አንድ ሰራተኛ በራሱ ጥፊት በድርጅት ንብረት ላይ ከተሰወነ የገንዘብ መጠን በላይ ጉዲት ማድረሱ በዱስፔሉን ኮሚቴ ከተረጋገጠ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚሰናበት ስለመሆኑ በህብረት ስምምነት ላይ ተደንግጎ በዚህ መሰረት ጥፊት የተፈፀመ ቢሆንም ሰራተኛው ከስራ ሳይሰናበት በገንዘብ መቀጮ ከደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቀነሰ እንዱከፍል በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ከደመወዝ እየተቀነሰ ሉከፍል የሚገባዉ በህብረት ስምምነቱ ላይ በተገለፀው የገንዘብ መጠን ድረስ ያለዉን ጉዲት እንጂ ከተቀመጠዉ ጣሪያ በላይ ላሆን የማይገባና ከዚህ በላይ ለሆነዉ ገንዘብ ሉጠየቅ የሚገባዉ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦ ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት ክርክርና በማስረጃ ተጣርቶ ሲወስን ብቻ አቶ ጌታቸው ሀይለ እና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርትና ልጅስቲክስ አገልግልት ድርጅት
No summary available.
ቀን፤- 01/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ጌታቸው ሀይለ- ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፕርትና ልጅስቲክስ አገልግልት ድርጅት- ነ/ፈጅ ቤተልሄም ግርማ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የዱስፔሉን ዉሳኔ በመቃወም የቀረበ ክስ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ነዉ።የክሱ ይዘት ባጭሩ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በከባድ መኪና ሹፋር የስራ መደብ ተቀጥሬ በማገልገል ላይ ሳለሁ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እያሽከረከርኩ እያለ በጅቡቲ ውስጥ አርታ(ዊያ) በተባለ ቦታ የመልከዓ ምድሩ አቀማመጥ አስቸጋሪ ቁልቁለትና መታጠፉያ በሆነበት ቦታ ላላ መኪና ደርቦ የእኔን መስመር ይዞ በመምጣቱ አደጋውን ለመከላከል በድንገት ፍሬን ሲያዝ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን አደጋው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ ከጅቡቲ ሪፐብላክ የመንገድ ደህንነት የሰጠው የምርመራ ሪፕርት የሚያረጋግጥ ቢሆንም የተጠሪ ድርጅት የዱስፔሉን ኮሚቴ ከባለሙያ ሪፕርት ውጭ እና አመልካች ሃሳብ ባልሰጠሁበት ሁኔታ በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ ግምት ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑን የዚህን ግምት ዋጋ 3% ሂሳብ ከአመልካች ደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቀነሰ እንዱከፍል ውሳኔ አስተላልፍ ከሀምላ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተቆረጠ ይገኛል፣ በመሆኑም በተጠሪ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዲት በመድን ፕሉሲው ሽፊን መሰረት ንብረቱ ተጠግኖ እያለ ያለአግባብ የአደጋ ተጠያቂና ጥፊተኛ በማድረግ የተወሰነብኝ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዱነሳልኝ እና የአደጋው ግምት 3% እንዱከፍል የተወሰነብኝ ከህግ ውጭ ነው ተብል የተቆረጠውም እንዱመለስልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቆ ተጠሪ በበኩለ የፕሉስ ማስረጃ አመልካች አደጋውን ማስቀረት ወይም መቀነስ በሚችልበት ሁኔታ አደጋው የተከሰተ በመሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት እንደላለዉ፣አመልካች ለዱስፔሉን ክስ የጽሁፍ መልስ፣ ከፕሉስ ሪፕርት ጋር እንዱሁም ከህብረት ስምምነት ድንጋጌ ጋር በማጣራት የፈፀመው ጥፊት ከስራ የሚያሰናብተው ቢሆንም ያለፈ መልካም አገልግልት ግምት ውስጥ በማስገባት አመልካች ላይ የተወሰደው አስተዲደራዊ የቅጣት እርምጃ ተገቢ እና ህጋዊ በመሆኑ ሉነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ስራቸው ሹፋር እንደመሆኑ ከስራቸው ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባቸው ነገሮች አንደ መኪናውን የሚያሽከረክሩበትን አግባብ ከአካባቢው አየር ሁኔታ እና ከመልከዓ ምድሩ ጋር ባገናዘበ መልኩ መሆን ያለበት መሆኑን እና በጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ በዝግታና በጥንቃቄ ማሽከርከር የሚጠበቅበት ሙያዊ ግዳታ ነው፣ ስለዚህ በጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ላይ መነዲት ያለበት በ2ኛ እና በ3ኛ ማርሽ እንደሆነ በዚህ ማርሽ ከተነዲ ከፉት ለፉት አደጋ ቢመጣበትም የእጅ ፍሬን በመያዝ መኪናውን አደጋ ሳይደርስ በቀላለ ማቆም እንደሚችል አመልካችም ተጠሪም ያቀረባቸው ምስክሮች ያስረደ ሲሆን አመልካች ከጅቡቲ ፕሉስ የመንገድ ደህንነት የተፃፈው ሪፕርትም ከሳሽ ሲያሽከረከሩት የነበረው መኪና ወደ ቀኝ መውደቁን ከመግለጽ ባለፈ አደጋው የተከሰተበትን ምክንያት የሚያመላክት ባለመሆኑ እና አመልካች በቸልተኝነት ጉዲት አለማድረሳቸውን የሚያስተባብል ያቀረቡት ማስረጃ ባለመኖሩ ተጠሪ ድርጅት ንብረት ላይ የደረሰው ጉዲት በአመልካች ቸልተኝነት ነው በማለት፣ ቅጣቱን በተመለከተ በድርጅቱ ህብረት ስምምነት መሰረት በአመልካች ጥፊት በድርጅቱ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዲት ከስራ የሚያሰናብት ቢሆንም የቅጣት ማቅለያ በማድረግ 3% እንዱቀጡ መወሰኑ የሰራተኛውን ጥቅም ያስጠበቀ በመሆኑ ቅጣቱ የተወሰነው የህብረት ስምምነት አንቀጽ 31 (3) በሚፈቅደው መንገድ በመሆኑ ህጋዊ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበዉን ይግባኝ ፍ/ቤቱም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ግድፈት የለበትም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞበታል።
አመልካች ይህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤
በድርጅቱ ህብረት ስምምነት መሰረት ጥፊቱ ከ250,000 ብር በላይ መሆኑ ከስራ ማሰናበት እንጂ በገንዘብ እንዱቀጣ ማድረጉ የህግ ስህተት ነው፣ ተጠሪ ይህንን ያደረገው ለአመልካች በማሰብ ሳይሆን አደጋው መድረሱ ካወቀበት ከ06/12/2010 ዓ.ም እርምጃ እስከወሰደበት 28/09/2011 ዓ.ም ድረስ ከ30 ቀናት በላይ በመሆኑ ነው፣በተጨማሪም የጥገና ወጪው ብር 353,162.81 ሆኖ እያለ በተሽከርካሪው ላይ ያልደረሰውን ግምት ጨምሮ ገንዘብ ለማስከፈል የወሰነው ቅጣት ህግና የህብረት ስምምነት ተቃራኒ በመሆኑ የህግ ስህተት ተፈጽሟል።በህብረት ስምምነቱ የተፈቀደውን በመቃረን በሰዓት 40 ኪ/ሜ ስለማሽከርከር ማስረጃ ሳይቀርብ ማስረጃ እንደቀረበ ተደርጎ በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰው ጥገና ግምት እያለ እንዲልቀረበ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዘና መርህንና ተገቢውን የስራና ሰራተኛ ጥቅም ያገናዘበ መሆን አለመሆኑ ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ታዟል።
ተጠሪ ያቀረበው መልስ ባጭሩ የተጠሪ ንብረት የሆነው ከባድ ተሽከርካሪ በአመልካች ቸልተኝነት በመገልበጡ ምክንያት የደረሰው ጉዲት መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ የማስጠገኛ ግምት ከቀረበ በኋላ ፔርፍርማ ሲሰበሰብ ግን አስቀድሞ በቀረበው የዋጋ ግምት ተሽከርካሪው ለማስጠገን የማይቻል መሆኑን ተሽከርካሪውን ለማስጠገን በወቅቱ ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጣርቶ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ በአመልካች በኩል ግምቱ ከዚህ በታች ስለመሆኑ ያቀረበው ምንም ማስረጃ ባለመኖሩ የአመልካች ቅሬታ ተቀባይነት የለውም።በስር ፍ/ቤት የግራ ቀኛችን ምስክሮች ሲሰሙ በተጠሪ በኩል የቀረቡ ምስክሮች አመልካች አደጋው ባደረሱበት ወቅት በሰዓት 40 ኪ/ሜ ፍጥነት ሲያሽከረክሩ የነበሩ ስለመሆኑ አመልካች ራሳቸው ሞልተው የፈረሙት ወደ ኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተላከ ቅጽ በችልቱ ቀርቦ ተረጋግጧል።የቀረቡ ምስክሮችም አደጋው የደረሰበት ቦታ ላይ ፍጥነት በሰዓት ከ30 ኪ/ሜ በታች በማድረግ በከባድ ማርሽ ተጠቅሞ ቢያሽከረክር ማንኛውም አደጋ ቢፈጠር ያለምንም ችግር ተሽከርካሪ ማቆም እንደሚቻል እና በፍጥነት ላይ ከሆነ በድንገት ፍሬን ሲያዝ የመንሸራተት ወይም የመገልበጥ አደጋ ሉደርስ እንዱሚችል እና አደጋው የደረሰው በአመልካች ጥንቃቄ ጉድለትና ቸልተኝነት መሆኑን አስረድቷል።አመልካች አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን ያስረዲ ነገር የለም፣ ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ላይ የሰጠው ትርጉም የተከተለ በመሆኑ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ስህተት የለዉም።የዱስፔሉን የቅጣት እርምጃ በተመለከተ ጥፊቱ ከስራ የሚያሰናብት ቢሆንም ከዚህ በፉት የነበረው ፀባይ፣ የአግልግልት ጊዜና የቤተሰብ አስተዲዲሪነት ከግምት በማስገባት ቅጣቱን በመቀነስ የአደጋዉ ግምት ዋጋ 3% በየወሩ 1/3ኛ እየተቆረጠ እንዱከፍል ማድረጉ የሚነቀፍበት የህግ ምክንያት የለም ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብ ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበንዉ አመልካቹ የዱስፑሉን ዉሳኔዉ በመቃወም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረበዉ የተፈጸመዉ ጥፊት ከባድ ነዉ ከተባለ ከስራ ማሰናበት እንጂ ይህንን ያህል ገንዘብ ቅጣት እንዱከፍል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ አይደለም በሚል ዉሳኔዉ በፍርድ ቤት እንዱታረም ነዉ።ተጠሪም በበኩለ በአመልካች ቸልተኝነት የደረሰዉ ጉዲት ከባድ በመሆኑና ጥፊቱ ከስራ የሚያሰናብት መሆኑን ነገር ግን አመልካች የሰጠዉ የረጅም ጊዜ አገልግልት እና የነበረዉ መልካም ባህርይ ከግምት በማስገባት ከስራ ከማሰናበት በመለስ ያለዉ ቅጣት እንደተወሰነበት እና ይህም ለአመልካች ጥቅም ተብል የተደረገ ስለመሆኑ ተከራክሯል።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ ለስራው የተሰጡትን መሣሪያዎችና እቃዎች ሁለ በጥንቃቄ የመጠበቅ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀጽ 13/3/ ስር የተመለከተ ሲሆን በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረስ ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 27/1/ሸ/ ድንጋጌ ያሣያል።ሆኖም ከባድ ቸልተኝነት የሚለውን ቃል መለኪያ በተመለከተ ህጉ በግልጽ አያሣይም።ይሁን እንጂ ቸልተኝነት የጥንቃቄ ጉድለት እንደመሆኑ መጠን የጥንቃቄ ዓይነትና ደረጃ እንደየድርጊቱና አድራጊው የስራ ድርሻ አኳያ በመመልከት ምላሽ ማግኘት እንደሚገባ ይህ ችልት በሰ/መ/ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።በተያዘዉ ጉዲይ ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ላይ በተመጣጣነ ማርሽ አስሮ ባለማሽከርከሩ አደጋው መድረሱ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ አመልካች ማስተባበያ ማስረጃ ያላቀረበበት ጉዲይ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ጉዲቱ ሉደረስ የቻለዉ በአመልካች ቸልተኝነት ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።በመሆኑም የአመልካች የጥፊት ደረጃ "ከባድ ቸልተኝነትን" ሉያቋቁም የሚችል መሆን አለመሆኑን ከስራው ባህርይ አንፃር መመልከት እና የቀረበዉን ማስረጃ በማመዛዘን በቁልቁለት መንገድ ላይ በከባድ ማረሽ ማሽከርከር እየተገባዉ በቀላል ማርሽ በሰዓት በ40 ኪ.ሜ ፍጥነት በማሽከርከር ጉዲት እንዱደረስ ስለማድረጉ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ጉዲይ በመሆኑ ይህንኑ ከመቀበል አልፍ ይህ ሰበር ችልት የፍሬ ነገር ጉዲይ የመመርመር ሃላፉነት የለበትም።በዚህም ምክንያት የድርጅቱ ንብረት ላይ የደረሰዉን ጉዲት ለማስጠገን ብር 2,820,778.92 የተገመተ ስለመሆኑ ከመድን ድርጅት የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት በማድረግ አመልካች አስተዲደራዊ ዉሳኔ መስጠቱን ከክርክሩ ተገንዝበናል።በልላ በኩል የጉዲቱን ለማስተካካል ወይም ለማስጠገን መጀመሪያ የቀረበዉ ግምት ብር 353,162.81 ስለመሆኑ አመልካች ያቀረበዉ ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያላገኘ ቢሆንም በህብረት ስምምነት ከተመለከተዉ ጣሪያ በላይ በመሆኑ የመጠን ጉዲይ መመርመር አስፈላጊ አይደለም።ስራ ላይ ባለዉ የድርጅቱ የህብረት ስምምነት አንቀጽ 33/1/ ተራ ቁጥር 24 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የከባድ መኪና አሽከርካሪ በራሱ ጥፊት በድርጅቱ ንብረት ላይ ከብር 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ/ በላይ ጉዲት ማድረሱ በዱስፔሉን ኮሚቴ ከተረጋገጠ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚሰናበት ስለመሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካደት ከመሆኑም በተጨማሪ በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ የተገለጸ ጉዲይ ነዉ።ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካች ጥፊት በቀጥታ ከስራ ለማስናበት የሚያበቃ መሆኑ አከራካሪ አይደለም።አመልካችም አጥብቆ የሚከራከረዉ ጥፊቱ ለስንበት የሚያበቃ ነዉ ከተባለ ተጠሪ ከስራ ሉያሰናብተኝ ሲገባዉ በገንዘብ መቅጣቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት ነዉ።
በዚህ ረገድ የዱስፔሉን ኮሜቲ የቅጣት ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ የድርጅቱን የህብረት ስምምነት አንቀጽ 33.3 ተራ ቁጥር 33.3.6 ሲሆን በዚህም መሰረት የከባድ መኪና ሾፈር ከብር 100,000 እስከ 200,000 ድረስ ለሚደርስ አደጋ ለመጀመሪያ ጥፊት ሲሆን ሰራተኛዉ የጉዲቱን ግምት ዋጋ 3% በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ እንዱከፍል የሚደነግግ መሆኑን መሰረት በማድረግ የአመልካችን የቀደመ መልካም ባህርይና አገልግልት ታሳቢ በማድረግ እንዱሁም የድርጊቱን ከባቢያዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ቅጣቱ ቀል እንዱወሰን የተደረገ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል።ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ ምንም እንኳን አመልካች ያደረሰዉ ጉዲት ከፍተኛ ቢሆንም የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተጠቅመዉ ለአነስተኛ ጉዲት ተብል በተገመተዉ ወሰን ዉስጥ ቅጣት መወሰኑ ሲታይ በአንድ በኩል ሰራተኛዉን በስራ ላይ በማቆየት የሥራ ዋስትናዉን ማስከበር በልላ በኩል ለደረሰዉ ጉዲት ደግሞ በህብረት ስምምነት የተቀመጠዉን ገንዘብ እንዱከፍል በማድረግ የሁለቱንም ወገን ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።በዚህ አግባብ ቅጣቱ ቀል መወሰኑ ከቅጣት ዓላማ አንጻር ሲታይ ስህተት ነዉ የሚያሰኝ ባይሆንም የገንዘብ መጠኑ ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ አመልካች ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ከደመወዙ እንዱቆረጥ የሚያደርግ ዉሳኔ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ ግን በኑሮዉ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጠር መሆኑን መገምት አዲጋች አይሆንም።ከላይ የተጠቀሰዉ የድርጅቱ የህብረት ስምምነት ድንጋጌ የገንዘብ መጠኑን እስከ ብር 200,000 ድረስ ሲገድብ ታሳቢ ያደረገዉም የደረሰዉ ጉዲት መጠን ከዚያ በላይ ሲሆን ጥፊቱ ከባድ ስለሚሆን ሰራተኛዉን ከስራ በማሰናበት ለደረሰዉ ጉዲት ግን በህግ አግባብ መጠየቅ የሚቻልበትን ሁኔታ መኖሩን ከግምት ያስገባ ነዉ።
ይሁንና የዱስፔሉን ኮሚቴ ዉሳኔ የሁለቱንም ወገን ጥቅም በማመዛን የተወሰነ ነዉ የሚባል ከሆነ አመልካች ከደመወዙ እየተቀነሰ ሉከፍል የሚገባዉ በህብረት ስምምነት አንቀጽ 33.3.6 መሰረት እስከ ብር 200,000 ድረስ ያለዉን ጉዲት እንጂ ከተቀመጠዉ ጣሪያ በላይ ላሆን አይገባም።ከዚህ በላይ ለሆነዉ ገንዘብ ሉጠየቅ የሚገባዉ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት የፍትሒብሄር ክስ ቀርቦ ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት ክርክርና በማስረጃ ተጣርቶ ሲወስንበት ብቻ ይሆናል።ጉዲዩ ከዚህ አኳያ ሲታይ አስተዲደራዊ ዉሳኔዉ አስቀድሞ በህብረት ስምምነት ያልተደነነገዉን ሁኔታ እና በሰራተኛዉ ላይ ከፍተኛ ጫና በሚፈጥር አግባብ ይልቁንም ተጠሪን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዉሳኔ በመሆኑ የህግ መሰረት የላለዉና ፍትሃዊነትም የጎደለዉ ሆኖ አግኝተናል።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች የዱስፔሉን ኮሚቴ ዉሳኔ ተገቢነትና ፍትሃዊነት ሲመረምሩ ቅጣቱ ቀል መወሰኑ በመርህ ደረጃ ለሰራተኛዉ ጥቅም ነዉ የሚለዉን መሰረት በማድረግ ዉሳኔዉን ማጽናታቸዉ ተገቢ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ በህብረት ስምምነት ከተመለከተዉ ጣሪያ ወሰን ማለፍ አለማለፈን ሳያረጋገጡና ጉዲቱንም ሳያመዛዝኑ ስራ ላይ ያለዉን የህብረት ስምምነታቸዉን ዓላማ እና ይዘት ያገናዘበ ባለመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል። በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/በዚህ ጉዲይ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተላቸው በመ/ቁ/75575 ላይ የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/የተጠሪ መ/ቤት በአመልካች ላይ ያስተላለፈዉ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ተሻሽል ተከታዩ ተወስኗል።
ሀ/አመልካች በከባድ ቸልተኝነት በተጠሪ ንብረት ላይ ላደረሰዉ ጉዲት ጥፊተኛ መባለ ተገቢ ነዉ ብለናል።
ለ/በአመልካች ጥፊት ምክንያት በተጠሪ ንብረት ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ማስጠገኛ የወጣዉን ወጪ ብር 2,820,778.92 ዉስጥ 3% በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ አመልካች እንዱከፍል በዱስፔሉን ኮሚቴ የተሰጠዉ ዉሳኔ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት አንቀጽ 33.3 ተራ ቁጥር 33.3.6 መሰረት ተሻሽል ብር 200,000 ድረስ ያለዉን ብቻ 3% በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ እንዱከፍል በማለት ወስነናል።
ሐ/ለአመልካች የተሰጠዉ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ላይ ስህተት ባለመኖሩ ጸንቷል።
መ/አመልካች ያደረሰዉ ጉዲት መጠን (ግምት) በፉደል ለ ላይ ከተጠቀሰዉ መጠን በላይ ነዉ የሚል ከሆነ ተጠሪ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብቱን ይህ ዉሳኔ የሚገድብ አይደለም ብለናል።
3ኛ/በዚሁ ዉሳኔ መሰረት እንዱፈጸም ለሚመለከተዉ ክፍል ይተላለፍ።ይጻፍ።
4ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፤
No topics extracted.