ተከሳሽ የዋስትና መብት ተጠብቆለት የዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመ ብይን ለመስጠት በተያዘው ቀነ ቀጠሮ አለመቅረቡ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ መርምሮ አስቀድሞ የሰራውን ብይን እንዲያነብ፤አስቀድሞ የተሰራ ብይን ከላለም በዔለቱ ወይም በቀጣይ ቀጠሮ ብይን እንዲይሰጥ የሚያግድው ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 161 እና ተከታይ ድንጋጌዎች፣ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20/4
No summary available.
ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - ዐ/ህግ አበራ ረታ ቀረቡ ተጠሪ፡- አስቴር አደሽ ደበላ - አልቀረቡም መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 80076 መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን ትዕዛዝ በማጽናት፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 006808 ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ የወንጀል ህግ አንቀጽ 447(ሀ)ን በመተላለፍ በቀን 12/12/2012 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 9፡30 ሰዓት ላይ በየካ ክፍለ ከተማ ምንሉክ ሆስፑታል የሴቶች እና ህጻናት ጾታዊ ጥቃት የወንጀል ምርመራ ክፍል በመቅረብ ተገኔ ረጋሳ የተባለት አሰሪዬ በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ሻይ መኝታ ቤታቸው ድረስ እንዲመጣላቸው ጠይቀውኝ ሳመጣላቸው የመኝታ ቤታቸውን በር በመቆለፍ አንገቴን በመያዝ ራሴን እንዲልከላከል በማድረግ አስገድደው በመድፈር እርግዝና እንዱከሰትብኝ ያደረጉ ስለሆነ በህግ ይጠየቁልኝ ስትል ላላውን ሰው በባለስልጣን ፉት ክስ በማቅረቧ ምክንያት የግል ተበዲይ በቀን 27/12/2012 ዓ.ም በፕሉስ ተይዘው አንድ ቀን ታሰረው እንዱያድሩ ያደረገች በመሆኑ በፈጸመችው ሀሰተኛ ክስ በማቅረብ ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው።
ተጠሪ ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ እንደላላቸው ገልጸው የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ሲጠየቁም ክደው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ ለተጠሪ የዋስትና መብት ጠብቆ መዝገቡ ላይ ብይን ለመስጠት በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርቡ በመቅረታችው ዓቃቤ ሕግ በቀረበው ማስረጃ ብይን ይሰጥልኝ በማለት ጠይቋል፤ ፍርድ ቤቱም ተጠሪ የተሰወሩት የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ይከላከለ አይከላከለ የሚለውን ብይን ሳይሰጥ በመሆኑ ተጠሪ በላለበት ብይን ለመስጠት የሚያስችል የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግም ሆነ አስገዲጅ የሰበር ውሳኔ የለም በማለት የዓቃቤ ሕግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ በተገኙ ጊዜ መዝገቡን እንዱንቀሳቀስ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህንኑ ትዕዛዝ በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አጽንቶታል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ሐምል 19 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም፡- የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በላለችበት ብይን ላሰጥ አይገባም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 37 እና የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 160 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን የሚቃረን ነው፤
የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ባልቀረበችበት ሁኔታ ብይን ቢሰጥ በተጠሪ መብት ላይ የሚያስከትለው የመብት ጥሰት የለም፤ ስለሆነም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በስር ፍርድ ቤቶች የሰተጠው ትዕዛዝ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ዐቃቤህግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 447(ሀ) ጠቅሶ ባቀረበው ክስ የአሁን ተጠሪ ቀርበው የዐቃቤህግ ማስረጃ ሲሰማ ከተከታተለ በኋላ ለመከላከል ብይን በተቀጠረበት ዔለት ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ምክንያት በማድረግ ተጠሪ በተገኙ ጊዜ ክስ የማንቀሳቀስ መብት ጠብቆ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋበትን አግባብ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ድንጋጌዎች አንፃር ለማጣራት የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ስላልቀረቡ መልስ በጽሁፍ የመስጠት መብታቸውን ፍርድ ቤቱ አልፍታል።
የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት በግልጽ መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ክሱን ሲከታተለ የነበረ እና የዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በተሰሙበት ዔለትም ቀርበው የነበረ መሆኑን፤ መዝገቡ ለብይን በተቀጠረበት ዔለት ሳይቀርቡ የቀሩ መሆኑን፤ ፍርድ ቤቱም ተጠሪ የተሰወሩት የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ይከላከለ አይከላከለ የሚለውን ብይን ሳይሰጥ በመሆኑ ተጠሪ በላለበት ብይን ለመስጠት የሚያስችል የወንጀል ሥነ-ሥርዓትም ሆነ አስገዲጅ የሰበር ውሳኔ የለም በማለት ተጠሪ በተገኙበት ጊዜ መዝገቡን እንዱንቀሳቀስ በማለት ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በመርህ ደረጃ የወንጀል የክርክር ሂደት ተከሳሾች ባለበት እንደሚደረግ፤ ይህም ሲደረግ የተከሰሱበትን ምክንያት አውቀው የመከራከር እና የመሰማት መብት ያላቸው መሆኑ፤ በልዩ ሁኔታ ደግሞ የፈጸሙት ወንጀል ቀርበው መከራከር የማይፈልጉና ከፍትሕ ስርዓቱ የሸሹ ግለሰቦች በሕጉ የተቀመጠው መስፈርት ተሟልቶ በተገኘ ጊዜ በፍትሕ ሥርዓቱ መጠየቅ ያለባቸው እና በላለበት ነገሩ ሉሰማ የሚችል ስለመሆኑ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 161 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ፍርድ ቤቱም አንድን ጉዲይ ተከሳሽ በላለበት ለማየት እንዱችል ተከሳሹ በቀጠሮ ቀን ያለ በቂ ምክንያት መቅረቱ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑም ይኸው ድንጋጌ ያስገነዝበናል።
በልላ በኩል የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20/4 ላይ የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፤ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፤ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት ያላቸው ስለመሆኑ ተመልክቷል።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ክሱ በሚሰማበትና የዓቃቤሕግ ምስክሮች በሚሰሙበት ጊዜ ችልት ቀርበው የነበረ መሆኑ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ በግልጽ ተመልክቷል፤ ይህም ተጠሪ በሕገ መንግስቱ የተጠበቀላቸውን መብት የተጠቀሙ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ተከሳሹ የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመና ብይን ለመስጠት በተያዘው ቀነቀጠሮ አለመቅረቡ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ መርምሮ አስቀድሞ የሰራውን ብይን እንዲያነብ፤ አስቀድሞ የተሰራ ብይን ከላለም በዔለቱ ወይም በቀጣይ ቀጠሮ ብይን እንዲይሰጥ አያደርገውም። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፍርድ ቤቱ የዓቃ ቤሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሹ ብይን ለመስጠት በተያዘው ቀነቀጠሮ አለመቅረቡን ምክንያት በማድረግ ተከሳሽ በቀረበ ጊዜ መዝገቡ ይንቀሳቀስ በማለት ብይን የሚሰጥ ከሆነ ፍርድ ቤቱ በአንድ በኩል የተከሳሽን የመከራከር መብት በሚያረጋግጥ መልኩ ክርክሩን ከመምራት፤ በልላ በኩል ደግሞ የተበዲዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት ከማረጋገጥ አንጻር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው ሰዎች ከፍትሕ ሂደቱ እንዲያመልጡ ከማድረግ አንጻር ያለበትን ሚዛኑን ጠብቆ ክርክሩን የመምራት ግዳታ በእጅጉ የሚጻረር ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዚህ አግባብ በማየት ተጠሪ በተገኙበት የተሰሙትን የዓቃቤ ሕግን ማስረጃዎች መርምሮ ተገቢ ነው ያለውን ብይን መስጠት ሲገባው ይህን ለማድረግ የሚያስችለኝ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግም ሆነ የሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ ውሳኔ የለም በማለት ተጠሪ በቀረቡ ጊዜ መዝገቡ ይንቀሳቀስ ሲል የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 13/07/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ ይህንኑ ትዕዛዝ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ተጠሪ በተገኙበት የተሰሙትን የዓቃቤ ሕግን ማስረጃዎች መርምሮ ተገቢ ነው ያለውን ብይን እንዱሰጥበት ገዲዩን መልሰንለታል።
No topics extracted.