በሕብረት ሥምምነት መሰረት የሰራተኛ ተወካይ የሆነ ግለሰብ የማሕበሩ ተወካይ በመሆኑ በዚህ አመራርነት የመገናኛ ብዙኋንን በመቀጠም በማሕበሩ አባላት ላይ ደርሰዋል ያለትን የመብት ጥሰቶችና ግድፈቶች በመግለጽ ሰራተኛዉ በአጠቃላይ ችግሮች አለበት የሚል የተደረገ ቃለምልልስ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ መልካም ግንኙነት የማያሻክርና ከባድ ጥፊት ተፈጽሟል የማያስብልና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አቶ ተከስተ ካሴ ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ድንጋጌ ተጥሷል በሚል ለስራ ስንብት ምክንያት ላሆን የሚችል ስላለመሆኑ
No summary available.
ሰኔ 02 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ነፃነት ተገኝ አመልካች- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጠሪ- አቶ ተከስተ ካሴ መዝገቡ ተመርመሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ እ.አ.አ. ከቀን 22/04/2020 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 42,863.37 እየተከፈለኝ በአውሮፔላን ጥገና አሰልጣኝነት ሳገለግል ቆይቻለሁ። ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በተቋቋመው የሰራተኛ ማህበር ውስጥ ምክትል ፀኃፉ በመሆን እያገለገልኩ ቆይቻለሁ። ይሁን እንጂ አመልካች ስለእኔ እውነት ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ስም እና ዝናዬን አጥፍተሃል፣ ከላልች ሰራተኞች ጋር በስራ ቦታ መተባበር እና ሰላማዊ የስራ ግንኙነት እንዲይኖር አድርገሃል በማለት የስራ ውላን አቋርጦታል። ከስራ ስሰናበት በህብረት ስምምነቱ መሰረት በተቋቋመው ኮሚቴው ውስጥ የሰራተኛ ማህበር ተወካይ አልነበረም። ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብል ያልተከፈለኝ ደሞዝ ተከፍልኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ፤ ወደ ስራ ልመለስ የማልችልበት አግባብ ካለ ደግሞ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዝያ ወር ሙለ ደሞዝ፣ እ.አ.አ. የ2020 ዓ.ም የዓመት እረፍት ክፍያ እንዱከፍለኝ እና የስራ ልምድ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ ተጠሪን ከስራ ያሰናበትናቸው የሰራተኛ ማህበር አባል በመሆናቸው ሳይሆን የመገናኛ ብዙሀንን በመጠቀም በድርጅታችን መልካም ስም እና ዝና ላይ የስም ማጥፊት ዘመቻ በማካሄዲቸውና በስራ ቦታ ላይ ሉኖር የሚገባውን መልካም የስራ ግንኙነት እና መግባባት የሚያበላሽ ተግባር በመፈፀማቸው ነው፤ ለአብነት ያህል የኛ ቲዩብ ከተባለ ሚዱያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አመልካች ድርጅት ሰራተኛ ሲቀጥርም ሆነ ሲያሰናብት መርህ የለውም፣ የድርጅት ሰራተኞች ለድርጅቱ አመራሮች ብቻ ተገዢ እንዱሆኑ ነው የሚሰራው፤ ድርጅቱም ሆነ አመራሩ የሚያስበው ለውጪ ሃገር ዜጎች እንጂ ኢትዮጵያዊ ለሆነው ሰራተኛ አይደለም፤ የኮቪድ 19 ስርጭትን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰራተኞችን በመቅጣት በፍርሃትና በመርበትበት እንዱኖር እያደረገ ነው ሲለ ስም አጥፍተዋል፤ ይህ የተጠሪ ድርጊት ከስራ የሚያስናብት በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው፤ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው እንኳን ቢባል በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው መተማመን በእጅጉ የሻከረ በመሆኑ ተጠሪ ወደ ስራ ሉመለሱ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ የሰጡት ቃለ-ምልልስ የአመልካች ድርጅትን ስም የሚያጠፊ፣ መልካም ስምና ዝና የሚያጎድፍ ወይም የሚያጥላላ ሳይሆን ያላቸውን የመናገር ነፃነት ተጠቅመው ያደረጉት እንደሆነ ከይዘቱ መረዲት ተችሎል፤ አመልካች በዚህ ምክንያት ተጠሪን ከስራ ማሰናበቱ ህገ-ወጥ ስለሆነ ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደሞዝ ብር 257,174.22 ተከፍሎቸው ወደ ስራቸው ይመለሱ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 377 መሰረት ተሰርዞበታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 07/12/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው 08 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ማህበር ጣልቃ መግባትን የሚመለከተውን ክስ ከተጠሪ ስንብት ጥያቄ ጋር አጣምረው ማቅረባቸው ተገቢ ነው ማለቱ፤ ተጠሪ ቃለ-ምልልስ ያደረጉት በግላቸው ሳይሆን ማህበሩን ወክለው ነው መባለ፤ ቃለ-ምልልሱ የተጋነነ ቢሆንም ካለው ሁኔታ አንፃር እውነት መሆኑን መረዲት ይቻላል ሲል የስር ፍርድ ቤት በደፈናው ድምዲሜ ላይ መድረሱ፤ እንዱሁም ተጠሪ ወደ ስራ እንዱመለሱ ተብል የተሰጠው ውሳኔ የአመልካች እና የተጠሪን የሻከረ የስራ ግንኙነት ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተጠሪ ወደ ስራ ይመለሱ በማለት የተወሰነበት አግባብ መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት አመልካች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ በቀን 15/02/2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ ተጠሪ ንግግሩን ያደረጉት ከማህበሩ በተሰጣቸው ውክልና እንጂ በራሳቸው አይደለም፤
አመልካችም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 26 በመተላለፍ የሰጠው ስንብት አግባብ ባለመሆኑ የስር ፍርድ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ሲል ውሳኔ መስጠቱ በአግባቡ ነው፤ ተጠሪ በቃለ-ምልልስ ወቅት ያነሳኋቸው ጉዲዮች እውነት መሆናቸውን በማስረጃ ጭምር በስር ፍርድ ቤት አረጋግጫለሁ፤
ተጠሪ ያደረጉት እያንዲንደ እንቅስቃሴ ከማህበሩ በተሰጣቸው ውክልና ላይ የተመሰረተ ሲሆን በግላቸው ከአመልካች ጋር ምንም አይነት የሻከረ ግንኙነትም ሆነ መቃቃር በላለበት አመልካች የተበላሸ የስራ ግንኙነት ያለን በመሆኑ ወደ ስራ ሉመለስ አይገባም ማለቱ ተገቢ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀው ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው በሕግ አግባብ መሆን አለመሆኑን? ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመለሱ መወሰኑ ተገቢነቱን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ እንደመረመርነው ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ አመልካች ከሥራ አሰናብቶኛል በማለት ውዝፍ ደመወዝ በመክፈል ወደሥራ እንዱመልሳቸው፤ ይህ ካልሆነም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩለ ተጠሪ የአመልካች ተግባር ያልሆነውን ሀሰተኛ መረጃ በመገናኛ ብዙኋን በመግለጽ መልካም ስምና ዝናውን የሚያጎድፍ ተግባር በመፈጸማቸውና ንብረት ጥቅሙ ላይ ጉዲት በማድረሳቸው ምክንያት የሥራ ውላቸው የተቋረጠ ስለሆነ የሥራ ሥንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሥራ ውል የሚቋረጠው አንደኛው በሕግ ወይም በሥምምነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተዋዋይ ወገኖች አነሳሽነት ነው። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 24 በሕግ መሰረት ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ተዘርዝረዋል። የአዋጁ አንቀጽ 25 ደግሞ በሥምምነት ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ይገልጻል። በአሰሪው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበት ሁኔታ በአዋጁ ከአንቀጽ 26-30 በዝርዝር ተመልክቷል። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 31 እና 32 ደግሞ በሰራተኛው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበትን ሁኔታ ደንግጓል። የአዋጁ ድንጋጌ አንቀጽ 31 በአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ለአሰሪው በመስጠት ሰራተኛው ውለን ማቋረጥ እንደሚችል የሚገልጽ ነው። ላላው በሰራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የሥራ ውል ማቋረጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 32(1)(ሀ እስከ ሐ) የተመለከተ ሲሆን በሕጉ የተዘረዘሩት ምክንያቶች አሰሪው የሰራተኛውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራል መንካቱ፣ በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር በሰራተኛው ላይ መፈጸም፣ ለሰራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት አደጋ ሉያደርስ የሚችል ምክንያት እያለ አሰሪው ተገቢውን እርምጃ ካልወሰደ ወይም ላላ አሰሪው ለሰራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዳታ በመደጋገም ካልፈጸመ ሰራተኛው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለን ማቋረጥ የሚችልበትን ሁኔታ አስቀምጧል። ከእነዚህ ማዔቀፍች ውጭ አሰሪው ሰራተኛን ከሥራ ሲያሰናብት ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት ይሆናል።
ሰራተኛ የአሰሪው ጥቅም ላይ ጉዲት የሚያደርስ ተግባር ከፈጸመ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብተው የሚችል ድርጊት ስለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ላይ ተመልክቷል። የአሰሪውን ሥም ማጥፊትም ሥራው ላይ ጉዲት ሉያደርስ የሚችል ድርጊት በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ ማዔቀፍ ላታይ የሚችል ነው። አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ በሰራተኛ ማሕበር አመራርነታቸው ሳይሆን በመገናኛ ብዙኋን በመጠቀም የአመልካች ደርጅት መልካም ስምና ዝና ላይ ሀሰተኛ የሥም ማጥፊት ዘመቻ የሚያካሂድ ቡድን ላይ ዋና ተዋናይ ሆነው አመልካች የሰራተኛውን ክብር የማይጠበቅ፣ ሕገ-ወጥ ፕሉሲ ተቀርጾ ሰራተኛ ላይ በደል እንደሚፈጸም፣ አመራሩ ከሕግ በላይ ነን የሚለና በማን አለበኝነት መንፈስ የሚመሩ ግለሶቦች ናቸው፣ ሕግን ያልተከተለ የውጭ ምደባ እንደሚደረግ፣ ምደባ በሥራ አፈጻጸም ሳይሆን ከአመራር ጋር ባለ ቀረቤታና ቁርኝት እንደሚፈጸም፣ የበረራ አስተናጋጆች ከቀረጥ ነጻ የሚያስገቧቸው ዔቃዎች ላይ ያልተገባ ድጋሜ ክፍያ እንደሚፈጸም በማለት ሀሰተኛ እና ስም የሚያጠፊ መረጃ ሰጥቷል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው በሰራተኞች ማሕበር ውስጥ በምክትል ሉቀመንበርነት ቦታ እየሰራሁ እያለ ማሕበሩን በመወከል የተገለጸ ነው፣ የአመልካችን ስም የሚያጎድፍ ሆነ የሰራተኛውን ሰላማዊ ግንኙነት የሚያጠፊ ተግባር ባልተፈጸመበት የተሳሳተ መረጃ ሰጥተሃል፣ ሰላማዊ የሆነ የሥራ ግንኙነት እንዲይኖር አድርገሃል በማለት ከግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ማሰናበቱ ሕገ-ወጥ ስንብት ነው የሚል ነው።
የማስረዲት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዲው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን በመለየት፣ የማስረጃ ተገቢነት (relevancy test)፣ የማስረጃው ተቀባይነትን (admissibility) ደንቦችን መከተል እና ለማስረጃው የሚሰጠውን ክብደት (weight of evidence) በመለየት የመወሰን ኃላፉነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ኃላፉነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው። ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃ ለመመዘን ኃላፉነት የተሰጠው የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና ተጠሪ የሰጡትን ቃለምልልስ ሲዱዉን አስቀርቦ በመመልከት ተጠሪ ቃለ ምልልሱን ያደረጉት በሰራተኛ ማሕበሩ ተዋካይ በመሆናቸዉ እንጂ በግል ያደረጉት አይደለም፣ በተጨማሪም በሰዓቱ ተጠሪ ሲናገሩ የነበሩት በግላቸዉ ስለደረሰባቸዉ በደል ሳይሆን ሰራተኛዉ በአጠቃላይ ችግሮች አለበት የሚል ይዘት ያለዉ መሆኑን እና ተጠሪ በቃለ ምልልሱ የገለፃቸዉ ጉዲዮች አለመከሰታቸዉን አመልካች ያስረዲበት ሁኔታ አለመኖሩን፣ ተጠሪ በቃለ ምልልሱ የተናገሩት የግል አስተያየታቸዉ ነዉ ቢባል እንኳን የአመልካችን ድርጅት ስም የሚያጠፊ እና የሚያጥላላ ሳይሆን ተጠሪ ያላቸዉን የመናገር ነፃነት ተጠቅመዉ ያደረጉት እንደሆነ ከይዘቱ መረዲቱን ጠቅሶ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80(3) ሆነ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም። የሥር ፍርድ ቤት የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት የፈጸመ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት አያሳይም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት በሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ/ም በተደረገው የሕብረት ሥምምነት አባሪ ክፍል አንድ ንዐስ ክፍል ሀ ተራ ቁጥር 3 ላይ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ መልካም ግንኙነት የሚያሻክር ከባድ ጥፊት መፈጸሙ ሆነ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ድንጋጌ መጣሱን የሚያስረዲ ሳይሆን ተጠሪ የማሕበሩ ተወካይ በመሆናቸዉ በማሕበሩ አባላት ላይ ደርሰዋል ያለትን የመብት ጥሰቶችና ግድፈቶች በመግለጻቸው ከሥራ መሰናበታቸው ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት ነው በማለት መወሰኑ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም።
ወደ ሁለተኛው ጭብጥ ስንመለስ ተጠሪ ወደሥራቸው እንዱመለሱ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በሚል የቀረበውን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነው። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(1)(2) የሥራ ውለ ከሕግ ውጭ በአሰሪው የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደሥራው እንዱመለስ ሉወሰን እንደሚችል ተመልክቷል። ሰራተኛው ወደሥራ ሉመለስ የማይችለው ከሥራው ጠባይ ግንኙነት የተነሳ ወይም ከክርክር ሂደት ከወሰደው ግንዛቤ በሥራ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር ያስከትላል ተብል በፍርድ ቤቱ ሲታመን እንደሆነ የአዋጁ አንቀጽ 43(3) ላይ ተደንግጓል። ከፍተኛ ችግር የሚለው የሕጉ አነጋገር ማንኛውንም ዓይነት ጉዲት ሰራተኛውን ወደሥራው እንዲይመለስ ማድረግ የማይችል መሆኑን እና የሚያስከትለው ጉዲት ጉልህ የሆነ መሆን እንዲለበት ያሳያል። ይህም ሕግ አውጭው በአንድ በኩል የሥራ ዋስትና ማረጋገጥ ለሰራተኛው ሆነ ለሀገር መሰረት የሆነውን የሰራተኛውን ቤተሰብ መጠበቅ እንዲለበት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ሲያሳይ በልላ በኩል የሥራ ሁኔታውን እና የኢንደስትሪውን ሰላም ማስጠበቅ ለምርታማነት መሰረት መሆኑን በመገንዘብ በሁለቱ እሳቤዎች መካከል ጉዲዩ እንዱገዛ የፕሉሲ ውሳኔ ላይ መድረሱን እና ጉዲዩም የፍርድ ቤት ፍቅድ ሥልጣን መሆኑን ያስገነዝባል። ፍርድ ቤት ፍቅድ ሥልጣን ምክንያታዊ በሆነ አግባብ እንዱጠቀም ኃላፉነት ያለበት ሲሆን ግራቀኙ ተከራካሪዎችም በተለይም አሰሪው ፍርድ ቤቱን ለማሳመን ሰራተኛው ወደሥራ ቢመለስ የሚስከትለውን ጉልህ የሆነ ጉዲት ማሳየት ይኖርበታል።
ተጠሪ በአመልካች ድርጅት የአውሮፔላን ጥገና ባለሙያ ሲሆኑ ከአመልካች አስተዲደር ጋር አለመግባባት መኖሩ ከሥራ ድርሻቸው አንጻር ወደሥራ መመለሳቸው አመልካች ላይ ጉልሕ ጉዲት የሚያስከትል መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው አስገዲጅ ትርጉም ሰራተኛው የጥበቃ ሰራተኛ መሆኑ እንዱሁም ከአለቆቹ ጋር በተለያየ ጊዜ ግጭት የሚፈጥር መሆኑና በእጁም ትጥቅ ያለ መሆኑ የሥራ ውለን ለማስቀጠል የማይቻል መሆኑን የሚያስረዲ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንዱሁም የአሰሪው ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዔከል ድርጅትን ጠቅላላ ንብረት ደህንነት የመጠበቅ ኃላፉነት ያለበት ሰው መሆኑን ግምት ወስጥ በማስገባት ወደሥራ ሉመለስ እንደማይገባ የተወሰነበት ነው። እንዱሁም በ
የተወሰነውም ገንዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ሰራተኛ መሆኑን በመገንዘብና ጥፊት ፈጽሟል የተባለው ከሥራ ኃለፉነቱ ጋር በተያያዘ በመሆኑ፤ ከአሰሪው ጋር ያለው መተማመን ከቀነስ ባለበት ኃላፉነት ወደሥራ መመለስ መልካም የሥራ ግንኙነት አይፈጥርም በሚል ነው። ተጠሪ ከሥራ ኃላፉነቱ ጋር የተያያዘ ጥፊት ፈጽሟል ያልተባለ በመሆኑና ቀደም ሲል በዚህ ችልት ከተወሰኑት ጉዲዮች ጋር የፍሬ ነገር ልዩነት ያለው ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ወደሥራ ቢመለሱ ሥራው ላይ ያለው ከፍተኛ ጉዲትን አመልካች ያላሳየ ስለሆነ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተጠሪ ወደሥራ እንዱመለሱ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም ብለናል። በልላ በኩል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 43(5) መሰረት ተጠሪ ወደሥራው እንዱመለስ የተሰጠው ውሳኔ በዚህ ችልት ታይቶ የጸና በመሆኑ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደሥራ ሉመለሱ ይገባል ብለናል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ህዲር 13 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ላይ ሐምል 09 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ተጠሪ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደሥራ ሉመለሱ ይገባል በማለት ወስነናል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጥቅምት 03 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.