የሰራተኛ ማህበር አመራር በግለ ሳይሆን በሰራተኛ ማሕበሩ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በሚዱያ የሚሰጥ የቃለምልልስ ማብራሪያ በጥቅለ አሰሪውን የማይወክለና ምክትል ሉቀመንበርነት በሚመራው ማሕበርና በማሕበሩ አባላት ላይ ደርሰዋል ያለትን የመብት ጥሰቶችና ግድፈቶች በመግለጻቸው የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ መልካም ግንኙነት የሚሻክር ከባድ ጥፊትና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ድንጋጌ መጣሱን የሚያስረዲ ሳይሆን በአሰሪው ዱሲፔሉን ኮሚቴው በሕብረት ሥምምነቱ በተመለከተው አግባብ የሰራተኛ ማሕበር ተወካዮች መሳተፍ ሲገባቸው ባልተገኙበት የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ አስፈላጊ ሂደቶችን ሳይከተል በተሰጠ ውሳኔ የሚደረግ የሥራ ስንብት ሕገ-ወጥ ስለመሆኑ የአሰሪው ስንብት ህገ ወጥ ከሆነ የሥራ ውለ ከሕግ ውጭ በአሰሪው የተቋረጠበት ሰራተኛው ወደሥራ ሉመለስ የማይችለው ከሥራው ጠባይ ግንኙነት የተነሳ ወይም ከክርክር ሂደት ከተወሰደው ግንዛቤ በሥራ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር ያስከትላል ተብል በፍርድ ቤቱ ሲታመን እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 43(3) ላይ የተደነገገው ከፍተኛ ችግር የሚለው የሕጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፔ እና አቶ ማርቆስ የሱወርቅ ማንኛውንም ዓይነት ጉዲት ሰራተኛውን ወደሥራው እንዲይመለስ ማድረግ የማይችል እና የሚያስከትለው ጉዲት ጉልህ ላሆን የሚገባና ሰራተኛው ከሥራ ኃላፉነቱ ጋር የተያያዘ ጥፊት ካልፈፀመና ወደሥራ ቢመለስ ሥራው ላይ የሚያደርሰዉ ከፍተኛ ጉዲትን አሰሪው ካላሳየ በቀር ሰራተኛው ወደስራው የሚመለስ ስለመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(1)(2)
No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፔ - ነ/ፈጅ ኃ/ማርያም ብርሃኔ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ማርቆስ የሱወርቅ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
ጉዲዩ በግል የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር የሥራ ውል መቋረጡ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት በአውሮፔላን ጥገና ባለሙያነት በወር ብር 20,805.89 እየተከፈለኝ ስሰራ ነበር፤ በተጨማሪም በሰራተኞች ማሕበር ውስጥም በምክትል ሉቀመንበርነት ቦታ እየሰራሁ እያለ ማሕበሩን በመወከል የተገለጸውን በግል ደረጃ የተሰጠ መረጃ በማድረግ፣ የአመልካችን ስም የሚያጎድፍ ሆነ የሰራተኛውን ሰላማዊ ግንኙነት የሚያጠፊ ተግባር ባልተፈጸመበት የተሳሳተ መረጃ ሰጥተሃል፣ ሰላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት እንዲይኖር አድርገሃል በማለት ከግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ማሰናበቱ ሆነ በዱሲፔሉን ኮሚቴው በሕብረት ሥምምነቱ መሰረት ከሰራተኛ ማሕበር ሁለት ተወካዮች በላለበት መወሰኑ ሕገ-ወጥ ስንብት ስለሆነ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልኝ ወደሥራ እንዱመልሰኝ፤ ይሕ ካልሆነ በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈለኝ የሚል ነው።
አመልካች ያቀረበው መልስ ተጠሪ በሰራተኛ ማሕበር አመራርነቱ ሳይሆን በመገናኛ ብዙኋን በመቀጠም የአመልካች ደርጅት መልካም ስምና ዝና ላይ ሀሰተኛ የሥም ማጥፊት ዘመቻ የሚያካሂድ ቡድን ላይ ዋና ተዋናይ ሆኖ ነው። ድርጊቱ የሥራ ቦታ ላይ መልካም ግንኙነትን የሚያበላሽና በድርጅቱ ንብረት ላይ የሚፈጸም ጉዲት ነው። ከናሁ ቲቪ ጋር ባደረገው ቃለመጠየቅ አመልካች የሰራተኛውን ክብር የማይጠብቅ፣ ሕገ-ወጥ ፕሉሲ ተቀርጾ ሰራተኛ ላይ በደል እንደሚፈጸም፣ አመራሩ ከሕግ በላይ ነን የሚለና በማን አለበኝነት መንፈስ የሚመሩ ግለሶቦች ናቸው በማለት የተሳሳተ መረጃ ሰጥቷል። ፉደል ፕስት ከተባለ ማሕበራዊ ሚዱያና በናሁ ቲቪ ሕግን ያልተከተለ የውጭ ምደባ እንደሚደረግ፣ ምደባ በሥራ አፈጻጸም ሳይሆን ከአመራር ጋር ባለ ቀረቤታና ቁርኝት እንደሚፈጸም፣ የበረራ አስተናጋጆች ከቀረጥ ነጻ የሚያስገቧቸው ዔቃዎች ላይ ያልተገባ ድጋሜ ክፍያ እንደሚፈጸም በማለት ሀሰተኛ እና ስም የሚያጠፊ መረጃ ሰጥቷል። ጉዲዩም በዱሲፔሉን ኮሚቴ የታየ ሲሆን የሰራተኛ ማሕበሩ በአግባቡ ያልተደራጀና አድራሻው ስለማይታወቅ የሰራተኛ ማሕበር ተወካይ አልተገኙም። ስንብቱ በተጠሪ ጥፊት ምክንያት የተደረገ ስለሆነ ሕጋዊ ነው፤ ወደሥራ ሉመለስ አይገባም። የ21 ቀን ደመወዝና የ25 ቀናት ዓመት ዔረፍት ያልተከፈለው ክሉራንስ ባለማቅረቡ ነው ብሎል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የግራቀኙን ማስረጃ በመስማት፣ የተቀረጸውን ድምጽ በማዲመጥ ተጠሪ የአመልካች ድርጅት መሰረታዊ የሰራተኞች ማሕበር ምክትል ሉቀመንበር ስለመሆኑ ከኢፋዳሪ የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዲዩ ሚኒስቴር የተጻፈው ደብዲቤ ያስረዲል።
የሰራተኛ ማሕበሩ የሥራ አስፈጻሚ አባላት መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረጉት ስብሳባ ማሕበራቸውና የማሕበሩ አባላት ላይ በአመልካች ድርጅት እየደረሱ ነው የሚለትን ሕገ-ወጥ የመብት ጥሰቶች በተመለከተ የማሕበሩ ሉቀመንበር፣ ምክትል ሉቀመንበር(ተጠሪ) እና ምክትል ጸሐፉ ለተለያዩ የመንግስት አካላትና የሰራተኛ ጉዲይ ለሚመለከታቸው መንግስታዊ ላልሆኑ ማሕበራት በሰራተኛ ማሕበሩ ሥም መግለጫና ማብራራያ እንዱሰጡ በሚዱያ ጭምር ቃለምልልሶችን እንዱያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጡንና በዚህ መሰረት ተጠሪ ከናሁ ቲቪ፣ ፉደል ፕስት ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ በሰራተኛ ማሕበሩ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት የተፈጸመ እንጂ በግል ያላደረጉት ስለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ተረድቷል። አመልካች በሚዱያ የተሰጠው ማብራሪያ በጥቅለ አመልካችን የማይወክለና የአመልካች ድርጊት አይደለም ከማለት ባለፈ በተጨባጭ የተደረገው ቃለምልልስ ስህተት ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም። የቃለምልልሱ ሙለ ይዘት ሲታይም ተጠሪ የሚወክለውን ማሕበር አስመልክቶ አመልካች ላይ ያላቸውን ቅሬታ የማሳወቅና በአመልካች ድርጅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የመግለጽ እንጂ የአመልካች ደርጅትን መልካም ሥምና ተግባር የማጥፊት፣ የኢንደስትሪ ሰላም የሚያደፈርስ ድርጊት ሆኖ አልተገኘም። የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፋደሬሽን ለፍርድ ቤቱ በላከው ማስረጃ አመልካች የሰራተኛ ማሕበሩን እውቅና ያለመስጠት፣ የማሕበሩን አባላት ሆነ አመራሮች ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ማባረሩን፣ በማሕበሩ አሰራር ጣልቃ መግባት ላይ ቅሬታ ቀርቦ ተግባሩን እንዱያቆም የተጠየቀ ስለመሆኑ ገልጿል።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 26(2)(ለ) መሰረት ሰራተኛው በሰራተኛ ማሕበሩ አባል መሆኑ ወይም በማሕበሩ ሕጋዊ ተግባራት ተካፊይ መሆኑ ሰራተኛውን ከሥራ ለማሰናበት የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለመሆኑ ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ማስረጃ ሲመለከት በሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ/ም የተደረገው የሕብረት ሥምምነት አባሪ ክፍል አንድ ንዐስ ክፍል ሀ ተራ ቁጥር 3 ላይ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ መልካም ግንኙነት የሚያሻክር ከባድ ጥፊት መፈጸሙ ሆነ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ድንጋጌ መጣሱን የሚያስረዲ ሳይሆን ተጠሪ በምክትል ሉቀመንበርነት በሚመራው ማሕበርና በማሕበሩ አባላት ላይ ደርሰዋል ያለትን የመብት ጥሰቶችና ግድፈቶች የሚጠቁም ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተጠሪ የተሰናበተው የሰራተኛ ማሕበሩን በመወከል ባደረገው ሕጋዊ ተግባር እንጂ ያጠፊው ጥፊት የላለ በመሆኑ አመልካች የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 26(2)(ለ) በመጻረር ተጠሪን ከሥራ ማሰናበቱ ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት መሆኑን ያስገነዝባል። በተጨማሪም የዱሲፔሉን ኮሚቴው በሕብረት ሥምምነቱ በተመለከተው አግባብ የሰራተኛ ማሕበር ተወካዮች መሳተፍ ሲገባቸው ባልተገኙበት የውሳኔ ሃሳብ ማቅረቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ሳይከተል የተደረገ ሕገ-ወጥ ስንብት መሆኑን ያስረዲል። ስንብቱ ሕገወጥ ቢሆንም ተጠሪ ወደሥራ ቢመለስ በግራቀኙ መካከል የተካረረ እንጂ መልካምና ጤናማ ግንኙነት ላይኖር ይችላል በሚል ተጠሪ ወደሥራው ሉመለስ አይገባም ተብል ተወስኗል፤ ተጠሪ ካሣ፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የዓመት ዔረፍት ክፍያ እንዱከፈለውና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዱሰጠው በማለት ወስኗል።
ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀብል በማከራከር በሥር ፍርድ ቤት እንደተረጋገጠው ተጠሪ በግላቸው ያጠፈት ጥፊት የለም፤ ከስራ የተሰናበቱት በሰራተኛ ማሕበር አመራርነታቸው በሰጡት ቃለምልልስ ሲሆን ቃለምልልሱ ስህተት አለመሆኑም የተረጋገጠ በመሆኑ የሥራ ውለ ቢቀጥል ለኢንደስትሪ ሰላሙ ችግር የሚፈጥር አይደለም። የተጠሪ የሥራ መደብ የአውሮፔላን ጥገና ባለሞያ በመሆኑና የሥራ ውላቸው የተቋረጠው ከሥራ ተግባራቸው ጋር በተያያዘ ጥፊት ባለመሆኑ በግራቀኙ መካከል ያለው የሥራ መተማመን ላይ ችግር የሚያመጣ አይደለም። ተጠሪ ወደሥራ አለመመለሳቸው ግን የመደራጀትና መብትን የመጠየቅ ባሕል የሚያዲክምና ለወደፉት መልካም የኢንደስትሪ ግንኙነት እንዲይኖር ስለሚያደርግ ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዛቸው ተከፍሎቸው ወደሥራቸው ሉመለሱ ይገባል በማለት ሲወሰን አመልካች ያቀረበውን መስቀለኛ ተቃውሞ ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። አመልካች በተጠሪ ይግባኝ በተሻሻለው ውሳኔ ላይና የመስቀለኛ ተቃውሞ መሰረዙ ላይ በ25/12/2013 እና በ26/12/2013 ዓ/ም የተጻፈ ሁለት የተለያዩ የሰበር አቤቱታዎች በአንድ መዝገብ ላይ አቅርቦ የሰበር አጣሪ ችልት ተጠሪ ወደሥራ ይመለሱ ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ሰላማዊ የሆነ የሥራ አካባቢ ከመጠበቅ አንጻር ተገቢነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ በማዘዙ መልስ የቀረበ ቢሆንም ሰበር ሰሚ ችልቱ በአንድ መዝገብ የቀረበው ሁለት የሰበር አቤቱታ በተመለከተ በሥር ፍርድ ቤት ክርክሩ መነሻ አንድ መሆኑን፣ በአንድ የሰበር መዝገብ ላቀርብ የሚገባው አንድ የሰበር አቤቱታ በመሆኑና የአቀራረብ ስህተት ያለበት መሆኑ እንዱሁም ለተጠሪ የደረሰው ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ/ም የተጻፈው አንደኛው የሰበር አቤቱታ ብቻ መሆኑ የተጠሪን የመደመጥ መብት የሚጥስ መሆኑን በመገንዘብ የሰበር አቤቱታው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91(1) እና 329(2) መሰረት ተጠቃልና ተሻሽል እንዱቀርብ በመታዘዙ አመልካች በ11/06/2014 ዓ/ም የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም ተጠሪ የሰጠው ቃለምልልስ ሀሰተኛ መረጃ የሆነ፣ የአመልካች ስምና ዝና የሚጎዲ ተግባር ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። የአመልካች ደርጅት ሥራ ከፍተኛ ውድድር ያለበትና እምነት ዋጋ ያለበት ነው፤ የተጠሪ አድራጎት በደንበኞችና በሥራ አጋሮች እምነት ላይና በሥራው ላይ ጉዲት አምጥቷል። ተጠሪ የሰጠው ቃለምልልስ ሀሰተኛ ነው፤ እውነት ቢሆን እንኳን ድርጅቱን በመጉዲት ሃሳብ የተናገረው በወንጀልም የሚያስጠይቅ ጥፊት ነው። ድርጊቱ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 13(6)፣ 14(2)(ሀ) እና 27(1)(ሸ) እንዱሁም በሕብረት ሥምምነቱ መሰረት ከሥራ የሚያሰናብት ጥፊት ነው። ድርጊቱም የተፈጸመው በግል እንጂ በማሕበር ተወካይነቱ አይደለም፤ የሰራተኛ ማሕበሩ የጻፈውን ማስረጃ እንደማያስተባበል ማስረጃ አድርጎ መውሰደ ስህተት ነው። ተጠሪ ድርጊቱን የፈጸመው በማሕበር አመራርነት ቢሆን እንኳን ማሕበሩ ስለአባላቱ መብትና ጥቅም እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ አመልካች ላይ ጉዲት ማድረስ በሕጉ አልተፈቀደለትም። አመልካችን የሚጎዲ ሃሳብ መግለጽ ሕገ-መንግስታዊ መብት አይደለም። የሥራ ስንብቱ ሕጋዊ ነው። የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ቢባል እንኳን የፈጸመው ድርጊት ከአሰሪው ጋር ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነትና መተማመን ለማስቀጥል የማይቻል፣ የኢንደስትሪ ሰላምን የሚያመጣ ባለመሆኑና በ
በተሰጠው ትርጉም መሰረት ተጠሪ ወደሥራው ሉመለስ የማይገባ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው።
ተጠሪ ያቀረቡት መልስ የሰበር አቤቱታው የአቀራራብ ስህተት ያለበት፣ በተሻሻለው የሰበር አቤቱታ ሰበር አጣሪ ችልት የሕግ ስህተቱን ሳይለይ መልስ አቅርብ መባላ ሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም። በሀሰት የጠፊ ስምና ዝና የለም። ሀሰተኛ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። በማሕበር ተወካይነቴ የተደረገ ቃለምልልስ ነው። ማሕበሩን በመወከል ሃሳብ መግለጽ መብት ነው። ከሥራ መደቤና ሙያዬ ጋር የተያያዘ ጥፊት ፈጽመሃል ያልተባልኩ በመሆኑ ወደሥራ መመለሴ ተገቢ ነው። በ
የተሰጠው ውሳኔ ከተያዘው ጉዲይ ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ መሆን አለመሆኑን? ተጠሪ ወደሥራ እንዱመለሱ መወሰኑ ተገቢነቱን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ እንደመረመርነው ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ አመልካች ከሥራ አሰናብቶኛል በማለት ውዝፍ ደመወዝ በመክፈል ወደሥራ እንዱመልሳቸው፤ ይህ ካልሆነም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩለ ተጠሪ የአመልካች ተግባር ያልሆነውን ሀሰተኛ መረጃ በመገናኛ ብዙኋን በመግለጽ መልካም ስምና ዝናውን የሚያጎድፍ ተግባር በመፈጸማቸውና የንብረት ጥቅሙ ላይ ጉዲት በማድረሳቸው ምክንያት የሥራ ውላቸው የተቋረጠ ስለሆነ የሥራ ሥንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሥራ ውል የሚቋረጠው አንደኛው በሕግ ወይም በሥምምነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተዋዋይ ወገኖች አነሳሽነት ነው። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 24 በሕግ መሰረት ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ተዘርዝረዋል። የአዋጁ አንቀጽ 25 ደግሞ በሥምምነት ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ይገልጻል። በአሰሪው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔታ በአዋጁ ከአንቀጽ 26-30 በዝርዝር ተመልክቷል። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 31 እና 32 ደግሞ በሰራተኛው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበትን ሁኔታ ደንግጓል። የአዋጁ ድንጋጌ አንቀጽ 31 የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ለአሰሪው በመስጠት ሰራተኛው ውለን ማቋረጥ እንደሚችል የሚገልጽ ነው። ላላው በሰራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የሥራ ውል ማቋረጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 32(1)(ሀ እስከ ሐ) የተመለከተ ሲሆን በሕጉ የተዘረዘሩት ምክንያቶች አሰሪው የሰራተኛውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራል መንካቱ፣ በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር በሰራተኛው ላይ መፈጸም፣ ለሰራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት አደጋ ሉያደርስ የሚችል ምክንያት እያለ አሰሪው ተገቢውን እርምጃ ካልወሰደ ወይም ላላ አሰሪው ለሰራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዳታ በመደጋገም ካልፈጸመ ሰራተኛው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለን ማቋረጥ የሚችልበትን ሁኔታ አስቀምጧል። ከእነዚህ ማዔቀፍች ውጭ አሰሪው ሰራተኛን ከሥራ ሲያሰናብት ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት ይሆናል።
ሰራተኛ የአሰሪው ጥቅም ላይ ጉዲት የሚያደርስ ተግባር ከፈጸመ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብተው የሚችል ድርጊት ስለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ላይ ተመልክቷል። የአሰሪውን ሥም ማጥፊትም ሥራው ላይ ጉዲት ሉያደርስ የሚችል ድርጊት በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ ማዔቀፍ ላታይ የሚችል ነው። አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ በሰራተኛ ማሕበር አመራርነታቸው ሳይሆን በመገናኛ ብዙኋን በመጠቀም የአመልካች ድርጅት መልካም ስምና ዝና ላይ ሀሰተኛ የሥም ማጥፊት ዘመቻ የሚያካሂድ ቡድን ላይ ዋና ተዋናይ ሆነው አመልካች የሰራተኛውን ክብር የማይጠብቅ፣ ሕገ-ወጥ ፕሉሲ ተቀርጾ ሰራተኛ ላይ በደል እንደሚፈጸም፣ አመራሩ ከሕግ በላይ ነን የሚለና በማን አለበኝነት መንፈስ የሚመሩ ግለሶቦች ናቸው፣ ሕግን ያልተከተለ የውጭ ምደባ እንደሚደረግ፣ ምደባ በሥራ አፈጻጸም ሳይሆን ከአመራር ጋር ባለ ቀረቤታና ቁርኝት እንደሚፈጸም፣ የበረራ አስተናጋጆች ከቀረጥ ነጻ የሚያስገቧቸው ዔቃዎች ላይ ያልተገባ ድጋሜ ክፍያ እንደሚፈጸም በማለት ሀሰተኛ እና ስም የሚያጠፊ መረጃ ሰጥቷል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው በሰራተኞች ማሕበር ውስጥ በምክትል ሉቀመንበርነት ቦታ እየሰራሁ እያለ ማሕበሩን በመወከል የተገለጸ ነው፣ የአመልካችን ስም የሚያጎድፍ ሆነ የሰራተኛውን ሰላማዊ ግንኙነት የሚያጠፊ ተግባር ባልተፈጸመበት የተሳሳተ መረጃ ሰጥተሃል፣ ሰላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት እንዲይኖር አድርገሃል በማለት ከግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ማሰናበቱ ሕገ-ወጥ ስንብት ነው የሚል ነው።
የማስረዲት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዲው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን በመለየት፣ የማስረጃ ተገቢነት (relevancy test)፣ የማስረጃው ተቀባይነትን (admissibility) ደንቦችን መከተል እና ለማስረጃው የሚሰጠውን ክብደት (weight of evidence) በመለየት የመወሰን ኃላፉነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ኃላፉነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው። ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃ ለመመዘን ኃላፉነት የተሰጠው የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ በመስማትና ተጠሪ የሰጡትን ቃለምልልስ በመመልከት ተጠሪ ከናሁ ቲቪ፣ ፉደል ፕስት ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ በሰራተኛ ማሕበሩ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት የተፈጸመ እንጂ በግል ያደረጉት አይደለም፣ አመልካች በሚዱያ የተሰጠው ማብራሪያ በጥቅለ አመልካችን የማይወክለና አመልካች ድርጊት አይደለም ከማለት ባለፈ በተጨባጭ የተደረገው ቃለምልልስ ስህተት ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም፣ የቃለምልልሱ ሙለ ይዘት ሲታይም ተጠሪ የሚወክለውን ማሕበር አስመልክቶ አመልካች ላይ ያላቸውን ቅሬታ የማሳወቅና በአመልካች ድርጅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የመግለጽ እንጂ የአመልካች ደርጅትን መልካም ሥምና ተግባር የማጥፊት፣ የኢንደስትሪ ሰላም የሚያደፈርስ ድርጊት ሆኖ አልተገኘም ሲል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ሆነ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም። የሥር ፍርድ ቤት የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት የፈጸመ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት አያሳይም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት በሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ/ም በተደረገው የሕብረት ሥምምነት አባሪ ክፍል አንድ ንዐስ ክፍል ሀ ተራ ቁጥር 3 ላይ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ መልካም ግንኙነት የሚሻክር ከባድ ጥፊት መፈጸሙ ሆነ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ድንጋጌ መጣሱን የሚያስረዲ ሳይሆን ተጠሪ በምክትል ሉቀመንበርነት በሚመራው ማሕበርና በማሕበሩ አባላት ላይ ደርሰዋል ያለትን የመብት ጥሰቶችና ግድፈቶች በመግለጻቸው ከሥራ መሰናበታቸው ሆነ የዱሲፔሉን ኮሚቴው በሕብረት ሥምምነቱ በተመለከተው አግባብ የሰራተኛ ማሕበር ተወካዮች መሳተፍ ሲገባቸው ባልተገኙበት የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ አስፈላጊ ሂደቶችን ሳይከተል የተደረገው ውሳኔ ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት ነው በማለት መወሰኑ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም።
ወደሁለተኛው ጭብጥ ስንመለስ ተጠሪ ወደሥራቸው እንዱመለሱ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በሚል የቀረበውን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነው። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(1)(2) የሥራ ውለ ከሕግ ውጭ በአሰሪው የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደሥራው እንዱመለስ ሉወሰን እንደሚችል ተመልክቷል። ሰራተኛው ወደሥራ ሉመለስ የማይችለው ከሥራው ጠባይ ግንኙነት የተነሳ ወይም ከክርክር ሂደት ከወሰደው ግንዛቤ በሥራ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር ያስከትላል ተብል በፍርድ ቤቱ ሲታመን እንደሆነ የአዋጁ አንቀጽ 43(3) ላይ ተደንግጓል። ከፍተኛ ችግር የሚለው የሕጉ አነጋገር ማንኛውንም ዓይነት ጉዲት ሰራተኛውን ወደሥራው እንዲይመለስ ማድረግ የማይችል መሆኑን እና የሚያስከትለው ጉዲት ጉልህ የሆነ መሆን እንዲለበት ያሳያል። ይህም ሕግ አውጭው በአንድ በኩል የሥራ ዋስትና ማረጋገጥ ለሰራተኛው ሆነ ለሀገር መሰረት የሆነውን የሰራተኛውን ቤተሰብ መጠበቅ እንዲለበት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ሲያሳይ በልላ በኩል የሥራ ሁኔታውን እና የኢንደስትሪውን ሰላም ማስጠበቅ ለምርታማነት መሰረት መሆኑን በመገንዘብ በሁለቱ እሳቤዎች መካከል ጉዲዩ እንዱገዛ የፕሉሲ ውሳኔ ላይ መድረሱን እና ጉዲዩም የፍርድ ቤት ፍቅድ ሥልጣን መሆኑን ያስገነዝባል። ፍርድ ቤት ፍቅድ ሥልጣን ምክንያታዊ በሆነ አግባብ እንዱጠቀም ኃላፉነት ያለበት ሲሆን ግራቀኙ ተከራካሪዎችም በተለይም አሰሪው ፍርድ ቤቱን ለማሳመን ሰራተኛው ወደሥራ ቢመለስ የሚያስከትለውን ጉልህ የሆነ ጉዲት ማሳየት ይኖርበታል።
ተጠሪ በአመልካች ድርጅት የአውሮፔላን ጥገና ባለሙያ ሲሆኑ ከአመልካች አስተዲደር ጋር አለመግባባት መኖሩ ከሥራ ድርሻቸው አንጻር ወደሥራ መመለሳቸው አመልካች ላይ ጉልሕ ጉዲት የሚያስከትል መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው አስገዲጅ ትርጉም ሰራተኛው የጥበቃ ሰራተኛ መሆኑ እንዱሁም ከአለቆቹ ጋር በተለያየ ጊዜ ግጭት የሚፈጥር መሆኑና በእጁም ትጥቅ ያለ መሆኑ የሥራ ውለን ለማስቀጠል የማይቻል መሆኑን የሚያስረዲ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንዱሁም የአሰሪው ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዔከል ድርጅትን ጠቅላላ ንብረት ደህንነት የመጠበቅ ኃላፉነት ያለበት ሰው መሆኑን ግምት ወስጥ በማስገባት ወደሥራ ሉመለስ እንደማይገባ የተወሰነበት ነው። እንዱሁም በ
የተወሰነውም ገንዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ሰራተኛ መሆኑን በመገንዘብና ጥፊት ፈጽሟል የተባለው ከሥራ ኃለፉነቱ ጋር በተያያዘ በመሆኑ፤ ከአሰሪው ጋር ያለው መተማመን ከቀነስ ባለበት ኃላፉነት ወደሥራ መመለስ መልካም የሥራ ግንኙነት አይፈጥርም በሚል ነው። ተጠሪ ከሥራ ኃላፉነቱ ጋር የተያያዘ ጥፊት ፈጽሟል ያልተባለ በመሆኑና ቀደም ሲል በዚህ ችልት ከተወሰኑት ጉዲዮች ጋር የፍሬ ነገር ልዩነት ያለው ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ወደሥራ ቢመለሱ ሥራው ላይ የሚያደርሰዉ ከፍተኛ ጉዲትን አመልካች ያላሳየ ስለሆነ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተጠሪ ወደሥራ እንዱመለሱ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም ብለናል። በልላ በኩል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(5) መሰረት ተጠሪ ወደሥራው እንዱመለስ የተሰጠው ውሳኔ በዚህ ችልት ታይቶ የጸና በመሆኑ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደሥራ ሉመለሱ ይገባል ብለናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 12 እና 28 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ተጠሪ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደሥራ ሉመለሱ ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጸም አዘናል። ይጻፍ አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠ እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.