አፈፃፀም ለአፈፃፀሙ መነሻ የሆነውን መሰረታዊ ፍርድ/ውሳኔ የሚከተል በመሆኑ ለአፈፃፀም መነሻ የሆነን ፍርድ በይግባኝ ያላሻረ ወይም እንዱሻሻል ያላደረገ ተከራካሪ ወገን በዋናው ጉዲይ ላይ ሉነሱ የሚገባቸውን የክርክር ነጥቦች በአፈፃፀም በተያዘው መዝገብ ላይ የክርክሩ መሰረት ሉያደርጋቸው የማይችልና የተሰጠው ፍርድ እንዱሻር የተደረገ መሆኑን በመጥቀስ የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ ከላለ አፈፃፀሙን የሚመራው ፍርድ ቤት ፍርደን የሚያስፈፅመው በስነ ስርዐት ህጉ በተዘረጋው ስርዐት መሰረት እንደ ፍርደ ይዘትና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ በፍርደ አግባብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.372፤378፤392(1)
No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ማርታ ዳሬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኢያሱ ፀጋዬ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ ላቀርብ የቻለው አመልካች ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.36077 ሀምላ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፀው በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች በወላይታ ሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ የአፈፃፀም ተከሳሽ ነበር።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ተጠሪ የአመልካችን ይዞታ ከፉት ለፉት 0.10 ሜ እና ከኋላ 0.70 ሜ እንዱለቅ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን በዚሁ ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀምልኝ በማለት ለወላይታ ሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት አመልክተዋል።ፍርድ ቤቱም አመልካች በውሳኔው መሰረት ይፈፀምልኝ ስትል ያቀረበችው ለማዘጋጃ ቤት እንዱያስፈፅም በተከታታይ ትዕዛዝ ተሰጥቶ በውሳኔው መሰረት ለመፈፀም የአሁን አመልካች ሳይት ፔላኑን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም በማለት በቁጥር 268/09/2013 በቀን 13/05/2013 ዓ.ም በተፃፈው መግለጫ የገለፁ ሲሆን ዲግም በተሰጠው ትዕዛዝ በቁጥር 400/26/13 በቀን 25/05/13 ዓ.ም በተፃፈው መግለጫ ከፍርድ ቤት ባለሞያ ጋር ለመስራት በጠየቁት መሰረት ከፍርድ ቤቱ ዲኛ ጋር እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ ከማዘጋጃ ቤት ባለሞያ ጋር አፈፃፀሙን ለማስፈፀም በሄድንበት የአሁን ተጠሪ ትርፍ ይዞታ ከያዘ ለማስለቀቅ ሲለካ ከዚህ በፉትም ሆነ አሁንም የአሁን ተጠሪ ወደ አመልካች ይዞታ አልፍ ይዟል የተባለው ከፉት ለፉት 0.10 ሜትር በጎን በኩል ወጣ ገባ አጥር ያለውን ተጠሪ እንዱያነሳ ተብል አንስቷል።ወጣ ገባ አጥር የፍልጥ እንጨት ለቅቆ ገብቷል።አሁን በድጋሚ እንዱያስለቅቀው በውሳኔው መሰረት ይፈጸም በሚል የቀረበው ለማስፈፀም በሄድንበት ተጠሪ በጎን በኩል በስተምስራቅ በኩል የተጠሪ ይዞታው ወደ አመልካች ገብቶ ያለ ስለሆነ ማዘጋጃ ቤቱ በዚህ ጉዲይ ላይ መግለጫ እንዱሰጥ ታዞ በቁጥር 351/9/13 በቀን 22/07/2013 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ክርክሩ ባለበት በስተምስራቅና በስተምዔራብ በኩል የተጠሪ ይዞታ በሳይት ፔላን 13.50 ሲሆን በመሬት ላይ ያለው ግን 13.40 በመሆኑ አጠቃላይ ካሬ ሜትር 499.50 ካ.ሜ ሆኖ በመሬት ላይ ያለው 442.43 ካ.ሜ ነው። የአመልካች ቁመትና ስፊት የሚያስረዲ ባይሆንም በሳይት ፔላን ላይ 279 ካ.ሜ ሲሆን በመሬት ላይ ሲለካ 244 ካ.ሜ እንደሆነ አረጋግጠው የሰጡት መግለጫ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። እዚህ ላይ ለማስፈፀም ተጠሪ ቤቱን አልፍ ወደ አመልካች ይዞታ ገብቶ የሰራበት የለም፤ሲለካ የተጠሪ ይዞታ ወደ አመልካች ይዞታ ነው የሚገባው ስለዚህ ከዚህ በፉት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ በመዝገብ ቁጥር.39060 በቀን 04/04/2010 ዓ.ም በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ከፉት ለፉት 0.10 ሜ ከኋላ በኩል ያለት ወጣ ገባ አጥሮች ተነስተው ይዞታው ለአመልካች የተሰጠ ስለሆነ አሁን በጎን በኩል 0.70 ሜ ተጠሪ አልፍ የያዘው ባለመኖሩ የግራ ቀኙ ይዞታቸው በሳይት ፔላኑ ላይ ካለው መሬት ላይ ያለው ሲለካ የሚያንስ በመሆኑ ተጠሪ አልፍ የያዘው ይዞታ ስለላለ የሚፈፀም ውሳኔ የለም፤ በውሳኔው መሰረት ከዚህ በፉት ወርደን የፈፀምን ስለሆነ አሁን የሚፈፀም ውሳኔ የለም በማለት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቶታል።
አመልካች የወላይታ ሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ፈጽመዋል በማለት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ቢያቀርቡም ሰበር ሰሚው ችልት በስር ፍርድ ቤቶች የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ውሳኔውን በሙለ ድምጽ አጽንቷል።
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ፡- በአመልካች እና በተጠሪ መካካል በስር ፍርድ ቤት ስንከራከር ቆይተን በዋና ክርክር የተወሰነልኝ በአፈፃፀም እንዱፈፀም በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.378፣ 386፣ 389 በሚያዘው መሰረት በወረዲው ፍርድ ቤት ላይ እንዱፈጽሙልኝ ባቀርብም በውሳኔው መሰረት ያልፈፀሙልኝ ስለሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.28187 በቀን 06/06/2011 ዓ.ም የይግባኝ ቅሬታ አቅርቤላቸው ቀደም ሲል በፍሬ ጉዲይ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ከፉት ለፉት 0.10 ሜ እና ከኋላ 0.70 ሜ አልፍ የያዘውን ለቆ እንዱወጣ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት በአፈፃፀም ይዞታውን ለአመልካች ያስረክብ ብል ወስኖልኛል። በዋና ውሳኔ መሰረት ያልፈፀሙልኝ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሮ በፍርደ መሰረት እንዱፈፀምልኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
በዚህ ጉዲይ የስር ፍርድ ቤቶች የሚፈፀም ፍርድ የለም በማለት የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ ዋናውን ፍርድ በተገቢው ያገናዘበ መሆን አለመሆኑ መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነ ጉዲዪ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ የሰጡት መልስ በአጭሩ፡- በዚህ ጉዲይ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በቅጽ 13 በሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ መሰረት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋናውን ውሳኔ የወሰነው በዓይን እይታ ሲሆን አፈፃፀም የሚፈጽመው ፍርድ ቤት ወርድ መሬት ላይ ለክቶ በማየት ላሆን ይገባል፤ ተጠሪ ከክፍለ ማዘጋጃ ቤት ሳይት ፔላን ያወጣሁት በ1998 ዓ.ም ሲሆን አመልካች በ2008 ከአስር ዓመት በኋላ አውጥታለች ይህም ቢሆን የአመልካች ሳይት ፔላን ወሰኑን/ድንበሩን/ ከላይም ሆኖ ከታች የማይገልጽ መሆኑን አረጋግጦ የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ በአግባቡ ስለሆነ የአመልካችን አቤቱታው ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀናልኝ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል።አፈፃፀም ለአፈፃፀሙ መነሻ የሆነውን መሰረታዊ ፍርድ/ውሳኔ የሚከተል በመሆኑ አፈፃፀሙን የሚመራው ፍርድ ቤት ፍርደን የሚያስፈፅመው በስነ ስርዐት ህጉ በተዘረጋው ስርዐት መሰረት እንደ ፍርደ ይዘትና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ሲሆን በዚህ አግባብም ለአፈፃፀም መነሻ የሆነን ፍርድ በይግባኝ ያላሻረ ወይም እንዱሻሻል ያላደረገ ተከራካሪ ወገን በዋናው ጉዲይ ላይ ሉነሱ የሚገባቸውን የክርክር ነጥቦች በአፈፃፀም በተያዘው መዝገብ ላይ የክርክሩ መሰረት ሉያደርጋቸው የማይችል መሆኑን ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.372፤378፤392(1) ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘት ለመገንዘብ የሚቻል ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ርክክብን አስመልክቶም እንደ ፍርደ የሚፈፀመው በውሳኔው ላይ የተመለከተውን ንብረት ባለገንዘቡ ራሱ ወይም ወኪለ እንዱረከብ በማድረግ ለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.402(1) በግልፅ ተመልክቷል።
በግራ ቀኙ መሃል ሲካሄድ የነበረው የሁከት ይወገድልኝ ክርክር ተጠሪ ወደ አመልካች ይዞታ በመግባት የያዙት ይዞታ አለመኖሩን በመግለፅ ቢከራከሩም በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.39060 ታህሳስ 09 ቀን 2010 ዓም በተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ተጠሪ ከአመልካች ይዞታ ፉት ለፉት 0.10 ሜትር እና ከኋላ በኩል 0.70 ሜትር ወደ አመልካች ይዞታ አልፈው መገኘታቸው እንዱሁም ይዞታቸው አራት ማዔዘን ቢሆንም አጥሩን ወጣ ገባ አድርገው ማጠራቸው ተረጋግጦ ይኸው ሁከት እንዱወገድ መወሰኑ፤ይህ ውሳኔም በይግባኝ ያልተሻረ የመጨረሻ ውሳኔ መሆኑ ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነጥብ ነው።በዚህ ውሳኔ አግባብም ከፉት ለፉት 0.10 ሜትር በጎን በኩል ወጣ ገባ ያለውን አጥር ተጠሪ እንዱያነሱ በማድረግ በፍርደ መሰረት መፈፀሙን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻው ተጠሪ ከአመልካች ይዞታ ከኋላ በኩል 0.70 ሜትር ወደ አመልካች ይዞታ አልፈው መያዛቸው ተረጋግጦ ይኸው ሁከት እንዱወገድ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ሲሆን ከላይ እንደተመለከተው ይህ የውሳኔ ክፍል በቦታው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን በመጥቀስ ተጠሪ ውሳኔው እንዱሻር ያደረጉ መሆኑን በመጥቀስ ያቀረቡት ክርክር ካለመኖሩም በላይ የቀረበም ማስረጃ የለም።ይህ ከሆነ ደግሞ በፍርደ አግባብ ሉፈፀም ሲገባ የሶድ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ የአፈፃፀም ጉዲዩ ሲቀርብለት ግራ ቀኙ በማያገባቸው የመንግስት ይዞታ ልኬት ተደርጎ የቀረበ በመሆኑ በመንግስት ይዞታ ላይ አልፍ ይዟል አልያዘም ብለን ማስላቱ አስፈላጊ አይደለም በፍርደ መሰረት ለመፈፀም አለመፍቀደና የአፈፃፀሙ ጉዲይ በመጨረሻ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ ውሳኔው ተሽሮ በፍርደ አግባብ እንዱያስፈፅም ሲታዘዝም ‛…ተከሳሽ በአካል የያዙት በሳይት ፔላኑ ላይ ከተመለከተው ያነሰ መሆኑን መነሻ በማድረግ ፤ተከሳሽ ቤቱን አልፍ ወደ ከሳሽ ይዞታ ገብቶ የሰራበት የለም ሲለካ የተከሳሽ ይዞታ ወደ ከሳሽ ይዞታ ነው የሚገባው…“ የሚል እርስ በእርሱ የሚጋጭ ምክንያት በማስቀመጥ በፍርደ መሰረት አለማስፈፀሙና ይህ የአፈፃፀም ትዕዛዝ በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
የወላይታ ሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ ቀን 06/08/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝና ይህንን ትዕዛዝ በማፅናት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 50777 በቀን 23/09/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 36077 ሐምል 15 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሸረዋል።
የወላይታ ሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም መዝገቡን በማንቀሳቀስ በመ/ቁ.39060 ታህሳስ 09 ቀን 2010 ዓም በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ አግባብ ተጠሪ ከአመልካች ይዞታ ከኋላ በኩል 0.70 ሜትር ወደ አመልካች ይዞታ አልፈው የያዙትን በማስለቀቅ እንዱያስረክብ ጉዲዩን መልሰንለታል።
ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።
No topics extracted.