርብም ከሳሽ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ላይ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም እና 04/02/2013 ዓ.ም የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 48 መሰረት ውሳኔው እንዱከለስ የጠየቀ ስለሆነ ክርክሩ ከክሱ አንጻር ተገቢነት የለውም። በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተከሳሽ የተጻፈው ደብዲቤ የአስተዲደር ውሳኔ መሆኑን እንዱሁም በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተወሰነው የአስተዲደር ውሳኔ ላይ በቀረበው ቅሬታ ላይ የሰጠው ምላሽ መሆኑን ችልቱ ተገንዝቧል። በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተከሳሽ የተጻፈው ደብዲቤ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት የተጻፈ ስለመሆኑ አላከራከረም። በዚህ ደብዲቤ ቅር በመሰኘት ከሳሽ ለተከሳሽ ቦርድ ሰብሳቢ ቅሬታ ያቀረበው በ26/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ነው። አዋጅ ቁጥር 1183/12 የወጣው ደግሞ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም ከመሆኑ አንጻር በአስተዲደር ውሳኔው ላይ ቅሬታው ለተከሳሽ ቦርድ ሰብሳቢ የቀረበው አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ስለሆነ ለተከሳሽ ቦርድ ሰብሳቢ የቀረበው ቅሬታ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 የሚሸፈን ሆኖ አልተገኘም። በዚህ መሰረት በአዋጁ አንቀጽ 51 ማንኛውም የክለሳ አቤቱታ ፍ/ቤት የሚቀርበው የመጨረሻ በሆነ የአስተዲደር ውሳኔ ላይ ብቻ መሆኑ የተደነገገ ስለሆነ የአስተዲደር ውሳኔውና በአስተዲደር ውሳኔው ላይ የቀረበው ቅሬታ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 በማይሸፈንበት ሁኔታ በአስተዲደር ውሳኔ ላይ በቀረበ ቅሬታ ላይ የተሰጠ ምላሽ ብቻ መሰረት በማድረግ ክለሳ አቤቱታ ማቅረብ የሚያስችል የህግ መሰረት የለም። በተጨማሪም በአዋጁ አንቀጽ 56(2) መሰረት ፍ/ቤት የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዲደር ውሳኔ ሉያጸና ወይም በሙለ ወይም በከፉል ሉሽር እንደሚችል የተደነገገ በመሆኑ የአስተዲደር ውሳኔው እና ቅሬታው በአዋጁ በማይሸፈኑበት ሁኔታ ፍ/ቤት በቅሬታው ላይ የተሰጠውን ምላሽ ብቻ መሰረት በማድረግ የአስተዲደር ውሳኔውን ማጽናት ወይም በሙለ ወይም በከፉል መሻር አይችልም። በመሆኑም ላልች መቃወሚያዎችን መመርመር ሳያስፈልግ የቀረበውን የክለሳ አቤቱታ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 ስር የማይሸፈን ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ብይን ሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች በቀን 28/03/2013 ዓ/ም ባቀረበው ማመልከቻ በተሰጠው ብይን ተፈፀሙ የሚላቸውን የህግ ስህተቶች ዘርዝሮ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ፍሬ ነገር ክርክር አላግባብ አዛብቶ በመረዲት እና የአስተዲደር ሥነ ሥርአት አዋጁን ተፈጻሚነት በተመለከተ የተሳሳተ ትርጓሜ በመስጠት የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተብል ብይኑ እንዱሻርና ስር ፍ/ቤት ወደ ፍሬነገሩ በመግባት ክርክሩን ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ እንዱወሰንልን በማለት ቅሬታውን አቅርቧል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 ስር አይሸፈንም በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 29/07/2014 ዓ.ም ባቀረበው መልስ የስር ክርክሩን አጠናክሮ የአስተዲደር ሥነ ሥርአት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ከመውጣቱ በፉት የተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ ከ11 ወራት በኋላ በወጣ ህግ ስለማይዲኝ እና ከአዋጁ መውጣት በፉት የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም ተብል ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪ በበኩለ በቀን 29/07/2014 ዓ.ም ባቀረበው መልስ የስር ፍ/ቤት በ1ኛ ተጠሪ የተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ከመውጣቱ በፉት የተሰጠ በመሆኑ የክለሳ አቤቱታው በአዋጁ የማይሸፈን ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጠው ብይን ትክክለኛና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ ሉጸና ይገባል። ይህ ታልፍ ብይኑ የሚሻር ከሆነ ግን የስር ፍ/ቤት ወደ ፍሬ ነገሩ በመግባት አከራክሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ከመታዘዙ በፉት በተጠሪዎች በኩል በተነሱት ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ብይን እንዱሰጥባቸው እንዱታዘዝ በማለት ጠይቋል። አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል። እንደመረመርንው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 አይሸፈንም፤ ፍርድ ቤቱም የክለሳ አቤቱታውን ለመመልከት ስልጣን የለውም በማለት ብይን የሰጠው በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በ1ኛ ተጠሪ የተጻፈው ደብዲቤ የአስተዲደር ውሳኔ መሆኑን እንዱሁም በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተወሰነው የአስተዲደር ውሳኔ ላይ ለቀረበው ቅሬታ የተሰጠ ምላሽ መሆኑን ተገንዝቦ፤ ነገር ግን በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በ1ኛ ተጠሪ የተጻፈው ደብዲቤ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት የተጻፈ በመሆኑና በዚህ ደብዲቤ ቅር በመሰኘት አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ቦርድ ሰብሳቢ ቅሬታ ያቀረበው በ26/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 1183/12 የወጣው ደግሞ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም በመሆኑ ለቦርደ ሰብሳቢ የቀረበው ቅሬታ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 የሚሸፈን አይደለም፤
የአስተዲደር ውሳኔውና በአስተዲደር ውሳኔው ላይ የቀረበው ቅሬታ በአዋጅ ቁጥር 1183/12 በማይሸፈንበት ሁኔታ በአስተዲደር ውሳኔ ላይ በቀረበ ቅሬታ ላይ የተሰጠ ምላሽ ብቻ መሰረት በማድረግ ክለሳ አቤቱታ ማቅረብ አይቻልም በሚል ነው።
በመሰረቱ የአስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ከወጣበት ምክንያት አንደ የአስተዲደር ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን እና ሥነ ሥርዓት በመደንገግ እንዱሁም በአስተዲደራዊ ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ ሰው የውሳኔዎቹን ህጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዲደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
‛የአስተዲደር ውሳኔ“ ማለት ደግሞ የአስተዲደር ተቋም በዔለት ተዔለት ተግባሩ በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ የሚሰጠው የአስተዲደር ውሳኔ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 2(3) ከተሰጠው ትርጉም መገንዘብ ይቻላል። በእንዱህ አይነት የአስተዲደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው ውሳኔው በከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዱከለስ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 48(2) እና 49(1) ስር ተመልክቷል። ስለሆነም ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው በአስተዲደር ተቋሙ በዔለት ተዔለት ተግባሩ በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ በሰጠው የአስተዲደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው የክለሳ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችል መደንገጉን ሲሆን ከዚህ በቀር የአስተዲደር ውሳኔው የተሰጠው አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ከተሰጠ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በመሆኑ የክለሳ አቤቱታ ላቀርብበት አይችልም እንዱሁም በእንዱህ አይነት ሁኔታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስልጣን አይኖረውም የሚባልበት የህግ ምክንያት የለም።
በ1952 ዓ.ም የፍትሐ ብሓር ሕግ ስለ አስተዲደር ክፍልች በሚደነግገው አንቀጽ ሶስት ምዔራፍ አንድ ቁጥር 401(1) እና 402(1) ሥር ከተመለከተው ግልጽ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው የአስተዲደር አካላት በህግ የታወቀላቸው የተግባር ስልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ ወይም በህጉ የተገደደትን ሁኔታዎች ወይም ፍርም ባለመከተል የሚፈጽሟቸው ሥራዎች ፈራሾች ሲሆኑ ይህን ፈራሽነት ማንኛውም ባለጉዲይ ሁለ ሉጠይቅ ይችላል። ስለሆነም አስተዲደሩ በህግ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ ሲወስን ወይም በህግ የተመለከቱ ሁኔታዎችን ወይም የተዘረጋውን ስርዓት ባለመከተል ወስኖ ሲገኝ በአስተዲደሩ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ አቤቱታ ቀርቦ ውሳኔው በፍርድ ፈራሽ እንዱሆን ሉወሰን እንደሚችል አስቀድሞም ቢሆን በፍትሐ ብሓር ህጉ ተቀባይነት ያገኘ ጉዲይ ነው።
ከዚህም ላላ አመልካች በፅሁፍ ባቀረበው የክለሳ የዲኝነት ጥያቄ ላይ እንዱሁም በተጠሪዎች የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተከትል ባቀረበው መከራከሪያ ላይ ወጥነት አለመኖሩን በማንሳት የስር ፍርድ ቤት የወሰነ ሲሆን ተጠሪዎችም ይህን በመከራከሪያነት አያይዘው ማንሳታቸውን ተመልክተናል። ክርክሩ የሚመራበትን ሥነ ስርዓት በተመለከተ የክለሳ ስነ ስርዓት ጉዲዮች ላይ አግባብነት ያላቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 58 ተደንግጓል። ስለሆነም ለክለሳ ለክርክሩ በአዋጁ የተመለከቱ ሥነ ሥርዓት ነክ ድንጋጌዎች የሚፈፀሙበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዲዩ የሚመራው በፍትሐ ብሐር ሥነ ሥርዓት ህጉ አግባብ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ከስነ ስርዓት ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ከሳሽ በህጉ የተፈቀደን መፍትሄ ከፍርድ ቤቱ ለማግኘት በፅሁፍ በግልጽ ዲኝነት መጠየቅ ይገባዋል።
በዚህ መልኩ በጽሁፍ ግልጽ የዲኝነት ጥያቄውን ካቀረበ በኋላ መቃወሚያን ለመወሰንም ይሁን በፍሬ ነገር ላይ በችልት የሚያቀርብ ክርክር መሰረታዊ አላማው በጽሁፍ ያቀረበውን ክርክር ለማብራራት እንጂ በጽሁፍ ማመልከቻ ላይ ያልሰፈረን የዲኝነት ጥያቄ ለማስተናገድ አይደለም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 83፣ 222፣ 224፣ 234፣ 235፣ 236፣ 241፣ 244፣ 245 እና ተያያዥ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዱት ቦርድ የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ጥቅሙን የሚነካና የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 48 መሰረት ውሳኔው እንዱከልስ ለመጠየቅ የቀረበ አቤቱታ መሆኑን የሚገልፅ ነው። ክርክሩ ላመራና ውሳኔ ላሰጥ የሚገባውም ይህንኑ የዲኝነት ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው።
ስለሆነም ግራ ቀኙ የየበኩላቸውን ክርክር ቢያቀርቡም የስር ፍርድ ቤት በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በ1ኛ ተጠሪ የተጻፈው ደብዲቤ የአስተዲደር ውሳኔ መሆኑን እንዱሁም በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በተወሰነው የአስተዲደር ውሳኔ ላይ በቀረበው ቅሬታ ላይ የሰጠው ምላሽ መሆኑን ችልቱ ተገንዝቧል በሚል ለያይቶ መወሰኑ በግልፅ የቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ እና ከፍ ሲል የጠቀስናቸውን የህጉን ድንጋጌዎች ይዘት የተከተለ አይደለም።
በአጠቃላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በግልጽ በጽሁፍ የቀረበውን የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በአስተዲደር ውሳኔ ላይ በቀረበ ቅሬታ ላይ የተሰጠ ምላሽን ብቻ መሰረት በማድረግ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ፤ ይህን ተከትልም መሰል የክለሳ አቤቱታ ማቅረብ የሚያስችል የህግ መሰረት የለም፤ አመልካች ያቀረበው የክለሳ አቤቱታ በአዋጁ የሚሸፈን አይደለም፤ እንዱሁም ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የሰጠው ብይን የሚነቀፍ ነው። የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ከእነሙለ ይዘቱ በአግባቡ ሳይጤን፤ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት የህጉ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ እንዱሁም ከክርክሩ ውጪ በመውጣት የተሰጠ ብይን በመሆኑም የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 05/01/2014 ዓ.ም የሰጠው ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ የግራ ቀኙን ቀሪ ክርክር ተመልክቶ እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰናል። የውሳኔው ግልባጭ ይድረሰው።
ከስር ፍርድ ቤት የመጣው መዝገብ በመጣበት አግባብ ይመለስ።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.