ሉከፍል የማይገባዉን ገንዘብ የከፈለ ሰዉ ገንዘቡ እንዱመለስለት የመጠየቅ መብት ያለዉ ቢሆንም፤ ስህተት ሳይኖር፣ የሚያስከፍለዉም የህግ ወይም የዉል ግዳታ ምክንያት ያለመኖሩን እየተረዲዉ የተከፊይ ሰው ስም እና የባንክ ሂሳብ ቁጥር በመፃፍ ገንዘብ ገቢ ያደረገ ሰው፤ በራስ ፍቃድ ታስቦበት እንደተከፈለ ስለሚቆጠር ገንዘቡ እንዱመለሰ መጠየቅ የሚቻል ስላለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 2165
No summary available.
ቀን - ህዲር 25 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ድንቃለም ግዛዉ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት ዘርፈ የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ ያላግባብ በልላ ሰዉ የባንክ ሂሳብ የተከፈለ ገንዘብ ይመለስልኝ በሚል የቀረበን ክስ መሰረት በማድረግ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታን የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ ከተከሳሽ ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖረን በባንክ ሂሳባቸዉ በስህተት ያስገባሁትን ብር 42,800.00 ክሱ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ከሳሽ ገንዘቡን ያስገቡት በስህተት ሳይሆን የተከሳሽን ስም እና የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸዉን ጽፈዉ መሆኑን እና ገንዘቡን ያስገቡትም አቶ ፍቅሩ የሚባል የከሳሽ ቤተሰብ ከተከሳሽ ልጅ አቶ ዲንኤል እልቅነዉ በደቡብ አፍሪካ አገር ብር 42,800.00 ዔዲ ለመመለስ መሆኑን ጠቅሰዉ ክሱ ዉድቅ እንዱሆን ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የማይገባዉን ክፍያ የፈጸመ ሰዉ ክፍያዉ እንዱመለስለት የመጠየቅ መብት እንዲለዉ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2164 ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ለከሳሽ ለመመለስ የማይገደደበትን ምክንያት በህጉ አንቀጽ 2165፣ 2166 እና 2177 ላይ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት የማስረዲት ሸክማቸዉን ያልተወጡ መሆኑና ከሳሽ ገንዘቡን ለተከሳሽ የከፈለት ከዉል ወይም ከህግ የመነጨ ግዳታ ሳይኖርባቸዉ ስለመሆኑ መረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሽ ብር 42,800.00 ከወጪ እና ኪሳራ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች ሚያዝያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም ተጽፍ በቀረበ ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የአመልካችን ስምና የባንክ ቁጥር ጠቅሰዉ ገንዘቡን በአመልካች ሂሳብ ገቢ ማድረጋቸዉ መረጋገጡን፣ ይህን ያደረጉት በስህተት መሆኑን በክሳቸዉ መሰረት ባላስረደበትና ገንዘቡ በአመልካች ሂሳብ ገቢ የተደረገዉም የአመልካች ልጅ ደቡብ አፍሪካ ሆኖ የተጠሪ ቤተሰብ ለሆነዉ ላበደረዉ ገንዘብ ዔዲ መክፈያ መሆኑን አመልካች አስረድተዉ እያለ ገንዘቡ ለተጠሪ ሉከፈል ይገባል በሚል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ታርሞ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል። አቤቱታዉ ተመርምሮም አመልካች ገንዘቡን ለተጠሪ ሉመልሱ ይገባል ተብል የመወሰኑን አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አከራክሮ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ እንዱቀርቡ ጥሪ የተደረገላቸዉ ቢሆንም ባለመቅረባቸዉ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
ከላይ በአጭሩ የተገለጸዉ የጉዲዩ አመጣጥ ሲሆን፣ ይህ ችልትም አቤቱታዉን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ ተጠቃሹ ገንዘብ እንዱከፈላቸዉ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት፣ ገንዘቡን በአመልካች የባንክ ሂሳብ ላይ ገቢ ያደረጉት ተሳስተዉ መሆኑን ነዉ። ተጠሪ ገንዘቡን ገቢ ያደረጉት ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም እና ጥቅምት 10 2011 ዓ.ም የአመልካችን ስም እና የባንክ ሂሳብ ቁጥር በመጥቀስ መሆኑን ጠቅሰዉ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ክርክር ተጠሪ ክደዉ ያልተከራከሩ ከመሆኑም በላይ በክሳቸዉ አባሪ በማድረግ ያቀረቡት ማስረጃም ይህንኑን የሚያሳይ ነዉ። ከዚህም የምንረዲዉ ተጠሪ ገንዘቡን በአመልካች ሂሳብ ላይ ገቢ ያደረጉት አስበዉበት እንጂ በስህተት አለመሆኑን ነዉ።
የፍትሐብሕር ህጋችን ያላግባብ ስለመበልጸግ በሚል ርዔስ ክፍል ሁለት ላይ የማይገባዉን ገንዘብ መክፈል (Undue payments) ስለሚያስከትላቸዉ ህጋዊ ዉጤቶቸን ይደነግጋል። የህጉ አንቀጽ 2164 ድንጋጌ ሉከፍል የማይገባዉን ገንዘብ የከፈለ ሰዉ ገንዘቡ እንዱመለስለት የመጠየቅ መብት ያለዉ መሆኑን በመርህ ደረጃ የሚደነግግ ሲሆን፣ በህጉ አንቀጽ 2165-2167 ያለት ድንጋጌዎች ደግሞ የተከፈለዉ ገንዘብ ለከፊዩ ሉመለስ የማይችልባቸዉን ልዩ ሁኔታዎች የሚደነግጉ ናቸዉ። ከዚህ ዉስጥ አንደ ስህተት ሳይኖር የተከፈለ ገንዘብን የሚመለከት ነዉ። በዚህም መሰረት ስህተት ሳይኖር ሉከፍለዉ የማይገባዉ ዔዲ መሆኑን እያወቀና የሚያስከፍለዉም ምክንያት ያለመኖሩን እየተረዲዉ በእራሱ ፍቃድ የከፈለ ሰዉ ገንዘቡ እንዱመለስለት መጠየቅ እንደማይችል የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2165 ግልጽ ድንጋጌ ያስገነዝባል። ተጠሪ ለአመልካች ኃላፉ ሉያደርጋቸዉ የሚችል የህግ ወይም የዉል ግዳታ የለም ብለዉ የሚያምኑ ከሆነ ገንዘቡን በአመልካች ሂሳብ ገቢ ያለማድረግ መብት እያላቸዉ፣ የአመልካችን ስም እና የባንክ ሂሳብ ቁጥር ጠቅሰዉ ገንዘቡን ገቢ ማድረጋቸዉ ሲታይ በስህተት ሳይሆን በእራሳቸዉ ፍቃድ አስበዉበት እንደከፈለ የሚቆጠር በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ተፈፃሚነት ያለዉ ድንጋጌ በህጉ አንቀጽ 2165 ላይ የተመለከተዉ ነዉ። በመሆኑም ተጠሪ በአመልካች የባንክ ሂሳብ ላይ ያስገቡት ገንዘብ እንዱመለስላቸዉ መጠየቅ አይችለም።
ጉዲዩን ከዚህ አንፃር አይቶ የተጠሪን ክስ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ፣ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የላላቸዉን ድንጋጌዎች በመጥቀስ አመልካች ገንዘቡን ለተጠሪ የመመለስ ግዳታ አለባቸዉ በሚል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ ያላግባብ የተከፈለ ገንዘብ ለከፊዩ ሉመለስ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ ከላይ የተመለከቱትን የህጉን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ ተከታዩ ተወስኗል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 08 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በትዕዛዝ የፀናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ላይ ያስገቡትን ብር 42,800.00 ለተጠሪ ሉመልሱ አይገባም ተብል ተወስኗል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.