ፍርድ ያረፈበት ንብረት በአፈፃፀም ደረጃ ላይ እያለ የተቃውሞ ማመልከቻ ክርክር በሚቀርብበት ጊዜ ተቃውሞ የቀረበው በሥረ-ነገሩ በተሰጠው ፍርድ ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ነው ወይሥ ለፍርድ አፈጻጸሙ በተከበረው ንብረት ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት ነው እነ ወ/ሮ መዓዛ አባተ (2 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ ጥሩአለም ረታ በመለየት ተቃውሞው የቀረበበትን ምክንያት የሚጠይቀውን የክርክር ሂደት መከተል እንጂ የአፈጻጸሙ ክርክር ዋናው ፍርድ በተሰጠበት መዝገብ ላይ የሚመራ ስላለመሆኑ (4 ሰዎች)
No summary available.
ቀን - ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ሲቲና ኢብራሂም - ቀረቡ ተጠሪ፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክርክር አድርገው ከውሳኔ በኋላ አፈጻጸም ላይ እያለ 1ኛ ተጠሪ ቀርበው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ 21 ዓመት ስንኖር በጋራ ያፈራናቸውን በካርታ ቁጥር 189 እና በካርታ ቁጥር 1622/85 የተመዘገቡት ቤቶች ላይ አመልካች ያላፈሯቸው እና መብት የላላቸው በመሆኑ ንብረቶቹ ላይ የቀዲሚ መብት ስላለኝ የአፈጻጸም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የተቃውሞ ማመልከቻ አቅርበዋል። አመልካች ያቀረቡት መልስ የ2ኛ ተጠሪ ሚስት እና የንብረት ባለድርሻ መሆናቸውን ገልጸው 1ኛ ተጠሪም ከንብረቱ ድርሻቸውን መካፈል ይችላለ ብለዋል። 2ኛ ተጠሪም በበኩላቸው አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ባለቤቶቼ ስለሆኑ ንብረቱን ለሦስት ክፍፍል ላደረግበት ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የዱላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንብረቱን 1ኛ ተጠሪን ጨምሮ ሁለም ለሦስት እንዱካፈለት ወስኗል።
1ኛ ተጠሪ ለጌዱኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው አከራክሮ ውሳኔውን አጽንቷል። የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግራቀኙን አከራክሮ 1ኛ ተጠሪ የሚከራከሩት፤
ንብረቱ የተፈራው 2ኛ ተጠሪ አመልካችን ከማግባታቸው በፉት በመሆኑ አመልካች በንብረቱ ላይ መብት የላቸውም በማለት ስለሆነ ጉዲዩን ሳያጣራ መወሰኑ ስህተት ነው በማለት ውሳኔውን በመሻር የግራቀኙ ማስረጃ ተሰምቶ እንዱወሰን ጉዲዩን መልሷል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ጉዲዩ ተወስኖ ያለቀ ነው። የእኔ እና የልጆቼ መብት ላይ ጉዲት የሚያደርስ በመሆኑ ንብረቱ ተሽጦ ልንከፊፈል ይገባል የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት 1ኛ ተጠሪ መብታቸውን ማስከበር የሚችለት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 ወይስ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ነው? ጉዲዩ ሥርዓቱን ጠብቆ የቀረበ መሆን አለመሆኑ እና የክልለ ሰበር ችልት ጉዲዩን መመለሱ ህጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በማዘዙ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ባቀረብኩት ክርክር መሰረት ጉዲዩ በማስረጃ ተጣርቶ እንዱወሰን መመለሱ ተገቢ ስለሆነ ውሳኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል። አመልካች በ1ኛ ተጠሪ መልስ ላይ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የተቃውሞ ማመልከቻ ክርክር የተመራበት ሥርዓት ሕጉን የተከተለ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክርክር አድርገው ከውሳኔ በኋላ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እያለ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የተቃውሞ ማመልከቻ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ 21 ዓመት ስንኖር በጋራ ያፈራናቸውን በካርታ ቁጥር 189 እና በካርታ ቁጥር 1622/85 የተመዘገቡት ቤቶች ላይ አመልካች ያላፈሯቸው እና መብት የላላቸው በመሆኑ ንብረቶቹ ላይ የቀዲሚ መብት ስላለኝ የአፈጻጸም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው። ተቃውሞ የቀረበበት ንብረት ፍርድ ያረፈበት መሆኑ እና ቤቶቹ ላይ አመልካች መብት የላቸውም የሚለው የማመልከቻው ይዘት ጉዲዩ የቀረበው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ዋናው ፍርድ መብቴን ይነካል በሚል እንደሆነ ያስገነዝባል። በልላ በኩል 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የአፈጻጸም ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል ማለታቸው እና የሥር ዱላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች እና 2ኛ ተጠሪን የአፈጻጸም ከሳሽ እና የአፈጻጸም ተከሳሽ በማለት መሰየሙ ተቃውሞ የቀረበው የአፈጻጸም ክርክሩ ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት እንደሆነ ግምት የሚያስወስድ ነው። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የመቃወሚያ ማመልከቻ የቀረበበት ምክንያት ዋናው ፍርድ ላይ ነው ወይስ አፈጻጸሙ ላይ የሚለው ጉዲይ አከራካሪ ያደረገው የማመልከቻው አቀራረብ ጉድለት እና የስር ፍርድ ቤት የአፈጻጸሙን ክርክር ዋናው ፍርድ በተሰጠበት መዝገብ በመምራቱ ነው።
የአፈጻጸም ክርክሩ ጉዲዩ በሥረ-ነገሩ በተያዘበት መዝገብ በሚመራበት ጊዜ በጉዲዩ ላይ የመቃወም ማመልከቻ ማቅረብ የሚፈልጉ ሰዎችን መብት እንዲይነካ ወይም ለተቃውሞው መልስና ክርክር ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተከራካሪዎች መሰረታዊ የሆነው የመደመጥ መብታቸው እንዲይታለፍ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል።
ተቃውሞ የቀረበው በሥረ-ነገሩ በተሰጠው ፍርድ ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ነው ወይሥ ለፍርድ አፈጻጸሙ በተከበረው ንብረት ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት ነው የሚለውን በመለየት ተቃውሞው የቀረበበትን ምክንያት የሚጠይቀውን የክርክር ሂደት መከተል ያስፈልጋል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት የተቃውሞ ማመልከቻ በቀረበ ጊዜ ተቃውሞ የቀረበበት ንብረት ላይ ተቃዋሚው መብቱን ካሳየ ፍርድ ቤቱ እንደ በቂ ምክንያት በመቁጠር የተያዘው ንብረት እንዱለቀቅ ትዕዛዝ ላሰጥ እንደሚችል ተመለክቷል። በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት የሚቀርብ ክርክር ጉዲዩ በሥረ-ነገሩ በመጀመሪያ ደረጃ እንደሚታይ የክስ ዲኝነት ሙለ የክርክር ሥርዓትን የሚከተል ሂደት አይደለም። ተቃዋሚው በአፈጻጸም የተያዘው ሆነ የተከበረው ንብረት የእርሱ ስለመሆኑ ማስረጃ ካቀረበ በቂ ምክንያት አለው ተብል ንብረቱ ከክርክሩ ውጭ የማድረግ ዓላማ ያለው እንጂ በተከበረው ንብረት ላይ የባለቤትነት ክርክር ለማድረግ እና ሉፈጸም የሚችል ፍርድ የሚሰጥበት ሥርዓት አይደለም። በልላ በኩል የመቃወም ማመልከቻው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በጉዲዩ ሥረ-ነገር ላይ የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ነክቷል በማለት ፍርድ ባረፈበት ንብረት ላይ በቀረበ ጊዜ ተቃዋሚው ክርክር ባስነሳው ጉዲይ ላይ የሚያገባው እና ቀድሞም ተከራካሪ መሆን የሚገባው ከነበረ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360(1)(2) እንደተመለከተው በማመልከቻው ላይ ላልች ተከራካሪዎች መልስ የሚሰጡበት እና ጉዲዩ ላይ እንደገና ሙለ ክርክር የሚደረግበት ሂደትን የሚከተል ሥርዓት ነው። ውጤቱም ቀድሞ የተሰጠውን ፍርድ መለወጥ ወይም ማሻሻል ድረስ ሉያስከትል የሚችል ነው።
1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የመቃወም ማመልከቻ ይዘቱ በሥረ-ነገሩ የተሰጠውን ፍርድ የሚመለከት እና ፍርደ የጋራ ንብረት መብቴን ነክቷል የሚል ነው። ይህም ማመልከቻው የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት አድርጎ የሚመራ እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም በመቃወም ማመልከቻው ላይ አመልካች እና ተጠሪ መልስ አቅርበውበት እንደገና ሙለ ክርክር ላደረግበት የሚገባ ነው። በክርክር አመራሩ የግራቀኙ ተከራካሪዎች የመደመጥ መብት መከበሩን ማረጋገጥ እና ሁለም ክርክር እና ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው ተግባራዊ መሆኑን መቆጣጠር የፍርድ ቤቶች ኃላፉነት ነው።
በሥር ፍርድ ቤት ለመቃወም ማመልከቻው መልስ ያቀረቡት አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ክርክሩን እንደገና ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ተገንዝበው በዚሁ አግባብ መልስ እና ጉዲዩን ለመከላከል የሚያስችል ማስረጃ ያቀረቡ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።
ከዚህ አኳያ የአመልካች እና 2ኛ ተጠሪ የመከላከል መብታቸው እስከተከበረ ድረስ፤ የ1ኛ ተጠሪ ተቃውሞ የቀረበው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት መሆኑን ተገንዝቦ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በውሳኔው 1ኛ ተጠሪ የሚከራከሩት፤ ንብረቱ የተፈራው 2ኛ ተጠሪ አመልካችን ከማግባታቸው በፉት በመሆኑ አመልካች በንብረቱ ላይ መብት የላቸውም በማለት ስለሆነ ክርክሩ በግራቀኙ ማስረጃ ተጣርቶ እንዱወሰን በማለት ጉዲዩን መመለሱ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥር 21 ቀን 2011 ዓ/ም፤ የጌዳኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ/ም እና የዱላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም የሰጡትን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ/ም በዚህ ችልት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.