ተደራራቢ ወንጀልች በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ (ሀሳባዊ መደራረብ) ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ጊዜያት የተፈፀሙ ድርጊቶችን (ቁሳዊ መደራረብ) የሚመለከቱ ሲሆኑ መደጋገም የቁሳዊ መደራረብ መለያ ባህሪ በመሆኑ ተመሳሳይ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜያት ቢፈፀሙ ወይም የተለያዩ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜ ተፈፅመው ቢገኙ ቁሳዊ መደራረብ አለ ለማለት የሚቻል ሲሆን፣ በአንድ ነጠላ ድርጊት ከአንድ በላይ የሆኑ ወንጀልች መፈፀማቸው የሀሳባዊ መደራረብ መለያ ባህሪ ስለመሆኑ የወ/ህ/አ.60(ሀ)እና(ለ) በተደራራቢ ክሶች ፍ/ቤት በወ/ሕ/አ/577/3/ ድንጋጌ መሰረት የአምባጓሮ ወንጀል ተፈጽሟል ብል ያመነ ከሆነ ዐቃቤ ሕግ የወ/ሕ/አ/539/1/ሀ/ ተጠቅሶ በዛው በተፈጠረ አምባጓሮ ድርጊት ምክንያት ሰው የሞተ መሆኑን በመጥቀስ ተከሳሽ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበውን ክስ ድርጊቱ የተደራራቢ ወንጀልን መስፈርት የማያሟላ መሆኑን በመረዲት 2ኛው ክስ በ1ኛው ክስ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ብል መወሰንና ታሪኩ ኬድ ኬሪ እና የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወንጀል የመስራት ሃሣብ የተፈፀመን ድርጊት ወንጀል እንደተደራረበ አድርጏ ተከሳሽ በ2ኛው ክስ ጥፊተኛ የሚባል ስላለመሆኑ
No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር ብርሃኑ መንግስቱ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- ታሪኩ ኬድ ኬሪ ተጠሪ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካችና በዚህ መዝገብ ያልቀረቡ ላልች 9 ተከሣሾችን ጨምሮ ያቀረበው የእርስ በእርስ ጦርነት የማነሳሳት ወንጀል የአሁን አመልካች በተከሰሰበት 5 ክሶች እንዱከላከል ብይን ሰጥቶ ክስና ማስረጃውን አልተከላከልክም ተብል ጥፊተኛ ተደርጏ በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ መወሰኑ እና በይግባኝም ውሣኔው ያለመታረሙ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲለ አቤቱታ በማቅረባቸው መነሻነት ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላይው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካችን 9ኛ ተከሣሽ በማድረግ፣ ላልች 9 ተከሣሾችን ጨምሮ በአጠቃላይ 6 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን፣ አመልካች ግን 6ኛ ክስ ላይ አልተጠቀሰም።
ዐቃቤ ሕግ አቅርቦት የነበረው ክስ በአጭሩ፡- 1ኛ ክስ በሁለም ተከሣሾች ላይ ሆኖ የወ/ሕ/አ/35/32 (1)(ሀ) 240/3 ስር የተደነገገውን ተላልፈው የእርስ በእርስ ጦርነት ለማነሳሳት ካልታወቁ ቡድኖች ሀሳብ በመቀበል መስከረም 6/2011 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 12፡45 ሰዓት ሲሆን በወረዲ ዐ1 ሴቄ ማርያም ሞሪንታ ሰፈር ተብል የሚጠራው ሰፈር የጋሞ ብሓር ተወላጅ የሆኑ ድንጋይ፣ ደላ፣ገጀራ፣ አካፊ እና የተለያየ ስለት ያላቸው መሳሪያዎች በመያዝ ‛ጋሞን ማን ነካ“ እና የኦሮሞን ቤት እየለዩ ንብረት ላይ ጉዲት በማድረስ እየፍከሩ የኦሮሞ ተወላጆች እኛን ገድለው እንዳት ይኖራለ እያለ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነውን ሰው በያዙት ደላና ድንጋይ ቀጥቅጠው በመግደል በፈፀሙት በተሳሳተ እንቅስቃሴ ውስጥ በራሳቸው ፍቃድ ተካፊይ በመሆን የእርስ በእርስ ጦርነት በማስነሳት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
2ኛ ክስ በሁለም ተከሣሾች ላይ፣- የወ/ሕ/አ/35፣ 32/1/ሀ/539/1/ሀ ተላልፈው ሰውን ለመግደል አስበው መስከረም 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዲ ዐ1 ልዩ ቦታው ሱቄ ማርያም ተብል በሚጠራው ሰፈር የኦሮሞ ተወላጆች እኛን ገድለው እንዳት ይኖራለ እያለ በጤፍ ማሳ ውስጥ ያለውን ዲኜ ፈየራ በያዙት ደላና ድንጋይ ቀጥቅጠው የገደለት በመሆኑ በፈፀሙበት ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
3ኛ ክስ በሁለም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/35፣32/1/ሀ እና 690/3/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሣሾች በሰው ንብረት ላይ ጉዲት ለማድረስ አስበው መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በግምት 12 ሰዓት በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ወ/01 የአቶ ብሩ ኢድ ንብረት የሆነ የተለያዩ ንብረቶች ጠቅላላ ግምታቸው 112,800.00 ብር፣ የአቶ ተሾመ መንገሻ ንብረት የሆነውን ኮድ 2-73289 አ.አ. ቪታራ መኪና ግምቱ ብር 300ሺ፣ የወ/ሮ ብርቄ ገብሬ የሆነውን ንብረት ጠቅላላ ግምቱ ብር 8,000.00 ብር፣ የአቶ ወርቁ ኢድ ንብረት ጠቅላላ ግምቱ ብር 425,000.00 በሆኑት ንብረቶች ላይ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።
4ኛ ክስ በሁለም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/ 35፣32/1/ሀ/ 555/ሀ/ ተላልፈው በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ እና ቦታ አቶ እስራኤል ተመስገን የተባለውን በያዙት ድንጋይና ደላ ደብድበውት ሲወድቅ ጥለውት የሄደ በመሆናቸው ክስ ቀርቦባቸዋል።
5ኛ ክስ በሁለም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/35፣32/1/ሀ/ 555/ሀ/ ተላልፈው ወ/ሪት ባንቱ ድናግዳን በያዙት ድንጋይና ደላ ወርውረው በተለያየ የሰውነት አካሎ ላይ ሲመቷት ስትወድቅ ጥለዋት በመሄዲቸው በፈፀሙት የሰው አካል ላይ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ተከሰዋል በሚል ክስ አቅርቧል። 6ኛ ክስ አመልካችን የሚመለከት ባለመሆኑ መመዝገብ አላስፈለገም።
አመልካች ክሱን ክድ በመከራከሩ ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን የሰማ ሲሆን የዐቃቤ ሕግ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣6ኛ፣8ኛ፣9ኛ እና 10ኛ ምስክሮች በአመልካች ላይ ያስረደት ነገር የለም። ነገር ግን 3ኛ፣7ኛ ምስክሮች በአመልካች ላይ የሰጡት ምስክርነት፡- 3ኛ ምስክር አመልካች ገጀራና ድንጋይ ይዘው ከሚያልፈ መሀል እሱም የነበረ መሆኑን፣ ዲኜ ፈይራ የተባለው ሰው ተገድል መገኘቱን ማን እንደገደለው ግን እንደማያውቅ፣ አመልካች ንብረት ማውደሙን እና ወደ ተጠለለ ሰዎች እየመራ የወሰደ መሆኑን መስክሯል። 7ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር በበኩለ የአሁን አመልካችን በችልት ለይቶ ማሳየቱን፣ በጊዜው የኦሮሞ ልጆችን ሲያሯሩጥ የነበረ መሆኑን ማሳ ውስጥም ሰው ሞቶ መገኘቱን እና በተጠለለ ሰዎች ላይም ጉዲት የደረሰ መሆኑን አውቃለሁ ሲል መስክሯል።
ፍ/ቤቱም የቀረበውን ክስ እና ማስረጃን መርምሮ በ1ኛ ክስን አስመልክቶ የቀረበው ማስረጃ የእርስ በእርስ ጦርነት ድርጊትን ሉገልጽ የሚችል አይደለም በሚል የቀረበውን ክስ ወደ አምባጓሮ ወይም በጠብ ተካፊይ ሆኖ መገኘትን የሚያሳይ ነው በማለት ድንጋጌውን ወደ 577/3/ በመቀየር አመልካችን ጨምሮ 1፣2፣5፣7፣10ኛ ተከሣሾች እንዱከላከለ፣ በ2ኛ ክስ አመልካችን ጨምሮ 2ኛ፣5ኛ፣7፣8ኛ፣ እና 10ኛ የስር ተከሣሾች በ539/1/ሀ/ ስር እንዱከላከለ፣3ኛ ክስን አስመልክቶ በድርጊቱ ሰው ያልሞተ መሆኑ ስለተረጋገጠ በሚል የቀረበውን ድንጋጌ ወደ 690/1/ለ/ በመቀየር አመልካችን ጨምሮ 1ኛ፣2ኛ፣5ኛ፣7ኛ፣8ኛ እና 10ኛ የስር ተከሣሾች እንዱከላከለ፣4ኛ ክስን አስመልክቶም ድንጋጌውን በመቀየር በ556/2/ሀ ስር አመልካችን ጨመሮ 1ኛ፣2ኛ፣5ኛ፣8ኛ እና 10ኛ የስር ተከሣሾች እንዱከላከለ፣ 5ኛ ክስንም እንዱሁ ወደ 556/2/ሀ በመቀየር አመልካችን ጨምሮ ላልች ተከሣሾች እንዱከላከለ ብይን ሰጥቷል። ከዚህ ውጪ ያለ የስር ተከሣሾችን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷል።
በዚሁ መሰረት አመልካች የመከላከያ ማስረጃውን አቅርቦ ያሰማ ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ክስና ማስረጃውን አልተከላከለም በሚል እንዱከላከል ብይን በተሰጠበት የህግ ድንጋጌዎች ስር ጥፊተኛ ነው ሲል የጥፊተኝነት ውሣኔ በመስጠት ቅጣቱን አስልቶ በ16/ አስራ ስድስት ዓመት/ ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሣኔ በመቃወም ነው።
አመልካች መጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠበቃው አማካይነት የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይዘቱም በአጭሩ፡- አመልካች በተከሰሰባቸው የወንጀል አይነቶች ላይ የወ/ሕ/አ/35 ተፈፃሚ ላሆን የሚገባው ያለመሆኑን፣ በአመልካች ላይ በተጠቀሰው ከባድ ወንጀል ቅጣቱም እድሜ ልክ ወይም ሞት በሚያስቀጣ ላይ በህብረቱ ውስጥ ተገኝተሀል በሚል ምክንያት ብቻ አመልካች ምን እንዲደረገ ተለይቶ ባልተከሰሰበት እና ባልተመሰከረበት ጥፊተኛ ተደርጉ ቅጣት መጣለ፣ ዲኜ ፈየራ የተባለው ሰው በተገደለበት በ6/1/2011 ዓ.ም. አመልካች በቦታው የነበረ ስለመሆኑ ባልተመሰከረበት፣ የዐቃቤ ሕግ 1ኛ፣2ኛ፣4ኛ፣ ምስክሮች አመልካች ከላይ በተጠቀሰው ቀን እንደላለ መስክረው ባለበት፣ 5ኛ፣7ኛ፣8ኛ፣10ኛ ምስክሮችም በአመልካች ላይ የመሰከሩት ነገር በላለበት፣ በ3ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርም ላይ ከአመልካች ጋር ጠበኛ በመሆኑ እንዲይመሰክር አመልክተን እያለ ጥፊተኛ መደረጉ፣ ተመስክሮበታል እንኳን ቢባል በወ/ሕ/አ/540 መሆን ሲገባው በ2ኛ ክስ 539/1/ሀ ጥፊተኛ ተደርጏ መቀጣቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሆኑን ስለሚያሳይ ስህተቱ እንዱታረምልኝ ሲል ጠይቋል።
አቤቱታው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች በወ/ሕ/አ/ 35/32/1/ሀ እና 577/3/፣539/2/ሀ፣690/1/ለ/ እና 556/2/ሀ/ን ተላልፍ ወንጀል ፈጽሟል ተብል በስር ፍ/ቤት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ የተወሰነበትን አግባብነት ከተጠቀሰው ድንጋጌና ከወንጀል ህግ አንቀጽ 23/2/ አንፃር ለመመርመር መዝገቡ ለችልቱ እንዱቀርብ በመታዘዙ ላቀርብ ችሎል።
ለተጠሪ መጥሪያ እንዱደርሰው ተደርጏም በ22/11/2013 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡እንደ አድማና አምባጓሮ የመሳሰለ ወንጀልች በአንቀጽ 35 2ኛ ሃሣብ አገላለጽ ከዐ/ሕግ የሚጠበቀው በህብረቱ ውስጥ ተከሣሽ መገኘቱን እንጂ ወንጀል አለመፈፀሙን የማስረዲት ሸክም ወደ ተከሣሽ የሚዞር መሆኑን፣ ያቀረብነውን ክስ ከጥርጣሬ በፀዲ መልኩ ያስረዲን በመሆኑ፣ ዲኜ ፈየራ የተባለው ሰው ግድያ ላይ አመልካች ከላልች ጋር አብሮ ስለመኖሩ በምስክር ያረጋገጥን መሆኑን፣ 3ኛ፣4ኛ እና 7ኛ ምስክሮች የኦሮሞ ወጣቶችን አመልካች ከላልች ጋር በመሆን እያባረረ ወደ በቀለ ኢድ የጤፍ ማሳ የወሰደ መሆኑ፣ ማሳ ውስጥም ዲኘ ፈየራ ሞቶ መገኘቱ መመስከሩን፣ የወ/ሕ/አ/539/1/ሀ ወደ 540 ይቀየርልኝ ያለውንም አስመልክቶ አመልካች ከላልች ጋር በመስማማት ድርጊቱ የፈፀመ በመሆኑ ድንጋጌውን የሚያቋቁም ከሆነው አንደ የተሟላ በመሆኑ ሉቀየር የሚገባው አለመሆኑን፣ በማንሳት የስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ ተገቢ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልኝ ብሎል።
የአመልካች ጠበቃም የቀደመው የሰበር አቤቱታን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገብ ተያይዞ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዚሁ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭር በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ መልስ በስር ፍ/ቤቶች ከተሰጠው ውሣኔ እና አጠቃላይ ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
የክርክሩ ሂደት የሚያሳየው በአመልካች ላይ ዐቃቤ ህግ 5 ክሶችን ጠቅሶ ከላልች ተከሣሸች ጋር ወንጀል ፈጽሟል ሲል ክስ የመሰረተበት መሆኑን፣ የተጠቀሱት ክሶችም 240/3፣ ለጦርነት የማነሳሳት ወንጀል፣539/1/ሀ/ ከባድ የሰው ግድያ፣690 በንብረት ላይ ጉዲት ማድረስ፣555/ለ/ በሰው አካል ላይ ከባድ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ፈጽሟል ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካች ክሱን ክድ የተከራከረ በመሆኑ ምስክሮች ተሰምተው ለጦርነት የማነሳሳት ወንጀለ ድንጋጌን እና በአካል ላይ ከባድ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ድንጋጌን ወደ አምባጓሮ እና ቀላል አካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል በመቀየር ላልቹ ክሶች በነበሩበት ሁኔታ አመልካች እንዱከላከል ፍ/ቤቱ ብይን የሰጠ በመሆኑ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ በማድረግ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።
በአጣሪ ችልቱ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በጭብጥነት ተይዞ ሉመረመር የሚገባው ዐቃቤ ሕግ እንዲቀረበው ክስ በማስረጃ ስለማስረዲት አለማስረዲቱና አስረድቷል ከተባለም አመልካች ክሱና ማስረጃውን ተከላክሎል ወይንስ አልተከላከለም የሚለውን እና ተጠቅሰው የቀረቡት ድንጋጌዎች በተደራራቢ ክስ የመቅረባቸውን አግባብነት ከወ/ሕ/አ/23/2//35 ፣60፣61 እና 141፣577/3/፣ 690 ድንጋጌዎች ጋር ሉመረመር የሚባው ሆኖ ተገኝቷል።
የወ/ሕ/አ/23/2/ በግልጽ የሚደነግገው፡- ‛አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፣ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው።“ በሚል ነው።
ከወንጀል ጉዲዮች የክስ ሂደት ጋር በተገናኘ ዓቃቤ ሕግ ሉያከናውናቸው ከሚገቡ ተግባራትና ኃላፉነቶች ዋናው የተከሰሰን ሰው የወንጀል ድርጊቱን በቀረበው ክስ አይነት ስለመፈፀሙ በበቂና አሳማኝ ማስረጃ የማስረዲት ሸክሙን መወጣት ያለበት ስለመሆኑ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 141 እና 142/1/ ድንጋጌ መረዲት እንችላለን።
የወ/ሕ/አ/577/3/ ፡- ‛ በአምባጓሮ ወቅት ከነበረው ሁኔታ የተነሳ በተለይም በጠበኞች መካከል በነበረው ቂም፣የጠብ ማጫር ወይም የስካር ሁኔታ ወይም የጦር መሣሪያዎችን፣ ድንጋዩችን ወይም ማቁሰል ወይም መግደል የሚችለ ላልች ነገሮችን የያዙ ወይም እነዚሁ ነገሮች የተሰጧቸው በመሆኑ በጠቡ መካከል ሰው የቆሰለ ወይም የተገደለ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው መደበ ቅጣት ሉደርስ ይችላል።“ በሚል ይደነግጋል።
በመሰረቱ ተደራራቢ ወንጀልች በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ (ሀሳባዊ መደራረብ) ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ጊዜያት የተፈፀሙ ድርጊቶችን (ቁሳዊ መደራረብ) የሚመለከቱ ሲሆኑ መደጋገም የቁሳዊ መደራረብ መለያ ባህሪ በመሆኑ ተመሳሳይ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜያት ቢፈፀሙ ወይም የተለያዩ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜ ተፈፅመው ቢገኙ ቁሳዊ መደራረብ አለ ለማለት የሚቻል ሲሆን፣ በአንድ ነጠላ ድርጊት ከአንድ በላይ የሆኑ ወንጀልች መፈፀማቸው የሀሳባዊ መደራረብ መለያ ባህሪ መሆኑን ከወ/ህ/አ.60(ሀ)እና(ለ) ድንጋጌ ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ላይ ዐቃቤ ሕግ ጠቅሶ ያቀረበውን ክስ ስንመለከት በፍ/ቤቱ ባይለወጥ ኖሮ 1ኛው ክስ የእርስ በእርስ ጦርነት ማነሳሳት የነበረ ሲሆን ይህን ግን የስር ፍ/ቤት የቀረበው ክስ እና ማስረጃ የተጠቀሰውን መስፈርት አያሟላም በሚል ወደ አምባጓሮ ድንጋጌ የቀየረው መሆኑን ነው።
ከላይ እንደተመለከትነው የወ/ሕ/አ/577/3/ ተጠቅሶ አመልካች ጥፊተኛ የተባለ ሲሆን አመልካች በድንጋጌው ጥፊተኛ ላደረግ የበቃው የወ/ሕ/አ/35 እና 32/1/ሀ ተጠቅሶ ከላልች ጋር በህብረት ወንጀለን ፈጽሟል በሚል በመሆኑ የወ/ሕ/አ/35 በግልጽ የሚደነግገው ደግሞ አድማና አምባጓሮ በተደረጉ ጊዜ በህብረቱ ውስጥ መገኘቱ የተረጋገጠበት ሰው የማይቀጣው በወንጀለ ተካፊይ አለመሆኑን ሉያስረዲ ከቻለ ብቻ መሆኑን ይደነግጋል። በመሆኑም አመልካች አምባጓሮው መፈፀሙ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ቁጥራቸው ትንሽ ይሁኑ እንጂ በቀረቡት ምስክሮች በዚህ ህብረት ውስጥ ስለመገኘቱ የመሰከሩበት በመሆኑ አመልካች አብረውት የተከሰሱት ሰዎች ድንጋይ፣ ደላ እና ላልች ማቁሰል የሚችለ መሳሪያዎችን በመያዝ እየፍከሩ የኦሮሞ ልጆች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ እሱም የተጠለለ ሰዎች ያለበትን ቦታ ይመራ የነበረ መሆኑን፣ የኦሮሞ ልጆችን ያባርር የነበረ መሆኑን፣ እንዱሁም መስከረም 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው ረብሻ ላይ የነበረ ስለመሆኑ እና በዚህ የአመልካቾች ድርጊት የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ንብረትም የወደመ መሆኑ በምስክሮች በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል።
አመልካች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ሰዓትና ቦታ በአምባጓሮው መካከል ስላለመኖሩ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ጥርጣሬን በሚፈጥር መልኩ ባቀረባቸው ማስረጃዎች አልተከላከለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የቀረበውን 1ኛ ክስ ወደ 577/3/ ቀይሮ ጥፊተኛ ማድረጉ ተገቢ እንጂ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ነገር ግን የስር ፍ/ቤት የወ/ሕ/አ/577/3/ ወንጀል ተፈጽሟል ብል ያመነ ከመሆኑ አንፃር ዐቃቤ ሕግ የወ/ሕ/አ/539/1/ሀ/ ጠቅሶ በዛው በተፈጠረ አምባጓሮው ድርጊት ምክንያት ሰው የሞተ መሆኑን በመጥቀስ አመልካች የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበውን ክስ ድርጊቱ የተደራራቢ ወንጀልን መስፈርት የማያሟለ መሆኑን በመረዲት 2ኛው ክስ በ1ኛው ክስ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ብል መወሰን ሲገባው በአንድ ወንጀል የመስራት ሃሣብ የተፈፀመን ድርጊት ወንጀለ እንደተደራረበ አድርጏ በ2ኛ ክስ ጥፊተኛ ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም. አመልካችን ጨምሮ የስር ላልች ተከሣሾች የወ/ሕ/አ/35/32/1/ሀ/ እና 690/1/ለ/ ተላልፈው በተለያዩ ሰዎች ንብረት ላይ ጉዲት ማድረሳቸውን አስመልክቶ በአመልካች ላይ ድርጊቱን ስለመፈፀሙ በማስረጃ የተረጋገጠበት በመሆኑ እንዱሁም ወንጀለ የተፈፀመበት ቀን አምባጓሮ ከተፈፀመበት ቀን የሚለይ በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ አመልካችን ጥፊተኛ በማድረግ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለ በመሆኑ ሉፀና የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ የተፈፀመው መሰረታዊ የህግ ስህተት ሉታረም የሚገባው በመሆኑ የበላይ ፍ/ቤትም የስር ፍ/ቤትን የህግ ስህተት ሳያርም ማለፈ ተገቢ ባለመሆኑ ውሣኔውን በማሻሻል ተከታዩን ወስነናል።
የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ጥፊተኛ ተብል ቅጣት ሉወሰንበት የሚገባው በወ/ሕ/አ/35፣32/1/ሀ እና 577/3 እና 690/1/ለ/ በአምባጓሮ እና በንብረት ላይ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ነው ብለን ወስነናል። አመልካች በወ/ሕ/አ/539/1/ሀ እና 556/2/ሀ ጥፊተኛ ተብል ቅጣት ሉወሰንበት አይገባም ብለን ወስነናል።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወ/ሕ/አ/577/3/ የአምባጓሮ ወንጀል ድንጋጌ፡- ‛በአምባጓሮ ወቅት ከነበረው ሁኔታ የተነሳ በተለይም በጠበኞች መካከል በነበረው ቂም፣የጠብ ማጫር ወይም የስካር ሁኔታ ወይም የጦር መሣሪያዎችን፣ ድንጋዮችን ወይም ማቁሰል ወይም መግደል የሚችለ ላልች ነገሮችን የያዙ ወይም እነዚሁ ነገሮች የተሰጧቸው በመሆኑ በጠቡ መካከል ሰው የቆሰለ ወይም የተገደለ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው መደበኛ ቅጣት ሉደርስ ይችላል።“ በሚል ይደነግጋል።
በንብረት ላይ ከባድ ጉዲት ማድረስ ወንጀልን የሚደነግገውና አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወ/ሕ/አ/690/1/፡- ‛ወንጀለ በወንጀል ክስ አቅራቢነትና ከሰባት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራትና መቀጮ ሉያስቀጣ በሚችል፡- ለ/ ወንጀለ የተፈፀመው በዛቻ፣በኃይል ወይም በብዙ ሰዎች ይልቁንም ሁከት፣ የሥራ መዝጋት ወይም የሥራ ማቆም አድማ በተነሳ ጊዜ በሰራተኞች ወይም በአሰሪዎች እንደሆነ----“ በሚል ይደነግጋል።
ከላይ በተገለፀው ድንጋጌ መሰረት በተፈፀመው የአምባጓሮ ወንጀል ምክንያት ሰው የተገደለ እንደሆነ አጥፉው በወ/ሕ/አ/577/3/ ስር በተደነገገው መሰረት ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው መደበኛ ቅጣት ሉደርስ ይችላል“፡ ይህም ማለት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539/1/ ስር እንደተደነገገው ሰው በመግደል ወንጀል ከፍተኛ መደበኛ ቅጣት ዔድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም ሞት ነው።
አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 577/3/ ስር በሞት ወይም በእድሜ ልክ እስራት ሉያስቀጣ በሚችል ወንጀል ጥፊተኛ ስለተባለ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 690/1/ ስር ጥፊተኛ የተባለበት ቅጣት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 184/1/ሀ/ መሰረት ከፍተኛው መደበኛ ቅጣት ውስጥ የተጠቃለለ ነው።
በመሆኑም የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት በላልች ተደራራቢ ወንጀልች ምክንያት ሉጣለ የሚገባቸውን የቅጣት ዓይነቶች ሁለ አካቶ የሚይዝ ስለመሆኑ በወ/ሕ/አ/ 184/1/ሀ/ ስር የተደነገገ በመሆኑ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን ተደራራቢ ወንጀል ማለትም የወ/ሕ/አ/690/1/ለ/ ቅጣቱ ሲሰላ ታሳቢ አይደረግም ብለን ወስነናል።
ሆኖም ግን በስር ፍ/ቤት ከተያዘው 3 የቅጣት ማቅለያ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ክርክሩ እንደተገነዘብነው አመልካች ይህን ድርጊት እንዱጸትም የገፊፊው አስቀድሞ በጋሞዎች ላይ ተፈጽሞ የነበረው ጉዲት መሆኑን መረዲት የሚቻል በመሆኑ ቅጣቱም ሉጣል የሚገባው ፍትህን ሉያሰፍን በሚችል መልኩ ሆኖ ስላገኘነው ይህን ወንጀል ለመፈፀም ያነሳሳውን ምክንያት እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመውሰድ 4 የቅጣት ማቅለያ እንዱያዝና ከተያዘው የቅጣት መነሻ ደረጃ ላይ መቀነስ ተገቢ ነው ብለን የቅጣት ደረጃውን ወደ ደረጃ 34 ዝቅ አድርገን በ15/ አስራ አምስት/ ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ተደርጏ ቅጣቱ ተሻሽል ተወስኗል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች እና አመልካች ለታሰረበት ማረሚያ ቤት እንዱደርስ ታዟል።
አመልካች የታሰረበት ማረሚያ ቤትም አመልካች ከዚህ ቀደም በዚህ ጉዲይ የታሰረው ታሳቢ ተደርጏ በተሻሻለው ውሣኔ መሰረት ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ታዟል።
የውሣኔው ግልባጭ አመልካች ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት በፍ/ቤቱ መልእክት ክፍል በኩል እንዱደረስ ታዟል።
መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.