በመርህ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈለዉ በስራ ገበታዉ ላይ ተገኝቶ ተገቢዉን አገልግልት ለሰጠ የመንግስት ሰራተኛ በመሆኑ እና ስራ ሳይሰራ ደመወዝ የሚከፈለዉ በህግ የተመለከተ ድንጋጌ ሲኖር ብቻ እና ይህም ለመርሁ ልዩ ሁኔታ በመሆኑ በጠባቡ መተርጎም የሚገባዉ ሲሆን በወንጀል ተጠርጠሮ ጉዲዩ በፍርድ ሂደት ላይ የነበረና በእስር ምክንያት በስራ ገበታዉ ላይ ላልተገኘ ሰራተኛ መስሪያ ቤቱ ደመወዝ ለመክፈል የሚገደድ ጉለላ የዔፅዋት ማዔከል፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፏብሉክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት እና አቶ ተስፊዬ ገ/ፃዱቅ የፍደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 36 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች
No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች:-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ የመንግስት ሰራተኛ ከክሱ ነፃ ሆኖ ወደ ስራዉ ከተመለሰ በኋላ ከደመወዝ ጋር በተያያዘ የሚኖረዉን ህጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ።
ክርክሩ በተጀመረበት በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ በ1ኛ አመልካች መስሪያ ቤት ውስጥ ክፍያ እና ሂሳብ ደጋፉ የስራ ሂደት መሪ በመሆን ሳገለግል የቆየሁ ሲሆን በማዔከለ ከስራዬ ጋር በተያያዘ ችግር ተፈጥሯል በሚል ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቶብኝ ከህዲር 21 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ሐምል 15 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በእስር ላይ ቆይቼ ከክሱ በነፃ ተሰናብቻለሁ። ነፃ ከተባልኩበት ጊዜ አንስቶ አሰሪዬ የነበረው 1ኛ አመልካች ወደ ስራ እንዱመልሰኝ እና ያልተከፈለኝ ደመወዝ እንዱከፍለኝ ብጠይቅም ቦታ ስለላለ 2ኛ ተጠሪ ምደባ ይስጥህ በማለት ደብዲቤ ጽፍልኛል። በዚሁም መሰረት 2ኛ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ውስጥ ከነሐሴ 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ምደባ እንዱሰጠኝ ደብዲቤ የፃፈልኝ ሲሆን ቢሮውም ፍቃደኛ በመሆን ክሉራንስ እንዲመጣ ጠይቆኝ 1ኛ ተጠሪ እንዱሰጠኝ በተደጋጋሚ ብጠይቀው ፍቃደኛ ሳይሆን ቆይቶ ከሁለት ወር በኋላ ያልተሟላ ክሉራንስ ሰጥቶኛል። የሰጠኝ ክሉራንስ ላይ የተገለፀው የደመወዝ መጠን በቀድሞው መሰረት ሲሆን መንግስት ለመደቡ ያደረገውን ጭማሪ ታሳቢ ያደረገ አይደለም። ጭማሪ ከመደረጉ በፉት እኔ ይሰራበት የነበረው መደብ ፔሳ 8 ደመወዙም ብር 6,547.00 ሲሆን ከጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም ወደ ብር 8236.00 እንዱሁም ከሐምል ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ወደ ብር 9,177.00 አድጓል። 1ኛ አመልካች በዚህ አግባብ ደብዲቤውን ለአዱሱ መስሪያ ቤት መፃፍ እያለበት ባለመፃፈ አገኝ የነበረው ጥቅም ቀርቶብኛል።
ስለሆነም ደብዲቤውን አስተካክል እንዱጽፍልኝ፣ 1ኛ ተጠሪ ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም ወር 2012 ዓ.ም ድረስ ያለውን ደመወዜን መንግስት በየጊዜው ያደረገውን ማሻሻያ ታሳቢ በማድረግ በጠቅላላው ብር 283,273.00 እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ አመልካች በበኩለ በሰጠው መልስ ተጠሪ በስሩ ይሰራ የነበረ ሰራተኛ መሆኑን፣ በመሀልም በወንጀል ተጠርጥሮ ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ምክንያት የስራ ውለ ተቋርጧል። ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ስራው መመለስ ቢችልም በመታሰሩ ምክንያት የተቋረጠበት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ግን ሉከፈለው አይገባም። በልላ መስሪያ ቤት በመመደቡ ምክንያትም በ1ኛ አመልካች መስሪያ ቤት ውስጥ ሲሰራ የነበረውን የስራ ዓይነትና ሲከፈለው የነበረውን የደመወዝ መጠን በአግባቡ በመግለጽ በቀን 19/01/2012 ዓ.ም የተሰጠው በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪም አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበለት አስተዲደራዊ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ የታሰረው ከስራው ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጥሮ በመሆኑ ከክሱ ነፃ ከተባለ በመታሰሩ ምክንያት የተቋረጠበት ደመወዝ ሉከፈለው ይገባል፤ የሚከፈለው በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ያገኝ በነበረው የደመወዝ መጠን እንጂ እስር ላይ እያለ መንግስት ለመደቡ ባደረገው ማሻሻያ መሰረት አይደለም በማለት ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከክሱ ነፃ እስከ ተባለበት ጊዜ ድረስ በወር ብር 6,547.00 ተባዝቶ እንዱከፈለው፤ ክሉራንሱም ይኸው የደመወዝ መጠን ተጠቅሶ ይሰጠው በማለት ወስኗል።
አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት በቅደም ተከተል ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች በቀን 27/05/2013 ዓ.ም በተፃፈ 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽሟል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ የአመልካች የደመወዝ ጥያቄ ስድስት ወር ካለፈ በኃላ የቀረበ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል በማለት ያቀረብነው መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ፤ አመልካች ከስራው ሲቀር ለ1ኛ አመልካች ያላሳወቀ ሲሆን በስራው ላይ ላልነበረና የስራ ውለ ለተቋረጠበት ሰራተኛ ደመወዝ እንድንከፍል መወሰኑ፤ አመልካች በተጠረጠረበት ወንጀል ነፃ ተብል ቢሰናበትም ሉመደብ የሚችለው ክፍት መደብ ሲኖር ብቻ ሲሆን 1ኛ አመልካች ጋር ተጠሪ የነበረበት መደብ በመያዙ በ2ኛ ተጠሪ በኩል ምደባ እንዱሰጠው ተደርጎ የስራ ውል ግንኙነቱ ለተቋረጠ ግለሰብ ውዝፍ ደመወዝ ክፈለ መባለ ከዚህ ቀደም ይህ ሰበር ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በአመልካች የቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ እና የውዝፍ ክፍያ ክርክር ውድቅ ሆኖ የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 56/2010 አንቀፅ 73(5) እና 86(1)(2) አንፃር መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጎ በቀን 06/07/2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረት ተገቢውን ክፍያ ለአመልካች ከፈፀሙ እና ጉዲዩ ካበቃ በኋላ የሰበር አቤቱታ ማቅረባቸው ተገቢነት የለውም፤ የይርጋ መቃወሚያውን በሚመለከት የተጠሪ ጉዲይ በአዋጁ የይርጋ ድንጋጌ ስር የሚጠቃለል አይደለም፤ የይርጋ ድንጋጌው ተፈፃሚነት አለው እንኳን ቢባል ለዚህን ያህል ጊዜ የታሰርኩትና ተዘዋውሮ የመስራት ነፃነቴ የተገደበው በ1ኛ አመልካች ምክንያት በመሆኑ የክፍያ ጥያቄው በይርጋ ሉታገድ አይገባም፤ የይርጋ ጊዜውም ሉቆጠር የሚገባው ከተከሰስኩበት ጉዲይ በነፃ ከተሰናበትኩበት ጊዜ አንስቶ በመሆኑ አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከርክሯል። አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ተጠሪ ላልሰራበት ደመወዝ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱከፈለዉ የመወሰኑን አግባብነት በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበዉ አቤቱታ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ከቆየ በኋላ በነፃ ተሰናብቶ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ምደባ የተሰጠዉ ቢሆንም ከምደባዉ በፉት ለነበሩት ጊዜያት 1ኛ አመልካች ደመወዙን በተለያዩ ጊዜያት ሲደረጉ ከነበሩት ጭማሪዎች ጋር ለመክፈል ፍቃደኛ ያለመሆኑን ነዉ። የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤትም ተጠሪ ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ነፃ እስከወጡበት ሐምል 15 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ያለዉ ሉከፈለዉ ይገባል በሚል የወሰነ ሲሆን የአመልካቾች መሰረታዊ የቅሬታ ነጥብም ተጠሪ ላልሰራበት ስራ ደመወዝ ሉከፈለዉ አይገባም የሚል ነዉ።
በመሰረቱ ደመወዝ የሚከፈለዉ ለተሰራ ስራ በአሰሪዉ አካል የሚከፈል የድካም ዋጋ በመሆኑ አንድ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈለዉ በመስሪያ ቤቱ በስራ ላይ ሆኖ በተመደበበት ስራ ለሰጠዉ አገልግልት መሆኑ እሙን ነዉ። ይህ መሰረታዊ መርህ ሲሆን በስራ ላይ ባልነበረበት ጊዜ ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈለዉ በህግ በልዩ ሁኔታ የተመለከተ ግልጽ ድንጋጌ ሲኖር ብቻ መሆኑንም ልብ ማለት ያስፈልጋል። በመሆኑም አንድ የመንግስት ሰራተኛ በስራ ላይ ባልነበረበት ጊዜ የሚያቀርበዉ የደመወዝ ይገባኛል ጥያቄ መርምሮ ዉሳኔ በመስጠት ረገድ አመልካች ስራ ሳይሰራ ደመወዝ ሉከፈለዉ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ ማየቱ ግድ ይላል። በዚህ ረገድ የፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በክፍል አራት ስር የስራ ሰዓት እና ፍቃድ የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን አንድ ሰራተኛ ስራ ሳይሰራ ደመወዝ ሉከፈለዉ የሚችለዉ ሰራተኛዉ ከስራዉ የቀረዉ በህዝብ በዓላት እና በሳምንት እረፍት ምክንያት፣ በዓመት እረፍት ፍቃድ ምክንያት፣ በወሉድ ፉቃድ ምክንያት፣ በህመም ፈቃድ ምክንያት፣ ለግል ጉዲይ በሚሰጥ ልዩ ፈቃድ ምክንያት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ በዚህ ክፍል በአንቀጽ 36 እና ተከታዮቹ ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉጪ በስራ ላይ ላልተገኘ ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈለዉ ስለመሆኑ አዋጁ አይደነግግም። በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምል ወር 2011 ዓ.ም ድረስ ከስራ ላይ የቀረዉ በወንጀል ተጠርጥሮ ጉዲዩ በፍርድ ሂደት ላይ የነበረ በመሆኑ ምክንያት ቢሆንም በዚህ እና በመሰል ሁኔታዎች ምክንያት ሰራተኛዉ ከስራ የቀረ እንደሆነ በስራዉ ላይ ባይገኝም መስሪያ ቤቱ ደመወዝ የመክፈል ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ አዋጁ በተለይ አይደነግግም። በመርህ ደረጃ ደመወዝ የሚከፈለዉ በስራ ገበታዉ ላይ ተገኝቶ ተገቢዉን አገልግልት ለሰጠ የመንግስት ሰራተኛ በመሆኑ እና ስራ ሳይሰራ ደመወዝ የሚከፈለዉ በአዋጁ የተመለከተ ድንጋጌ ሲኖር ብቻ መሆኑ እና ይህም ለመርሁ ልዩ ሁኔታ በመሆኑ በጠባቡ መተርጎም የሚገባዉ ሲሆን በእስር ምክንያት በስራ ገበታዉ ላይ ላልተገኘ ሰራተኛ መስሪያ ቤቱ ደመወዝ ለመክፈል የሚገደድበት ህጋዊ ምክንያት የለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ አስተዲደር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከዚህ አንፃር ማየት ሲገባዉ ተጠሪ በመታሰሩ ምክንያት በስራ ገበታዉ ላይ ተገኝቶ ለመስሪያ ቤቱ ተገቢዉን አገልግልት ባልሰጠበት ሁኔታ አመልካቾች ከታህሳስ ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምል 2011 ዓ.ም ድረስ ያለዉን ደመወዙን ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ እና በየደረጃዉ ያለ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ችልቶችም ይህንን አለማረማቸዉ ሰራተኛዉ በስራ ገበታዉ ላይ ሳይገኝ ደመወዝ ሉከፈል የሚችልባቸዉን ልዩ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የፋዳራል የመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ላይ የተመለከተዉን እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከላይ በተመለከተዉ መዝገብ ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በልላ በኩል ተጠሪ ባቀረበዉ አቤቱታ 1ኛ አመልካች ደብዲቤ በተገቢዉ ሁኔታ ሳይጽፍለት በመቅረቱ ምክንያት ለሁለት ወራት ያህል ደመወዝ ሳያገኝ መቅረቱን ጠቅሶ ተከራክሯል። የሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤቱ አመልካቾች ተጠሪ ያልሰራበትን ዉዝፍ ደመወዝ አመልካቾች የመከፈል ኃላፉነት አለባቸዉ የሚል አቋም በመያዙ ምክንያት 1ኛ አመልካች ደብዲቤዉን በተገቢዉ ሁኔታ ባለመፃፈ ምክንያት ተጠሪ አጥቻለሁ ያለዉን የሁለት ወር ደመወዝ 1ኛ አመልካች ኃላፉነት ያለበት መሆን ያለመሆኑን በተለይ መርምሮ ዉሳኔ አልሰጠበትም። ይሁንና በዚህ ረገድ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ከዉዝፍ ደመወዝ ክፍያ በተጨማሪ 1ኛ አመልካች ከደብዲቤ አፃፃፍ ጋር በተያያዘ በፈጸመዉ ጥፊት ለደረሰበት ጉዲት የሁለት ወር ደመወዝ ሉከፈለኝ ይገባል የሚል ይዘት ያለዉ በመሆኑ ተጣርቶ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤት በአ/መ/ቁጥር 1377/12 በቀን 16/06/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 30/03/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ፣ እንዱሁም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 27/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ሉከፈለዉ የሚገባዉን ደመወዝ አመልካቾች የመክፈል ኃላፉነት የለባቸዉም ተብል ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ተገቢዉን አሟልቶ ደብዲቤ አለመጻፈንና በዚህም ምክንያት 1ኛ አመልካች የሁለት ወር ደመወዝ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆን ያለመሆኑን ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር አጣርቶ ተገቢዉን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 12/06/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ሄ/መ